የኀብረተሰብ ተሳትፎና በጎ ፈቃድ ማስተባበሪያ ኮሚሽን - አዲስ አበባ
809 subscribers
2.14K photos
47 videos
265 links
Download Telegram
በመዲናችን የ2018 ዓ.ም የበጋ በጎ ፈቃድ ፕሮግራም በነገው እለት በይፋ ይከፈታል።

የተለያዩ ሰብዓዊና ማኅበራዊ አገልግሎቶች የተካተቱበት ይህ ፕሮግራም ከ2 ሺህ 500 በላይ በጎ ፈቃደኞች እንዲሁም ባለድርሻ አካላትና ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች በተገኙበት ነው ይፋ የሚደረገው።

በመዲናዋ ባለፈው የክረምት በጎ ፈቃድ መርሀ ግብር 8.2 ቢሊዮን የሚገመት የበጎ ፈቃድ አገልግሎት ተሰጥቷል። በጎ ፈቃደኛ ባለሀብቶችን በማሳተፍ 3 ሺህ 100 የአቅመ ደካሞችና አረጋውያን ቤቶች የተገነቡ ሲሆን 14 ሺህ 724 የኅብረተሰብ ክፍሎች በተገነቡ ቤቶች ተጠቃሚ ሆነዋል።

በዓላትን ምክንያት በማድረግ በተከናወኑ መርሀ ግብሮች 614 ሺህ 269 በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ የሚገኙ ዜጎች ማዕድ ተጋርተዋል።

በነፃ የህክምና አገልግሎት 226 ሺህ 887 ከፍለው መታከም የማይችሉ የመዲናችን ነዋሪዎች ነጻ የህክምና አገልግሎት ያገኙ ሲሆን የባለድርሻ አካላት እና የበጎ ፈቃደኞች ተሳትፎ በማደጉ በክረምት የታቀዱ የበጎ ፈቃድ መርሃ ግብሮች ስኬታማ ነበሩ።

በክረምት የበጎ ፈቃድ አገልግሎት የተገኙ ውጤቶችን በማስቀጠል ለማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ችግሮች የተጋለጡ የኅብረተሰብ ክፍሎችን በዘላቂነት ተጠቃሚ ለማድረግ የበጋ በጎ ፈቃድ ፕሮግራም ልዩ ትኩረት ተሰጥቶት በነገው ዕለት ይፋ ይደረጋል።
10
በማኅበራዊ ድረ ገፆቻችን ቤተሰብ ለመሆን ቀጣዩን ማስፈንጠሪያ ይጫኑ ወይም QR ኮዱን ስካን ያድርጉ!

https://linktr.ee/cpvcc2015
የኀብረተሰብ ተሳትፎና በጎ ፈቃድ ማስተባበሪያ ኮሚሽን - አዲስ አበባ
Photo
የአዲስ አበባን አዲስና ውብ ገፅታ ያላበሱ ሰው ተኮር የልማት ስራዎችን አጠናክሮ መቀጠል እንደሚገባ ተገለፀ።

አዲስ አበባን አዲስና ስሟን የሚመጥን ገፅታ እንዲኖራት እያደረጉ ያሉ የልማት ስራዎችን አጠናክሮ መቀጠል እንደሚገባ የመዲናዋ በጎ ፈቃደኞችና የኅብረተሰብ ተወካዮች ገልፀዋል።

ከሁሉም ክፍለ ከተሞች የተውጣጡ በጎ ፈቃደኞች እና የብሎክ ካውንስል አመራሮች በመዲናዋ በመልሶ ማልማት በማጠናቀቂያ ምዕራፍ ላይ የሚገኘውን የአራዳ ፓርክ ጎብኝተዋል።

የአራዳ ፓርክ በከተማዋ እየተከናወኑ ካሉ የኮሪደር ልማት ፕሮጀክቶች መካከል አንዱ ሲሆን የወንዝ ዳርቻ ልማትን ጨምሮ፣ የንግድ፣ የስፖርት፣ የመዝናኛና ሌሎች ታሪካዊና ዘመናዊ ፕሮጀክቶችን አካቷል።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የኅብረተሰብ ተሳትፎና በጎ ፈቃድ ማስተባበሪያ ኮሚሽን ምክትል ኮሚሽነር ወ/ሮ አስራት ንጉሴ በጉብኝት መርሀ ግብሩ ላይ ተገኝተው ባስተላለፉት መልዕክት በመዲናዋ ነዋሪዎችን ታሳቢ ያደረጉ ሰው ተኮር ማኅበራዊና ኢኮኖሚያዊ ልማቶች እየተከናወኑ መሆኑን ተናግረዋል።

ፒያሳን ጨምሮ ለኑሮ ምቹ ያልሆኑ አካባቢዎችን መልሶ በማልማት ከተማዋ ስሟን የሚመጥን ገፅታ እንድትይዝ ማድረግ መቻሉን የተናገሩት ወ/ሮ አስራት ይህ ተግባር የማይቻሉ የሚመስሉ ጉዳዮችን በመድፈር  በራስ አቅም በአጭር ጊዜ ውስጥ ለውጥ ማምጣት እንደሚቻል የአመራሩና የባለሙያው ቁርጠኝነት የታየበት ውጤታማ ስራ እንደሆነ ገልፀዋል።

የጉብኝቱ ተሳታፊዎች በበኩላቸው አዲስ አበባን አዳዲስ ውብ ገፅታ ያላበሱ የኮሪደር ልማት ውጤቶችን በመመልከታቸው የተሰማቸውን ደስታ ገልፀው መዲናዋን የቱሪዝም መዳረሻ እንድትሆን ለማድረግ የተጀመረውን ሰው ተኮር የልማት እንቅስቃሴ ማስቀጠል እንደሚገባ ጠቁመዋል።

ከከተማዋ የቆዳ ስፋት ውስጥ 5,400 ሄክታር መሬት በኮሪደር እንደለማና ፒያሳን ጨምሮ ከእንጦጦ ፓርክ እስከ ፒኮክ መናፈሻ 1,030 ሄክታር መሬት እንዲሁም 21 ኪ.ሜ የወንዝ ዳርቻ በልማት መሸፈኑን ከከተማዋ የኮሪደርና የወንዝ ዳርቻ ልማት አስተዳደር ባለስልጣን ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።
👍6
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ እና ጠቅላይ ሚኒስትር ናሬንድራ ሞዲ በዛሬው እለት በፓርላማ ተገኝተው የህንድ ጠቅላይ ሚኒስትሩ በየኢፌዴሪ የሕዝብ ተወካዮች እና የፌዴሬሽን ምክር ቤቶች የጋራ ስብሰባ ላይ ንግግር አድርገዋል።

Prime Minister Abiy Ahmed and Prime Minister Narendra Modi in attendance at Parliament today, where the Indian Prime Minister addressed both the House of People’s Representatives and the House of Federation in a joint session.

#PMOEthiopia
5👍1
የበጎ ፈቃድ ማኅበራት ጥምረት 2ኛ ዓመት የስራ ዘመን 1ኛ መደበኛ ጉባዔውን አካሄደ።

የአዲስ አበባ ከተማ የበጎ ፈቃድ ማኅበራት ጥምረት 2ኛ ዓመት የስራ ዘመን 1ኛ መደበኛ ጉባኤውን ዛሬ አካሂዷል። ጥምረቱ የተመሰረተበትን 2ኛ ዓመት ምክንያት በማድረግም ነባር ስራ አስፈፃሚዎችን አዳዲስ ስራ አስፈፃሚ ኮሚቴዎች በመምረጥ ተክቷል።

በጉባዔው ማኅበራቱ ከኮሚሽኑ ጋር ተቀናጅተው ያከናወኗቸው የበጎ ፈቃድ አገልግሎት ሪፖርት ቀርቦ ውይይት ተደርጎበታል። በመዲናዋ የበጎ ፈቃድ ባህል መዳበር የሲቪክ ማህበራት ሚና ከፍተኛ እንደሆነም በውይይቱ ተጠቁሟል፡፡

ጥምረቱ በቀጣይ የስራ አቅጣጫዎች ዙሪያ ውይይት በማድረግ ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የኅብረተሰብ ተሳትፎና በጎ ፈቃድ ማስተባበሪያ ኮሚሽን ጋር የመገባቢያ ሰነድ ተፈራርሟል፡፡

ጥምረቱ በመዲናዋ የሚከናወኑ የበጎ ፈቃድ ስራዎችን በማስተባበርና በጎ ፈቃደኞች እውቀትና ልምድ የሚለዋወጡበት፣ ውጤታማ የበጎነት ስራ መስራት የሚያስችል አደረጃጃት በመሆኑ የተቋቋመበትን ዓለማ ማሳካት እንዲችል ኮሚሽኑ ድጋፍና ክትትል እያደረገ መሆኑን የኮሚሽኑ የበጎ ፈቃድ አገልግሎት ዳይሬክተር አቶ ዳዊት ሙሉጌታ ተናግረዋል፡፡

የመዲናዋ የበጎ ፈቃድ ማህበራት ጥምረት የስራ አስፈጻሚዎች የስራ ዘመን ከ2 ዓመት መብለጥ እንደሌለበትና አዳዲስ አመራሮችን በዲሞክራሲያዊ መንገድ በመተካት በከተማችን ማኅበራዊና ኢኮኖሚያዊ ጉድለቶችን በጋራ መፍታት የሚያስችል አቅምና ምቹ ሁኔታ መፍጠር እንደሚገባ በማህበራቱ የጥምረት ሰነድ ላይ በዝርዝር ተመላክቷል።
3
በቦሌ ክፍለ ከተማ በኅብረተሰቡ ተሳትፎ በመገንባት ላይ የሚገኘው እና 1.3 ኪሎ ሜትር ርዝመት ያለው የውስጥ ለውስጥ አስፓልት መንገድ በመጠናቀቂያ ምዕራፍ ላይ ይገኛል።

በክፍለ ከተማው ወረዳ 7 አስተዳደር በመንግሥት፣ በኅብረተሰቡና በአካባቢው በሚገኙ ኢንዱስትሪዎች ትብብር በመገንባት ላይ የሚገኘው እና 1.3 ኪሎ ሜትር ርዝመት ያለው የውስጥ ለውስጥ የአስፓልት መንገድ የሰቤዝና የውኃ መፋሰሻ ስራ የተጠናቀቀ ሲሆን አስፓልት የማልበስ ስራ ተጀምሯል።

የውስጥ ለውስጥ አስፓልት መንገዱ በአካባቢው ማኅበረሰብ ለረዥም ጊዜ ሲያነሳ የቆየ የመልካም አስተዳደር ጥያቄ ሲሆን ግንባታው በፍጥነት እና በጥራት እንዲጠናቀቅ ክትትል እየተደረገ መሆኑን ከክፍለ ከተማው ኮሙኒኬሽን ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።
4
የኮሚሽኑ ሰራተኞችና በጎ ፈቃደኞች በክረምት የተተከሉ ችግኞችን ተንከባከቡ።

የአዲስ አበባ ከተማ የኅብረተሰብ ተሳትፎና በጎ ፈቃድ ማስተባበሪያ ኮሚሽን ሰራተኞችና የየካ ክፍለ ከተማ በጎ ፈቃደኞች ካዛንችስ በግንፍሌ የወንዝ ዳርቻ በክረምት ወቅት የተተከሉ ችግኞችን ተንከባክበዋል።

በመርሀ ግብሩ ላይ የተገኙት የኮሚሽኑ ዋና ኮሚሽነር አቶ ይመር ከበደ የተተከሉ ችግኞችን የፅድቀት መጠን ለመጨመር እንደኮሚሽን የበጎ ፈቃድ ፕሮግራሞች እቅድ አካል በማድረግ የእንክብካቤ ስራ እየተከናወነ መሆኑን ተናግረዋል።

በጎ ፈቃደኞችና መላው የከተማዋ ነዋሪ የተተከሉ ችግኞች እንዳይደርቁ የእንክብካቤ ስራውን አጠናክሮ እንዲቀጥልም ኮሚሽነሩ ጥሪ አቅርበዋል።

የኮሚሽኑ ሰራተኞች በበኩላቸው በክረምት ወቅት የተከሏቸውን ችግኞች በየጊዜው በመንከባከብ እንዲፀድቁ ለማድረግ እንደሚሰሩ ገልፀዋል።

በሌሎች የማኅበራዊ ሚዲያ አማራጮች ቤተሰብ ለመሆን ማስፈንጠሪያውን ይጫኑ!

https://linktr.ee/cpvcc2015
1
የኀብረተሰብ ተሳትፎና በጎ ፈቃድ ማስተባበሪያ ኮሚሽን - አዲስ አበባ
Photo
የኃይማኖት ተቋማት በሥነ-ምግባር የታነፀ መልካም ትውልድ የመገንባት ኃላፊነታቸውን እንዲወጡ ተጠየቀ።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የኅብረተሰብ ተሳትፎና በጎ ፈቃድ ማስተባበሪያ ኮሚሽን ከአዲስ አበባ የሐይማኖት ተቋማት ጉባኤ ጋር በመተባበር "ማኅበራዊ ኃላፊነቱን የሚወጣና በሥነ-ምግባር የታነፀ ትውልድ በጋራ እንገንባ!" በሚል መሪ ቃል በበጎ ፈቃድ አገልግሎትና በማኅበራዊ ኃላፊነት ደንብ ቁጥር 161/2016 ዙሪያ የሐይማኖት ተቋማት መሪዎች የተሳተፉበት ምክክር አካሂዷል።

በሥነ-ምግባር የታነፀ፣ ኃላፊነቱን የሚወጣ፣ ምክንያታዊ ትውልድ በመገንባት ረገድ የኃይማኖት ተቋማት ከፍተኛ ድርሻ እንዳላቸው በመድረኩ ላይ ተገኝተው መልዕክት ያስተላለፉት ኮሚሽነር ይመር ከበደ አፅንዖት ሰጥተዋል።

በጎ ፈቃደኝነት ለመልካም ትውልድ ግንባታ መሰረት የሚጥል መሆኑን የተናገሩት ኮሚሽነሩ መስጠትን ማለማመድ፣ ይቅር ማለትንና ፍቅርን ማስተማር የተቋማቱ ሚናና ኃላፊነት መሆኑን በመረዳት ከመንግስት ተቋማት ጋር በጋራ መስራት ይጠበቅባቸዋል ብለዋል።

የአዲስ አበባ የሐይማኖት ተቋማት ጉባኤ ዋና ፀሐፊ መጋቢ ታምራት አበጋዝ በበኩላቸው ሀገራዊ እሴቶችን የሚያከብር፣ ለሀገር እድገትና ለውጥ አስተዋፆዖ ያለው፣ ሰርቶ መለወጥን ልምድ ያደረገ ማኅበረሰብ በመፍጠር መገለጫዎቻችን ያልሆኑ መጤ ባህሎችን ማረም የሐይማኖት አባቶች ሚና መሆኑን አስምረውበታል።

ልጆቻችን በበጎ ፈቃደኝነት እንዲያገለግሉ በማድረግ ሀገራቸውን የሚወዱ ወጣቶች ማፍራት ብሎም በከተማዋ የለውጥ እንቅስቃሴ ውስጥ ጉልህ ድርሻቸውን መወጣት እንዲችሉ ማድረግ የእኛ የሐይማኖት አባቶች ኃላፊነት ነው ሲሉ ዋና ፀሐፊው ጨምረው ገልፀዋል።

ስራ መናቅን፣ ስንፍናን፣ ሌብነትንና ተረጅነትን የሚጠየፍ ትውልድ በጋራ መገንባት የምንችለው ከቤተሰብ፣ ከትምህርት ቤትና ከተቋማት ጀምሮ በሚደረግ በጎ አስተምሮና የሥነ-ምግባር ቀረፃ ስራ መሆኑን የተናገሩት የሐይማኖት አባቶች በመድረኩ የተሰጡ ኃላፊነቶችን ለመስራት ዝግጁ መሆናቸውን አስረድተዋል።

በማኅበራዊ ሚዲያው የሚታየውን ጫፍ የወጣና ያልተገራ አካሄድ መንግስት ከሚወስደው ርምጃ ባለፈ የሐይማኖት ተቋማት በሥነ-ምግባር ግንባታ ላይ እንሰራለን ነው ያሉት።

ታህሳስ/2018 ዓ.ም
8👍1
የኀብረተሰብ ተሳትፎና በጎ ፈቃድ ማስተባበሪያ ኮሚሽን - አዲስ አበባ
Photo
ነዋሪው በአካባቢ መሠረተ ልማት፣ በሠላምና በበጎ ፈቃድ ስራዎች የሚያደርገው ተሳትፎ እየደገ መምጣቱን በአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት  የሴቶች፣ ሕጻናትና ማኅበራዊ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ገለጸ፡፡

ቋሚ ኮሚቴው በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳዳር የኅብረተሰብ ተሳትፎና በጎ ፈቃድ ማስተባባሪያ ኮሚሽንን የስድስት ወራት የስራ አፈፃጸም ዙሪያ ድጋፍና ክትትል አድርጓል። የቋሚ ኮሚቴው ሰብሳቢ የተከበሩ ወ/ሮ ሶፊያ ዓለሙ የከተማዋ ነዋሪ በአካባቢ መሠረተ ልማት፣ በሠላም እሴት ግንባታና በበጎ ፈቃድ ስራዎች ዙሪያ እያደረገ ያለው ተሳትፎ እያደገ መምጣቱን ገልጸዋል፡፡

በጎ ፈቃደኝነትን ባሕሉ ያደረገ በአካካባቢ መሠረተ ልማት ስራዎችና በሠላም እሴት ግንባታ ላይ በንቃት የሚሳተፍና የባለቤትነት ስሜት የፈጠረ ንቁ ማኅበረሰብ ለመገንባት እየተደረገ ባለው ጥረት ውስጥ ኮሚሽኑ ያከናወናቸው ስራዎችና የተገኙ ውጤቶች የተሻሉ መሆናቸውን የገለፁት የቋሚ ኮሚቴው አባላት የኮሚሽኑ ዕቅድ እያደገ ከመጣው የነዋሪው ተሳትፎ አኳያ ተመጣጣኝ መሆን እንዳለበት ጠይቀዋል፡፡

የቋሚ ኮሚቴው አባላት በመስክ ምልከታ በነዋሪው ተሳትፎ የተገነቡ የአካባቢ መሠረተ ልማቶች ላይ ጉዳት መድረሱን ማስተዋለቸውን ገልፀው ኮሚሽኑ ጉዳት የደረሰባቸውን መሠረተ ልማቶች በፍጥነት እንዲጠገኑ ከሚመለከታቸው ተቋማት ጋር መስራት ይጠበቅብርታል ብለዋል። በመሰረተ ልማት ጥበቃም ህብረተሰቡ የድርሻውን እንዲወጣ የባለቤትነት ድርሻ መስጠትና ግንዛቤውን ማሳደግ ይጠበቃል።

ቋሚ ኮሚቴው ያነሳቸው ገንቢ አስተያቶች ለኮሚሽኑ ውጤታማነት የላቀ ሚና እንዳላቸው የገለጹት ኮሚሽነር ይመር ከበደ  የስደስት ወራት አፈጻጸምን መሠረት በማድረግ የኮሚሽኑ ዕቅድ እንደሚከለስ ተናግረዋል፡፡  የአካባቢ መሠረተ ልማት ብልሽትን ለመከላከል ነዋሪው ልማቶችን በባለቤትነት እንዲንከባከባቸው የግንዛቤ ማስጨበጫ ስራ በመሰራቱ ውጤት መመዝገቡን የተናገሩት ኮሚሽነሩ ጉዳት የሚያደርሱ አካላትን ተጠያቂ የማድረግ ስራ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል አስረድተዋል፡፡

በዳዊት ንጉሴ
ታህሳስ 20/2018 ዓ.ም አዲስ አበባ
3