የኀብረተሰብ ተሳትፎና በጎ ፈቃድ ማስተባበሪያ ኮሚሽን - አዲስ አበባ
818 subscribers
2.14K photos
47 videos
265 links
Download Telegram
“የህዳሴ ግድባችን :- የኢትዮዽያ ልጆች ከሃሳብ አመንጪነት እስከ ፈፃሚነት በላብ ፣ በደምና አጥንት መስዋትነት የገነቡት የሉአላዊነታችን መሰረት ነዉ “

#ኢትዮጵያ ችላለች #GERD #Ethiopia #addisababa
የኀብረተሰብ ተሳትፎና በጎ ፈቃድ ማስተባበሪያ ኮሚሽን - አዲስ አበባ
Photo
“ የህዳሴ ግድብ ነገ የሚኖረንን የብርሃን ቀንዲል የሚያሳይ ታላቅ ገድል ነው “
ፕሬዝዳንት ታዬ አጽቀሥላሴ

የህዳሴ ግድቡ ትናንት የነበረውን የኢትዮጵያ የመንፈስ ጥንካሬ የሚያረጋግጥ፣ ዛሬ ያለንን ጥበብ እና ብልሃት የሚቃኝ ፣ ነገ የሚኖረንን የብርሃን ቀንዲል የሚያሳይ ታላቅ ገድል ነው ሲሉ ፕሬዝዳንት ታዬ አጽቀሥላሴ ተናግረዋል፡፡

ታላቁ የሕዳሴ ግድብ ግንባታ ተጠናቆ መመረቁን ተከትሎ ''ኢትዮጵያ ችላለች'' በሚል መሪ ቃል በአዲስ አበባ ከፍተኛ ሕዝባዊ የድጋፍ እና የምስጋና ሰልፍ ተካሂዷል።

ፕሬዝዳንት ታዬ አጽቀሥላሴ በዚሁ ወቅት ባደረጉት ንግግር፤ የህዳሴ ግድብ ሃሳባዊ ሃይሉ ብርቱ፤ መልእክቱም እንችላለን ነው ብለዋል፡፡

የህዳሴ ግድብ የኢትዮጵያን የመንፈስ ጥንካሬ የሚያረጋግጥ፣ ዛሬ ያለንን ጥበብ እና ብልሃት የሚቃኝ ፣ ነገ የሚኖረንን የብርሃን ቀንዲል የሚያሳይ ታላቅ ገድል ነው ሲሉም ተናግረዋል፡፡

#ኢትዮጵያ ችላለች #GERD #Ethiopia #addisababa
1
በ2017 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ማጠናቀቂያ ፈተና 8.4 በመቶ ተማሪዎች 50 በመቶ እና ከዚያ በላይ አምጥተዋል - ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ
***

በ2017 ዓ.ም ትምህርት ዘመን የ12ኛ ክፍል ማጠናቀቂያ ፈተና 8.4 በመቶ ተማሪዎች 50 በመቶ እና ከዚያ በላይ ውጤት ማስመዝገባቸውን የትምህርት ሚኒስትሩ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ ገለጹ፡፡

ሚኒስትሩ የትምህርት ዘመኑን የ12ኛ ክፍል ማጠናቀቂያ ፈተና ውጤትን አስመልክተው መግለጫ እየሰጡ ይገኛሉ፡፡

50 በመቶ እና ከዚያ በላይ ውጤት ካስመዘገቡት መካከል የማኅበራዊ ሳይንስ ተፈታኞች 5.2 በመቶ፣ ተፈጥሮ ሳይንስ ተፈታኞች ደግሞ 11.4 በመቶ የ እንደሆኑ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ጠቅሰዋል፡፡

585 ሺህ 882 ተማሪዎች ፈተናውን ተፈትነዋል፡፡

#addisababa #Ethiopia
2
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የዓለም የአቶሚክ ሳምንት (World Atomic Week) ጉባኤ ለመሳተፍ ሩሲያ ገብተዋል።

Prime Minister Abiy Ahmed is currently attending the World Atomic Week conference in Moscow, Russia.

#PMOEthiopia
👍2
ከአለም አቀፍ የአቶሚክ ፎረም ጎን ለጎን ከቤላሩስ ፕሬዝዳንት አሌክሳንደር ሉካሼንኮ ጋር በሁለትዮሽና አለም አቀፍ ጉዳዮች ላይ ውይይት አድርገናል።
በተጨማሪም የግብርና ሜካናይዜሽንን ጨምሮ በተለያዩ የኢንቨስትመንት ጉዳዮች ላይ በጋራ የምንሰራበት ሁኔታን ተመልክተናል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)
👍2
“አላማችን ግልፅ ነው፡ አስተማማኝ፣ ግልፅ እና አርአያነት ያለው የኑክሌር ፕሮግራም ለኢትዮጵያ ብሩህ የወደፊት ጊዜ" ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በዓለም አቀፍ የአቶሚክ ፎረም ላይ ያደረጉት ንግግር.
Abiy Ahmed Ali
3
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ከፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን ጋር የኃይል ማመንጫ፣ ግብርና፣ የጤና ጥበቃ ልማት እና የመከላከያ ትብብርን ጨምሮ ሰፊ ጉዳዮች ላይ ተወያይተዋል። ውይይቱ ለማኅበረሰብ አገልግሎት የሚውል ንፁህ ኃይል ምንጭ የሚውል የጋራ የኒኩሊየር ኃይል ማመንጫ የማልማት ስምምነቶችን ጨምሮ የጋራ ፍላጎት በሆኑ ጉዳዮች ላይ ተካሂዷል።

Prime Minister Abiy Ahmed held talks with President Vladimir Putin on a wide range of issues, including energy, agriculture, healthcare development, and defense cooperation. The discussions also covered shared interests including the signing of agreements to jointly develop a nuclear power plant for clean energy and social utility.

#PMOEthiopia
2👍1
ዛሬ በአቃቂ ቃሊቲ ክፍለከተማ እጅግ የተጎሳቆሉ ቤቶችን በማፍረስ የገነባናቸውን 253 ቤቶች የቅድሚያ ቅድሚያ ለሚገባቸዉ የሀገር ባለውለታዎች፣ ሀገር ሲያገለግሉ ለማህበራዊ ችግር ለተጋለጡ የአልጋ ቁራኛዎች፣ ጧሪ ደጋፊ ለሌላቸዉ የህብረተሰብ ክፍሎች አስተላልፈናል ።

ባለፈዉ እሁድ ያስተላለፍናቸው ላይ የዛሬው 253 ቤቶች ሲጨመሩ እሰከአሁን በዘንድሮው የክረምት የበጎ ፈቃድ አገልግሎት በ 3 ወራት ጊዜ ውስጥ ከገነባናቸው 3 ሺህ በላይ ቤቶች ውስጥ 1 ሺህ 924 ቤቶችን የቅድሚያ ቅድሚያ ለሚገባቸው ወገኖቻችን ማስተላለፍ ችለናል።

ቤቶቹ የጸዱ፣ መሰረታዊ ግብአቶች የተሟሉላቸዉ፣ ዘመናዊ እና ጤናማ የአኗኗር ዘይቤን የሚፈጥሩ፣ የራሳቸው ቅጥር ጊቢና የጋራ መገልገያዎች ያላቸው፣ የህፃናት መዝናኛና መጫወቻ እንዲሁም የንግድ ሱቆችን ያካተቱ ናቸው።

ይህንን የበጎ ፈቃድ ተግባር ከጎናችን ሆናችሁ ለምትደግፉ ልበ ቀናዎች እና ያተባበራችሁ የከተማችን አመራሮች በሙሉ በተጠቃሚዎች ስም ምስጋናዬ ይድረሳችሁ።

ፈጣሪ ኢትዮጵያንና ሕዝቦቿን ይባርክ

መልካም የመስቀል ደመራ በዓል
ከንቲባ አዳነች አቤቤ
6👍1👏1
ዛሬ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ክቡር አቶ ተመስገን ጥሩነህ እና ሌሎችም ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች በተገኙበት በአይነቱ የመጀመሪያ እና እጅግ ዘመናዊ የሆነዉን የህፃናትና ወጣቶች ቴአትርና ሲኒማ ኮምፕሌክስን መርቀን ስራ አስጀምረናል ።

የከተማችን አስተዳደር በሚሰራቸዉ የልማት ስራዎች ሁሉ ኪነ ጥበብን አበይት የትኩረት አቅጣጫዉ አድርጎ እየተገበረ ይገኛል ።በዚህም ባለፉት ጥቂት አመታት ነባሮቹን በማደስ እና ዘመናዊ እና ደረጃቸዉን የጠበቁ እንዲሆኑ በማድረግ እንዲሁም አዳዲስ እና ዘመኑን የዋጁ ቴክኖሎጂ የተገጠመላቸዉ የቲያትርና የሲኒማ ኮምፕሌክሶች ገንብተን ለኪነ ጥበብ ዘርፉ እድገት አስተዋፆ እያበረከትን እንገኛለን ።

ዛሬ ያስመረቅነዉ የህፃናትና ወጣቶች ቴአትርና ሲኒማ ኮምፕሌክስ ፦
ባለ14 ወለል ህንፃ ፣2 ዘመናዊ ሲኒማ ቤቶችን
፣የቲያትር አዳራሽ ፣ 3 የተለያዩ አዳራሾችን ፣ የሆቴል እና ሪስቶ ራት ዘመናዊ ካፍቴሪያዎችን እና ፓርኪንግ አገልግሎት ይዟል ።

የጥበብ ስራ በአዳራሽ ብቻ የተወሰነ ባለመሆኑ እና ወደ ማህበረሰቡ ቀረብ እንዲል በከተማችን በተገበርነዉ ሁለንተናዊ ለዉጥ የተለያዩ የዉጭ የኪነ ጥበብ ስራ የሚከወንባቸዉ ከ 160 በላይ አንፊ ቲአትርና ፕላዛዎችን ገንብተን ለአገልግሎት አዉለናል ።

የኪነ ጥበብ ዘርፉ በፈጠረዉ ምቹ ሁኔታ የዉስጥ ቁጭትን በመፍጠር ትዉልድን በመልካም ስራ እንድናንፅ ከወዲሁ ጥሪዬን አቀርባለዉ ።

ፈጣሪ ኢትዮዽያንና ሕዝቦቿን ይባርክ
ከንቲባ አዳነች አቤቤ
1👍1
የሆረ ፊንፊኔ ኢሬቻ አከባበር ባህላዊ እሴቱን ጠብቆ እጅግ በደመቀና ባማረ ሁኔታ ተጠናቅቋል ።

የሆረ ፊንፊኔ እሬቻ ክብረ በዓል የኦሮሞ ህዝብ ብቻ ሳይሆን በርካታ ብሔር ብሔረሰቦች፣ የተለያዩ አገራት ጎብኚዎች፣ የባህልና ታሪክ ተመራማሪዎች በታደሙበት በልዩ ሁኔታ ደምቆ ፍፁም ሰላማዊ ሆኖ ተጠናቅቋል ።

በኮሪደር እና በወንዝ ዳርቻዎች ልማት ያማረችዉ አዲስ አበባችን ለአደባባይ ክብረ በዓላት፣ ለበዓሉ ታዳሚያንና ከመላዉ ዓለም ለሚመጡ ቱሪስቶች ተጨማሪ ድምቀት እና ምቾት ሆናለች ።

በዓሉ እጅግ ባማረ፣ ደማቅና ሰላማዊ በሆነ መልኩ እሴቱንና ቱፊቱን ጠብቆ እንዲጠናቀቅ ላደረጋችሁ አካላት ሁሉ ፣ በተለይም ለከተማችን ነዋሪዎች የላቀ ምስጋናዬን አቀርባለሁ ።

ፈጣሪ ኢትዮዽያንና ሕዝቦቿን ይባርክ
ከንቲባ አዳነች አቤቤ
7👍1
"ሠንደቅ ዓላማችን ለኢትዮጵያ ታላቅ የከፍታ ዘመን ብሥራት፣ ለብሔራዊ አንድነታችን፣ ለሉዓላዊነታችንና ለኢትዮጵያ ሕዳሴ"
2
3ኛውየአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት አምስተኛ ዓመት የስራ ዘመን 1ኛ መደበኛ ጉባዔውን ማካሄድ ጀምሯል፡፡

ምክር ቤቱ የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት 3ኛ ዙር አራተኛ ዓመት የስራ ዘመን 4ኛ መደበኛ ጉባዔ ቃለ ጉባኤ በማጽደቅ በተለያዩ አጀንዳዎች ላይ በመወያየት ውሳኔዎችን ያስተላልፋል::

ምክር ቤቱ የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ተመራጭ አባላት ከመራጩ ህዝብ ጋር ባደረጉት ውይይት ላይ በተነሱ ጥያቄዎች ላይ ምላሽ ይሰጣል፡፡

በተመሳሳይ ምክር ቤቱ የተለያዩ ሹመቶችን በማጽደቅ ይጠናቃል ተብሎ ይጠበቃል፡፡
2
3ኛዉ የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት 5ኛ ዓመት የስራ ዘመን 1ኛመደበኛ ጉባዔዉን እያካሄደ ይገኛል

ምክር ቤቱ 3ኛዉ የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት 5ኛ ዓመት የስራ ዘመን 1ኛመደበኛ ጉባዔዉን በእድዋ ድል መታሰቢያ በሚገኘዉ የምክር ቤቱ አዳራሽ እያካሄደ ነዉ፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት ዋና አፈ-ጉባዔ ወ/ሮ ቡዜና አልቃድር በመክፈቻ ንግግራቸዉ እንደተናገሩት 2018 ዓ.ም ህዳሴ ግድብን ያጠናቀቅንበት በርካታ ፕሮጀክት በሩብ ዓመቱ የተጀመሩበት ዓመት በመሆኑ እንኳን ደስ አላችሁ ብለዋል፡፡

አክለዉም ለ18ኛዉ የሰንደቅ ዓላማ ቀን እንኳን አደረሳችሁ ብለዋል፡፡

የዛሬዉ አጀንዳዎችም ፤-የምክር ቤቱን 4ኛ የስራ ዘመን 4ኛ መደበኛ ጉባዔ ቃለ ጉባዔ ማፅደቅ፤በከተማዋ ባሉ ክፍለ ከተሞች የተመረጡ የምክር ቤት ዓባላት በበጀት ዓመቱ በ1ኛ ሩብ ዓመት ህዝብ ጋር ወርደዉ በአደረጉት ዉይይት ለቀረቡላቸዉ ጥያቄዎች ለጉባዔዉ በማቅረብ በክብርት ከንቲባ አዳነች አቤቤ እና በሌሎች የምክር ቤት አባላት ምላሽ መስጠት እና ልዩ ልዩ ሹመቶችን ማፅደቅ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

በመጨረሻም በቀረበዉ የምክር ቤቱ 4ኛ የስራ ዘመን 4ኛ መደበኛ ቃለ ጉባዔ ላይ ምክር ቤቱ ሃሳብ ሰጥቶበት በሙሉ ድምፅ ፀድቆ ጥያቄዎች በምክር ቤት አባላት እየቀረቡ ይገኛሉ፡፡
2
በአዲስ አበባ ምክር ቤት አባላት የተነሱ ጥያቄዎች

የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት 5ኛ ዓመት የስራ ዘመን 1ኛ መደበኛ ጉባኤውን እያካሄደ ይገኛል፡፡

በጉባኤው የምክር ቤት አባላቱ ከመረጣቸው ህዝብ ጋር ባደረጉት የመራጭ ተመራጭ የገፅ ለገፅ ውይይት ምላሽ ያስፈልጋቸዋል ተብለው የተነሱ የህዝብ ጥያቄዎችን ለከተማ አስተዳደሩ ከንቲባ አዳነች አቤቤ አቅርበዋል፡፡

የተነሱት ጥያቄዎች ፡-

👉 በበዓል ሰሞን እና ምሽትን ተገን በማድረግ የትራንስፖርት ታሪፍ ጭማሪ ነዋሪዎችን ያማረሩ በመሆናቸው ለዚህም በቀጣይ ምን ታስቧል?

👉 ‎ንፁህ የመጠጥ ውሃ ለነዋሪዎች ለማቅረብ ከተማ አስተዳደሩ የያዛቸው እቅዶች ምንድን ናቸው?

👉 በአንድ አንድ የእሁድ ገበያ መደብሮች ከተቀመጠው ዋጋ በላይ ማስከፈል፣ ጥራታቸው ዝቅ ላሉ ምርቶች እኩል ዋጋ መጠየቅ እንደሚስተዋል እና ይህን ችግር ለመቅረፍ በቀጣይ ምን ታስቧል?

👉 በመዲናዋ የኮሪደር ልማት ያልደረሰባቸው አካባቢዎች የኮሪደር ልማትን ለማዳረስ ከተማ አስተዳደሩ ምን አቅዷል?

👉 የጤና ጣብያ እጥረት ያለባቸው አካባቢዎችን ችግር ለመቅረፍ ምን እንደታቀደ ቢገለፅ?

👉 መሰረቱ የማይናወጥ አካታች የወል ትርክት ለመገንባት ብሎም ተራማጅ አስተሳሰብ ማስረጽ፤ የእንችላለን ስነ-ልቦና ብሎም ልመናና ኋላ ቀር አስተሳሰብን በመስበር በኪነ- ጥበብ እያዋዙ ጠንካራ ኢንዱስትሪ ለመገንባትና ዘርፉን ለመደገፍ ከተማ አስተዳደሩ ምን አስቧል?

👉 ‎የኑሮ ሁኔታን በተመለከተ እየተሰራ ያለው ስራ ጎን ለጎን የኑሮ ጫናን ለመቀነስ፣ የነዋሪዎችን እርካታ ለማረጋገጥ የት፣ ምን ተሰርቷል?

👉 በመስከረም ወር የተካሄዱት ታላላቅ በዓላት በስኬት የመጠናቀቃቸውን ያህል በቀጣይም መሰል በዓላት በስኬት እንዲጠናቀቁ ምን ታስቧል? ይሄንንስ ድል እንዴት አገኘነው?

👉 የኮሪደር ልማቱን ህብረተሰቡ በእኔነት እንዲጠብቀው፤ ከተማውን ከተሜ ሆኖ እዲጠብቃት የግንዛቤ ማስጨበጫ ተሰጥቷል ወይ?

👉 ህብረተሰብ ከተማዋን ከተሜ ሆኖ እዲጠብቃት የሕግ ማዕቀፍ አለ? ማዕቀፍ አያስፈልግም ወይ?

👉 ወጣቶች ኮደርስ ስልጠና ወስደው ወደ ስራ አልገቡም፤ ምን ታስቧል?

👉 የፌዴራል መንግስት የሰራተኞች ደሞዝ እንዲስተካከል ወስኗል ከተማ አስተዳደሩ ይህንን ተፈፃሚ ለማድረግ ምን ዝግጅት አድርጓል?

የሚሉ ጥያቄዎች በምክር ቤቱ አባላት የተነሱ ሲሆን ለጥያቆዎቹም በከንቲባ አዳነች አቤቤ ምላሽ ይሰጥባቸዋል ተብሎ ይጠበቃል፡፡
2