የኀብረተሰብ ተሳትፎና በጎ ፈቃድ ማስተባበሪያ ኮሚሽን - አዲስ አበባ
835 subscribers
2.14K photos
47 videos
265 links
Download Telegram
የረዳን ፈጣሪ ይመስገን !!
እንኳን ደስ አላችሁ!!

ዛሬ በመዲናችን 31.5 ኪሎ ሜትር ርዝመት ያላቸዉ 13 የመንገድ ፕሮጀክቶችን እና 8 ድልድዮችን አጠቃላይ 21 ፕሮጄክቶችን መርቀን ለአገልግሎት ክፍት አድርገናል፡፡

ከተማችንን ለማዘመን ከኮሪደር ልማት ስራዎቻችን ባሻገር የመንገድ መሰረተ ልማት ተደራሽነትን ለማረጋገጥ ልዩ ትኩረት ሰጥተን እየሰራ እንገኛለን፡፡

ዛሬ የተመረቁት እነዚህ የመንገድ መሰረተ ልማቶች ፦

ከአጉስታ- ወይራ መጋጠሚያ፣ቱሉዲምቱ ኮንዶሚኒያም መቃረቢያ፣
ከቃሊቲ ቀለበት መንገድ ዐደባባይ - በአቃቂ ድልድይ-ቱሉ ዲምቱ ዐደባባይ፣
ከቃሊቲ ቀለበት መንገድ አደባባይ ቡልቡላ-ቂሊንጦ 2ኛ ቀለበት መንገድ አደባባይ፣
የለቡ አደባባይ ማሻሻያ ፕሮጀክት፣
ከአፍሪካ ህንፃ- ጀሞ መስታዎት ፋብሪካ፣
ከቂርቆስ ማርገጃ - ቡልጋሪያ፣
ከቤላ -ፈረንሣይ ፓርክ - ፈረንሣይ አቦ ቤተክርስቲያን፣
ከናሰዉ ሪል ስቴት አርሴማ ቀለበት መንገድ እና ዮናስ ሆቴል ኬብሮን ፋርማሲ አስፋልት መንገዶች ናቸው፡፡

ፈጣሪ ኢትዮጵያን እና ህዝቧቿን ይባርክ
ከንቲባ አዳነች አቤቤ
21 ፕሮጀክቶች ተጠናቀው ለአገልግሎት ክፍት ሆኑ፣

ዛሬ በመዲናችን 31.5 ኪ.ሜትር ርዝመት ያላቸዉ 13 የመንገድ ፕሮጀክቶችን እና 8 ድልድዮችን በአጠቃላይ 21 ፕሮጄክቶችን መርቀን ለአገልግሎት ክፍት አድርገናል፡፡

ዛሬ የተመረቁት እነዚህ የመንገድ መሰረተ ልማቶች ፦

👉ከአጉስታ- ወይራ መጋጠሚያ፣ቱሉዲምቱ ኮንዶሚኒያም መቃረቢያ
👉ከቃሊቲ ቀለበት መንገድ ዐደባባይ - በአቃቂ ድልድይ-ቱሉ ዲምቱ ዐደባባይ
👉ከቃሊቲ ቀለበት መንገድ አደባባይ ቡልቡላ-ቂሊንጦ 2ኛ ቀለበት መንገድ አደባባይ
👉የለቡ አደባባይ ማሻሻያ ፕሮጀክት
👉ከአፍሪካ ህንፃ- ጀሞ መስታዎት ፋብሪካ
👉ከቂርቆስ ማርገጃ - ቡልጋሪያ
👉ከቤላ -ፈረንሣይ ፓርክ - ፈረንሣይ አቦ ቤተክርስቲያን
👉ከናሰዉ ሪል ስቴት አርሴማ ቀለበት መንገድ እና ዮናስ ሆቴል ኬብሮን ፋርማሲ አስፋልት መንገዶች ናቸው።
ተግተዉ የሰሩትን ሁሉ እናመሰግናለን !

የከተማ አስተዳደራችን 15,960 ፕሮጀክቶችን ከዛሬ ጀምሮ ለህዝብ አገልግሎት ክፍት ማድረግ ጀምረናል ።

በተለያዩ የከተማዋ ክፍሎች የተገነቡ አጭር እና አቋራጭ መንገዶች ፤ የትራፊክ ማሳለጫ ተሻጋጋሪ ድልድዮች የትራፊክ ፍሰትን በማቀላጠፍ እና ፕሮጀክቶቻችን በማያያዝ ለነዋሪው ኢኮኖሚያዊ እና ማህበራዊ እድገት ጉልህ ድርሻ ያለቸው ናቸው ።

ፕሮጀክቶቹ ከ50 እስከ 60 ስፋት ያላቸዉ ድልድዮቹ እስከ 300 ሜትር ርዝመት ያላቸዉ ግዙፍ መንገዶች ያካተቱ ናቸው።
እነዚህ ፕሮጀክቶች፤ ከዉጪ በሚገኝ ብድር ይገነባል ተብሎ የተጀመረ ቢሆንም ብድሩ ሳይገኝ ቀርቶ በከተማ አስተዳደሩ አቅም መገንባት የተቻለ ነዉ።

የከተማችን ነዋሪዎችም የተገነቡ መንገዶችን በአግባቡ እንድትጠቀሙበት አደራ እያልኩኝ ፤ግንባታው ተጠናቆ ለአገልግሎት እንዲበቃ የበኩላችሁን ድርሻ ላበረከታችሁ የአዲስ አበባ ከተማ መንገድ ባለስልጣን ፤ የመንግስት እና የግል ድርጅቶች ፣ ኮንትራክተሮች ፣ አማካሪ ድርጅቶች እና የአቃቂ ቃሊቲ እና የቦሌ ክለከተማ አመራሮች እና ነዋሪዎች እና ድርሻ ለነበራችሁ ሁሉ በከተማ አስተዳደሩ እና በራሴ ስም ላመሰግናችሁ እወዳለሁ።

ፈጣሪ ኢትዮጵያ እና ህዝቦቿን ይባርክ!
👍2
በእርግጥም የተሻለው ሁሉ ይገባችኋል !

ዛሬ ማለዳ በ11 ክፍለ ከተሞች ከ5 ቢለዬን ብር በላይ ወጪ ተደርጎባቸዉ የተገነቡ 122 የስፖርት ማዘውተሪያ እና 1,155 የህፃናት መጫወቻ ማዕከላትን በጥቅሉ 1277 ፕሮጀክቶችን ለአገልግሎት ክፍት አድርገናል።

ይህ ውሳኔያችን በአዕምሮና በአካል የዳበረ ትውልድ ለመገንባት ከከተማችን ሀብት መሬት እና በጀት፤ ከእኛ ከአመራሮች እና ከሰራተኛው ደግሞ ጉልበት እና ጊዜ እፍታውን ወስደን እንዲሁም ማህበረሰቡን በማስተባበር ለትውልዱ ቅድሚያ ስጥተን ዛሬን ብቻ ሳይሆን ነገን ገንብተናል ።
ባለፋት 3 ዓመታት ለስራ ቦታዎች እና ለመኖሪያ አካባቢዎች ጭምር ትኩረት በመስጠት በድምሩ 3,789 የህፃናት የመጫወቻ ማዕከላትን እና 1,530 የስፖርት ማዘውተሪያ ሥፍራዎችን ገንብተን ለአገልግሎት ክፍት አድርገናል።

“ድር ቢያብር አንበሳ ያስር” እንዲሉ እነዚህ ደረጃዉን ጠብቀን የገነባናቸዉ መሰረተ ልማቶች 50 % ወጪያቸው የተሸፈነዉ በማህበረሰቡ መሆኑ ልዩ ያደርጋቸዋል።

በመጨረሻም፣ ለወጣቶችና ህጻናት የስፖርት ማዘውተሪያና መጫወቻ ማዕከላትን ለመገንባት ስናደርገው በነበረው ጥረት ሁሉ የላቀ አስተዋጽኦ ላበረከቱና ላስተባበሩ አካላት ምስጋናዬን አቀርባለሁ።

ፈጣሪ ኢትዮጵያን እና ህዝቧቿን ይባርክ
ከንቲባ አዳነች አቤቤ
3
የኀብረተሰብ ተሳትፎና በጎ ፈቃድ ማስተባበሪያ ኮሚሽን - አዲስ አበባ
Photo
በአዕምሮና በአካል የዳበረ ትውልድ ለመገንባት በሰጠነው ልዩ ትኩረት ዛሬ በ11 ክ/ከተሞች የሰራናቸው ፕሮጀክቶች ተመርቀው ለወጣቶችና ህፃናት ክፍት ተደርገዋል::

👉 122 የስፖርት ማዘውተሪያዎዎች
👉1155 የህፃናት መጫወቻ ማዕከላት
👉ባለፋት 2 ዓመታት ደግሞ ለህፃናት መጫወቻ በድምሩ 3,789
👉ባለፉት 3 ዓመታት ደግሞ የስፖርት ማዘውተሪያ 1,530 ሥፍራዎችን ገንብተን ለአገልግሎት ክፍት አድርገናል።

የዚህ ሥራ ውጤት ሰው ተኮር መሆናችንን ያስመሰከረ እና የገባነውን ቃል በተግባይ ለመፈፀማችን ማሳያ ነው።
👍2
የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት 4ኛ መደበኛ ጉባኤን ዛሬ ማካሄድ ይጀምራል

የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት 4ኛ ዓመት የሥራ ዘመን 4ኛ መደበኛ እና የበጀት አመቱን ማጠቃለያ ጉባኤ ሃምሌ 4 እና 5 ቀን 2017 ዓ.ም በአድዋ ድል መታሰቢያ ያካሄዳል።

በጉበኤዉ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የ2017 በጀት ዓመት የዕቅድ አፈጻጸም ሪፖርት እና የ2018 በጀት ዓመት ዋና ዋና አቅጣጫዎች ይቀርባሉ ተብሎ ይጠበቃል።
👏1
3ኛው የአዲስ አበባ ምክር ቤት 4ኛ አመት የስራ ዘመን 4ኛ መደበኛ ጉባኤ መካሄድ ጀምሯል።

የጉባኤው አጀንዳዎች፦

1. የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የ2017 በጀት ዓመት ዕቅድ አፈጻጸም ሪፖርትና የ2018 በጀት ዓመት እቅድ የትኩረት አቅጣጫዎች፣

2. የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ዋና ኦዲተር መስሪያ ቤት የ2017 በጀት ዓመት የኦዲት ሪፖርትን ማድመጥ፤

3. የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ፍርድ ቤቶች የ2017 በጀት አመት ዕቅድ አፈጻጸም ሪፖርት ላይ ተወያይቶ ማጽደቅ፣

4. የአዲስ አበባ ከተማ አስፈጻሚ አካላትን ስልጣንና ተግባር እንደገና ለመወሰን የወጣውን አዋጅ ቁጥር 84/2016 ለማሻሻል የቀረበው ረቂቅ አዋጅ ላይ ተወያይቶ ማጽደቅ፤

5. የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የ2018 በጀት ረቂቅ አዋጅ ላይ በመወያየት ማጽደቅ

6. ልዩ ልዩ ሹመቶችን ማጽደቅ፣

#addisababa
ሰላምና ፀጥታን በተመለከተ፣

👉በሠላምና ፀጥታ ጉዳዮች የኅብረተሰቡን ተሳትፎ ለማጎልበት በአካባቢ ሠላም፣ በአብሮነትና ትብብር የሰላም እሴት ግንባታ ዙሪያ በድግግሞሽ ከ7.9 ሚሊዮን በላይ የኅብረተሰብ ክፍሎችን በግንዛቤ በብሎክ የማኅበረሰብ አቀፍ ምክክር መድረኮች ላይ ማሳተፍ ተችሏል።

👉በማኅበረሰብ አቀፍ ፀጥታ አጠባበቅ ላይም አካባቢን በመጠበቅ፣ ለወንጀለኞች መደበቂያ ሊሆኑ የሚችሉ ሁኔታዎች በማጽዳትና የሥጋት ቦታዎችን ለይቶ መከላከል እንዲቻል የሠላም ሠራዊት አደረጃጀቶችን እና የማኅበረሰብ ክፍሎችን በማሳተፍ ሕዝቡን የሰላም ባለቤት ማድረግ ተችሏል።

👉የወንጀል ድርጊቶችን በመቀነስ ረገድ ከ3,628 በላይ የፀጥታ መረጃዎችና ጥቆማዎች በመሰብሰብና በማደራጀት ህገ ወጥ የገንዘብ ዝውውር እና ሃሰተኛ ሰነድ፣ከከባድና ቀላል ወንጀል፣ ከትምህርት ተቋማት ደህንነት፣ ለፀጥታና ደህንነት አስጊ ከሆኑ ሁኔታዎችና ግጭቶች እንዲሁም ከተለያዩ አዋኪ ድርጊቶች፤ ከኢኮኖሚ አሻጥርና ህገ ወጥ የንግድ ቁጥጥር ጋር በተያያዘ ከሌሎች ሕግ አስከባሪ አካላት ጋር በመቀናጀት 11,517 የወንጀል ድርጊቶችና የፀጥታ ስጋቶችን የመለየት፣ የመከላከል እና እርምጃ እንዲወሰድ የማድረግ ሥራ ተሰርቷል።
1
የተቋም ግንባታና አገልግሎነት አሰጣጥ በተመለከተ

👉በተቋማት ምቹ የስራ አካባቢ ለመፍጠር ከ2 ሽህ 147 በላይ የመንግስት ሰራተኞች በህጻናት ማቆያ ልጆቻቸውን እንዲከባከቡ በማድረግ ተጠቃሚ እንዲሆኑ ተደርጓል።

👉በተቋማት ከ185 በላይ የመንግስት ሰራተኞች ካፍቴሪያዎችን በመገንባት እና አገልግሎት እንዲሰጡ በማድረግ እንዲሁም ከ150 የሸማች ሱቆችን ወደ ስራ በማስገባት ሰራተኞ የኑሮ ውድነቱን እንዲቋቋም የሚያስችል ምቹ ሁኔታ ተፈጥሯል።

👉ከ21 ሽህ 046 የተገልጋይ ማረፊያ በማዘጋጀት ምቹ የአገልግሎት መስጫ ተቋማት ተገንብተዋል።

👉በተቋማት 347 አገልግሎቶችን ዲጂታላይዝ በማድረግ ብልሹ አሰራር፣የተገልጋይ እንግልትና ምልልስ በማስቀረት የሚቀርቡ ቅሬታዎች እንዲቀንሱ አድርጓል።

👉በሌብነትና ብልሹ አሰራር ተግባር ውስጥ የገቡ 4 ሽህ 965 አመራሮች፣ ፈጻሚዎች እና ተገልጋዩችን ተጠያቂ በማድረግ ህጋዊ እና አስተዳደራዊ እርምጃዎች ተወስዷል።