5 ቀን ቀረው!
ሐምሌ 24 ፣2017 700 ሚሊዮን ችግኝ በአንድ ጀንበር። እንዘጋጅ!
5 days5 days#PMOEthiopia remaining!
July 31, 2025 #Ethiopia will attempt planting 700 million seedlings in one day. Let’s get ready as the count down begins.
#አረንጓዴዐሻራ
#GreenLegacy
#PMOEthiopia

ከተማችንን የምንሰራት ፣ ጤናማ ትውልድ እንዲገነባ፣ እንዲረከባት እና እንዲያበለፅጋት ነው !
በ2017 በጀት ዓመት ከገነባናቸዉ 28 የጤና ፕሮጀክቶች መካከል 22 ያህሉን በዛሬው እለት አስመርቀን ለአገልግሎት ክፍት አድርገናል ።
በሁሉም ክፍለ ከተሞች ዛሬ አስመርቀን ለአገልግሎት ክፍት ያደረግናቸው የጤና ጣቢያዎች ከወትሮው በተለየ ሁኔታ ከመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል አገልግሎት ጋር እኩል ደረጃ ያላቸው ሲሆን የሚሰጡት አገልግሎት ጥራት ከፍ እንዲል ከ4 ቢልዮን በላይ ወጪ የተደረገባቸዉ በዘመናዊ የህክምና መሳሪያ ግብአት እና ባለሙያዎች ጭምር እንዲደራጁ ተደርገዋል ።
እነዚህም ለከተማችን ነዋሪዎች ጥያቄዎች ምላሽ የሚሰጡ፤ ፍትሃዊ የጤና አገልግሎትን ተጠቃሚነት የሚያረጋግጡ እንዲሁም በቅንነት፣ በትጋት እና በታማኝነት የማገልገል ማሳያችን ናቸው።
ፕሮጀክቶቹ በጥራትና በፍጥነት ተጠናቅቀው ለህዝብ አገልግሎት እንዲበቁ ያደረጋችሁ በሙሉ በራሴና በከተማ አስተዳደሩ ስም የላቀ ምስጋናዬ ይድረሳችሁ።
ፈጣሪ ኢትዮጵያንና ህዝቦቿን ይባርክ
ከንቲባ አዳነች አቤቤ

👍4
የኀብረተሰብ ተሳትፎና በጎ ፈቃድ ማስተባበሪያ ኮሚሽን - አዲስ አበባ
Photo
ዓድዋን በደማችን፤ ዓባይን በላባችን!
(ፍቃዱ ከተማ)
ታሪክ በሁለት መልኩ ይፃፋል፤ አንድም በደም ሌላም በላብ፡፡ ታሪክ ሠሪዎቹ ኢትዮጵያውያን እነዚህን ገድሎች በደም ዓድዋ ላይ ፤ በላብ ደግሞ ጉባ ላይ ፈጽመውታል፡፡
የካቲት 23/1833 በሰው ልጆች ታሪክ እስከዚያኔው ያልተፈጸመን አንድ ገድል ኢትዮጵያውያን በደማቸው ጻፉ፡፡ ይኽ ገድል ድሆችና ኋላ ቀሮች ናቸው በሚል ንቀት ኢትዮጵያን በወረረው የፋሺስት ወራሪ ኃይል ላይ ዓድዋ ላይ የተመዘገበ ነበር፡፡ በዚህም ፍትሃዊነትና ሃገር ወዳድነት በተግባር እስካሉ ድረስ ተጨቋኞች ጨቋኞችን፤ ጥቁሮች ነጮችን በሚገባ እንደሚያሸንፉ ለዓለም እስተምረዋል፡፡
በዓድዋ ጦርነት ኢትዮጵያውያን በጊዜው የነበራቸውን የውስጥ ልዩነት ወደ ጐን ትተው ብሔር፣ እምነት፣ ጾታ፣ ዕድሜ፣ ባህል ወዘተ… ሳይለያቸው ደማቸውን በአንድነት አፍስሰውና አጥንታቸውን ከስክሰው ለኢትዮጵያውያን ብቻ ሳይሆን ለጭቁን ሕዝቦችና ለጥቁሮች ኩራት የሆነ ወርቃማ ድል በክብር ጽፈዋል፡፡
ሲተባበሩ ታሪክ መስራት የሚቀላቸው ኢትዮጵያውያን፤ ከዓድዋ ድል ከ129 ዓመታት በኋላ በደም ሳይሆን በላባቸው ዓለምን የሚያስገርምና ኢፍትሃዊነትን የሚሰባብር ድል ጉባ ላይ ደገሙ፤ በታላቁ የዓባይ ግድብ!
ከዓባይ ግድብ ዕውን መሆን በፊት የዓባይ ወንዝ ለኢትዮጵያውያን የሚያዩት ግን የማይጠቀሙበት የቁጭት ምንጭ ነበረ፡፡ ለዓባይ የሚዘፈኑ ዘፈኖች ሁሉ ቁጭትንና ሃዘንን የሚያንጸባርቁም ነበሩ፡፡ በደጃፏ የዓባይ ወንዝ ውኃ የሚፈስ ኢትየጵያዊ እናትም የኤሌክትሪክ ኃይል አጥታ ዓይኗ በከሰልና ማገዶ ጭስ እየተጨናበሰ ዘመናትን በችግር ገፍታለች፡፡
ዓባይ በሱዳን በተለይም በግብጽ የኃይል፣ የመስኖ የመዝናኛ ምንጭ ከመሆን አልፎ መጫወቻ ተደርጎ ወደ በረሃ በመውሰድ ውኃው ሲባክን፣ ከ85% በላይ የውኃው አመንጪ የሆነችው ኢትዮጵያ ግን በሴራ በገዛ ሃብቷ እንዳትጠቀም ተደርጋ ኖራለች፡፡
ይኸ እውነታ ግን በ2003 መጋቢት 24 የዓድዋ የመንፈስ ልጆች በሆኑ ኢትዮጽያውያን ላብ ለአንዴና ለመጨረሻ እንዲለወጥ ተወሰነ፡፡ ተወስኖም አልቀረ፤ በማህፀን ካለ ጽንስና በመቃብር ካለ አስክሬን በስተቀር ኢትዮጵያውያን ደመወዛቸውን፣ ጡረታቸውን፣ እንስሳታቸውን ወዘተ… ለግድቡ እውን መሆን አዋጥተው የዘመናት ቁጭትን ወደላቀ ኩራት አሸጋገሩ፡፡ ከቀጥተኛ የመንግሥት በጀት ውጪ በሀገር ውስጥና በውጪ ያሉ ኢትዮጵያውያን የ23 ነጥብ 1 ቢሊዮን ብር የገንዘብ ድጋፍ አድርገዋል፡፡
በዚህም በዓባይ ወንዝ እንዳንጠቀም አይኤምኤፍ እና ዓለም ባንክን ጨምሮ አበዳሪ ተቋማት ገንዘብ እንዳይሰጡ ለማድረግ ተጋርጦ የነበረው የጅሎች ሴራ በኢትዮጵያውያን ተደረመሰ፡፡
ዛሬ ላይ ኢትዮጵያውያን የግድቡን ሥራ ለፍጻሜ አብቅተው የመስከረም ሙሽራቸውን የዓባይ ግድብን ምረቃ ለማብሰር ድል ያለ ሠርግ እየደገሱ ነው፡፡ በሠርጉም በዓድዋ በደም፤ በዓባይ ደግሞ በላብ ኢትዮጵያውያን አሳምረው ድል ማድረጋቸው ለዓለም ይበሠራል፡፡ ለኢትዮጵያ ብልጽግና መሠረት የመጣሉም ሥራ ተጠናክሮ እንዲቀጥል ቃል የሚገባበት ይሆናል!

👍1
የኀብረተሰብ ተሳትፎና በጎ ፈቃድ ማስተባበሪያ ኮሚሽን - አዲስ አበባ
Photo
የቅዱስ ፓውሎስ ሆስፒታል ሚሊኒየም የህክምና ኮሌጅ ከ100 ሺህ በላይ ለሚሆኑ ዜጎች ነጻ የሕክምና አገልግሎት እንደሚሰጥ ገለፀ።
በተያዘው ክረምት በበጎ ፈቃድ አገልግሎት ከ100 ሺህ በላይ ለሚሆኑና ከፍለው መታከም ለማይችሉ ዜጎች ነጻ ህክምና አገልግሎት የመስጠት ሥራውን በዛሬው እለት መጀመሩን የቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል ሚሊኒየም የህክምና ኮሌጅ ገልጿል፡፡
የሜዲካል ኮሌጁ ምክትል ሥራ አስፈፃሚ ጀማል ሺፋ፤ "የክረምት በጎ ፈቃድ ሥራ ሁሌም የሚሰራ ቢሆንም በዚህ ዓመት ከሐምሌ 21 እስከ ሐምሌ 27 ቀን 2017 ዓ.ም ባሉት ሰባት ተከታታይ ቀናት ብቻ በሚሰጠው የነጻ ምርመራ 100 ሺሕ ሰዎችን ተጠቃሚ ለማድረግ እቅድ ተይዟል" ብለዋል፡፡
በ2016 ዓ.ም. ተመሳሳይ ወቅት ከ94 ሺህ ለሚበልጡ ሰዎች የነጻ ሕክምና አገልግሎት እንደተሰጠ አስታውሰው፤ የዘንድሮውን መርሃ-ግብር "በጎ ፈቃደኝነት ለጤናማ ማኅበረሰብ" በሚል መሪ ቃል እየተከናወነ እንደሚገኝም አብራርተዋል፡፡
ነጻ ምርመራው በተለይ የካንሰር፣ የጎሮሮ፣ የዓይን እና መሰል ትላልቅ የበሽታ አይነቶችን የነጻ ምርመራ እንደሚያደርጉ ከ50 በላይ የሕክምና መሳሪያዎች ተዘጋጅተዋል ብለዋል፡፡
የበጎ ፈቃድ አገልግሎቱ በምርመራ ዘርፍ ብቻ ሳይሆን ለአቅመ ደካሞችን ቤት ማደስ፣ ደም መለሰገስ፣ እና ሌሎችም የበጎ አድራጎት ሥራዎች ላይ መሳተፍን እንደሚጨምር አሀዱ ሬድዮ ዘግቧል፡፡

👍6
Join this link to help our channel: https://t.me/reallyzvezdabot?start=_tgr_QIw8vuU5MDg0
👍1
የወርቃማ ሰኞ የዕውቀት ሽግግርና የልምድ ልውውጥ መድረከ ተካሔደ።
በዛሬው የኮሚሽኑ የወርቃማ ሰኞ መርሀ ግብር ልምዳቸውን ያካፈሉት የበጎ ፈቃድ ዘርፍ ምክትል ኮሚሽነር ወይዘሮ አስራት ንጉሴ ናቸው፡፡
በተለየዩ የኃላፊነት ደረጃዎች ማገልገላቸውን የገለጹት ወይዘሮ አስራት በበጎ ፈቃድ አገልግሎት ወገንን ማገልገል የሚሰጠው የሕልና እርካታ የላቀ መሆኑን ገልፀዋል። ምክትል ኮሚሽነሯ በማህበራዊ ትረስት ፈንድ ተቋም የነበራቸው ቆይታ በሕይወታቸው ትልቅ ቦታ የሚሰጡት እንደሆነ ነው የተናገሩት፡፡
በማኅበራዊ ትረስት ፈንድ ጽህፈት ቤት ይተገበሩ የነበሩ ስራዎች ተጠናክረው እንዲቀጥሉ ከበጎ ፈቃድና ኅብረተሰብ ተሳትፎ ማስተባባሪያ ኮሚሽን ጋር እንዲዋሀዱ መደረጋቸው ተግባራት ይበልጥ እንዲጠናከሩና ውጤታማ እንዲሆኑ አስተዋዖ እንደሚኖራቸው አብራርተዋል፡፡
የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት የአስፈፃሚ አካላትን ስልጣንና ተግባር እንደገና በማሻሻል ማኅበራዊ ትረስት ፈንድ ፅህፈት ቤትን ከኮሚሽኑ ጋር እንዲዋሃድ ማድረጉ ይታወሳል።
የኮሚሽኑ አመራሮችና ሰራተኞች ለምክትል ኮሚሽነሯ የእንኳን ደህና መጡ አቀባበል አድርገውላቸዋል።

👍2
የኀብረተሰብ ተሳትፎና በጎ ፈቃድ ማስተባበሪያ ኮሚሽን - አዲስ አበባ
Photo
በቦሌ ክፍለ ከተማ በክረምት በጎ ፈቃድ ፕሮግራም ለ5,000 ከፍለው መታከም የማይችሉ ነዋሪዎች ነፃ የጤና ምርመራና ሕክምና አገልግሎት ተጀመረ፡፡
የቦሌ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ከጥቁር አንበሳ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ጋር በመተባበር ለሦስት ተከታታይ ቀናት የሚቆይ የክረምት በጎ ፍቃድ ነፃ የጤና ምርመራና የሕክምና አገልግሎት ዛሬ አስጀምረዋል። በፕሮግራሙ ላይ የቦሌ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ዋና ሥራ አስፈጻሚ ዶ/ር እሸቱ ለማ ባደረጉት ንግግር በጎነት በቅንነት የሚከናወን መልካም ሥራ መሆኑን አውስተው፣ በሀገር አቀፍ ደረጃ በልዩ ልዩ መስኮች እየተከናወኑ ያሉ የበጎ ፍቃድ አገልግሎቶች ድጋፍ የሚሹ ወገኖችን በማገዝና አብሮነትን በማጠናከር ረገድ ከፍተኛ ድርሻ እንዳላቸው ተናግረዋል፡፡
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የኅብረተሰብ ተሳትፎና በጎ ፍቃድ ማስተባበሪያ ኮሚሽን ምክትል ኮሚሽነር ወ/ሮ አሥራት ንጉሤ በመድረኩ ተገኝተው ባስተላለፉት መልዕክት በክረምት የበጎ ፍቃድ አገልግሎት ከሚከናወኑ ተግባራት አንዱ በሆነው የጤና ዘርፍ ክፍለ ከተማው በነፃ ሕክምና እና በደም ልገሣ ሰፊ ሥራ እያከናወነ እንደሚገኝ ገልፀው “ዛሬ የተጀመረው የነፃ የጤና ምርመራና ሕክምና አገልግሎት የጤና ድጋፍ ለሚሹ ወገኖች ትልቅ እድል መሆኑን ተናግረዋል።
በመዲናዋ ይህ የበጎ ፈቃድ አገልግሎት ተጠናክሮ እንደሚቀጥልም ነው ምክትል ኮሚሽነሯ የተናገሩት። ወ/ሮ አስራት መርሐ ግብሩን ያዘጋጁትን የቦሌ ክፍለ ከተማ አስተዳደርን እና የጥቁር አንበሳ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታልን ምስጋና አቅርበዋል።
የጥቁር አንበሳ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል እንደ ጤና እና የትምህርት ተቋምነቱ ከመደበኛ ሥራው ጎን ለጎን ማኅበራዊ ኃላፊነቱን ለመወጣት በስፋት እንደሚንቀሳቀስ የሆስፒታሉ ዋና ሥራ አስፈጻሚው ዶ/ር አብዱራዛቅ አሕመድ ገልፀው ሆስፒታሉ ባለፈው ዓመትም በተመሳሳይ በቦሌ ክፍለ ከተማ ነፃ የጤና ምርመራና ሕክምና አገልግሎት በመስጠት ለወገን ደራሽነቱን በተግባር ማሳየቱን ጠቅሰዋል።
ከሐምሌ 28-30/2017 ዓ.ም ለሶስት ቀባት በሚቆየው በዚህ ነፃ የህክምና አገልግሎት 180 የጤና ባለሙያዎች እንደሚሳተፉ ተመላክቷል።

❤4👍2
በቂርቆስ ክፍለ ከተማ በክረምት በጎ ፈቃድ ፕሮግራም የ12 አቅመ ደካሞችን የመኖሪያ ቤት ችግር የሚቀርፈው የG+3 ህንፃ ግንባታ በመጠናቀቅ ላይ ነው።
በቂርቆስ ክፍለ ከተማ ወረዳ 05 በክረምት የበጎ ፈቃድ ፕሮግራም በመንግስት የልማት ድርጅቶች አማካኝነት 12 አቅመ ደካሞችንና አረጋውያንን ተጠቃሚ የሚያደርግ ባለአራት ወለል ህንፃ ግንባታ በመጠናቀቅ ላይ ይገኛል።
የመኖሪያ ህንፃው ሲጠናቀቅ ከ60 በላይ ቤተሰቦችን የመኖሪያ ቤት ችግር ይቀርፋል ተብሎ ይጠበቃል። የግንባታ ስራው እየተፋጠነ መሆኑንና በቅርብ ተጠናቆ ለተጠቃሚዎች እንደሚተላለፍ የክፍለ ከተማው የኅብረተሰብ ተሳትፎና በጎ ፈቃድ ማስተባበሪያ ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ኢብራሂም አባስ ተናግረዋል።
ከተማ አስተዳደሩ በ90 ቀናት የክረምት በጎ ፈቃድ ፕሮግራም በጎ ፈቃደኞችን በማስተባበር 2 ሺህ 500 መኖሪያ ቤቶችን ገንብቶ ለአቅመ ደካሞች፣ አረጋውያንና ለሀገር ባለውለታዎች ለማስተላለፍ እየሰራ ይገኛል።
"በጎ ፈቃደኝነት ለማኅበረሰብ ለውጥ!"

❤2👍1
ኤካ ኮተቤ ጠቅላላ ሆስፒታል በነገው ዕለት ከ100 ሺህ በላይ ከፍለው መታከም ለማይችሉ የከተማዋ ነዋሪዎች ነፃ የጤና ምርመራና የህክምና አገልግሎት መስጠት ይጀምራል።
በመርሃ ግብሩ ማስጀመሪያ ላይ የኢፌድሪ ጤና ሚኒስቴር ከፍተኛ አመራሮች፣ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የኅብረተሰብ ተሳትፎና በጎ ፈቃድ ኮሚሽን የስራ ኃላፊዎች እንዲሁም የየካ ክፍለ ከተማ እና የኤካ ኮተቤ ሆስፒታል አመራሮች እንደሚገኙ ይጠበቃል።
በክረምት የበጎ ፈቃድ መርሀ ግብር ከ100 ሺህ በላይ ዜጎችን ተጠቃሚ የሚያደርገው ይህ አገልግሎት በየካ ክፍለ ከተማ ግቢ ውስጥ ለአንድ ሳምንት የሚሰጥ ሲሆን በርካታ ስፔሻሊስትና ሰብ ስፔሻሊስት በጎ ፈቃደኛ ሀኪሞች ይሳተፉበታል።
መርሃ ግብሩን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የሕብረተሰብ ተሳትፎና በጎ ፈቃድ ማስተባበሪያ ኮሚሽን - አዲስ አበባ ከየካ ክፍለ ከተማ አስተዳደርና ከኤካ ኮተቤ ጠቅላላ ሆስፒታል ጋር በመተባበር አዘጋጅቶታል። ከፍለው መታከም የማይችሉ በመዲናዋ የሚኖሩ አቅመ ደካሞች ይህን እድል በመጠቀም ጤናቸውን እንዲጠብቁ የመርሃ ግብሩ አዘጋጆች ጥሪ አቅርበዋል።

❤5👍1
የኀብረተሰብ ተሳትፎና በጎ ፈቃድ ማስተባበሪያ ኮሚሽን - አዲስ አበባ
Photo
ኤካ ኮተቤ ጠቅላላ ሆስፒታል ከ100 ሺህ በላይ ከፍለው መታከም የማይችሉ ነዋሪዎችን ተጠቃሚ የሚያደርግ ነፃ የህክምና አገልግሎት አስጀመረ።
ኤካ ኮተቤ ጠቅላላ ሆስፒታል ከአዲስ አበባ ከተማ የኅብረተሰብ ተሳትፎና በጎ ፈቃድ ማስተባበሪያ ኮሚሽንና ከየካ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ጋር በመተባበር ከ100 ሺህ በላይ ከፍለው መታከም የማይችሉ ነዋሪዎችን ተጠቃሚ የሚያደርግ ነፃ የህክምና አገልግሎት "በጎ ፈቃደኝነት ለጤናማ ማኅበረሰብ!" በሚል መሪ ሃሳብ በዛሬው ዕለት አስጀምሯል።
በየካ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ግቢ ውስጥ በተካሄደው የማስጀመሪያ መርሃ ግብር ላይ የኢፌድሪ ጤና ሚኒስቴር ሚኒስትር ዶ/ር መቅደስ ዳባና የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የኅብረተሰብ ተሳትፎና በጎ ፈቃድ ማስተባበሪያ ኮሚሽን ኮሚሽነር ይመር ከበደን ጨምሮ በየደረጃው የሚገኙ የስራ ኃላፊዎች ተገኝተዋል።
የሀገራችን የጤና ፖሊሲ ቅድመ መከላከልን ማዕከል ያደረገ እንደመሆኑ ጤናማና አምራች ዜጋ ማፍራት ተቀዳሚ ተልዕኮ መሆኑን የገለፁት ክብርት ሚኒስትር ዶ/ር መቅደስ ዳባ ነዋሪዎች በየጊዜው ምርመራ በማድረግ ራሳቸውን ማወቅና ተላላፊ ያልሆኑ በሽታዎችን መከላከል እንደሚገባ ተናግረዋል። የጤና ሙያ በጎ ፈቃደኝነትን የሚጠይቅ ማኅበረሰብ የማገልገል ዲሲፕሊን እንደሆነ ያወሱት ሚኒስትሯ በየዓመቱ ነፃ የህክምና አገልግሎት የመስጠት ባህል እየዳበረ መምጣቱንም ነው የገለፁት። ሚኒስትሯ በዚህ ሰብዓዊ አገልግሎት እየተሳተፉ ያሉ በጎ ፈቃደኛ የህክምና ባለሙያዎችን፣ ተቋማትንና ኃላፊዎችን አመስግነዋል።
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የኅብረተሰብ ተሳትፎና በጎ ፈቃድ ማስተባበሪያ ኮሚሽን ኮሚሽነር ይመር ከበደ በበኩላቸው በህክምናው ዘርፍ ባህል እየሆነ የመጣው አገልግሎት ነፃ ህክምናን ነጮች የሚሰጡት እንደሆነ ተደርጎ ይቆጠር የነበረውን አስተሳሰብ የሰበረ አዲስ ባህል መሆኑን ተናግረዋል። ለነፃ የህክምና አገልግሎት ባህል መዳበርና መስፋፋትም ጤና ሚኒስትር ከፍተኛ አስተዋፅዖ እንዳለው የገለፁት ኮሚሽነሩ የማህበረሰቡን ጤና መጠበቅ በሁሉም ዘንድ ሊዘወተር የሚገባ ሰብዓዊ ሥራ መሆኑን ጠቁመዋል።
የኤካ ኮተቤ ሆስፒታል በየዓመቱ ለበርካታ ዜጎች ነፃ የህክምና አገልግሎት በመስጠት ማኅበራዊ ኃላፊነቱ እየተወጣ እንደሆነና ዛሬ ባስጀመረው አገልግሎትም ከ100 ሺህ በላይ ከፍለው መታከም ለማይችሉ ዜጎች ለአንድ ሳምንት የሚቆይ የነጻ ምርመራ፣ የህክምናና የምክር አገልግሎት መስጠር መጀመሩን የሆስፒታሉ ዋና ስራ አስኪያጅ ዶ/ር ሙሉቀን ተስፋዬ ተናግረዋል።

❤3👍1
የአፍሪካ ኅብረት ሰራተኞች በቀበና ወንዝ ዳርቻ ከ1 ሺህ 500 በላይ ችግኞችን ተክለዋል።
የአፍሪካ ኅብረት ሰራተኞች ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የኅብረተሰብ ተሳትፎና በጎ ፈቃድ ማስተባበሪያ ኮሚሽን ጋር በመተባበር "በመትከል ማንሰራራት!" በሚል መሪ ቃል አረንጓዴ አሻራቸውን አኑረዋል።
የአፍሪካ መዲናና 3ኛዋን የዓለም የዲፕሎማሲ ከተማ የሆነችውን አዲስ አበባ ለኑሮ ምቹ ለማድረግ ከሚከናወኑ ተግባራት መካከል አረንጓዴ አሻራ አንዱ መሆኑን የተናገሩት የአዲስ አበባ ከተማ የኅብረተሰብ ተሳትፎና በጎ ፈቃድ ማስተባበሪያ ኮሚሽን ኮሚሽነር ይመር ከበደ የኅብረቱ ሰራተኞች በዚህ ታሪካዊ ተግባር ላይ ላደረጉት ተሳትፎ ምስጋና በማቅረብ ዛሬ የተከሏቸውን ችግኞች እስኪፀድቁ ድረስ እንዲንከባከቡ ጠይቀዋል።
ኢትዮጵያ የአየር ንብረት ለውጥ ፈተናዎችን ለመቋቋም ለአካባቢ ጥበቃ ስራ ትኩረት ሰጥታ በመስራት ላይ ትገኛለች ሲሉ የጠቀሱት ኮሚሽነሩ የኢትዮያን የአረንጓዴ አሻራ ተነሳሽነት ሁሉም አፍሪካውያን ሊተገብሩት ይገባል ብለዋል።
የኮሚሽኑ የበጎ ፈቃድ ዘርፍ ምክትል ኮሚሽነር ወ/ሮ አስራት ንጉሴ በበኩላቸው የአፍሪካ ኅብረት ሰራተኞች ማኅበር ባለፉት ሰባት አመታት ማኅበራዊ ኃላፊነቱን ሲወጣ መቆየቱን ገልፀው ዛሬ በአረንጓዴ አሻራ መርሀ ግብር ላይ የኅብረቱን ሰራተኞች አስተባብሮ ላደረገው ተሳትፎ ምስጋናቸውን አቅርበዋል።
የኅብረቱ ሰራተኞች በችግኝ ተከላ መርሀ ግብር ላይ መሳተፋቸውና ለአካባቢ ጥበቃ ስራ አስተዋፅዖ በማበርከታቸው መደሰታቸውን ገልፀው በቀጣይ ጊዜም በመሰል የበጎ ፈቃድ አገልግሎቶች ላይ ተሳትፏቸውን ለማጠናከር ቃል ገብተዋል።