የኀብረተሰብ ተሳትፎና በጎ ፈቃድ ማስተባበሪያ ኮሚሽን - አዲስ አበባ
826 subscribers
2.14K photos
47 videos
265 links
Download Telegram
የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት የተለያዩ ሹመቶችን በመስጠት ተጠናቋል።

በ3ኛው የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት 4ኛ ዓመት የስራ ዘመን 4ኛ መደበኛ ጉባኤ ከንቲባ አዳነች አቤቤ ያቀረቡትን የተለያዩ ሹመቶች አፅድቋል።

በዚህም መሰረት
1-አቶ አብዱልቃድር ሬድዋን :-በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የአዲስ አበባ ከተማ ፍይናስ ቢሮ ሃላፊ መሆናቸውን ለምክር ቤቱ እንዲያውቀው ተደርጓል::

2. አቶ ኦልያድ ስዮም :-የከተማ ቦታ ማስለቀቅ ጉዳዮች እና ይግባኝ ሰሚጉባኤ ፍርድ ቤት ፕሬዝዳንት ሆነው ተሹመዋል ።

3-አቶ መኮንን ያኢ :-የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የመሬት ልማት ቢሮ ሀላፊ ሆነው ተሹመዋል ።
👍31
የኀብረተሰብ ተሳትፎና በጎ ፈቃድ ማስተባበሪያ ኮሚሽን - አዲስ አበባ
Photo
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የ2018 በጀት ዓመት እቅድ የትኩረት አቅጣጫዎች፤

👉የተጀመረውን ተቋማዊ ሪፎርም አጠናክሮ የማስቀጠል፣

👉በፕሮጀክቶች አፈፃጸም ያገኘነዉን ድል በአገልግሎትና መልካም አስተዳደር መድገም፤

👉የአዲስ መሶበ Vertual Service አንድ ማዕከል አገልግሎትን ማስፋትና ማጠናከር፤

👉የገቢ አሰባሰባችንን በማዘመን የገቢ እቅድ ማሳካት፤

👉 የቤት ልማት ፕሮግራሞችን በግል ዘርፉ፣በሕብረት ሥራ ማኅበራት፣በመንግስትና በግል የአጋርነት ፕሮግራም በስፋት ተግባራዊ ይደረጋል፤

👉የኑሮ ውድነትን ለማረጋጋት፣ የሌማት ትሩፋትና የከተማ ግብርናን ስችንን ማስፋት፤

👉 የውሃ አቅርቦትና የተጀመሩ ሜጋ ኘሮጀክቶችን በመሟላ ሁኔታ ለማጠናቀቅ መስራት፤

👉የተጀመረዉን የትምህርት ሪፎርም በማጠናከር የትምህርት ጥራት የማረጋገጥ

👉የጤና አገልግሎት ይበልጥ የማሻሻልና የማዘመን ሥራ ተጠናክሮ ይቀጥላል፣

👉 የወጣቶች የሥራ አድል እና አምራች ኢንዱስትሪን የማስፋትና ተወዳዳሪነቱን የማሳደግ ስራ በልዩ ትኩረት ይከናወናል፤

👉 የሕብረተሰብ ተሣትፎና የበጎ ፍቃድ አገልግሎትን አጠናክሮ ማስቀጠል፡

👉 በከተማችን ጽዳትና ውበት መስክ የተገኘዉን ስኬት በማላቅ ከምንጊዜውም በላቀ ትኩረት ይሰራል፤

👉የከተማችንን የቱሪስት መዳረሻ ቦታዎች ይበልጥ በማስተዋወቅ እና እንዲጎበኙ በማድረግ ከዘርፉ ከተማችን ማግኘት የሚገባትን ሁለንተናዊ ፋይዳ እንድታገኝ ማድረግ፤

👉ሌሎች የሰው ተኮር ስራችንን ህዝባችንን እያሳተፍን አጠናክረን እንቀጥላለን፡፡

👉ለአገራችን ዘላቂ ሠላም እና የሕግ የበላይነት መረጋገጥ ላይ በትጋት ይሰራል፤

👉ነጻ፣ ሠላማዊ፣ ፍትሐዊና ዲሞክራሲያዊ ምርጫ እንዲካሄድ ምቹ ሁኔታ መፍጠር፤

👉 በአጠቃላይ ከተማችን ለነዋሪዎቿ ምቹ፣ ሀገራዊ፣ አህጉራዊና አለም አቀፍ ሚናዋን በብቃት የምትወጣ ስሟና ግብሯ የተናበበ ስማርት ከተማ እንድትሆን የጀመርነዉን ልማት  በጥራት፣ በስፋትና በፍጥነት አጠናክረን እንቀጥላለን፡፡

በ3ኛው የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት 4ኛ ዓመት የስራ ዘመን 4ኛ መደበኛ ጉባኤ የ2018 እቅድ የቀጣይ ትኩረት አቅጣጫ በማስቀመጥ ተጠናቀቀ::
2👍1
በቀላሉ በእጅ ስልክዎ በዋትስ አፕ ቻናል ፈጣንና ወቅታዊ መረጃዎችን እናደርስዎታለን! ፈጥነው ይቀላቀሉን!

Follow the የኅብረተሰብ ተሳትፎና በጎ ፈቃድ ማስተባበሪያ ኮሚሽን channel on WhatsApp: https://whatsapp.com/channel/0029VbBAQRrGOj9kUsLU7A0Z
ኮሚሽኑ የ90 ቀናት እቅድ አፈጻፀሙን ከክፍለ ከተማና ከማዕከል አመራሮች ጋር በመገምገም አቅጣጫ አስቀምጧል።

እስከ ጳጉሜን 5/2017 ዓ.ም በሚቆየው የዘጠና ቀናት እቅድ የክረምት በጎ ፈቃድ አገልግሎት እና የኅብረተሰብ ተሳትፎ ተግባራት ልዩ ትኩረት ተደርጎባቸዋል።

15 መርሃ ግብሮችን ያካተተው የክረምት በጎ ፈቃድ አገልግሎት ውጤታማ እንዲሆን ከባለድርሻ አካላት ጋር በመቀናጀትና በጎ ፈቃደኞችን በስፋት በማሳተፍ በጥብቅ ዲሲፕሊን እንዲመራ ምክትል ኮሚሽነር አቶ ደረጀ ካሳ አቅጣጫ ሰጥተዋል።

ነዋሪውን በማሳተፍ የምናከናውናቸው የአካባቢ ልማት እና የሞዴል ብሎክ ፈጠራ ተግባራትን ከመደበኛ ስራዎች ጋር አቀናጅቶ በጊዜ የለኝም መንፈስ መስራት ይገባል ብለዋል ምክትል ኮሚሽነሩ።

በሌሎች የማኅበራዊ ሚዲያ አማራጮች ለመከታተል ቀጣዩን ማስፈንጠሪያ ይጫኑ፣
https://linktr.ee/cpvcc
👍21👎1
የወርቃማው ሰኞ መርሃ ግብር በሰራተኛው እና አመራሩ መካከል መልካም ግንኙነትንና የስራ ትብብርን መፍጠሩ ተገለፀ።

የኮሚሽኑ አመራሮችና ሰራተኞች የ2017 በጀት ዓመት የወርቃማው ሰኞ መርሃ ግብር ውጤታማነትን አስመልክቶ በቀረበ የዳሰሳ ጥናት ዙሪያ ውይይት አካሂደዋል።

በበጀት ዓመቱ በየሳምንቱ ሲካሄድ የቆየው የወርቃማው ሰኞ ፕሮግራም በዛሬው ዕለት የተጠቃለለ ሲሆን ባስገኘው ፋይዳና ውጤታማነት ዙሪያ በሰው ኃብት ዳይሬክቶሬት የዳሰሳ ጥናት ሰነድ ቀርቦ ውይይት ተደርጎበታል።

ወርቃማው ሰኞ በኮሚሽኑ በቡድን የመስራት አቅምን ማጎልበቱ፣ በሰራተኞችና አመራሮች መካከል መልካም ግንኙነትን በማዳበር ትብብርን መፍጠሩ እንዲሁም የስራ ተነሳሽነትን ማሳደጉን የሰው ኃብት አስተዳደር ዳይሬክተሯ ወ/ሮ ሮማን ከሊል ጥናቱን ባቀረቡበት ወቅት ተናግረዋል።

በጀት ዓመቱ በውጤት እንዲጠናቀቅ መሰል ግንኙነትን የሚያጠናክሩ መርሃ ግብሮችን ማስቀጠል ይገባል ያሉት ኮሚሽነር ይመር ከበደ ወርቃማው ሰኞ በቀጣይ በጀት ዓመትም ሰራተኛውን ለስራ በሚያነሳሳ፣ እውቀትና ክህሎት በሚጨምርና በቡድን የመስራት ባህልን በሚያሳድግ መልኩ መተግበር እንደሚገባ ገልጸዋል።

#reelschallengereelschallenge
#viralreelschallenge
#followerseveryone
👍3
በ2017 የሥራ ዘመን ትርጉም ያለው እና ለመጪው የ2018 የቀጠለ የእድገት ጉዞ ጠንካራ መሠረት የሚሆን እድገት ፈፅመናል። በዚህ መነሻም የሚኒስትሮች ምክር ቤት ለመጪው ዓመት ለትግበራ የተዘጋጀውን የ2018 የተሟላ የሁሉም ዘርፎች እቅድ እና ሀገራዊውን የልማት እቅድ ለመገምገም ተሰብስቧል።

ከግምገማ እና ውይይታችን ጎን ለጎንም የአረንጓዴ ዐሻራችንን አሳርፈናል።

ጠቅላይ ሚንስትር አብይ አህመድ
4
"አረንጓዴ አሻራ ለመጪው ትውልድ የተሻለች ሀገርን የምንገነባበት ትልቅ ተነሳሽነት ነው" ኮሚሽነር ይመር ከበደ

አረንጓዴ አሻራ ለመጪው ትውልድ የተሻለች ሀገርን የምንገነባበት ትልቅ ተነሳሽነት ነው ሲሉ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የኅብረተሰብ ተሳትፎና በጎ ፈቃድ ማስተባበሪያ ኮሚሽን ኮሚሽነር ይመር ከበደ ገለፁ።

ኮሚሽነሩ ይህን ያሉት የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ሥራ አስኪያጅ ጽህፈት ቤት እና ሌሎች ተቋማት "በመትከል ማንሰራራት" በሚል መሪ ሀሳብ በእንጦጦ ፓርክ ባዘጋጁት የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር ላይ ተገኝተው ነው። በመሆኑም ሁላችንም ለችግኝ ተከላ እና እንክብካቤ የምናደርገውን ተሳትፎ አጠናክረን መቀጠል አለብን ነው ያሉት።

አዲስ አበባ፣ሐምሌ 8/2017 ዓ.ም
#Ethiopian_News_Agency
👍3
የኀብረተሰብ ተሳትፎና በጎ ፈቃድ ማስተባበሪያ ኮሚሽን - አዲስ አበባ
Photo
“ከሲኦል ወጥቼ ወደ ገነት ነው የገባሁት” - የአዋሬ መልሶ ልማት ተጠቃሚው አቶ አበበ እሸቱ

የአዋሬ ነዋሪ የሆኑት አካል ጉዳተኛው አባት አቶ አበበ እሸቱ ሦስት መንግሥታትን ማሳለፋቸውን እና የአሁኑ አራተኛቸው መሆኑን ይናገራሉ።

ይሁንና “ባለፍኩባቸው ዘመናት ሁሉ እንደዚህ ያለ ነገር አይቼም ሰምቼም አላውቅም፤ ምክንያቱም ከትቢያ እና ከስቃይ ተነሥቼ ለዚህ ክብር የበቃሁት አሁን ነው” ይላሉ።

አዋሬ አሁን የያዘችውን መልክ ሳትይዝ በፊት ስፍራው የተጨናነቀ ለኑሮ የማይመችም ነበር።

የእርሳቸውም ቤት ግድግዳ በተበሳሱ ቆርቆሮዎች የተሸፈነ በመሆኑ ቆርቆሮው በንፋስ እንዳይነሣ አየሰጉ፣ ክረምት ሲመጣ ዝናብ እየገባ ሲቸገሩ እንደነበር ያስታውሳሉ።

“ዝናብ ሲዘንብ ቤቴ እንደ ዓባይ ይሞላል፣ ፀሐይ ሲሆን እንደ እሳተ ጎመራ ያቃጥላል፤ በጥቅምት እና በኅዳር ደግሞ ቤቴ እንደ ፍሪጅ ይቀዘቅዛል” ሲሉ ያለፉበትን አስከፊ ጊዜ ያስታውሳሉ።

“በአዋሬ ደሳሳ ቤቴ ውስጥ አብረውኝ ይኖሩ የነበሩ ውሾች በብርድ ሞተውብኛል፤ እኔም በርካታ ጊዜ በበሽታ ተጠቅቻለሁ፤ የሚሉት አባት አሁን ያ ጊዜ መቀየሩን እና የተሻለ ቤትም እንደተሰጣቸው በደስታ ተሞልተው ይናገራሉ።

በአዋሬች በተሠሩ የመልሶ ማልማት ሥራዎች ነዋሪው የተሻሉ ዘመናዊ ቤቶች ተገንብተውለት በደስታ እየኖረ ነው።

አንዳንዶቹ ቤቶች የቤት ዕቃ የተሟላላቸው ሲሆን፣ የተሟሏ ቤት ውስጥ የገቡት የአካል ጉዳተኛው አቶ አበበ እሸቱ፣ "ከሲኦል ወደ ገነት" እንደገባሁ ነው ምቆጥረው ሲሉ ደስታቸውን ይገልጻሉ።

ለሕፃናት፣ ለአዋቂ፣ እንዲሁም ለአካል ጉዳተኞች ታሳቢ ተደርጎ የተሠራው መሠረተ ልማቱ፣ ነፋሻማነቱን እና ፅዳቱን በማድነቅ ለጠቅላይ ሚኒስተር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ምስጋናን እና ምርቃታቸውን አቅርበዋል።

#EBC #ebcdotstream #AddisAbaba #housedevelopment #አዋሬ
4👍1
"በመትከል ማንሰራራት!"

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የኅብረተሰብ ተሳትፎና በጎ ፈቃድ ማስተባበሪያ ኮሚሽን አመራሮችና ሰራተኞች "በመትከል ማንሰራራት!" በሚል መሪ ሀሳብ አረንጓዴ አሻራቸውን አኖሩ።

የኮሚሽኑ አመራሮችና ሰራተኞች 7ኛውን ዙር አረንጓዴ አሻራቸውን ዛሬ ማለዳ በቂርቆስ ክፍለ ከተማ አስቀምጠዋል። በመርሃ ግብሩ ላይ የተገኙት የኮሚሽኑ ዋና ኮሚሽነር ይመር ከበደ አረንጓዴ አሻራ ለመጭው ትውልድ የምትመች ሀገር ለመገንባት ወሳኝ ሀገራዊ አጀንዳ መሆኑን ገልፀው ሁሉም በዚህ ታሪካዊ ተግባር በንቃት እንዲሳተፍ ጠይቀዋል።

ኮሚሽኑ በከተማ አስተዳደሩ የታቀደውን የችግኝ ተከላ ግብ ለማሳካት በጎ ፈቃደኞችንና መላ ኅብረተሰቡን ከጉድጓድ ዝግጅት ጀምሮ እያሳተፈ ይገኛል።
#GreenLegacy
#addisababa
#Ethiopia
ትውልድን መገንባት ቀዳሚው ሥራችን ነው!

ዛሬ የመረቅናቸዉ 150 የትምህርት ፕሮጀክቶች በታማኝነት የማገልገል እና የትጋት ዉጤቶች ናቸዉ።

በእርጅና ብዛት የተጎሳቀሉ ፣ግብአት የያልተሟላላቸዉ እና ለመማር ማስተማሩ ሂደት እንቅፋት የፈጠሩ፣ በሂደትም በተማሪዎቻችን የ12ኛ ክፍል አጠቃላይ ውጤት ላይ አሉታዊ ተፅዕኖ የፈጠሩ እና የትምህት ጥራት ያጓደሉ ችግሮችን ቀርፈን በአጭር ጊዜ 6ኛ እና 8ኛ ክፍልን ጨምሮ በ2ኛ ደረጃ የተማሪዎቻችን አበረታች ውጤት አስመዝግበናል ።

የተሻሻሉ የመማሪያ ክፍሎች፣ ቤተ መፃህፍትና ቤተ ሙከራ፣ የህፃናት ማረፊያ፣ ፅዱና አረንጓዴ ቅጥር ጊቢ፣ የስፖርት ማዘውተሪያ ያላቸውን የትምህርት መሰረተ ልማቶች እያስፋፋን እንገኛለን። የተቀናጀና የተናበበ እቅድ በመንደፍ የስራ ባህላችንን በማሻሻል በሰራናቸው ስራዎች ውጤታማ ሆነናል።

በዚህ ስራ በመሳተፍ ትውልዱ ላይ መልካም ዘርን የዘራችሁትን ሁሉ ላመሰግን እወዳለሁ።

የአዲስ አበባ ከተማ አሰተዳደር የከተማዋን የትምህርት ተደራሽነት ለማረጋገጥ እና የትምህርት ቤቶችን መሰረተ ልማት ለማሻሻል በያዘው እቅድ ባለፉት አምስት ዓመታት 110 አዳዲስ ትምህርት ቤቶች ተገንብተዋል። በነባር ትምህርት ቤቶች ውስጥ የማስፋፋያ ስራ በመስራትም ከ30 ሺህ በላይ የመማሪያ ክፍሎችን መገንባት እና 334 መመገቢያ አዳራሾች፣ 206 ቤተ ሙከራ እና ቤተመጽሐፍት፣ የስፖርት ማዘውተሪያ ስፍራ መገንባት ችለናል። እንዲሁም ትምህርት ቤቶች አካታች፣ ምቹ፣ ውብና ንፁህ፣ የደህንነትና የውበት ደረጃን የጠበቀ አጥር መገንባት ተችሏል፡፡

ፈጣሪ ኢትዮጵያን እና ህዝቦቿን የባርክ
ክብርት ከንቲባ አዳነች አቤቤ
👍3
የረዳን ፈጣሪ የተመሰገነ ይሁን!

ዛሬ የ2017 በጀት ዓመት እቅድ አፈፃፀም ግምገማ እና የ2018 በጀት ዓመት እቅድ ውይይት ማካሄድ ጀምረናል።

የ2017 በጀት ዓመት ከመቼውም የበለጠ ስኬት ያስመዘገብንበት ነው ፤ የእቅድ አፈፃፀማችን 95 በመቶ ተሳክቷል።

መዲናችንን ለሀገር ክብር የምትመጥን፣ እንደ ስሟ “ውብ አበባ" ለማድረግ በኮሪደር ልማት፣ በከተማ መልሶ ማልማት እና በወንዞች ዳርቻ ልማት ስራዎች፤ በስራ እድል ፈጠራ እና የገቢ እቅድን በማሳካትና ያገኘነውን ገቢ በቁጠባና ብክነትን በማስወገድ ለዘላቂ ልማትና ድህነት ቅነሳ በማዋል ዙሪያ በተከናወኑ ስራዎች አመርቂ ውጤቶችን አስመዝግበናል።

በሁሉም ስራዎቻችን ውስጥ ህብረተሰቡን በማሳተፍ የዘላቂና አስተማማኝ ሰላም ቀጣይነትን ያረጋገጥንበት፣ የበጀት ጉድለትን በህብረተሰብ ተሳትፎና በጐ አገልግሎት እየሞላን ከህዝብ ጋር ተቀራርበን በመስራት ውጤታማ የሆንበት በጀት ዓመት ነው።
ለነዚህ ሁሉ ስኬቶች አብራችሁን የለፋችሁ፣ ከራሳችሁ በላይ ህዝባችንን ያስቀደማችሁ የከተማችን ነዋሪዎች እና የደከማችሁና ውጤት ያስመዘገባችሁ አመራሮቻችንን እና ሰራተኞቻችንን ከልብ እናመሰግናችኋለን።

ፈጣሪ ኢትዮጵያንና ህዝቦቿን ይባርክ
ከንቲባ አዳነች አቤቤ
ምቹ መኖሪያ አካባቢ ለመፍጠር እየሰሩ መሆኑን የኮልፌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 3 ነዋሪዎች ተናገሩ፡፡

አዲስ አበባን ለስሟ የሚመጥን ገፅታ አላብሶ እንደ ስሟ ውብ፣ ለነዋሪዎቿ ምቹ፣ ወደ ከተማይቱ ጎራ ለሚሉት ደግሞ ሳቢ በማድረግ የአፍሪካ የብልጽግና ተምሳሌት እንድትሆን በእቅድ ተይዞ ዘርፈ ብዙ ተግባራት እየተከናወኑ ይገኛሉ። ከነዚህ አበይት ተግባራት መካከል አንዱና ዋነኛው ሞዴል ብሎኮችን መፍጠር ነዉ።

በክፍለ ከተማው ወረዳ 03 አስተዳደር የተቀናጀ ሞዴል ብሎኮችን በመፍጠር ምቹና ውብ አካባቢን እውን ለማድረግ ነዋሪዎችን ያሳተፈ እንቅስቃሴ ተጠናክሮ ቀጥሏል።

በወረዳው የረጲ የጋራ መኖሪያ ቤት ነዋሪዎች እንደሚሉት አካባቢያቸውን ሞዴል ለማድረግ የተሟላ መሰረተ ልማት፣ አስተማማኝ ጥበቃ፣ መናፈሻና መዝናኛ፣ ፅዳትና ውበት እንዲሁም የህጻናት መጫወቻ ሠርተዋል።

ነዋሪዎች ብሎካቸውን በማልማት፣ በማፅዳት፣ በማስዋብና ሠላማዊ በማድረግ እየተሳተፉ እንደሚገኙ ተናግረዋል፡፡ በቀጣይም የተጀመሩ ሞደል ብሎኮችን አጠናክሮ በማስቀጠል ሌሎች ተጨማሪ ምቹ ብሎኮችን ለመፍጠር ተሳትፏቸውን አጠናክረው እንደሚቀጥሉ መናገራቸውን የክፍለ ከተማው ኮሙኒኬሽን ፅህፈት ቤት ዘግቧል።

#reelschallengereelschallenge
#housedevelopment
#GreenLegacy