የኀብረተሰብ ተሳትፎና በጎ ፈቃድ ማስተባበሪያ ኮሚሽን - አዲስ አበባ
809 subscribers
2.14K photos
47 videos
265 links
Download Telegram
የኀብረተሰብ ተሳትፎና በጎ ፈቃድ ማስተባበሪያ ኮሚሽን - አዲስ አበባ
Photo
ነዋሪው በአካባቢ መሠረተ ልማት፣ በሠላምና በበጎ ፈቃድ ስራዎች የሚያደርገው ተሳትፎ እየደገ መምጣቱን በአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት  የሴቶች፣ ሕጻናትና ማኅበራዊ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ገለጸ፡፡

ቋሚ ኮሚቴው በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳዳር የኅብረተሰብ ተሳትፎና በጎ ፈቃድ ማስተባባሪያ ኮሚሽንን የስድስት ወራት የስራ አፈፃጸም ዙሪያ ድጋፍና ክትትል አድርጓል። የቋሚ ኮሚቴው ሰብሳቢ የተከበሩ ወ/ሮ ሶፊያ ዓለሙ የከተማዋ ነዋሪ በአካባቢ መሠረተ ልማት፣ በሠላም እሴት ግንባታና በበጎ ፈቃድ ስራዎች ዙሪያ እያደረገ ያለው ተሳትፎ እያደገ መምጣቱን ገልጸዋል፡፡

በጎ ፈቃደኝነትን ባሕሉ ያደረገ በአካካባቢ መሠረተ ልማት ስራዎችና በሠላም እሴት ግንባታ ላይ በንቃት የሚሳተፍና የባለቤትነት ስሜት የፈጠረ ንቁ ማኅበረሰብ ለመገንባት እየተደረገ ባለው ጥረት ውስጥ ኮሚሽኑ ያከናወናቸው ስራዎችና የተገኙ ውጤቶች የተሻሉ መሆናቸውን የገለፁት የቋሚ ኮሚቴው አባላት የኮሚሽኑ ዕቅድ እያደገ ከመጣው የነዋሪው ተሳትፎ አኳያ ተመጣጣኝ መሆን እንዳለበት ጠይቀዋል፡፡

የቋሚ ኮሚቴው አባላት በመስክ ምልከታ በነዋሪው ተሳትፎ የተገነቡ የአካባቢ መሠረተ ልማቶች ላይ ጉዳት መድረሱን ማስተዋለቸውን ገልፀው ኮሚሽኑ ጉዳት የደረሰባቸውን መሠረተ ልማቶች በፍጥነት እንዲጠገኑ ከሚመለከታቸው ተቋማት ጋር መስራት ይጠበቅብርታል ብለዋል። በመሰረተ ልማት ጥበቃም ህብረተሰቡ የድርሻውን እንዲወጣ የባለቤትነት ድርሻ መስጠትና ግንዛቤውን ማሳደግ ይጠበቃል።

ቋሚ ኮሚቴው ያነሳቸው ገንቢ አስተያቶች ለኮሚሽኑ ውጤታማነት የላቀ ሚና እንዳላቸው የገለጹት ኮሚሽነር ይመር ከበደ  የስደስት ወራት አፈጻጸምን መሠረት በማድረግ የኮሚሽኑ ዕቅድ እንደሚከለስ ተናግረዋል፡፡  የአካባቢ መሠረተ ልማት ብልሽትን ለመከላከል ነዋሪው ልማቶችን በባለቤትነት እንዲንከባከባቸው የግንዛቤ ማስጨበጫ ስራ በመሰራቱ ውጤት መመዝገቡን የተናገሩት ኮሚሽነሩ ጉዳት የሚያደርሱ አካላትን ተጠያቂ የማድረግ ስራ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል አስረድተዋል፡፡

በዳዊት ንጉሴ
ታህሳስ 20/2018 ዓ.ም አዲስ አበባ
3
የኀብረተሰብ ተሳትፎና በጎ ፈቃድ ማስተባበሪያ ኮሚሽን - አዲስ አበባ
Photo
አዲስ አበባን ስሉጥ ከተማ (Smart City) የማድረግ ውጤታማ ጉዞ!

የስሉጥ ከተማ መገለጫ የሆኑትን ዘመናዊ ተቋማት የመገንባት ህልም እውን ለማድረግ እንዲያስችል፣ ተቋማት አገልግሎታቸውን በማዘመን፣ ቴክኖሎጂን በመጠቀም ተገልጋዩ ቀልጣፋ አገልግሎት እንዲያገኝ ውጤታማ ስራዎች እየተሰሩ ነው፡፡ ይኸውም፣ በህዝብ አገልግሎት ሰጪ ተቋማት ዘንድ ይስተዋል የነበረውን እንግልት ለማስቀረት በርካታ ስራዎች ተሰርተዋል፡፡

በተለይም ተቋማት አገልግሎታቸውን ከሰው ንክኪ የራቁ እና ለህዝብ ፍትሃዊ አገልግሎት ማቅረብ እንዲችሉ በቴክኖሎጂና በመሰረተ ልማት የታገዙ፣ እንዲሁም ቀልጣፋ አገልግሎት መስጠት እንዲችሉ ከተማ አስተዳደሩ በትኩረት እየሰራ ሲሆን፣ በዚህም ለሁሉም ምቹ የሆነች ስማርት ከተማን መፍጠር ተችሏል፡፡

ለአብነትም መሶብ የአንድ ማዕከል አገልሎት፣ በወሳኝ ኩነት ፣ በሆስፒታሎች እና ጤና ጣቢያዎች ፣ በፍቃድ አስጣጥና እድሳት፣ የገቢ አሰባሰብን እና በትላንትናው ዕለት የተመረቁት ዘመናዊ የፓሊስ ማዕከላትን ጨምሮ በርካታ አገልግሎት ሰጪ ተቋማት፤ አገልግሎታቸውን በቴክኖሎጂ በማሳደግ ከዚህ ቀደም የሚስተዋለውን እንግልትን በማስቀረት የህዝብ ሀብት እንዳይባክን አድርጓል፡፡

አዲስ አበባን ስሉጥ ከተማ (Smart City) ለማድረግ የተጀመረው ርዕይ፣ አሁን ላይ በርካታ የህዝብ አገልግሎቶች በቴክኖሎጂ የታገዙና የተደራጁ እንዲሆኑ በማድረግ ከተማዋን ዘመናዊ ምቹ እና ለሁሉም ተስማሚ እንድትሆን አስችሏል፡፡

አዲስ አበባን ለማልማት፣ ሁሉንም የልማት አማራጮች በመዘርጋት ነዋሪዎቿ ተጠቃሚ እንዲሆኑ ማስቻል የምንግዜም ተቀዳሚ ተግባር ሆኖ ይቀጥላል፡፡
1
አዲስ አበባ÷የሁላችን የጋራ አምባ፤ የአፍሪካ የብልፅግና መልክ!

ውብ፣ ፅዱ እና ለነዋሪዎቿ ምቹ እና የአፍሪካ መዲና የሆነችዉ አዲስ አበባ፣ ታሪኳንና ባህሏን ከዘመናዊነት እና ቴክኖሎጂ ጋር አዋህዳ ሁለንተናዊ የብልፅግና ጉዞዋን በተግባር እያረጋገጠች ነው፡፡

ዓለም በአንድ ቃል! ምስክርነት ከሰጠባቸው የኮሪደር እና የወንዝ ዳር መሠረተ-ልማቶች በተጨማሪ ታሪኳንና ቅርሷን በማደስ በትላንት፣በዛሬና ነገ ፅኑ ድልድይ የገነባቻቸዉ ተጠቃሽ እና ትዕምርት የሆኑ በርካታ ሰዉ ተኮር ልማት ስራዎቿ ይገኙበታል፡፡

ዘርፈ-ብዙነትን ከተላበሱ የልማት ስራዎቿ፤-ልምድ መቀመርያ የሆኑ እና የነገ- ሀገር ተረካቢ የሆኑ ህፃናት ከቅድመ ወሊድ እስከ ትምህርት ቤት ምገባ ልዩ ትኩረት የምትሰጥበት የቀዳማይ ልጅነት ፕሮግራም፣ የቱሪስት የስህበት ማዕከል የሆኑ ፓርኮቿ፣ ህዝብ የጋራ ትውስታ እና ተዝናኖት የሚያሳልፍባቸው በርካታ ፕላዛዎች እና የህፃናት መጫወቻ ስፍራዎች፣ ደረጃቸውን የጠበቁ የእግረኛ እና ብስክሌት መንገዶች፣ የመሮጫ ትራኮች እና የተለያየ መጠን ያላቸው የስፓርት ሜዳዎች፣ ዘመናዊ የመኪና ፓርኪንግ እና ተርሚናሎች፣ግሪን የትራንስፖርት አማራጮች፣ ጥራት እና ስፋት ያለው የመንገድ መሰረተ-ልማቶች ጨምሮ በርካታ ዓለም አቀፍ እና አህጉር አቀፍ ኮንፈረንሶችን በብቃት የማስተናገድ ዓቅም የገነባች ከተማ፣ አዲስ አበባ ለመሆን በቅታለች፡፡

በሌላ በኩልም አገልግሎት አሰጣጥን የተሳለጠ እና ፍትሀዊ እንዲሆን የመሶብ አንድ ማዕከልን ከከተማ እስከ ክፍለ-ከተማ በመተግበር፤የተቋማትን አገልግሎት በቴክኖሎጂ በማስተሳሰር ቀላል፣ ምቹና ወጪ ቆጣቢ አገልግሎት ተደራሽ ለማድረግ እየሰራች ያለች ከተማ "አዲስ አበባ "የሁላችን የጋራ አምባ፤ የአፍሪካ የብልፅግና መልክ በመሆን ብዙ… ድንቅ ስራዎችን በተግባር አያጎናፀፈች ቀጥላለች፡፡
5
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
በኢትዮጵያ ሰፋ ያለው የኢኮኖሚ ሽግግር አካል የሆነው ኢንደስትሪ ልማት የሥራ ፈጠራን እያፋጠነ የሀገር ውስጥ አምራቾችን እያጠናከረ መጥቷል። በትኩረት በሚሰራበት የኢንደስትሪ ማስፋፋት እና የውጭ ምርቶችን በሀገር ውስጥ የመተካት ሥራ ሀገራችን ከውጭ በሚገቡ ምርቶች ላይ ያላት ጥገኝነት እየቀነሰ መጥቷል። የውጭ ምንዛሬ እየቆጠበ ነው። የሀገር ውስጥ የእሴት ሰንሰለት ጥንካሬን እየገነባ ይገኛል። በኢንደስትሪ ፓርኮች የሚደረግ ኢንቨስትመንት፣ ለሀገር ውስጥ አምራቾች የሚደረግ ድጋፍ ብሎም የኢትዮጵያ ታምርት ምርቶችን የማስተዋወቅ ሥራዎች እድገትን እያፋጠኑ ይገኛሉ። የሥራ ክህሎትን እና ፈጠራን በማሳደግ ዘላቂነት ያለው እሴት እና እድል በሀገር ውስጥ እንዲፈጠር አድርገዋል።

#PMOEthiopia
#VisionOfProsperity
#የኢትዮጵያብልጽግናራእይ
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
የአብርሆት ቤተ-መጻሕፍትን ወደ ላቀ የዲጂታል ምዕራፍ የሚያሸጋግሩ ሦስት የቴክኖሎጂ ፕሮጀክቶች ይፋ የተደረጉበት ሥነሥርአት
ከንቲባ አዳነች አቤቤ
መጪውን የገና በዓል ምክንያት በማድረግ፣ በከተማችን በሚገኙ ክፍለ ከተሞችና ወረዳዎች ለሚኖሩ ከ300 ሺህ በላይ ምንም የገቢ ምንጭ ለሌላቸው፣ ለማህበራዊ ችግር ለተጋለጡ፣ ዝቅተኛ ገቢ ላላቸውና አቅመ ደካማ ወገኖቻችን የማዕድ ማጋራት መርሐ-ግብር አካሂደናል።

የገና በዓል የኢየሱስ ክርስቶስ የልደት በዓልና የፍቅር መገለጫ በመሆኑ፣ በማዕድ ማጋራት ለተቸገሩ ወገኖቻችን ያለንን ፍቅር በተግባር የምንገልጽበት ነው። ይህ የበጎነት ተግባር የከተማችንን ጥልቅ የመረዳዳትና የአብሮነት እሴት ይበልጥ የሚያጸና ሲሆን፤ ዛሬም ጊዜያዊ ችግርን ለማለፍ እጅ ለአጅ ተያይዘን የምንቆም እና ለዘላቂ ልማት የምንተጋ ታላቅ ሕዝቦች መሆናችንን በተግባር ያረጋገጥንበት ነው።

በሁሉም በዓላት ካላቸው ላይ ለወገኖቻቸው በማካፈል፣ ለዚህ በጎ ተግባር መሳካት ደከመኝ ሰለቸኝ ሳይሉ አብረውን ለቆሙ ልበ-ቀና ባለሀብቶች፣ በትጋት ላስተባበሩ ወጣቶችና አመራሮች በራሴ፣ በከተማ አስተዳደሩ እንዲሁም በተጠቃሚ ወገኖቻችን ስም ከልብ የመነጨ ምስጋናዬን አቀርባለሁ።

በዓሉ የፍቅር፣ የሰላምና የደስታ እንዲሆንላችሁ ከወዲሁ ከልብ እመኛለሁ!
ፈጣሪ ኢትዮጵያን እና ሕዝቦቿን ይባርክ!
መልካም በዓል!

ከንቲባ አዳነች አቤቤ
3
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
ከንቲባ አዳነች አቤቤ የገና በዓልን ምክንያት በማድረግ ለ300 ሺህ 185 ዝቅተኛ ገቢ ያላቸው ነዋሪዎች ማዕድ አጋሩ!

የቲክቶክ አድራሻችን👇👇👇
https://vt.tiktok.com/ZS5PpnAJ5/


#በጎ_ልቦች
#addisababa
3
Follow the የኅብረተሰብ ተሳትፎና በጎ ፈቃድ ማስተባበሪያ ኮሚሽን channel on WhatsApp: https://whatsapp.com/channel/0029VbBAQRrGOj9kUsLU7A0Z

👆👆👆ዋትስአፕ ቻናላችንን በመቀላቀል ወቅታዊ መረጃዎችን እናደርስዎታለን!
የገናን በዓል ምክንያት በማድረግ፣ ዛሬ በዋዜማው 381 ቤቶችን ከሙሉ የቤት ዕቃና ከበዓል ማሳለፊያ ጋር በስጦታ አስረክበናል።

ከእነዚህ ቤቶች መካከል፦ 273ቱ ቀደም ሲል የወዳደቁ የቀበሌ ቤቶች የነበሩ ሲሆኑ፣ ሙሉ በሙሉ ፈርሰው እንደገና በመገንባት ለቀድሞ ለነዋሪዎች የተላለፉ ናቸው።
108ቱን ደግሞ ለአቅመ ደካሞችና ዝቅተኛ ገቢ ላላቸው ወገኖች፤ ለሀገር የአካል ዋጋ ለከፈሉ የጀግናው የመከላከያ ሰራዊትና የፌደራል ፖሊስ አባላት፤ ለኪነ ጥበብ ባለሙያዎች እንዲሁም ለሀገር ባለውለታዎች አስተላልፈናል።
ቤቶቹ የሕፃናት መጫወቻን ጨምሮ ሌሎች ማህበራዊ አገልግሎቶች የተሟሉላቸው፣ አዲስ የተገነቡ ዘመናዊ መንደሮች ናቸው።

ከተማችንን ውብ አበባ ስናደርግ፣ የነዋሪዎቻችንን የኑሮ ዘይቤ በማዘመን እና የኑሮ ጫናዎችን እያቃለልን ጭምር ነው ።

በከተማችን ከለውጡ ወዲህ በሰው ተኮር እሳቤ እየተመራን የበጎ ፍቃድ ተሳትፎ ባህል እየሆነ በመምጣቱ 45 ሺህ ቤቶችን በበጎ ፍቃድ ተሳትፎ በመገንባት ለማህበራዊ ችግር ለተጋለጡ ወገኖችና ለሀገር ባለውለታዎች በማድረስ እምባቸውን ማበስ ተችሏል።

“ሃምሳ ሎሚ ለሃምሳ ሰው ጌጡ ነው” እንደሚባለው፤ ሁላችንም እየተባበርን ጊዜያዊ ችግሮችን በጋራ በመሻገር ለዘላቂ ልማት እንተጋለን።

ለበጎ ፍቃደኞችና ለአስተባባሪዎች በሙሉ በተለይም የኤን .ኤ ቢዝነስ ቬንቸርስ እና ምርጦቹ 7000 ቤተክርስቲያንን በተጠቃሚዎቹ፣ በከተማው አስተዳደሩ እና በራሴ ስም ከልብ አመሰግለሁ።
መልካም በዓል!

ፈጣሪ ኢትዮጵያን እና ህዝቦቿን ይበርክ!
ከንቲባ አዳነች አቤቤ
6