የኀብረተሰብ ተሳትፎና በጎ ፈቃድ ማስተባበሪያ ኮሚሽን - አዲስ አበባ
837 subscribers
2.14K photos
47 videos
265 links
Download Telegram
የቂርቆስ ክፍለ ከተማ የ2017 ዓ.ም የክረምት በጎ ፈቃድ ፕሮግራሞችን በነፃ ህክምና በደም ልገሳ አስጀምሯል።

የቂርቆስ ክፍለ ከተማ አስተዳደር "በጎ ፈቃደኝነት ለማህበረሰብ ለውጥ!" በሚል መሪ ሃሳብ የ2017 የክረምት በጎ ፈቃድ አገልግሎት ፕሮግራሞችን በደም ልገሳና በነፃ የህክምና አገልግሎት አስጀምሯል።

መርሃ ግብሩን በንግግር የከፈቱት የክፍለ ከተማው ዋና ስራ አስፈጻሚ ዶ/ር አዲሱ ሻንቆ የበጎ ፍቃድ አገልግሎት ዜጎች ውስጣቸው ከሚሰማቸው ሰብዓዊ አመለካከት ተነስተው የሚከውኑት መልካም ተግባር መሆኑን ተናግረዋል።

በጎ ፈቃደኞች በክፍለ ከተማው በበጋ ወቅት በተከናወኑ የበጎ ፈቃድ ተግባራት ላይ ከፍተኛ ተሳትፎ ማድረጋቸውን የገለፁት ዋና ስራ አስፈጻሚው በአስተዳደሩ ስም ምስጋና አቅርበውላቸዋል።

በበጋ በጎ ፈቃድ 45 ሺ 987 ፈቃደኞችን በማስተባበር የአቅመ ደካሞችን ቤት መገንባት መቻሉን የገለጹት የኅብረተሰብ ተሳትፎና በጎ ፈቃድ ማስተባበሪያ ፅህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ኢብራሂም አባስ በሌሎች የበጎ ፍቃድ ተግባራትም ከፍተኛ ውጤት መመዝገቡን ጠቁመዋል ሲል የክፍለ ከተማው ኮሙኒኬሽን መረጃ ያመለክታል።

የክረምት በጎ ፈቃድ አገልግሎት በከተማ ደረጃ ባለፈው ሳምንት በ15 ፕሮግራሞች በከንቲባ አዳነች አቤቤ ይፋ መደረጉ ይታወሳል።

#volunteersmakeadifference
#voou@CommunityPVC
👍5
የኀብረተሰብ ተሳትፎና በጎ ፈቃድ ማስተባበሪያ ኮሚሽን - አዲስ አበባ
Photo
የዘንድሮው የአረንጓዴ ዐሻራ መርሃ ግብር "በመትከል ማንሰራራት" የሚል መሪ ቃል የተሰጠው ነው።

የአረንጓዴ ዐሻራ እጅግ ዘርፈ ብዙ ትርፋቶችን ያስገኘ ስራ ነው። በዚህ ዓመት ከሚተከለው ችግኝ ጋር ከ47.5 ቢሊየን ገደማ እንደርሳለን። ይህም በሚቀጥለው ዓመት ከምንተክለው ጋር ሲደመር 54 ቢሊየን ልንደርስ ያስችለናል።

በዚህ መርሃ ግብር ያመናችሁ፣የተሳተፋችሁ እጆቻችሁ ጭቃ የነካ፥ የተከላችሁ፥ የተንከባከባችሁ ኢትዮጵያውያን፣በኢትዮጵያ የምትገኙ ዲፕሎማቶች፣ይህንን ህልም የደገፋችሁ የየትኛው ሃገር ዜጎች በሙሉ እንኳን ደስ አላችሁ፥ እንኳን ደስ ያለን ልላችሁ እወዳለሁ።

ከነገ ጀምሮ በየዕለቱ የኢትዮጵያ ማንሰራራት ማሳያ በሆነው የአረንጓዴ ዐሻራ መርሃ ግብር ሁሉም የህብረተሰብ ክፍልና የዲፕሎማቲክ ማህበረሰቡ እንዲሳተፍ ጥሪዬን አቀርባለሁ።

Sagantaa Ashaaraa Magariisaa baranaaf yaada ijoo "Dhaabuudhaan Bayyanachuu" jedhutu kennameefi.

Hojiin Ashaaraa Magariisaa bu'aawwan hedduu kan argamsiisedha. Biqiltuuwwan barana dhaabamuuf jiran waliin gara biliyoona 47.5 geenya. Kun isa bara dhufu dhaabnu waliin yoo ida'ame biliyoona 54 gahuu nudandeessisa.

Warri sagantaa kanatti amantan, kan hirmaattan, warri harki keessan dhoqqee tuqe, warri dhaabdan, Itoophiyaanonni kunuunsitan, dippiloomaatonni Itoophiyaatti argamtan, lammiileen biyya kamiyyuu kan abjuu kana deeggartan hundi baga gammaddani, baga gammanne jechuun barbaada.

Borirraa eegalee guyyaa guyyaadhaan sagantaa #Ashaaraa Magariisaa Itoophiyaa agarsiiftuu bayyanachuu Itoophiyaa ta'e irratti kutaaleen hawaasaa hundiifi hawaasni dippiloomaasii akka hirmaattanin waamichakoo dhiyeessa.

This year’s Green Legacy program is themed: “Renewal Through Planting.”

The Green Legacy is a comprehensive national initiative. This year alone, we aim to plant enough seedlings to bring the total to 47.5 billion. With continued commitment and participation, we aspire to reach 54 billion seedlings by next year.

I extend my heartfelt congratulations to all Ethiopians who believed in this vision—to those who took part, touched the soil, planted the seedlings, nurtured them, championed the cause, and supported the dream, both at home and abroad.

Starting tomorrow, I call on all sectors of society and the diplomatic community to actively engage in the Green Legacy program—a daily symbol of Ethiopia’s renewal, resilience, and collective spirit.

The 2025 #GreenLegacy launch program - in pictures.

#PMOEthiopia
👍21
"ለግብፅና ለሱዳን እንዲሁም ለተፋሰሱ ሀገራት መንግስታት በሙሉ መስከረም ላይ ህዳሴን ስናስመርቅ የደስታችን ተካፋይ እንዲሆኑ በይፋ እንጋብዛለን።" ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አህመድ

ማስፈንጠሪያውን ተጭነው በኤክስ(x) አማራጭ ይከታተሉን!
https://x.com/CommunityPVC/status/1941202898945519904?t=xe23JmMnVJ6v2otMRnjnCg&s=19
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ካቢኔ 4ኛ ዓመት 13ኛ መደበኛ ስብሰባዉን በሶስት ወሳኝ ከተማ አቀፍ አጀንዳዎች ላይ ተወያይቶ የሚከተሉትን ውሳኔዎች አሳልፏል፡፡

1ኛ:- የከተማዋን ፈጣን ለዉጥ ታሳቢ በማድረግ፣ ወጪን ለመቀነስ ፣ አገልግሎት አሰጣጥን ለማሻሻል እና ወጤታማነትን ለማሳደግ እንዲረዳ ተጠንቶ የቀረበዉ የአስፈፃሚ አካላትን ስልጣንና ተግባር የማሻሽያ አዋጅ ላይ ተወያይቶ ለምክር ቤት እንዲቀርብ ዉሳኔ አሳልፏል፡፡

በዚህም መሠረት :-
1..ቱሪዝም ዘርፍ ራሱን ችሎ በኮሚሽን እንዲቋቋም፤
2..የዲዛይን እና ግንባታ ሥራዎች ቢሮ እና የትላልቅ ፕሮጀክቶች ግንባታ ፅ/ቤት እንዲዋሀዱ፤

3.. ማኅበራዊ ትረስት ፈንድ ፅ/ቤት ከኅብረተሰብ ተሳትፎና በጎ ፈቃድ ማስተባበሪያ ኮሚሽን ጋር እንዲዋሀድ፣

4..የከተማ ውበትና አረንጓዴ ልማት ቢሮ የህዝብ መፀዳጃ ቤቶችን የማልማት ተግባርን ለውሃና ፍሳሽ ባለሥልጣን ማስተላለፍን ያከተተ ማሻሻያዎች ተደርጎ ለምክ ቤት እንዲቀርብ ወስኗል።

2ኛ:-ለአስተዳደራዊ አመቺነት ፣ ለአገልግሎት ተደራሽነት እና ወጪን ለመቀነስ እንዲያግዝ በፕላን ልማት ቢሮ ተጠንቶ በቀረበዉ የሶስት የወረዳዎች አስተዳደር ወሰን ማሻሻል ጥናት ላይ ተወያይቶ አገልግሎት ተደራሽነትን እና ወደፊት በከተማዋ የሚመጣውን ልማት ታሳቢ ያደረገ በመሆኑ የቀረበውን ማሻሻያ ሀሳብ በሙሉ ድምፅ አፅድቋል፡፡

3ኛ:-በጤና ቢሮ በኩል ተጠንቶ በቀረበዉ የማህበረሰብ አቀፍ ጤና መድህን አባላት ክፍያ መጠን ላይ ተወያይቶ ዉሳኔ አሳልፏል፡፡

4ኛ. አገራዊ ፋይዳ ያላቸውን ፕሮጀክቶች ላይ የቀረበ የመሬት ልማት ጥያቄ ላይ በመወያየት አፅድቋል ።
3
የረዳን ፈጣሪ ይመስገን !!
እንኳን ደስ አላችሁ!!

ዛሬ በመዲናችን 31.5 ኪሎ ሜትር ርዝመት ያላቸዉ 13 የመንገድ ፕሮጀክቶችን እና 8 ድልድዮችን አጠቃላይ 21 ፕሮጄክቶችን መርቀን ለአገልግሎት ክፍት አድርገናል፡፡

ከተማችንን ለማዘመን ከኮሪደር ልማት ስራዎቻችን ባሻገር የመንገድ መሰረተ ልማት ተደራሽነትን ለማረጋገጥ ልዩ ትኩረት ሰጥተን እየሰራ እንገኛለን፡፡

ዛሬ የተመረቁት እነዚህ የመንገድ መሰረተ ልማቶች ፦

ከአጉስታ- ወይራ መጋጠሚያ፣ቱሉዲምቱ ኮንዶሚኒያም መቃረቢያ፣
ከቃሊቲ ቀለበት መንገድ ዐደባባይ - በአቃቂ ድልድይ-ቱሉ ዲምቱ ዐደባባይ፣
ከቃሊቲ ቀለበት መንገድ አደባባይ ቡልቡላ-ቂሊንጦ 2ኛ ቀለበት መንገድ አደባባይ፣
የለቡ አደባባይ ማሻሻያ ፕሮጀክት፣
ከአፍሪካ ህንፃ- ጀሞ መስታዎት ፋብሪካ፣
ከቂርቆስ ማርገጃ - ቡልጋሪያ፣
ከቤላ -ፈረንሣይ ፓርክ - ፈረንሣይ አቦ ቤተክርስቲያን፣
ከናሰዉ ሪል ስቴት አርሴማ ቀለበት መንገድ እና ዮናስ ሆቴል ኬብሮን ፋርማሲ አስፋልት መንገዶች ናቸው፡፡

ፈጣሪ ኢትዮጵያን እና ህዝቧቿን ይባርክ
ከንቲባ አዳነች አቤቤ
21 ፕሮጀክቶች ተጠናቀው ለአገልግሎት ክፍት ሆኑ፣

ዛሬ በመዲናችን 31.5 ኪ.ሜትር ርዝመት ያላቸዉ 13 የመንገድ ፕሮጀክቶችን እና 8 ድልድዮችን በአጠቃላይ 21 ፕሮጄክቶችን መርቀን ለአገልግሎት ክፍት አድርገናል፡፡

ዛሬ የተመረቁት እነዚህ የመንገድ መሰረተ ልማቶች ፦

👉ከአጉስታ- ወይራ መጋጠሚያ፣ቱሉዲምቱ ኮንዶሚኒያም መቃረቢያ
👉ከቃሊቲ ቀለበት መንገድ ዐደባባይ - በአቃቂ ድልድይ-ቱሉ ዲምቱ ዐደባባይ
👉ከቃሊቲ ቀለበት መንገድ አደባባይ ቡልቡላ-ቂሊንጦ 2ኛ ቀለበት መንገድ አደባባይ
👉የለቡ አደባባይ ማሻሻያ ፕሮጀክት
👉ከአፍሪካ ህንፃ- ጀሞ መስታዎት ፋብሪካ
👉ከቂርቆስ ማርገጃ - ቡልጋሪያ
👉ከቤላ -ፈረንሣይ ፓርክ - ፈረንሣይ አቦ ቤተክርስቲያን
👉ከናሰዉ ሪል ስቴት አርሴማ ቀለበት መንገድ እና ዮናስ ሆቴል ኬብሮን ፋርማሲ አስፋልት መንገዶች ናቸው።
ተግተዉ የሰሩትን ሁሉ እናመሰግናለን !

የከተማ አስተዳደራችን 15,960 ፕሮጀክቶችን ከዛሬ ጀምሮ ለህዝብ አገልግሎት ክፍት ማድረግ ጀምረናል ።

በተለያዩ የከተማዋ ክፍሎች የተገነቡ አጭር እና አቋራጭ መንገዶች ፤ የትራፊክ ማሳለጫ ተሻጋጋሪ ድልድዮች የትራፊክ ፍሰትን በማቀላጠፍ እና ፕሮጀክቶቻችን በማያያዝ ለነዋሪው ኢኮኖሚያዊ እና ማህበራዊ እድገት ጉልህ ድርሻ ያለቸው ናቸው ።

ፕሮጀክቶቹ ከ50 እስከ 60 ስፋት ያላቸዉ ድልድዮቹ እስከ 300 ሜትር ርዝመት ያላቸዉ ግዙፍ መንገዶች ያካተቱ ናቸው።
እነዚህ ፕሮጀክቶች፤ ከዉጪ በሚገኝ ብድር ይገነባል ተብሎ የተጀመረ ቢሆንም ብድሩ ሳይገኝ ቀርቶ በከተማ አስተዳደሩ አቅም መገንባት የተቻለ ነዉ።

የከተማችን ነዋሪዎችም የተገነቡ መንገዶችን በአግባቡ እንድትጠቀሙበት አደራ እያልኩኝ ፤ግንባታው ተጠናቆ ለአገልግሎት እንዲበቃ የበኩላችሁን ድርሻ ላበረከታችሁ የአዲስ አበባ ከተማ መንገድ ባለስልጣን ፤ የመንግስት እና የግል ድርጅቶች ፣ ኮንትራክተሮች ፣ አማካሪ ድርጅቶች እና የአቃቂ ቃሊቲ እና የቦሌ ክለከተማ አመራሮች እና ነዋሪዎች እና ድርሻ ለነበራችሁ ሁሉ በከተማ አስተዳደሩ እና በራሴ ስም ላመሰግናችሁ እወዳለሁ።

ፈጣሪ ኢትዮጵያ እና ህዝቦቿን ይባርክ!
👍2
በእርግጥም የተሻለው ሁሉ ይገባችኋል !

ዛሬ ማለዳ በ11 ክፍለ ከተሞች ከ5 ቢለዬን ብር በላይ ወጪ ተደርጎባቸዉ የተገነቡ 122 የስፖርት ማዘውተሪያ እና 1,155 የህፃናት መጫወቻ ማዕከላትን በጥቅሉ 1277 ፕሮጀክቶችን ለአገልግሎት ክፍት አድርገናል።

ይህ ውሳኔያችን በአዕምሮና በአካል የዳበረ ትውልድ ለመገንባት ከከተማችን ሀብት መሬት እና በጀት፤ ከእኛ ከአመራሮች እና ከሰራተኛው ደግሞ ጉልበት እና ጊዜ እፍታውን ወስደን እንዲሁም ማህበረሰቡን በማስተባበር ለትውልዱ ቅድሚያ ስጥተን ዛሬን ብቻ ሳይሆን ነገን ገንብተናል ።
ባለፋት 3 ዓመታት ለስራ ቦታዎች እና ለመኖሪያ አካባቢዎች ጭምር ትኩረት በመስጠት በድምሩ 3,789 የህፃናት የመጫወቻ ማዕከላትን እና 1,530 የስፖርት ማዘውተሪያ ሥፍራዎችን ገንብተን ለአገልግሎት ክፍት አድርገናል።

“ድር ቢያብር አንበሳ ያስር” እንዲሉ እነዚህ ደረጃዉን ጠብቀን የገነባናቸዉ መሰረተ ልማቶች 50 % ወጪያቸው የተሸፈነዉ በማህበረሰቡ መሆኑ ልዩ ያደርጋቸዋል።

በመጨረሻም፣ ለወጣቶችና ህጻናት የስፖርት ማዘውተሪያና መጫወቻ ማዕከላትን ለመገንባት ስናደርገው በነበረው ጥረት ሁሉ የላቀ አስተዋጽኦ ላበረከቱና ላስተባበሩ አካላት ምስጋናዬን አቀርባለሁ።

ፈጣሪ ኢትዮጵያን እና ህዝቧቿን ይባርክ
ከንቲባ አዳነች አቤቤ
3