የኀብረተሰብ ተሳትፎና በጎ ፈቃድ ማስተባበሪያ ኮሚሽን - አዲስ አበባ
809 subscribers
2.14K photos
47 videos
265 links
Download Telegram
በመዲናዋ የሚሰሩ አዳዲስ የመንገድ መሠረተ ልማት ስራዎች በዘላቂነት በኮሪደር ልማት ደረጃ እንደሚሰሩ፡- ከንቲባ አዳነች አቤቤ ተናገሩ፡፡

ከንቲባ አዳነች አቤቤ በሁሉም አካባቢዎች የኮሪደር ልማት ስራን ለማዳረስ ምን እንደታቀደ ለቀረበላቸው ጥያቄ በሰጡት ማብራሪያ የመኖሪያ ቤትን ጨምሮ በቂ ዝግጅትን የሚጠይቅ ነው ብለዋል፡፡

በመሆኑም በዚህ ዓመት አዲስ የኮሪደር ልማት ስራዎች እንደማይኖር የገለጹት ከንቲባ አዳነች አቤቤ ነገር ግን በመዲናዋ የሚሰሩ አዳዲስ የመንገድ መሠረተ ልማት ስራዎች በኮሪደር ልማት እስታንዳርድ ዘላቂነት እንዲኖራቸው ተደርጎ ይሰራሉ ብለዋል፡፡
2
በ3ኛው የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት አምስተኛ ዓመት የስራ ዘመን 1ኛ መደበኛ ጉባዔ አቶ ሃፍታይ ገብረእግዚኣብሔር አለማየሁ የአዲስ አበባ ከተማ ኮሙኒኬሽን ቢሮ ኃላፊ አድርጎ በሙሉ ድምፅ አስፅድቋል::
2
3ኛዉ የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት 5ኛ ዓመት የስራ ዘመን 1ኛመደበኛ ጉባዔ ላይ ለተነሱ ጥያቄዎች ምላሽና ማብራሪያ ተሰጥቷል፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ ብልፅግና ቅ/ፅ/ቤት ኃላፊ አቶ ሞገስ ባልቻ ለምክር ቤቱ አባላት በሰጡት ማብራሪያ እና ምላሽ እንደገለፁት ምክር ቤቱ በመደበኛነት እያደረገ ያለዉ ቁጥጥር እና ድጋፍ በበከተማችን ለተመዘገቡ ተጨባጭ ዉጤቶች ማሳያ ነዉ ብለዋል፡፡

የምክር ቤቱ የህዝብ ተወካዮች አባላት ከወከላቸዉ ህዝብ ጋር በሚያደርጉት ተከታታይ ዉይይቶች የሚመጡ አስተያየቶችና ጥያቄዎችን አስፈፃሚዉ አካላት በግብዓትነት ወስዶ በፍጥነት እንዲያርም በመቻሉ በህዝቡና በመንግስት መካከል ጠንካራ ግንኙነት እንዲፈጠር ተችሏል ሲሉ ተናግረዋል፡፡

ሃገራዊና ከተማ አቀፍ የተለያዩ ሃይማኖታዊና ህዝባዊ በዓላት ህዝቡ በነቂስ ወጥቶ የድሉ ባለቤት መሆኑን እና በሰላም ወጥቶ በሰላም በግባት መቻሉ የለዉጣችን ማሳያ የሆነ ሌለኛዉ የከተማዋን ገፅታ የቀየረ እና የፖለቲካ ስብራትን መጠገን የቻለ ድል መሆኑንም ገልፀዋል፡፤

ለዚህም ሶስት አካላት በዋናነት መመስገን የሚገባቸዉና የማይተካ ሚና አላቸዉ ያሉት አቶ ሞገስ ባልቻ የከተማዋ ነዋሪ ፤የፀጥታ መዋቅሩ እና የፖለቲካ አመራሩ ናቸዉ ብለዋል፡፡

የእነዚህን ድምር ዉጤት ስናይ የከተማችንን ገፅታ በመቀየር የከተማችን ተፈላጊነት እንዲጨምር በማድረግ እና ከተማችን ዓለም አቀፋዊ እዉቅና በማግኘት የትኩረት ማእከል እንድትሆን ማስቻሉ ነዉ ብለዋል፡፡

በመጨረሻም ሁለተናዊ የድል ሚስጥሩ የገባነዉን ቃል ወደ ተግባር በመቀየር መስራት የመቻላችን ዉጤት ስለሆነ ይህን አጠናክሮ ማስቀጠልና ትልቁ ህልማችን ላይ መድረስ ይገባል በማለት ለምክር ቤት አባላትና ለከተማዋ ነዋሪ ልባዊ ምስጋናቸዉን አቅርበዋል፡፡
3
በክረምት የመኖሪያ ቤቶች ግንባታ የተለያዩ ባለድርሻ አካላትን በማሳተፍ የ 3ሺህ 400 ቤቶች ግንባታ የተጀመረ ሲሆን ከእነዚህ መካከል የ2ሺህ 500 ቤቶች ግንባታ ተጠናቆ ለአቅመ ደካሞችና ለሃገር ባለዉለታ ዜጎች ተላልፏል፡፡ -ከንቲባ አዳነች አቤቤ
3
ከብልጽግና ፓርቲ ሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባላት ጋር በመሆን የተጠናቀቀውን የሳር ቤት-ጀርመን አደባባይ-ጋርመንት እና ፉሪ አካባቢ የኮሪደር ልማት ሥራ ጎብኝተናል። 589 ሄክታር በላይ የሚሸፍነው ከባቢ ከካዛንቺስ ቀጥሎ ሰፊው የልማት ስፍራ ሆኗል። ፕሮጀክቱ 16.5 ኪሎ ሜትር የአስፋልት መንገድ፣ የ3 ኪሎ ሜትር ተጨማሪ የውስጥ ለውስጥ መንገድ ብሎም 33 ኪሎ ሜትር የተዘረጋ የእግረኛ መንገድ አካትቷል። የፕላዛዎች፣ የስፖርት ማዘውተሪያ ስፍራዎች፣ የሕፃናት መጫወቻዎች እና 5.2 ኪሎ ሜትር የወንዝ ዳርቻ ልማት ሥራ ተከናውኗል። የመኪና ማቆሚያዎች፣ የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎች ኃይል መሙያ ስፍራዎች፣ በግል እና የመንግሥት ተቋማት የተገቡ 1107 ሱቆች በልማት ሥራው የተሠሩ ናቸው። የኮሪደር ልማቱ 50.5 ሄክታር አረንጓዴ ሥፍራ፣ የሕዝብ መጸዳጃዎች፣ 13.3 ኪሎ ሜትር የብስክሌት መጋለቢያ መንገድ፣ 38 የአውቶቡስ እና ታክሲ መጫኛ-ማውረጃዎችን አካትቷል። እንደዚህ ያሉት ሀገራዊ የኮሪደር ልማት ፕሮጀክት ሥራዎች የኢኮኖሚ እንቅስቃሴውን ከማሳደግ ባሻገር የትራፊክ እንቅስቃሴን በማሻሻል፣ ማኅበራዊ መስተጋብርን በማጠንከር ደማቅ ለእንቅስቃሴ ምቹ እና ዘላቂነት ያላቸው የከተማ ሥፍራዎች በመፍጠር ረገድ ዐቢይ ሚና በመጫወት ላይ ይገኛሉ።

Together with members of the Prosperity Party Executive Committee, we visited the completed corridor development project extending from Sar Bet to German Square, the Garment Factory, and the Furi area. Covering more than 589 hectares, it stands as the second largest and widest site after Kazanchis. The project includes the construction of 16.5 km of asphalt roads, an additional 3 km of internal roads, and pedestrian walkways stretching a total of 33 km. It features plazas, sports facilities, children’s playgrounds, and 5.2 km of riverbank development. In addition, there are parking areas and terminals, an electric car charging station, and 1,107 shops built by both private and government entities. The development also encompasses 50.5 hectares of green spaces, public toilets, 13.3 km of bicycle lanes, and 38 taxi and bus bays. Our national corridor development projects like this one are playing a vital role in boosting local economic activity, improving mobility, and enhancing social interaction by creating vibrant, accessible, and sustainable urban spaces.

PM Abiy Ahmed Ali
ዛሬም የረዳን ፈጣሪ የተመሰገነ ይሁን !

ከሳርቤት - ጀርመን አደባባይ- ጋርመነት ፉሪ የሚዘልቀውን የኮሪደር ልማት ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትራችን ዶ/ር ዐቢይ አሕመድ እና የብልፅግና ፓርቲ ስራ አስፈፃሚ አባላት በተገኙበት መርቀን ለአገልግሎት ክፍት አድርገናል ።

ሕዝባችንን በታማኝነት፣ በቅንነት ለማገልገል የገባነውን ቃል ቆጥረን እየተገበርን እንገኛለን። የተሰሩት መሰረተ ልማቶች ከተማችንን ለነዋሪዎቿ ምቹ፣ በዓለም አቀፍ ደረጃ ተወዳዳሪ የሚያደርጋት፣ ለዜጎቻችን ሰፊ የስራ ዕድል የፈጠረ እንዲሁም ዘላቂ ልማትን ለማረጋገጥ መሰረታዊ የሆነ ለዉጥ ማምጣት በሚያስችል መልኩ የተሰራ ነው።

በልማቱ ከመሬት በላይ ከሚታየው እኩል ከመሬት በታች ጭምር የተሰሩ በርካታ ስራዎች የከተማችንን አገልግሎት የሚያሳልጥ፣ በዘላቂነት ስማርት ሲቲ ለማድረግ የሰነቅነዉን ራዕይ ለማሳካት የሚያስችል መሰረታዊ ስራ የተሰራበት፣ ሰፊ የስራ ዕድል የተፈጠረበት ሲሆን፤ ለቱሪዝም ዘርፉ ተጨማሪ እሴት፤ የስበት ማዕከል የሆኑ ፅዳት፣ ውበት፣ አገልግሎትን ያጣመሩ ስራዎችም በስፋት ተሰርተውበታል ።

ይህ የኮሪደር ልማት በሁለተኛ ዙር ከጀመርነው 6ኛዉና ከካዛንቺስ ኮሪደር ቀጥሎ በከተማችን ሁለተኛው ረጅሙ እና ሰፋ ያለ አካባቢ የሚሸፍነው ሲሆን ከ589 ሄክታር በላይ ቦታ የለማበት ነው።

• እስከ 60 ሜትር የሚሰፋ 16.5 ኪ.ሜ አስፓልት መንገድ ( በተጨማሪ 3 .5 ኪ. ሜ የውስጥ ለውስጥ መንገድ) አለው ፣
• 33 ኪ.ሜ የእግረኛ መንገድ ፣
• 13.3 ኪ.ሜ የሳይክል መንገድ ፣
• 21 የተለያዩ ፕላዛዎች ፣
• ክረምት ከበጋ ፣ በቀን እና በምሽት አገልግሎት የሚሰጡ 20 የስፖርት ማዘውተሪያ ስፍራዎች፣
• 20 የልጆች መጫወቻ ቦታዎች ፣
• 5.2 ኪ.ሜ ርዝመት ያለው የወንዝ ዳርቻ ልማት ፣
• 20 የመኪና ማቆሚያ ቦታና ተርሚናሎች ፣ 1 የመኪና ቻርጂንግ ስቴሽን ፣
• በግለሰቦች እና በመንግስት የተገነቡ 1,107 የንግድ ቤቶች ፣
• 50.5 ሄክታር ስፋት ያላቸዉ አረንጓዴ ቦታዎች ፣
• 40 የህዝብ መፀዳጃ ቤቶች ፣
• 38 የታክሲና አውቶቡስ ቤይ ፣
• 13 ካፌዎች እና 1 ሬስቶራንት እንዲሁም ከ 1 ሄክታር በላይ የነርሰሪ ቦታን በዉስጡ አካትቶ ይዟል ።

ይህንን ለከተማችን ተጨማሪ ድምቀት ፣ ለዜጎቻችን መጠነ ሰፊ የስራ እድል እና የእውቀት ሽግግር የፈጠረን ፣ ለነዋሪዎቿ ደግም ምቾትን ያጎናፀፈውን ግዙፍ የኮሪደር ልማት ፕሮጀክት በታለመለት ጊዜ በጥራት እና በፍጥነት እንዲጠናቀቅ ላደረጋችሁ ፣ ከመደበኛ ስራችሁ ጎን ለጎን ሌት ተቀን ለለፋችሁ በየደረጃዉ ያላችሁ የከተማችን አመራሮች፣ ባለሞያዎች፣ እንዲሁም በልማት ስራው ሁልጊዜም የዘወትር ድጋፍ እና ትብብሩ ላልተለየን የአካባቢው ነዋሪ ማህበረሰብ ልባዊ ምስጋናዬን አቀርባለሁ።

ፈጣሪ ኢትዮጵያን እና ሕዝቦቿን ይባርክ
ከንቲባ አዳነች አቤቤ
4
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 6ኛ ዙር፣ 5ኛ ዓመት፣ 2ኛ መደበኛ ስብሰባ ላይ ለሚቀርቡላቸው ጥያቄዎች ምላሽና ማብራሪያ ይሰጣሉ።

Prime Minister Abiy Ahmed will respond to questions and provide explanations during the 6th round, 5th year, 2nd regular session of the House of People's Representatives.

#PMOEthiopia
2
ብዝሃ ዘርፍ ትብብርን በተመለከተ

የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ ከግብርና መር ወደ ብዝሃ ዘርፍ እንዲሸጋገር የተነደፈው ፖሊሲ በእጅጉ ውጤታማ ሆኗል። መንግስት ከህዝብ ጋር ተሳስሮ ልማት እንዲያመጣ ግልጽ አቅጣጫ የተቀመጠውም ከለውጡ ወዲህ ነው። ለአብነትም መንግስትና ህዝብ ተሳስረው በአረንጓዴ አሻራ አማካኝነት 48 ቢሊዮን ችግኞችን መትከል ችለዋል። ለዚህ ስኬት ደግሞ ከ25 ሚሊዮን በላይ ኢትዮጵያዊያን ሳይታክቱ በነጻ በየ ዓመቱ ወጥተው ችግኞችን መትከል ችለዋል። ይህም የመንግስትና ህዝብ ቅንጅትን በተግባር ያሳየ ነው።

#የጠሚሩምላሾች
#PMOEthiopia
የእዳ ሽግሽግን በተመለከተ

ኢትዮጵያ አሁን ላይ እዳዋን ለመክፈል ምንም ችግር የለባትም። በሪፎርሙ አመካኝነት ከ4 አስከ 4 ነጥብ 5 ቢሊዮን ዶላር የሚደርስ የእዳ ሽግሽግ ተደርጓል። ሀገራዊ ለውጡን ተከትሎም መንግስት አንድም ዶላር የንግድ ብድር አልወሰደም። ይህም እዳን ለመቆጣጠር ያለንን ጽኑ አቋም ያሳያል።

#የጠሚሩምላሾች
#PMOEthiopia
ግብርናን በተመለከተ

የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ ሪፎርም በሁሉም መመዘኛዎች ከፍተኛ ለውጥ በፍጥነት ማስመዝገብ ችሏል። ለአብነትም ግብርና ብቻውን የ7 ነጥብ 3 በመቶ እድገት አስመዝግቧል።

በምርት ደረጃም ሩዝን ወስደን ብናይ ከነበረበት 1 ነጥብ 5 ሚሊዮን ኩንታል ወደ 63 ኩንታል ማሳደግ የተቻለ ሲሆን የስንዴ ምርትንም ከለውጡ በፊት ከነበረበት 47 ሚሊዮን ኩንታል ወደ 280 ሚሊዮን ኩንታል በአጠረ ጊዜ ውስጥ አሳድግነዋል።

#የጠሚሩምላሾች
#PMOEthiopia
ገቢን በተመለከተ

ያለፈው በጀት ዓመት ኢትዮጵያ በታሪኳ ከፍተኛ ገቢ ያገኘችበት ነው። ለአብነትም ከሸቀጦች ወጪ ንግድ 8 ነጥብ 3 ቢሊዮን ዶላር ተገኝቷል። ከሬሚታንስ 7 ነጥብ 4 ቢሊዮን ብር ገቢ የተገኘ ሲሆን ገቢ ምርቶችን በሀገር ውስጥ በመተካትም በቢሊዮን ዶላር ማዳን ተችሏል። በዚህም የኢትዮጵያ ሪዘርቭ በ10 እጥፍ አድጓል።

#የጠሚሩምላሾች
#PMOEthiopia