የኀብረተሰብ ተሳትፎና በጎ ፈቃድ ማስተባበሪያ ኮሚሽን - አዲስ አበባ
809 subscribers
2.14K photos
47 videos
265 links
Download Telegram
"ተረጂነት የመስራት ጉልበትን የሚበላ ካንሰር ነው" - ክቡር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)፣ የኢ.ፌ.ዴ.ሪ ጠቅላይ ሚኒስትር

#የጠሚሩምላሾች
#PMOEthiopia
2
ሰላምና ጸጥታን በሚመለከት

የኢትዮጵያን እድገት የማይሹ ሀገራት በጦርነት እንደማያሸንፉን ያውቁታል። ያላቸው ምርጫ ባንዳዎችን መላክ ነው። ኢትዮጵያን በቅጡ ያላወቁ የውስጥ ባንዳዎች ደግሞ ከጠላት ጋር በማበር ዓላማቸውን የሚያሳኩ ይመስላቸዋል። ይህ ፈጽሞ ሊሳካ አይችልም። ኢትዮጵያ ውስጥ የሚያስፈልገው ብቻው መንገድ ሰላማዊ የስልጣን ሽግግር ነው። መንግስት ችግሮች አሉኝ የሚሉ አካላት ጋር ቁጭ ብሎ በመነጋገር ችግሮችን በሰላማዊ መንገድ ለመፍታት አሁንም ክፍት ነው።

#የጠሚሩምላሾች
#PMOEthiopia
3
የፕሪቶሪያ የሰላም ስምምነት ላይ የተቀመጡ ዋነኞቹ ጉዳዮች ምንድን ናቸው:-

- ህወሃት ያካሄደው ምርጫ ህጋዊ ምርጫ ባለመሆኑ መሰረዝ
- በትግራይ ክልል ህጋዊ ባለሆነ ምርጫ የተቋቋመው የክልሉ አስተዳደርና ምክር ቤት እንዲፈርስ
- ከሁሉም ወገን የተወጣጣ ጊዜያዊ አስተዳደር ማቋቋም
- በህዝብ የተመረጠውን የፌደራል መንግስት ስርዓት ማክበር
- በክልሉ ታጥቀው ሲንቀሳቀሱ የነበሩ ሃይሎች ትጥቅ መፍታትና በተሃድሶ ወደ መደበኛ ህይወታቸው መመለስ
- የተቋረጡ አገልግሎቶችን ወደ ስራ ማስመለስ
- ከቀያቸው የተፈናቀሉ ዜጎችን መመለስ
- የትኛውም የውጭ ግንኙነት የማከናወን ስልጣን ያለው የፌደራል መንግስቱ ብቻ መሆኑን ማክበር የሚሉት ናቸው።

#የጠሚሩምላሾች
#PMOEthiopia
👍3
በትግራይ ክልል ያለውን የሰላም ሁኔታ በሚመለከት

በትግራይ ክልል ተጨማሪ ወጊያ እንዲካሄድ አንፈልግም። ከዚያ ይልቅ ተባበረን ሀገር ማልማት ነው የምንፈልገው። ከዚያ ውጭ መንግስትን በሃይል ለመጣል ፍላጎት ካለ እሱ ፈጽሞ ሊሳካ አይችልም። የፌደራል መንግስት ለትግራይ ክልል የሚመድበው በጀት ለልማት ሳይሆን ለታጣቂ እየዋለ ነው። ይህ ትክክል አይደለም። ትግራይ ልማት ያስፈልጋታል። በመሆኑም በሰላማዊ መንገድ በትብበር ለልማት መስራት ይገባል።

#የጠሚሩምላሾች
#PMOEthiopia
2
7ኛውን ሀገራዊ ምርጫ በተመለከተ

ምርጫውን ለማከናወን መንግስት በቂ አቅምና ዝግጁነት አለው። 7ኛው ሀገራዊ ምርጫ እስካሁን በኢትዮጵያ ከተካሄዱ ምርጫዎች የተሻለ እንደሚሆን ጥርጥር የለውም። ምርጫው ዴሞክራሲያዊና ብዘሃ ድምጾች ያሉት እንዲሆን በሃላፊነት እንሰራለን። እኛ እንደ ፓርቲም፤ እንደ መንግስትም ዝግጁ ነን። ተፎካካሪ ፓርቲዎችም ከወዲሁ መዘጋጀት አለባቸው።

#የጠሚሩምላሾች
#PMOEthiopia
2
ተቋማዊ ሪፎርም በሚመለከት

በአገልግሎት አሰጣጥ ያለውን እንግልት ለመቀነስ የተጀመረው መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት በሀገር አቀፍ ደረጃ እየሰፋ ነው። አሁን ላይ 18 ማዕከላት አገልግሎት እየሰጡ ነው። ሶስት ማዕከላት ደግሞ በቅርቡ ስራ ይጀምራሉ ተብሎ ይጠበቃል። በተያዘው በጀት ዓመትም ይህን ቁጥር ወደ 100 ለማድረስ እየተሰራ ነው። ይህም በአገልግሎት አሰጣጥ ላይ ከፍተኛ ለውጥ እንደሚያመጣ ይጠበቃል።

#የጠሚሩምላሾች
#PMOEthiopia
1
የዓባይ ውሃ ፍትሃዊ ተጠቃሚነትን በሚመለከት

ኢትዮጵያ በብሔራዊ ጥቅሟ ላይ ኢ-ፍትሃዊና ኢ-ርታዊ ውሳኔ የተወሰነባት ሀገር ናት። ዓባይን መጠቀም ተፈጥሯዊና ህጋዊ መብቷ ነው። ሃብቱም በጋራ ለመጠቀም በቂ ነው። ኢትዮጵያ አሁንም ያላት አቋም ግልጽ ነው። ግብጻዊያንም ሱዳናዊያንም ወንድሞቻችን ናቸው። ስለዚህ የሚያዋጣው በመነጋገርና በመተባበር በጋራ ማደግ ነው። እኛ ማንንም በሚጎዳ መልኩ አናቅድም አንሰራም።

#የጠሚሩምላሾች
#PMOEthiopia
2
ቀይ ባህርን በተመለከተ

የቀይ ባህር ጉዳይ ህጋዊ፣ ታሪካዊ፣ መልከዓ ምድራዊና ኢኮኖሚያዊ ጥያቄ ነው ብለን እናምናለን። ይህንን በተረጋጋ መንገድ ማየት ያስፈልጋል። ኢትዮጵያን የቀይ ባህር የማጣት ውሳኔ ማን ወሰነ ብለን ስንፈልግ ተቋማት አልገቡበትም። ይህን የሚያህል የህልውና ጉዳይ ማን እንደወሰነ መጠየቅ ተገቢ ነው። ኢትዮጵያ ተዘግቶባት መኖር አትችልም። ለጎረቤቶቻችን መናገር የምንፈልገው ኢትዮጵያ ስታደግ ለቀጣናውም ልማት ምንጭ ትሆናለች። የምንፈልገው በትብብር ማደግ ነው።

#የጠሚሩምላሾች
#PMOEthiopia
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት ለቀረቡላቸው ጥያቄዎች በሰጡት ማብራሪያ ያነሷቸው ሃሳቦች-ክፍል ሁለት

ሰላምና ጸጥታን በሚመለከት
የኢትዮጵያን እድገት የማይሹ ሀገራት በጦርነት እንደማያሸንፉን ያውቁታል። ያላቸው ምርጫ ባንዳዎችን መላክ ነው። ኢትዮጵያን በቅጡ ያላወቁ የውስጥ ባንዳዎች ደግሞ ከጠላት ጋር በማበር ዓላማቸውን የሚያሳኩ ይመስላቸዋል። ይህ ፈጽሞ ሊሳካ አይችልም። ኢትዮጵያ ውስጥ የሚያስፈልገው ብቻው መንገድ ሰላማዊ የስልጣን ሽግግር ነው። መንግስት ችግሮች አሉኝ የሚሉ አካላት ጋር ቁጭ ብሎ በመነጋገር ችግሮችን በሰላማዊ መንገድ ለመፍታት አሁንም በሩ ክፍት ነው።

የፕሪቶሪያ የሰላም ስምምነት ላይ የተቀመጡ ዋነኞቹ ጉዳዮች ምንድን ናቸው
- ህወሃት ያካሄደው ምርጫ ህጋዊ ምርጫ ባለመሆኑ መሰረዝ
- በትግራይ ክልል ህጋዊ ባለሆነ ምርጫ የተቋቋመው የክልሉ አስተዳደርና ምክር ቤት እንዲፈርስ
- ከሁሉም ወገን የተወጣጣ ጊዜያዊ አስተዳደር ማቋቋም
- በህዝብ የተመረጠውን የፌደራል መንግስት ስርዓት ማክበር
- በክልሉ ታጥቀው ሲንቀሳቀሱ የነበሩ ሃይሎች ትጥቅ መፍታትና በተሃድሶ ወደ መደበኛ ህይወታቸው መመለስ
- የተቋረጡ አገልግሎቶችን ወደ ስራ ማስመለስ
- ከቀያቸው የተፈናቀሉ ዜጎችን መመለስ
- የትኛውም የውጭ ግንኙነት የማከናወን ስልጣን ያለው የፌደራል መንግስቱ ብቻ መሆኑን ማክበር የሚሉት ናቸው።

በትግራይ ክልል ያለውን የሰላም ሁኔታ በሚመለከት
በትግራይ ክልል ተጨማሪ ወጊያ እንዲካሄድ አንፈልግም። ከዚያ ይልቅ ተባበረን ሀገር ማልማት ነው የምንፈልገው። ከዚያ ውጭ መንግስትን በሃይል ለመጣል ፍላጎት ካለ እሱ ፈጽሞ ሊሳካ አይችልም። የፌደራል መንግስት ለትግራይ ክልል የሚመድበው በጀት ለልማት ሳይሆን ለታጣቂ እየዋለ ነው። ይህ ትክክል አይደለም። ትግራይ ልማት ያስፈልጋታል። በመሆኑም በሰላማዊ መንገድ በትብበር ለልማት መስራት ይገባል።

7ኛውን ሀገራዊ ምርጫ በተመለከተ
ምርጫውን ለማከናወን መንግስት በቂ አቅምና ዝግጁነት አለው። 7ኛው ሀገራዊ ምርጫ እስካሁን በኢትዮጵያ ከተካሄዱ ምርጫዎች የተሻለ እንደሚሆን ጥርጥር የለውም። ምርጫው ዴሞክራሲያዊና ብዘሃ ድምጾች ያሉት እንዲሆን በሃላፊነት እንሰራለን። እኛ እንደ ፓርቲም፤ እንደ መንግስትም ዝግጁ ነን። ተፎካካሪ ፓርቲዎችም ከወዲሁ መዘጋጀት አለባቸው።

ተቋማዊ ሪፎርም በሚመለከት
በአገልግሎት አሰጣጥ ያለውን እንግልት ለመቀነስ የተጀመረው መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት በሀገር አቀፍ ደረጃ እይሰፋ ነው። አሁን ላይ 18 ማዕከላት አገልግሎት እየሰጡ ነው። ሶስት ማዕከላት ደግሞ በቅርቡ ስራ ይጀምራሉ ተብሎ ይጠበቃል። በተያዘው በጀት ዓመትም ይህን ቁጥር ወደ 100 ለማድረስ እየተሰራ ነው። ይህም በአገልግሎት አሰጣጥ ላይ ከፍተኛ ለውጥ እንደሚያመጣ ይጠበቃል።

ዲጂታላይዜሽንን በሚመለከት
ኢትዮጵያ ውስጥ 2 ነጥብ 4 ሚሊዮን ወጣቶች በነጻ የኮዲንግ ስልጠና ወስደዋል። ይህ ትልቅ ቁጥር ነው። 93 ሚሊዮን ደንበኞች ደግሞ የቴሌኮም አገልግሎት ተጠቃሚ ሲሆኑ 55 ሚሊዮን ዜጎች ደግሞ የሞባይል ባንኪንግ ተጠቃሚ መሆን ችለዋል። ይህ ኢትዮጵያን ዲጂታላይዝ ለማድረግ የጀመረነው ስራ በአጭር ጊዜ ውስጥ ተጨባጭ ለውጥ እያመጣ መሆኑን አመላካች ነው።
የዓባይ ውሃ ፍትሃዊ ተጠቃሚነትን በሚመለከት
ኢትዮጵያ በብሔራዊ ጥቅሟ ላይ ኢ-ፍትሃዊና ኢ-ርታዊ ውሳኔ የተወሰነባት ሀገር ናት። ዓባይን መጠቀም ተፈጥሯዊና ህጋዊ መብቷ ነው። ሃብቱም በጋራ ለመጠቀም በቂ ነው። ኢትዮጵያ አሁንም ያላት አቋም ግልጽ ነው። ግብጻዊያንም ሱዳናዊያንም ወንድሞቻችን ናቸው። ስለዚህ የሚያዋጣው በመነጋገርና በመተባበር በጋራ ማደግ ነው። እኛ ማንንም በሚጎዳ መልኩ አናቅድም አንሰራም።

ቀይ ባህርን በተመለከተ
የቀይ ባህር ጉዳይ ህጋዊ፣ ታሪካዊ፣ መልከዓ ምድራዊና ኢኮኖሚያዊ ጥያቄ ነው ብለን እናምናለን። ይህንን በተረጋጋ መንገድ ማየት ያስፈልጋል። ኢትዮጵያን የቀይ ባህር የማጣት ውሳኔ ማን ወሰነ ብለን ስንፈልግ ተቋማት አልገቡበትም። ይህን የሚያህል የህልውና ጉዳይ ማን እንደወሰነ መጠየቅ ተገቢ ነው። ኢትዮጵያ ተዘግቶባት መኖር አትችልም። ለጎረቤቶቻችን መናገር የምንፈልገው ኢትዮጵያ ስታደግ ለቀጣናውም ልማት ምንጭ ትሆናለች። የምንፈልገው በትብብር ማደግ ነው።

#የጠሚሩምላሾች
#PMOEthiopia
4
በመዲናችን የ2018 ዓ.ም የበጋ በጎ ፈቃድ ፕሮግራም በነገው እለት በይፋ ይከፈታል።

የተለያዩ ሰብዓዊና ማኅበራዊ አገልግሎቶች የተካተቱበት ይህ ፕሮግራም ከ2 ሺህ 500 በላይ በጎ ፈቃደኞች እንዲሁም ባለድርሻ አካላትና ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች በተገኙበት ነው ይፋ የሚደረገው።

በመዲናዋ ባለፈው የክረምት በጎ ፈቃድ መርሀ ግብር 8.2 ቢሊዮን የሚገመት የበጎ ፈቃድ አገልግሎት ተሰጥቷል። በጎ ፈቃደኛ ባለሀብቶችን በማሳተፍ 3 ሺህ 100 የአቅመ ደካሞችና አረጋውያን ቤቶች የተገነቡ ሲሆን 14 ሺህ 724 የኅብረተሰብ ክፍሎች በተገነቡ ቤቶች ተጠቃሚ ሆነዋል።

በዓላትን ምክንያት በማድረግ በተከናወኑ መርሀ ግብሮች 614 ሺህ 269 በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ የሚገኙ ዜጎች ማዕድ ተጋርተዋል።

በነፃ የህክምና አገልግሎት 226 ሺህ 887 ከፍለው መታከም የማይችሉ የመዲናችን ነዋሪዎች ነጻ የህክምና አገልግሎት ያገኙ ሲሆን የባለድርሻ አካላት እና የበጎ ፈቃደኞች ተሳትፎ በማደጉ በክረምት የታቀዱ የበጎ ፈቃድ መርሃ ግብሮች ስኬታማ ነበሩ።

በክረምት የበጎ ፈቃድ አገልግሎት የተገኙ ውጤቶችን በማስቀጠል ለማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ችግሮች የተጋለጡ የኅብረተሰብ ክፍሎችን በዘላቂነት ተጠቃሚ ለማድረግ የበጋ በጎ ፈቃድ ፕሮግራም ልዩ ትኩረት ተሰጥቶት በነገው ዕለት ይፋ ይደረጋል።
10
በማኅበራዊ ድረ ገፆቻችን ቤተሰብ ለመሆን ቀጣዩን ማስፈንጠሪያ ይጫኑ ወይም QR ኮዱን ስካን ያድርጉ!

https://linktr.ee/cpvcc2015
የኀብረተሰብ ተሳትፎና በጎ ፈቃድ ማስተባበሪያ ኮሚሽን - አዲስ አበባ
Photo
የአዲስ አበባን አዲስና ውብ ገፅታ ያላበሱ ሰው ተኮር የልማት ስራዎችን አጠናክሮ መቀጠል እንደሚገባ ተገለፀ።

አዲስ አበባን አዲስና ስሟን የሚመጥን ገፅታ እንዲኖራት እያደረጉ ያሉ የልማት ስራዎችን አጠናክሮ መቀጠል እንደሚገባ የመዲናዋ በጎ ፈቃደኞችና የኅብረተሰብ ተወካዮች ገልፀዋል።

ከሁሉም ክፍለ ከተሞች የተውጣጡ በጎ ፈቃደኞች እና የብሎክ ካውንስል አመራሮች በመዲናዋ በመልሶ ማልማት በማጠናቀቂያ ምዕራፍ ላይ የሚገኘውን የአራዳ ፓርክ ጎብኝተዋል።

የአራዳ ፓርክ በከተማዋ እየተከናወኑ ካሉ የኮሪደር ልማት ፕሮጀክቶች መካከል አንዱ ሲሆን የወንዝ ዳርቻ ልማትን ጨምሮ፣ የንግድ፣ የስፖርት፣ የመዝናኛና ሌሎች ታሪካዊና ዘመናዊ ፕሮጀክቶችን አካቷል።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የኅብረተሰብ ተሳትፎና በጎ ፈቃድ ማስተባበሪያ ኮሚሽን ምክትል ኮሚሽነር ወ/ሮ አስራት ንጉሴ በጉብኝት መርሀ ግብሩ ላይ ተገኝተው ባስተላለፉት መልዕክት በመዲናዋ ነዋሪዎችን ታሳቢ ያደረጉ ሰው ተኮር ማኅበራዊና ኢኮኖሚያዊ ልማቶች እየተከናወኑ መሆኑን ተናግረዋል።

ፒያሳን ጨምሮ ለኑሮ ምቹ ያልሆኑ አካባቢዎችን መልሶ በማልማት ከተማዋ ስሟን የሚመጥን ገፅታ እንድትይዝ ማድረግ መቻሉን የተናገሩት ወ/ሮ አስራት ይህ ተግባር የማይቻሉ የሚመስሉ ጉዳዮችን በመድፈር  በራስ አቅም በአጭር ጊዜ ውስጥ ለውጥ ማምጣት እንደሚቻል የአመራሩና የባለሙያው ቁርጠኝነት የታየበት ውጤታማ ስራ እንደሆነ ገልፀዋል።

የጉብኝቱ ተሳታፊዎች በበኩላቸው አዲስ አበባን አዳዲስ ውብ ገፅታ ያላበሱ የኮሪደር ልማት ውጤቶችን በመመልከታቸው የተሰማቸውን ደስታ ገልፀው መዲናዋን የቱሪዝም መዳረሻ እንድትሆን ለማድረግ የተጀመረውን ሰው ተኮር የልማት እንቅስቃሴ ማስቀጠል እንደሚገባ ጠቁመዋል።

ከከተማዋ የቆዳ ስፋት ውስጥ 5,400 ሄክታር መሬት በኮሪደር እንደለማና ፒያሳን ጨምሮ ከእንጦጦ ፓርክ እስከ ፒኮክ መናፈሻ 1,030 ሄክታር መሬት እንዲሁም 21 ኪ.ሜ የወንዝ ዳርቻ በልማት መሸፈኑን ከከተማዋ የኮሪደርና የወንዝ ዳርቻ ልማት አስተዳደር ባለስልጣን ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።
👍6
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ እና ጠቅላይ ሚኒስትር ናሬንድራ ሞዲ በዛሬው እለት በፓርላማ ተገኝተው የህንድ ጠቅላይ ሚኒስትሩ በየኢፌዴሪ የሕዝብ ተወካዮች እና የፌዴሬሽን ምክር ቤቶች የጋራ ስብሰባ ላይ ንግግር አድርገዋል።

Prime Minister Abiy Ahmed and Prime Minister Narendra Modi in attendance at Parliament today, where the Indian Prime Minister addressed both the House of People’s Representatives and the House of Federation in a joint session.

#PMOEthiopia
5👍1
የበጎ ፈቃድ ማኅበራት ጥምረት 2ኛ ዓመት የስራ ዘመን 1ኛ መደበኛ ጉባዔውን አካሄደ።

የአዲስ አበባ ከተማ የበጎ ፈቃድ ማኅበራት ጥምረት 2ኛ ዓመት የስራ ዘመን 1ኛ መደበኛ ጉባኤውን ዛሬ አካሂዷል። ጥምረቱ የተመሰረተበትን 2ኛ ዓመት ምክንያት በማድረግም ነባር ስራ አስፈፃሚዎችን አዳዲስ ስራ አስፈፃሚ ኮሚቴዎች በመምረጥ ተክቷል።

በጉባዔው ማኅበራቱ ከኮሚሽኑ ጋር ተቀናጅተው ያከናወኗቸው የበጎ ፈቃድ አገልግሎት ሪፖርት ቀርቦ ውይይት ተደርጎበታል። በመዲናዋ የበጎ ፈቃድ ባህል መዳበር የሲቪክ ማህበራት ሚና ከፍተኛ እንደሆነም በውይይቱ ተጠቁሟል፡፡

ጥምረቱ በቀጣይ የስራ አቅጣጫዎች ዙሪያ ውይይት በማድረግ ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የኅብረተሰብ ተሳትፎና በጎ ፈቃድ ማስተባበሪያ ኮሚሽን ጋር የመገባቢያ ሰነድ ተፈራርሟል፡፡

ጥምረቱ በመዲናዋ የሚከናወኑ የበጎ ፈቃድ ስራዎችን በማስተባበርና በጎ ፈቃደኞች እውቀትና ልምድ የሚለዋወጡበት፣ ውጤታማ የበጎነት ስራ መስራት የሚያስችል አደረጃጃት በመሆኑ የተቋቋመበትን ዓለማ ማሳካት እንዲችል ኮሚሽኑ ድጋፍና ክትትል እያደረገ መሆኑን የኮሚሽኑ የበጎ ፈቃድ አገልግሎት ዳይሬክተር አቶ ዳዊት ሙሉጌታ ተናግረዋል፡፡

የመዲናዋ የበጎ ፈቃድ ማህበራት ጥምረት የስራ አስፈጻሚዎች የስራ ዘመን ከ2 ዓመት መብለጥ እንደሌለበትና አዳዲስ አመራሮችን በዲሞክራሲያዊ መንገድ በመተካት በከተማችን ማኅበራዊና ኢኮኖሚያዊ ጉድለቶችን በጋራ መፍታት የሚያስችል አቅምና ምቹ ሁኔታ መፍጠር እንደሚገባ በማህበራቱ የጥምረት ሰነድ ላይ በዝርዝር ተመላክቷል።
3
በቦሌ ክፍለ ከተማ በኅብረተሰቡ ተሳትፎ በመገንባት ላይ የሚገኘው እና 1.3 ኪሎ ሜትር ርዝመት ያለው የውስጥ ለውስጥ አስፓልት መንገድ በመጠናቀቂያ ምዕራፍ ላይ ይገኛል።

በክፍለ ከተማው ወረዳ 7 አስተዳደር በመንግሥት፣ በኅብረተሰቡና በአካባቢው በሚገኙ ኢንዱስትሪዎች ትብብር በመገንባት ላይ የሚገኘው እና 1.3 ኪሎ ሜትር ርዝመት ያለው የውስጥ ለውስጥ የአስፓልት መንገድ የሰቤዝና የውኃ መፋሰሻ ስራ የተጠናቀቀ ሲሆን አስፓልት የማልበስ ስራ ተጀምሯል።

የውስጥ ለውስጥ አስፓልት መንገዱ በአካባቢው ማኅበረሰብ ለረዥም ጊዜ ሲያነሳ የቆየ የመልካም አስተዳደር ጥያቄ ሲሆን ግንባታው በፍጥነት እና በጥራት እንዲጠናቀቅ ክትትል እየተደረገ መሆኑን ከክፍለ ከተማው ኮሙኒኬሽን ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።
4
የኮሚሽኑ ሰራተኞችና በጎ ፈቃደኞች በክረምት የተተከሉ ችግኞችን ተንከባከቡ።

የአዲስ አበባ ከተማ የኅብረተሰብ ተሳትፎና በጎ ፈቃድ ማስተባበሪያ ኮሚሽን ሰራተኞችና የየካ ክፍለ ከተማ በጎ ፈቃደኞች ካዛንችስ በግንፍሌ የወንዝ ዳርቻ በክረምት ወቅት የተተከሉ ችግኞችን ተንከባክበዋል።

በመርሀ ግብሩ ላይ የተገኙት የኮሚሽኑ ዋና ኮሚሽነር አቶ ይመር ከበደ የተተከሉ ችግኞችን የፅድቀት መጠን ለመጨመር እንደኮሚሽን የበጎ ፈቃድ ፕሮግራሞች እቅድ አካል በማድረግ የእንክብካቤ ስራ እየተከናወነ መሆኑን ተናግረዋል።

በጎ ፈቃደኞችና መላው የከተማዋ ነዋሪ የተተከሉ ችግኞች እንዳይደርቁ የእንክብካቤ ስራውን አጠናክሮ እንዲቀጥልም ኮሚሽነሩ ጥሪ አቅርበዋል።

የኮሚሽኑ ሰራተኞች በበኩላቸው በክረምት ወቅት የተከሏቸውን ችግኞች በየጊዜው በመንከባከብ እንዲፀድቁ ለማድረግ እንደሚሰሩ ገልፀዋል።

በሌሎች የማኅበራዊ ሚዲያ አማራጮች ቤተሰብ ለመሆን ማስፈንጠሪያውን ይጫኑ!

https://linktr.ee/cpvcc2015
1