የኀብረተሰብ ተሳትፎና በጎ ፈቃድ ማስተባበሪያ ኮሚሽን - አዲስ አበባ
835 subscribers
2.14K photos
47 videos
265 links
Download Telegram
ኑሮ ውድነት ከሰብል ምርት ጋር እጥረት እንዳይገጥም ህብረት ስራ ማህበራትን ያላቸውን ካፒታል የሰብል ምርቶችን በመግዛት ስቶክ እንዲኖራቸው ተደርገዋል:: ምክትል ከንቲባ እና የኢንዱስትሪ ልማት ቢሮ ሃላፊ አቶ ጃንጥራር አባይ

• 216 የእሁድ ገበያዎች በአይነትና በጥራት ምርቶቻቸዉን በወጣላቸው ስታንዳርድ መሰረት እንደቀርቡ የማድረግ ስራን በከተማዋ የተቋቋመው የግብረ ሃይል አደረጃጀት ቁጥጥር እያደረገ እና ህጋዊ እርምጃ እየወሰደ በትኩረት እየተሰራ ነው፡፡

• ኮሪደር ልማቱን በተመለከተ ዘለቄታዊነት ያላቸውን የከተማውን እድገት ሊያፋጥኑ የሚችሉ ሁሉን አቀፍ ስራዎችን ለመስራት አስተዳደሩ ያለውን ምቹ ሁኔታ በማየት የቀጣይ ስራዎችን ጨምሮ በቅድመ ዝግጀት ስራዎች የሚሰሩትን በትኩረት አቅደን እና ዲዛይን አድርገን ተወያይተን በቀጣይ የበለጠ የሚሰራ ይሆናል፡:

• የአዲስ አበባ ከተማ የኑሮ ውድነትን ለመቀነስ የከተማ አስተዳደሩ የፐብሊክ ትራንስፖርት፤የቤት አቅርቦት፣የስራ እድል ፈጠራ ፣የትምህርት ቤት ምገባ እና ምገባ ማዕከላት ከተማ አስተዳደሩ ከፍተኛ በጀት በመደብ እየሰራ ይገኛል::

ከዚህም በተጨማሪ በከተማችን የሚገኙ 4 የገበያ ማዕከላት በቂ ምርት እንዲኖራቸው የማድረግ ስራ እተሰራ ሲሆን እነዚህም ስራዎች የኑሮ ውድነትን ለመቀነስ ከፍተኛ አስተዋፅኦ ያላቸዉ መሆኑን ልንገነዘብ ይገባል::
👍5
የበጎ ፈቃድ ማኅበራት ጥምረት በበጎ ፈቃድ አገልግሎትና ማኅበራዊ ኃላፊነት ደንብ ዙሪያ ምክክር አካሄደ።

በአዲስ አበባ ከተማ የኅብረተሰብ ተሳትፎና በጎ ፈቃድ ማስተባበሪያ ኮሚሽን የቋቋመው የበጎ ፈቃድ ማኅበራት ጥምረት ከተማ አስተዳደሩ ባዘጋጀው የበጎ ፈቃድ አገልግሎትና ማኅበራዊ ኃላፊነት ደንብ ቁጥር 161/2017 ዙሪያ ውይይት አካሂዷል።

ውይይቱ የጥምረቱ አባል ማኅበራት የበጎ ፈቃድ አገልግሎት ተቋማዊ ቅርፅ እንዲይዝና ኢኮኖሚያዊ አስተዋፅዖው እንዲታወቅ፣ የመረዳዳትና የመተሳሰብ እሴት እንዲዳብር የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ላወጣው ደንብ ተግባራዊነት የድርሻቸውን እንዲወጡ ለማድረግ እንደሚያግዝ በመድረኩ ተመላክቷል።

በሌላ በኩል ጥምረቱ በበጀት ዓመቱ ያለፉ ወራት ያከናወናቸው ዋና ዋና ተግባራት አፈፃጸም ቀርቦ ውይይት የተደረገ ሲሆን የጥምረቱን አባል ማህበራት የእርስ በርስ ግንኙነት በማጠናከረ የነዋሪዎችን ማኅበራዊና ኢኮኖሚያዊ ችግሮችን መፍታት እንደሚጠበቅ ተገልጿል።

በአዲስ አበባ ከተማ የሚገኙ የበጎ ፈቃድ ማኅበራት ከአንድ ዓመት በፊት በጋራ መስራት የሚያስችላቸውንና የማህበረሰቡን ተጠቃሚነት የሚያረጋግጡበት እንዲሁም እርስ በርስ ተሞክሯቸውን የሚለዋወጡበት ጥምረት መመስረታቸው ይታወሳል።

"በጎ ፈቃደኝነት ለማኅበረሰብ ለውጥ!"

ሚያዚያ 29/2017 ዓ.ም (አዲስ አበባ)
የማኀበራዊ ሚዲያ አማራጮቻችን፥
‎ፌስቡክ - https://www.facebook.com/cpvcc.2015
‎ቴሌግራም - https://t.me/CommunityPVC
‎ቲክቶክ - https://www.tiktok.com/@aacpvcc
‎ዩቱዩብ - https://youtube.com/@communityparticipationvolu8714
‎ዌብሳይት - www.aacpvcc.gov.et
የ2017/18 በጀት ዓመት የክረምት በጎ ፈቃድ ፕሮግራሞች ውጤታማ ለማድረግ በጎ ፈቃደኞችን ለአገልግሎት የማብቃት ስራ እየተከናወነ ነው።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የኅብረተሰብ ተሳትፎና በጎ ፈቃድ ማስተባበሪያ ኮሚሽን የ2017/18 በጀት ዓመት የክረምት በጎ ፈቃድ ፕሮግራሞች ለማሳካት በጎ ፈቃደኞችን ለአገልግሎት ብቁ የማድረግ የቅድመ ዝግጅት ስራ እያከናወነ ይገኛል።

የበጎ ፈቃድ አገልግሎት በራስ ተነሳሽነት ጊዜን፣ ጉልበትንና ገንዘብን ለማህበረሰብ ሁለንተናዊ ለውጥ በነፃ የማዋል ተግባር ሲሆን ይህንን ዓለም አቀፍና ወሰን የሌለው አገልግሎት በጥሩ ስብዕናና በመልካም ሥነ-ምግባር መተግበር ይገባል።

በከተማ ደረጃ አንድ ሺህ በጎ ፈቃደኞች በበጎ ፈቃድ ጽንሰ ሀሳብና በአገልግሎት ሥነ-ምግባር ዙሪያ በተለያዩ ዙሮች ስልጠና የወሰዱ ሲሆን ለመጭው የክረምት በጎ ፈቃድ አገልግሎት እስከ ወረዳ ድረስ ከ11 ሺህ በላይ በጎ ፈቃደኞች የሥነ-ምግባር ስልጠና ይወስዳሉ።

የ2017/18 የክረምት በጎ ፈቃድ አገልግሎት የከተማዋን ነዋሪዎች ማኅበራዊና ኢኮኖሚያዊ ተሳትፎና ተጠቃሚነት በሚያረጋግጥ መልኩ እየተዘጋጀ ሲሆን ከግንቦት 30 በፊት በተለያዩ ፕሮግራሞችና መርሀ ግብሮች ይፋ ይደረጋል።

"በጎ ፈቃደኝነት ለማኅበረሰብ ለውጥ!"
ሚያዚያ 29/2017 ዓ.ም (አዲስ አበባ)
የማኀበራዊ ሚዲያ አማራጮቻችን፥
‎ፌስቡክ - https://www.facebook.com/cpvcc.2015
‎ቴሌግራም - https://t.me/CommunityPVC
‎ቲክቶክ - https://www.tiktok.com/@aacpvcc
‎ዩቱዩብ - https://youtube.com/@communityparticipationvolu8714
‎ዌብሳይት - www.aacpvcc.gov.et
👍3
ከንቲባ አዳነች አቤቤ የአዲስ አበባ ከተማ ነዋሪዎችን ተጠቃሚ የሚያደርጉ የተለያዩ የሰው ተኮር ስራዎች መሰራታቸዉን እና እየተሰሩ መሆናቸዉን ከኢቲቪ ጋር በነበራቸዉ ቆይታ ገልፀዋል፡፡

ከንቲባዋ እንደገለፁት ምንም ገቢ የሌላቸዉ የከተማችን ነዋሪዎች በቀን 1 ጊዜ እንኳን መመገብ የሚቸገሩ የከተማችን ነዋሪዎች አሁን 36 ሺ የሚሆኑ ወገኖቻችን ትኩስ እና ንፁህ ምግብ በቀን 1 ጊዜ መመገብ የቻሉበት እና በዚህም ምግብ ብቻ ሳይሆን ክብርም፤ፍቅርም ያገኙበት ፕሮግራም መሆኑን ገልጸዋል::

በተጨማሪም ትዉልድ ላይ ትኩረት በማድረግ በተማሪዎች ምገባ በየትቤ/ቱ 1 ሚሊዮን የሚጠጉ ተማሪዎች በቀን 2 ጊዜ እንዲመገቡ ማድረግ የተቻለበትና የትምህርት ቁሳቁስ ግብዓት በሟሟላት የወላጆችን ጫናን ለማቃለል መንግስት ሃላፊነት ወስዶ እየሰራበት መሆኑንም አብራርተዋል፡፤

ከንቲባዋ አክለዉም በሰዉ ተኮር ስራወች ሰፋፊ እና በሚሊዮን የሚቆጠር የስራ እድል መፍጠር የተቻለበት እና በመሰረታዊነት የሰዉ ህይወት የተቀየረበት መሆኑን ገልፀዉ በሴፍቲኔት ብቻ ወደ 100ሺ የሚሆኑ የከተማችን ነዋሪዎች ባለፉት ዓመታት ወደ ተሻለ ህይወት በተጨባጭ ማሻገር የተቻለበት ነዉ ብለዋል፡፡

#viralreelschallenge
#followerseveryone
#addisababa
#Ethiopia
#etv@CommunityPVC
ከተቋማት ጋር በአጋርነት በተሰሩ የኅብረተሰብ ተሳትፎና የበጎ ፈቃድ ተግባራት ተጨባጭ ለውጦች መጥተዋል።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የኅብረተሰብ ተሳትፎና በጎ ፈቃድ ማስተባበሪያ ኮሚሽን ባለፉት አስር ወራት ከተቋማት ጋር በአጋርነት በተሰሩ ተግባራት ዙሪያ ከባለድርሻ አካላት ጋር ምክክር አካሂዷል።

በአጋርነት በተሰሩ ተግባራትም የኅብረተሰቡን ተሳትፎ እና እርስ በርስ የመደጋገፍ እሴት በማጎልበት ተጨባጭ ውጤት መመዝገቡ ተጠቁሟል።

ተቋማት የኅብረተሰቡን ተሳትፎና ተጠቃሚነት ይበልጥ በማሳደግ የአካባቢ መሠረተ ልማት ስራዎችንና የበጎ ፈቃድ ፕሮግራሞችን ስኬታማ በማድረግ ረገድ የነበራቸው ሚና እድገት ማሳየቱን የኮሚሽኑ ዋና ኮሚሽነር ይመር ከበደ ገልፀዋል።

በኅብረተሰቡ ውስጥ በራስ እቅም ችግሮችን ለይቶ የመፍታት ባህል መጎልበቱ የተገለፀ ሲሆን የከተማ አስተዳደሩ ተቋማት ከኮሚሽኑ ጋር ተቀናጅተው የሰሯቸው ተግባራት ማኅበራዊና ኢኮኖሚያዊ ጉድለቶችን በመሙላት ለከተማዋ ፈጣን እድገት ከፍተኛ አስተዋፅዖ እያበረከቱ በመሆኑ ተጠናክረው እንዲቀጥሉ ኮሚሽነሩ አሳስበዋል።

የመድረኩ ተሳታፊዎች በበኩላቸው በከተማዋ ለሰው ተኮርና ለህዝብ ተሳትፎ ተግባራት ውጤታማነት የአጋርነት ሚናቸውን እንደሚያስቀጥሉና በበጀት ዓመቱ በትሥስር ያቀዷቸውን ግቦች ለማሳካት እንደሚሰሩ ተናግረዋል።

አዲስ አበባ፣ ሚያዚያ 30/2017 ዓ.ም
በሌሎች የማኅበራዊ ሚዲያ አማራጮች ለመከታተል ቀጣዩን ማስፈንጠሪያ ይጫኑ፣
https://linktr.ee/cpvcc
1👍1👎1
የኀብረተሰብ ተሳትፎና በጎ ፈቃድ ማስተባበሪያ ኮሚሽን - አዲስ አበባ
Photo
"የኮሙኒኬሽንና የህዝብ ግንኙነት ስራዎችን ለማሳለጥ ብቃት ያለዉ ባለሙያ መኖር እና የተቀናጀና የተናበበ ወጥነት ያለዉ አዳጊ የተግባር እንቅስቃሴ ማስፈን ወሳኝ ሚና ያለዉ በመሆኑ ምንግዜም መርህ አድርገን ልንተገብረዉ የሚገባ ጉዳይ ነዉ"አቶ ሁሴን ዝናብ

ይህ የተገለፀዉ የአዲስ አበባ ከተማ ኮሙኒኬሽን ቢሮ በስሩ የሚገኙ የሴክተር ተቋማት የኮሙኒኬሽን ዘርፍ የ 9 ወራት እቅድ አፈፃፀም እና የ6 ወራት የክትትልና ድጋፍ ምልከታ ምዘና ዉጤት ላይ መሠረት አድርጎ በገመገመበት ወቅት ነዉ፡፤።

በግምገማዉ ላይ የበጀት ዓመቱ የሴክተር ተቋማት የ9 ወራት አበይት ቁልፍ ተግባራት እቅድ አፈፃፀም ያለበት ደረጃ ፣በኮሙኒኬሽን የተግባቦት ስራዎች መረጃን በመሸጥና ተደራሽ በማድረግ የሀሳብ የበላይነት ከማረጋገጥ አኳያ እንዲሁም የንቅናቄ ስራዎች ያሉበት ሁኔታ እና በግማሽ ዓመት በጥንካሬና በክፍተት የታዩ የሴክተሮች የምዘና ዉጤት ትኩረት የተደረገባቸዉ አጀንዳዎች ናቸዉ።

የከተማዋን ሁለተናዊ አዳጊ የተለያዩ የልማት እንቅስቃሴዎችንና የከተማዋ ነዋሪዎች የመረጃ ፍላጎት እርካታ ሊመጥኑ የሚችሉ የመረጃ ጥራትና ተደራሽነትን በኮሙኒኬሽን ተግባቦት የማስፋት፤ዘመናዊ የመረጃ ፍሰትን የማሳለጥ እና የተናበበና የተቀናጀ ወጥነት ያለዉ የክትትልና ድጋፍ መኖሩ ከባለፈዉ አፈፃፀማችን ተሻሽሎና ጎልቶ የታየበት ዉጤት መሆኑ በቀረቡት ሪፖርቶችና በተደረገዉ ግምገማዊ ዉይይት ተመላክቷል፡፡

የቢሮዉ ም/ቢሮ ኃላፊ አቶ ሁሴን ዝናብ ከዚህ ጋር ተያይዞ እንደገለፁት በሁሉም አደረጃጀቶች ባደረግነዉ የተቀናጀ የክትትልና ድጋፍ አግባብ የከተማዋን የተለያዩ አጀንዳዎች በመልዕክት በመምራት በከተማዋ የሃሳብ የበላይነት እንዲሰፍን ማድረግ የተቻለበትና ይህም በጋራ የመጣ ትልቅ ስኬት መሆኑን ተናግረዋል፡፡
የቢሮው ም/ኃላፊና የዲጂታልና ሞኒተሪንግ ዘርፍ ኃላፊ አቶ በትግሉ ዲባባም ሁለንተናዊ የመረጃ ተደራሽነትን በማስፋትና ለማህበረሰባችን ወቅታዊና ታዕማኒነትን ያማከለ የመረጃ ምንጭ መሆን እንዳለባቸውና የኮሙኒኬሽንና የህዝብ ግንኙነት ስራዎችን ለማሳለጥ እና የተቀራረበ አፈፃፀም በሴክተሮች መካከል ለማምጣት ብቃት ያለዉ ባለሙያ መኖር እና የተቀናጀና የተናበበ ወጥነት ያለዉ አዳጊ የተግባር እንቅስቃሴ ማስፈን ወሳኝ ሚና ያለዉ በመሆኑ ምንግዜም መርህ አድርገን ልንተገብረዉ የሚገባ መሆኑንም ጠቁመዋል፡፡

በመጨረሻም በ9 ወራት ያልተፈፀሙ ስራዎችን ለይቶ ማቀድ እና መስራት፤ ሁሉም ሴክተሮች የማህበራዊ ፕላት ፎርሞችን አማራጭ ማስፋትና መጠቀም እንዲሁም የተከታይ ቁጥርን ማሳደግ ላይ በንቃት መሳተፍ፤ ልምድና ተሞክሮን ማስፋት፤ ሴክተሮች የመረጃ ምንጭ እንዲሆኑ ማድረግ፤ የክትትልና ድጋፍ እንዲሁም ስልጠናዎችን ማጠናከር እና የበጀት፤ የሰዉ ሃይል እና የግብዓት ችግሮችን መፍታት በበጀት ዓመቱ ቀሪ ጊዜያት ሊተኮርባቸዉ የሚገቡ የቀጣይ አቅጣጫ መሆናቸዉንም አመላክተዋል፡፤

ተሳታፊዎችም የመጣዉ የጋራ ዉጤት በሁለተናዊ መልኩ ቢሮዉ ያደረገዉ የክትትልና ድጋፍ አግባብ ወሳኝ ሚና እንደነበረዉ ገልፀዉ በቀጣይም ይህን የበለጠ አጠናክሮ በማስቀጠል ሁላችንም ወደ ተቀራረበ አፈፃፀም እንድንመጣ በትጋት መስራት ይጠበቅብናል ብለዋል፡፡
👍52
የኀብረተሰብ ተሳትፎና በጎ ፈቃድ ማስተባበሪያ ኮሚሽን - አዲስ አበባ
Photo
የ2017 ዓ.ም የክረምት በጎ ፈቃድ አገልግሎት በ15 ፕሮግራሞችና በ19 መርሃ ግብሮች ይፋ ተደርጓል።

👉ፕሮግራሙ 800 ሺህ የኅብረተሰብ ክፍሎችን የሚያሳትፍ ሲሆን ከ2.2 ሚሊዮን በላይ በጎ ፈቃደኞች ይሳተፉበታል። ከሰኔ/2017 ዓ.ም እስከ መስከረም 30/2018 ዓ.ም ለአራት ወራት በሚቆየው በዚህ መርሃ ግብር 6.2 ቢሊዮን ብር የሚገመት አገልግሎት ይከናወንበታል።

👉ፕሮግራሞቹም:-
1) ሰብዓዊና ማኅበራዊ አገልግሎት፥
👉2,500 ቤቶችን በአዲስ መልክ በመገንባት 12,500 የህብረተሰብ ክፍሎችን ተጠቃሚ ማድረግ ፤
 👉23,650 በጎ ፈቃደኞችን በማሳተፍ 500,000 የህብረተሰብ ክፍሎችን ማዕድ ማጋራት፣
👉አንድ ሰው ለአንድ ቤተሰብ መርሀ ግብር 44,000 የህብረተሰብ ክፍሎችን ለ3 ወራትና ከዚያ በላይ የሚዘልቅ ትስስር መፍጠር ተጠቃሚ ማድረግ፤ 
👉440 ወላጆቻቸውን ያጡና ለችግር የተጋለጡ ህፃናት በተለያዩ አማራጮች ድጋፍ እንዲያገኙ ማድረግ፤

2) ልዩ ፍላጎት ድጋፍ ፕሮግራም
👉በልዩ ፍላጎት ድጋፍ 11 የአምዕሮ ህሙማን፣ የአረጋዊያንና የህፃናት መርጃ ማዕከላት  በመጎብኘት 3,600 ወገኖች ተጠቃሚ ለማድረግና 550 በጎ ፈቃደኞችን በማሳማራት አገልግሎት እንዲሰጡ ማስቻል፤

3) አረንጓዴ ልማትና አካባቢ ጥበቃ ፕሮግራም
 👉በ7ኛው ዙር የአረንጓዴ አሻራ (Green legacy) መርሀ ግብር 1.5 ሚሊዮን በጎ ፈቃደኞችን ማሳተፍ፣
👉በከተማ ፅዳት መርሃ ግብር 500 ሺህ በጎ ፈቃደኞችን ማሳተፍና 1 ሺህ ሜትር ኪዩብ ቆሻሻ ማፅዳት
👉55 ሺህ በጎ ፈቃደኞችን በማሳተፍ 200 ኪሎ ሜትር የጎርፍ ማስወገጃ ቱቦ መጥረግና አደጋን መቀነስ።

4) ማኅበራዊ ልማት ፕሮግራም
👉20 ሺህ በጎ  ፈቃደኞችን በከተማ  ግብርና ልማት ላይ ማሰማራት
👉15 ሺህ በጎ ፈቃደኞች በህዝብ መዝናኛ ቦታዎችና በኮሪደር ልማት ተግባራት ላይ ማሳተፍ፡

5) ትምህርትና ስልጠና ፕሮግራም
👉በክረምት ማጠናከሪያ ትምህርት በ5 ዋና ዋና የትምህርት ዓይነቶች 65,000 ተማሪዎችን ለማስተማር፡ 
👉በአጫጭር የክህሎት ስልጠና መርሀ ግብር ወጣት ማዕከላትን በመጠቀም 20,000 ተማሪዎችን ተጠቃሚ ማድረግ፣
👉6000 በጎ ፈቃደኞች ከታላላቆቻቸው የሕይወት ልምድና ተሞክሮ
እንዲወስዱ ማድረግ፣
👉11 ሺህ የኅብረተሰብ ክፍሎች የጎልማሶች ትምህርት ተጠቃሚ ማድረግ፡

6) የጤና እንክብካቤ ፕሮግራም
👉በከተማችን የሚገኙ የመንግስትና የግል የህክምና ተቋማትን እንዲሁም የህክምና ቡድኖችን በማሳተፍ 125,530 የህብረተሰብ ክፍሎች ነፃ የህክምና ድጋፍና አገልግሎት እንዲያገኙ ማድረግ፤ 
👉40,000 በጎ ፈቃደኞችን በማሳተፍ 40,000 ዩኒት ደም ለመሰብሰብ፤
👉3,000 በጎ ፈቃደኞች በተመረጡ ሆስፒታሎች የተለያዩ አገልግሎት እንዲሰጡ ማድረግ፤ 
👉12 የመንግስት ሆስፒታሎችን በመጎብኘት ለ1,200 ህሙማን የተለያዩ ድጋፎች ማድረግ፤

7) የመንገድ ትራፊክ ደህንነት ፕሮግራም
👉በመንገድ ትራፊክ አገልግሎት ፕሮግራም በከተማችን በሚገኙ አደባባዮችና አገናኝ መንገዶች ላይ 7,000 በጎ ፈቃደኞን ለማሰማራትና የትራፊክ ፍሰቱን ማሳለጥ፡

8) የአገልግሎት ሰጪ ተቋማት ድጋፍ ፕሮግራም
👉በተለያዩ አገልግሎት ሰጪ ተቋማት 8,000 በጎ ፈቃደኞችን በየደረጃው በማሳተፍ አገልግሎት እንዲሰጡ ማድረግ፤

9) የሙያ በጎ ፈቃድ ፕሮግራም
👉በሙያ በጎ ፈቃድ አገልግሎት 8,000 በጎ ፈቃደኛ የሆኑ መምህራን፣ የህክምና ባለሙያዎች፣ ኢንጅነሮች፣ አርቲስቶች፣ የህግ ባለሙያዎች… ወዘተ በሙያቸው አገልግሎት እንዲሰጡ ማድረግ፤

10) ማኅበራዊ ሚዲያን ለበጎነት ፕሮግራም
👉ማህበራዊ ሚድያው ለበጎ ተግባር እንዲውል 6,000 ወጣቶችን ከሚመለከታቸው አካላት ጋር ተቀናጅቶ ስልጠናና ግንዛቤ በመፍጠር በማህበራዊ ሚድያው በጎ ተፅኖ እንዲፈጥሩ ማስቻል፡

11) በጎነት ለሠላም እሴት ግንባታ ፕሮግራም
👉በኃይማኖታዊ፣ ህዝባዊና ሀገራዊ ሁነቶች ላይ 55 ሺህ በጎ ፈቃደኞችን ማሳተፍ፡

12) የአደጋ ጊዜ በጎ ፈቃድ ፕሮግራም
👉ሰው ሰራሽና የተፈጥሮ አደጋዎች ከመከሰታቸው በፊትና በሚከሰቱ ወቅት የሚሰማሩ 1 ሺህ በጎ ፈቃደኞች ቅድመ አደጋ ስልጠና እንዲወስዱ ማድረግ 

13) ስፖርታዊ እንቅስቃሴ ፕሮግራም
👉550 በጎ ፈቃደኛ የስፖርት ባለሙያዎች በሙያቸው አገልግሎት እንዲሰጡ ማስቻል፣

14) ኪነጥበብና መዝናኛ ፕሮግራም
👉ለ55 ሺህ የኪነ ጥበብ ዝንባሌ ያላቸው ወጣቶች አጫጭር የትያትር፣ የሥነ-ፅሁፍ፣ የጋዜጠኝነት፣ የውዝዋዜና የድምፅ ስልጠና እንዲያገኙ ማድረግ፡

15) ወሰንና ድንበር የለሽ ፕሮግራም
👉በወሰንና ድንበር የለሽ መርሀ ግብሮች የአዲስ አበባን የበጎነት ተሞክሮ ወደ ክልሎችና ጎረቤት ከተሞች ለማስፋትና የህዝብ ለህዝብ ግንኙነትን ማጠናከር የሚሉት ናቸው።

"በጎ ፈቃደኝነት ለማኅበረሰብ ለውጥ!"
#volunteernow
 
የኀብረተሰብ ተሳትፎና በጎ ፈቃድ ማስተባበሪያ ኮሚሽን - አዲስ አበባ
Photo
በክረምት የበጎ ፈቃድ አገልግሎት መክፈቻ ወቅት አቶ ይመር ከበደ የኅብረተሰብ ተሳትፎና በጎ ፈቃድ ማስተባበሪያ ኮሚሽን ኮሚሽነር በንግግራቸው ስለበጎ ፈቃድ አገልግሎት ያነሷቸው ነጥቦች፡-

የበጎ ፍቃድ አገልግሎት ትርጉም እንደዬማህበረሰቡ የእድገት ደረጃና ከባቢያዊ ሁኔታ የሚለያይ ሲሆን በዋንኛነት ሰዎች/ግለሰቦች ከሰብአዊነት አመለካከት ተነስተው ለሚኖሩበት ማህበረሰብ ልማት “ያለማንም አስገዳጅነት በራሳቸው መልካም ፈቃድ ብቻ ተነሳስተው ያለምንም ቅድመ ሁኔታ ዘር፣ ቋንቋ፣ ኃይማኖት ወይም የኑሮ ደረጃ ሳይለዩ በተቋም ወይም በተናጠል ለሰዎች የሚያደርጉት ከክፍያ ነፃ አገልግሎት ነው፡፡

በጎነት ባለፀጋዎች ብቻ የሚከዉኑት፣ ከገንዘብ ጋር የሚያያዝ ተግባር አድርገው የሚያስቡ አሉ፡፡ ነገር ግን በጎ ፈቃደኝነት በምንሰጠው ገንዘብ ብቻ የሚለካ ፅንሰ ሀሳብ አይደለም፡፡ ማንኛውም ሰው ጉልበቱን፣ ጊዜውን፣ ገንዘቡን፣ ሀሳቡን ወይም አብሮነቱን በመግለፅና በመስጠት በጎ ማድረግ እንደሚችል የበጎ ፈቃደኝነት ዓለም አቀፍ ብያኔ ያስረዳል፡፡

ዓለም ሰው ሰራሽና ተፈጥሯዊ ተግዳሮቶች በሚገጥሟት ጊዜ፤ አፋጣኝ ምላሽ ለመስጠት ቀድመዉ የሚገኙት በጎ ፈቃደኞች ናቸው፡፡ ምድር ለሰው ልጆች የተሻለች ትሆን ዘንድ ፈተናዎችን በመጋፈጥና ተፈጥሮን በመንከባከብ ረገድ በጎ ፈቃደኝነት ትልቁን ድርሻ ይወስዳል። ይህንንም በመረዳት በአንዳንድ የአለማችን ሀገራት የበጎ ፈቃደኝነት አገልግሎት ተሳትፎ የህዝባቸዉን 40 ከመቶ በላይ የሚሸፍን የበጎነት አገልግሎት ስራ ላይ ይሳተፋሉ፡፡

በበርካታ ሀገራት ደግሞ በኢኮኖሚያቸዉ ላይ አወንታዊ ተፅዕኖ ከመፍጠር አኳያ የበጎ ፈቃድ አገልግሎት የዓመታዊ ነፍስ ወከፍ ገቢያቸውን (GDP) ከ2-3 በመቶ አስተዋፅኦ ያበረክታል። ከአፍሪካ ሀገራት በጎ ፈቃደኝነት ከፍተኛው ኢኮኖሚያዊ አስተዋፅዖ የሚያበረክትባት ሀገር ሩዋንዳ በቀዳሚነት ተጠቀሳለች፡፡ በሩዋንዳ የበጎ ፈቃድ አገልግሎት ከዓመታዊ የነፍስ ወከፍ ገቢዋ አኳያ ሲሰላ 30 በመቶ ይሸፍናል፡፡ በጎረቤት ሀገር ኬኒያ ደግሞ 3.66 በመቶ አስተዋፅዖ እንዳለው በጥናት የተረጋገጡ መረጃዎች ያመለክታሉ፡፡

በኢትዮጵያ እስከአሁን ድረስ የበጎ ፈቃድ አገልግሎት ኢኮኖሚያዊ አስተዋፅዖ ተለክቶ ባይታወቅም በጎ ፈቃደኝነት ተቋማዊ ባልነበረበትም ወቅት የመስጠት፣ የመደጋገፍ ባህልና እሴት የነበራት፣ ዜጎች ተደጋግፈው የሚኖሩባት፤ ችግራቸውን በጋራ የሚፈቱባት፣ ማህበራዊ መስተጋብር ያቆራኛቸው ህዝቦች ያሉባት ሀገር ናት፡፡ ይህ ባህል ከጥቂት ዘመን ወዲህ በመጤ ባህሎች ተቀዛቅዞ አደጋ ላይ ወድቆ የነበረ ቢሆንም ከለውጡ ወዲህ ተቋማዊ በሆነ መንገድ እንዲመራ በማድረግ የመተሳሰብ እሴት እንደገና እንዲያብብ፣ መረዳዳትና መደጋገፍ እንዲጎለብት በፖሊሲ ተደግፎ በመከናወን ላይ ይገኛል፡፡

ከ2010 ዓ.ም የክረምት ወራት ጀምሮ እጅግ በተለየ መንገድ በለውጡ አመራር የብልፅና መንግስት ሰው ተኮር ፕሮግራም የሚመራ የበጎ ፈቃድ አገልግሎት እንዲስፋፋ በክቡር ጠቅላይ ሚኒስትራችን አማካኝነት የአረጋዊያንን ቤቶች በመገንባት፣ ማዕድ በማጋራት፣ ደም በመለገስ እና በአርንጓዴ አሻራ ፕሮግራሞች ሰፋፊ አገልግሎቶች የተጀመሩበትና በርካታ የማህበረሰብ ክፍሎች ይህንን በጎ አርዓያ የተከተሉበት ሁኔታ እንዲፈጠር አስችሏል፡፡ በሂደቱም የብልፅግና መንግስት ሰው ተኮር ክዋኔዎች በርካታ ስኬቶችን አስገኝቷል፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የበጎ ፈቃደኝነት አገልግሎት በከተማችን ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ፈተናዎችን ለመሻገር አስፈላጊ መሆኑን ተገንዝቦ ተግባሩ በተቋም እንዲመራ በማድረግ ስኬታማ ስራዎችን አከናውኗል፡፡ የበጎ ፈቃድ አገልግሎት ተቋማዊ ከሆነበት ባለፉት 7 የለውጥ ዓመታት ወዲህ በተለያዩ ፕሮግራሞች በተፈጠረው ግንዛቤ የከተማችን ነዋሪዎች፣ ባለሃብቶች፣ ወጣቶችና ሌሎች ተቋማት፣ የበጎ ፈቃድ ማህበራት እና ግለሰቦች በአገልግሎቱ ላይ ከጊዜ ወደ ጊዜ ተሳትፏቸው እያደገ መጥቷል፡፡ ይህም የበጎነት አገልግሎት ባህል ወደመሆን በመሸጋገር ላይ መሆኑን ማሳያ ነው፡፡

#በጎነት_አያጎድልም
#followerseveryone
#volunteersmakeadifference
#viralreelschallenge
#addisababa
#Ethiopia
6👍1
605 ሚሊዮን ብር የሚገመት የክረምት የበጎ ፈቃድ አገልግሎት በለሚኩራ ክፍለ ከተማ

የለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ አስተዳደር "በጎ ፈቃደኝነት ለማኅበረሰብ ለውጥ" በሚል መሪ ቃል ከ300 ሺህ በላይ በጎ ፈቃደኞች የሚሳተፉበት የክረምት የበጎ ፈቃድ አገልግሎት አስጀመረ።

የለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ የብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት አደረጃጀት ዘርፍ ኃላፊ ወ/ሪት ወይንሸት አስናቀ የብልጽግና መንግስት ወደ ስልጣን ከመጣበት ጊዜ አንስቶ በርካታ ሰው ተኮር ተግባራትን ማካሄዱንና እርስ በርስ በመደጋገፍ የእህትማማችነትና የወንድማማችነት ስሜትን ለመፍጠር ብዙ ጥረቶችን ማድረጉን ጠቅሰው በቀጣይም ሰፋፊ የሰው ተኮር ስራዎች ተጠናክረው ይቀጥላሉ ብለዋል።

የክፍለ ከተማው የኅብረተሰብ ተሳትፎና በጎ ፈቃድ ማስተባበሪያ ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ብርሃኑ ገ/ጊዮርጊስ በበጋው መርሃ ግብር በርካታ የበጎ ፈቃድ ስራዎች በስኬት መጠናቀቃቸውን አስታውቀዋል።

ከሰኔ/2017 ጀምሮ እስከ መስከረም 30/ 2018 በሚቆየው የክረምት የበጎ ፈቃድ መርሃ ግብር ከ300 ሺ በላይ በጎ ፈቃደኞችን በማሳተፍ በ18 የበጎ ፈቃድ ዘርፎች 77 ሺ ዜጎችን ተጠቃሚ በማድረግ መንግስት ሊያወጣው የሚችለውን ከ605 ሚሊዮን በላይ ብር ለማዳን መታቀዱ ኃላፊው መናገራቸውን የክፍለ ከተማው ኮሙኒኬሽን ዘገባ ያስረዳል።

#volunteersmakeadifference
#addisababa
#vol@CommunityPVC
1👍1