3ተኛዉ የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት 5ኛ ዓመት የስራ ዘመን 1ኛመደበኛ ጉባዔ ላይ ለተነሱ ጥያቄዎች ምላሽና ማብራሪያ ተሰጥቷል፡፡
በምክትል ከንቲባ ማእረግ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ፐብሊክ ሰርቪስና የሰዉ ሃብት ልማት ቢሮ ኃላፊ ዶ/ር ጀማሉ ጀምበር በሰጡት ማብራሪያ እና ምላሽ እንደገለፁት የአገልግሎት አሰጣጥን በማዘመን የተገልጋዩን እርካታ ለማረጋገጥ ከከተማ አስተዳደሩ ጋር ልዩ ትኩረት ተሰጥቶ እየተሰራ ይገኛል ብለዋል፡፡
በከተማችን በቅርቡ ተመርቀዉ ወደስራ የገቡት አዲስ የመሶብ የአንድ ማዕከል ዲጂታል አገልግሎት ለዚህ ማሳያ ነዉ ሲሉ ተናግረዋል፡፡
በዚህ የአንድ ማዕከል አገልግሎት ሰፊ አገልግሎት እና ሰፊ ተገልጋይ እንዲሁም ቅሬታ የሚበዛባቸዉ ተቋማት በመለየት አደረጃጀትን እና አሰራርን በመዘርጋት እንዲሁም ምቹ ሁኔታዎችን በመፍጠር ወደ ትግበራ መግባት መቻሉን ጠቁመዋል፡፡
በዋና መስሪያ ቤት በአራዳ ክፍለ ከተማ 13 የሚሆኑ የከተማ አስተዳደሩ ተቋማት 107 አገልግሎቶችን በመያዝ የተለዩ የፌደራል ተቋማትን በማካተት እየተሰራ አንደሚገኝም ተናግረዋል፡፡
በተመሳሳይም በቦሌ ክፍለ ከተማ በአዲስ የመሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት 12 የከተማ አስተዳደሩ ተቋማት 96 አገልግሎቶችን እንዲሁም የተለዩ የፌደራል ተቋማትን በማካተት በጥቅሉ 114 አገልግሎቶች እንዲገቡ ተደርጓል፤
በአመለካከት ፣በእዉቀት እና በክህሎት የበቁ ነባርና አዳዲስ ተመረቂ ባለሙያዎችን በማሰልጠንና በመመደብ ፤የቅሬታ አፈታት ስርዓትን በማዘመን ፤ከተቋማት ጋር በቅንጅት በመስራት ይፈጠራሉ ተብለዉ የሚገመቱ ችግሮችን ከወዲሁ ለማረም የተቻለበት ሁኔታ ተፈጥሯል ብለዋል፡፡
በዚህም ከየትኛዉም በኩል የሚመጡ የዜጎች ምልልስ በማስቀረት፤ወጪና ጊዜን በመቆጠብ የተገልጋይን እርካታ ከፍ ማድረግ የተቻለበት ሁኔታ መፈጠሩን ዶ/ር ጀማሉ ጀምበር ተናግረዋል፡፡
ይህም ከከተማ አስተዳደሩ ጋር በሌሎች ክፍለ ከተሞች ለማስፋፋት እቅድ ተይዞ በልዩ ትኩረት በቅንጅት እንደሚሰራ ገልፀዋል፡፡
በሌላ በኩልም አዲሱ የደመወዝ ጭማሪ በተመለከተ ለተነሳላቸዉ ጥያቁ ቅድመ ዝግጅት ስራዎች መጠናቀቃቸዉና ክፍያዉ በቅርቡ ሙሉ በሙሉ ተግባራዊ እንደሚሆን አመላክተዋል ::

❤2
በከተማዋ የተከናወኑ ሁነቶች እና አበይት የአደባባይ በዓላት ስኬት ከህዝቡ ጋር በጋራ በመሰራቱ የተገኘ ውጤት መሆኑን ከንቲባ አዳነች አቤቤ ገለፁ
3ኛው የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት 5ኛ ዓመት የስራ ዘመን 1ኛ መደበኛ ጉባኤውን እያካሄደ ይገኛል ፡፡
በጉባኤው የተለያዩ የምክር ቤት አባላት ምላሽና ማብራሪያ ያስፈልጋቸዋል ያሉትን ጥያቄና አስተያየት አቅርበዋል ፡፡
የምክር ቤት አባላት ያቀረቧቸውን ጥያቄ የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ አዳነች አቤቤ ምላሽ እየሰጡ ይገኛሉ ፡፡
አዲስ አበባ ላይ በተሰሩና እየተሰሩ ባሉ የኮሪደር ልማት ከተማዋ ዓለም ዓቀፍ ጉባኤዎችን የማዘጋጀት ዓቅሟ እያደገ መጥቷል፤ በእነዚህ ጉባኤዎችና በመስከረም ወር የተከናወኑ ዓበይት የአደባባይ በዓላት በከተማዋ የተከናወኑበት ወር ሲሆን እነዚህ ሁነቶች በድምቀት ተከብረው አልፈዋል ለዚህ ሰኬት የተሰሩ ስራዎች ምንድናቸው ለሚለው የምክር ቤት አባላት ጥያቄ ከንቲባዋ ምላሽ ሰጥተዋል፡፡
ለበዓላቱና ለሁነቶቹ ስኬት ከህዝቡና ከባለድርሻ አካላት ጋር ውይይት በማድረግ ግልፅነት በመፍጠር ወደ ስራ መገባቱን ነው ከንቲባ አዳነች አቤቤ የገለፁት፡፡
በተለይ በተከናወኑ ጉባኤዎች፣ ሆቴሎች የአገልግሎት ጥራትን በማሳደግ እና ክፍያን ተመጣጣኝ በማድረግ ላደረጉት ትብብር ምስጋና ይገባል ሲሉ ከንቲባዋ ገልፀዋል፡፡
ህዝቡ አጠቃላይ እንግዶቹን በኢትዮጵያዊ አንግዳ ተቀባይነት ያደረገው ተሳትፎ የሚደነቅ ነው ያሉት ከንቲባዋ፤ በከተማዋ የተከናወኑ ሁነትና የአደባባይ በዓላት አብሮነትን እና አንድነትን በተግባር ያሳዩ ናቸው ሲሉ ገልፀዋል፡፡
ህዝቡ መሰረተ ልማቶች የኔ ናቸው ብሎ በመንቀሳቀሱ በከተዋማ በተከበሩ በርካታ ዓበይት በዓላት እና ሁነቶች አንድም የተበላሸ የኮሪደር ልማት አለመኖሩን የገለፁት ከንቲባዋ ይህም በሌሎቹ ስራዎች ተጠናክሮ ይቀጥላል ሲሉ ማብራሪያ ሰጥተዋል፡፡

ክብርት ከንቲባ አዳነች አቤቤ የኑሮ ውድነት ጫና ለማቃለል የሚደረገውን ብርቱ ጥረት በተመለከተ የሰጡት ማብራሪያ :-
👉በበዓላት ወቅት የሚፈጠሩ የዋጋ ውድነቶችን ለመከላከል አቅደን ሰርተናል።
👉በታላላቅ የገበያ ማዕከላት የምርት እጥረት እንዳይኖር ተሰርቷል።
👉በክቡር ጠ/ሚ ዶ/ር ዐብይ አህመድ አቅጣጫ መሰረት ምርቶች ከሁለም ክፍሎች እንዲገቡ ከማህበራት በጋራ እየተሰራ ነው።
👉የንግድ ኮርፖሬሽንን የማጠናከር ስራ ተሰርቷል። የእሁዱ ገበያ እና የምገባ ማዕከላትን ማጠናከር ስራ ተከናውኗል። 500 ሺህ ለሚሆኑ ነዋሪዎችም የማዕድ ማጋራት ስራ ባለሀብቶችን በማሳተፍ ተከናውኗል። የዳቦ ዋጋንም በመደጎም ለህዝባችን ማሻሻል ተችሏል።
👉የእሁድ ገበያን ለማጠናከርም ብርቱ ስራዎች ተሰርተዋል ፤ ክፍተቶች እንዲታረሙ ይሰራል።
👉የጤና መድህን ፣ ትራንስፖርት ወዘተ 14 ቢሊዮን ብር የድጎማ በጀት ተይዞ እየተሰራ ሲሆን በዋንኛነት ግን የህዝባችንን ህይወት በዘላቂነት ለማሻሻል እየተሰራ ነው፡፡

በመዲናዋ የሚሰሩ አዳዲስ የመንገድ መሠረተ ልማት ስራዎች በዘላቂነት በኮሪደር ልማት ደረጃ እንደሚሰሩ፡- ከንቲባ አዳነች አቤቤ ተናገሩ፡፡
ከንቲባ አዳነች አቤቤ በሁሉም አካባቢዎች የኮሪደር ልማት ስራን ለማዳረስ ምን እንደታቀደ ለቀረበላቸው ጥያቄ በሰጡት ማብራሪያ የመኖሪያ ቤትን ጨምሮ በቂ ዝግጅትን የሚጠይቅ ነው ብለዋል፡፡
በመሆኑም በዚህ ዓመት አዲስ የኮሪደር ልማት ስራዎች እንደማይኖር የገለጹት ከንቲባ አዳነች አቤቤ ነገር ግን በመዲናዋ የሚሰሩ አዳዲስ የመንገድ መሠረተ ልማት ስራዎች በኮሪደር ልማት እስታንዳርድ ዘላቂነት እንዲኖራቸው ተደርጎ ይሰራሉ ብለዋል፡፡

3ኛዉ የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት 5ኛ ዓመት የስራ ዘመን 1ኛመደበኛ ጉባዔ ላይ ለተነሱ ጥያቄዎች ምላሽና ማብራሪያ ተሰጥቷል፡፡
የአዲስ አበባ ከተማ ብልፅግና ቅ/ፅ/ቤት ኃላፊ አቶ ሞገስ ባልቻ ለምክር ቤቱ አባላት በሰጡት ማብራሪያ እና ምላሽ እንደገለፁት ምክር ቤቱ በመደበኛነት እያደረገ ያለዉ ቁጥጥር እና ድጋፍ በበከተማችን ለተመዘገቡ ተጨባጭ ዉጤቶች ማሳያ ነዉ ብለዋል፡፡
የምክር ቤቱ የህዝብ ተወካዮች አባላት ከወከላቸዉ ህዝብ ጋር በሚያደርጉት ተከታታይ ዉይይቶች የሚመጡ አስተያየቶችና ጥያቄዎችን አስፈፃሚዉ አካላት በግብዓትነት ወስዶ በፍጥነት እንዲያርም በመቻሉ በህዝቡና በመንግስት መካከል ጠንካራ ግንኙነት እንዲፈጠር ተችሏል ሲሉ ተናግረዋል፡፡
ሃገራዊና ከተማ አቀፍ የተለያዩ ሃይማኖታዊና ህዝባዊ በዓላት ህዝቡ በነቂስ ወጥቶ የድሉ ባለቤት መሆኑን እና በሰላም ወጥቶ በሰላም በግባት መቻሉ የለዉጣችን ማሳያ የሆነ ሌለኛዉ የከተማዋን ገፅታ የቀየረ እና የፖለቲካ ስብራትን መጠገን የቻለ ድል መሆኑንም ገልፀዋል፡፤
ለዚህም ሶስት አካላት በዋናነት መመስገን የሚገባቸዉና የማይተካ ሚና አላቸዉ ያሉት አቶ ሞገስ ባልቻ የከተማዋ ነዋሪ ፤የፀጥታ መዋቅሩ እና የፖለቲካ አመራሩ ናቸዉ ብለዋል፡፡
የእነዚህን ድምር ዉጤት ስናይ የከተማችንን ገፅታ በመቀየር የከተማችን ተፈላጊነት እንዲጨምር በማድረግ እና ከተማችን ዓለም አቀፋዊ እዉቅና በማግኘት የትኩረት ማእከል እንድትሆን ማስቻሉ ነዉ ብለዋል፡፡
በመጨረሻም ሁለተናዊ የድል ሚስጥሩ የገባነዉን ቃል ወደ ተግባር በመቀየር መስራት የመቻላችን ዉጤት ስለሆነ ይህን አጠናክሮ ማስቀጠልና ትልቁ ህልማችን ላይ መድረስ ይገባል በማለት ለምክር ቤት አባላትና ለከተማዋ ነዋሪ ልባዊ ምስጋናቸዉን አቅርበዋል፡፡

❤3
#የሕይወት_ልምድ ክፍል 1 በዩቱዩብ ቻናላችን ይከታተሉን!
አቶ አሸናፊ ታዬ ለወጣቶች የሰጡትን የሕይወት ዘመን ተሞክሮ እነሆ!
https://youtu.be/ccp2doVIC0I?si=NElTBnhAbk-sAC1Q

YouTube
የሕይወት ልምዴን ለአዲሱ ትውልድ -ራስን መቀየር ለትውልድ መትረፍ
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ኅብረተሰብ ተሳትፎና በጎ ፈቃድ ማስተባባሪያ ኮሚሽን በበጎ ፈቃድ ዘርፍ ከሚሰራቸው ስራዎች አንዱ የስኬታማ ሰዎችን ልምድ ማካፈያ መድረክ ማዘጋጀት ነው፡፡ በዚህ መሠረት አቶ አሸናፊ ታዬ የዩኒቨርሲቲ ሌክቸርና የዲፓርትመንት መሪ የነበሩ፣ የራሳቸውን ድርጅት መስርተው በአስተሳሰብና በሕይወት ክህሎት ዘርፍ የማማከርና ስልጠና በመስጠት ላይ የሚገኙ ናቸው፡፡ ከዚህ በተጨማሪ…
ከብልጽግና ፓርቲ ሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባላት ጋር በመሆን የተጠናቀቀውን የሳር ቤት-ጀርመን አደባባይ-ጋርመንት እና ፉሪ አካባቢ የኮሪደር ልማት ሥራ ጎብኝተናል። 589 ሄክታር በላይ የሚሸፍነው ከባቢ ከካዛንቺስ ቀጥሎ ሰፊው የልማት ስፍራ ሆኗል። ፕሮጀክቱ 16.5 ኪሎ ሜትር የአስፋልት መንገድ፣ የ3 ኪሎ ሜትር ተጨማሪ የውስጥ ለውስጥ መንገድ ብሎም 33 ኪሎ ሜትር የተዘረጋ የእግረኛ መንገድ አካትቷል። የፕላዛዎች፣ የስፖርት ማዘውተሪያ ስፍራዎች፣ የሕፃናት መጫወቻዎች እና 5.2 ኪሎ ሜትር የወንዝ ዳርቻ ልማት ሥራ ተከናውኗል። የመኪና ማቆሚያዎች፣ የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎች ኃይል መሙያ ስፍራዎች፣ በግል እና የመንግሥት ተቋማት የተገቡ 1107 ሱቆች በልማት ሥራው የተሠሩ ናቸው። የኮሪደር ልማቱ 50.5 ሄክታር አረንጓዴ ሥፍራ፣ የሕዝብ መጸዳጃዎች፣ 13.3 ኪሎ ሜትር የብስክሌት መጋለቢያ መንገድ፣ 38 የአውቶቡስ እና ታክሲ መጫኛ-ማውረጃዎችን አካትቷል። እንደዚህ ያሉት ሀገራዊ የኮሪደር ልማት ፕሮጀክት ሥራዎች የኢኮኖሚ እንቅስቃሴውን ከማሳደግ ባሻገር የትራፊክ እንቅስቃሴን በማሻሻል፣ ማኅበራዊ መስተጋብርን በማጠንከር ደማቅ ለእንቅስቃሴ ምቹ እና ዘላቂነት ያላቸው የከተማ ሥፍራዎች በመፍጠር ረገድ ዐቢይ ሚና በመጫወት ላይ ይገኛሉ።
Together with members of the Prosperity Party Executive Committee, we visited the completed corridor development project extending from Sar Bet to German Square, the Garment Factory, and the Furi area. Covering more than 589 hectares, it stands as the second largest and widest site after Kazanchis. The project includes the construction of 16.5 km of asphalt roads, an additional 3 km of internal roads, and pedestrian walkways stretching a total of 33 km. It features plazas, sports facilities, children’s playgrounds, and 5.2 km of riverbank development. In addition, there are parking areas and terminals, an electric car charging station, and 1,107 shops built by both private and government entities. The development also encompasses 50.5 hectares of green spaces, public toilets, 13.3 km of bicycle lanes, and 38 taxi and bus bays. Our national corridor development projects like this one are playing a vital role in boosting local economic activity, improving mobility, and enhancing social interaction by creating vibrant, accessible, and sustainable urban spaces.
PM Abiy Ahmed Ali

ዛሬም የረዳን ፈጣሪ የተመሰገነ ይሁን !
ከሳርቤት - ጀርመን አደባባይ- ጋርመነት ፉሪ የሚዘልቀውን የኮሪደር ልማት ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትራችን ዶ/ር ዐቢይ አሕመድ እና የብልፅግና ፓርቲ ስራ አስፈፃሚ አባላት በተገኙበት መርቀን ለአገልግሎት ክፍት አድርገናል ።
ሕዝባችንን በታማኝነት፣ በቅንነት ለማገልገል የገባነውን ቃል ቆጥረን እየተገበርን እንገኛለን። የተሰሩት መሰረተ ልማቶች ከተማችንን ለነዋሪዎቿ ምቹ፣ በዓለም አቀፍ ደረጃ ተወዳዳሪ የሚያደርጋት፣ ለዜጎቻችን ሰፊ የስራ ዕድል የፈጠረ እንዲሁም ዘላቂ ልማትን ለማረጋገጥ መሰረታዊ የሆነ ለዉጥ ማምጣት በሚያስችል መልኩ የተሰራ ነው።
በልማቱ ከመሬት በላይ ከሚታየው እኩል ከመሬት በታች ጭምር የተሰሩ በርካታ ስራዎች የከተማችንን አገልግሎት የሚያሳልጥ፣ በዘላቂነት ስማርት ሲቲ ለማድረግ የሰነቅነዉን ራዕይ ለማሳካት የሚያስችል መሰረታዊ ስራ የተሰራበት፣ ሰፊ የስራ ዕድል የተፈጠረበት ሲሆን፤ ለቱሪዝም ዘርፉ ተጨማሪ እሴት፤ የስበት ማዕከል የሆኑ ፅዳት፣ ውበት፣ አገልግሎትን ያጣመሩ ስራዎችም በስፋት ተሰርተውበታል ።
ይህ የኮሪደር ልማት በሁለተኛ ዙር ከጀመርነው 6ኛዉና ከካዛንቺስ ኮሪደር ቀጥሎ በከተማችን ሁለተኛው ረጅሙ እና ሰፋ ያለ አካባቢ የሚሸፍነው ሲሆን ከ589 ሄክታር በላይ ቦታ የለማበት ነው።
• እስከ 60 ሜትር የሚሰፋ 16.5 ኪ.ሜ አስፓልት መንገድ ( በተጨማሪ 3 .5 ኪ. ሜ የውስጥ ለውስጥ መንገድ) አለው ፣
• 33 ኪ.ሜ የእግረኛ መንገድ ፣
• 13.3 ኪ.ሜ የሳይክል መንገድ ፣
• 21 የተለያዩ ፕላዛዎች ፣
• ክረምት ከበጋ ፣ በቀን እና በምሽት አገልግሎት የሚሰጡ 20 የስፖርት ማዘውተሪያ ስፍራዎች፣
• 20 የልጆች መጫወቻ ቦታዎች ፣
• 5.2 ኪ.ሜ ርዝመት ያለው የወንዝ ዳርቻ ልማት ፣
• 20 የመኪና ማቆሚያ ቦታና ተርሚናሎች ፣ 1 የመኪና ቻርጂንግ ስቴሽን ፣
• በግለሰቦች እና በመንግስት የተገነቡ 1,107 የንግድ ቤቶች ፣
• 50.5 ሄክታር ስፋት ያላቸዉ አረንጓዴ ቦታዎች ፣
• 40 የህዝብ መፀዳጃ ቤቶች ፣
• 38 የታክሲና አውቶቡስ ቤይ ፣
• 13 ካፌዎች እና 1 ሬስቶራንት እንዲሁም ከ 1 ሄክታር በላይ የነርሰሪ ቦታን በዉስጡ አካትቶ ይዟል ።
ይህንን ለከተማችን ተጨማሪ ድምቀት ፣ ለዜጎቻችን መጠነ ሰፊ የስራ እድል እና የእውቀት ሽግግር የፈጠረን ፣ ለነዋሪዎቿ ደግም ምቾትን ያጎናፀፈውን ግዙፍ የኮሪደር ልማት ፕሮጀክት በታለመለት ጊዜ በጥራት እና በፍጥነት እንዲጠናቀቅ ላደረጋችሁ ፣ ከመደበኛ ስራችሁ ጎን ለጎን ሌት ተቀን ለለፋችሁ በየደረጃዉ ያላችሁ የከተማችን አመራሮች፣ ባለሞያዎች፣ እንዲሁም በልማት ስራው ሁልጊዜም የዘወትር ድጋፍ እና ትብብሩ ላልተለየን የአካባቢው ነዋሪ ማህበረሰብ ልባዊ ምስጋናዬን አቀርባለሁ።
ፈጣሪ ኢትዮጵያን እና ሕዝቦቿን ይባርክ
ከንቲባ አዳነች አቤቤ

❤4