የኀብረተሰብ ተሳትፎና በጎ ፈቃድ ማስተባበሪያ ኮሚሽን - አዲስ አበባ
823 subscribers
2.14K photos
47 videos
265 links
Download Telegram
የኀብረተሰብ ተሳትፎና በጎ ፈቃድ ማስተባበሪያ ኮሚሽን - አዲስ አበባ
Photo
በመዲናዋ ባለፉት አምስት ወራት ከ5 ነጥብ 7 ቢሊዮን ብር በላይ የሚገመቱ የበጎ ፍቃድ ሥራዎች ተከናውነዋል- ኮሚሽኑ

ባለፉት አምስት ወራት ከ5 ነጥብ 7 ቢሊዮን ብር በላይ የሚገመቱ የበጎ ፍቃድ ሥራዎች መከናወናቸውን የአዲስ አበባ የህብረተሰብ ተሳትፎና የበጎ ፍቃድ ማስተባበሪያ ኮሚሽን ገለጸ።

የኮሚሽኑ ኮሚሽነር ይመር ከበደ እንደተናገሩት በ2017 በጀት ዓመት በከተማዋ ከክረምት በጎ ፍቃድ ባለፈ የበጋ በጎ ፍቃድ አገልግሎቶች ተጠናክረው ቀጥለዋል።

'በጎነት በሆስፒታል' በሚል ነጻ የህክምና አገልግሎትን ጨምሮ ደም ልገሳ፣ የአቅመ ደካሞች ቤት ዕድሳት፣ ማዕድ ማጋራትና ሌሎችም ከ13 በላይ የበጎ ፍቃድ አገልግሎቶች እየተከናወኑ ነው ብለዋል።

ባለፉት አምስት ወራት ከ5 ነጥብ 7 ቢሊዮን ብር በላይ የሚገመቱ የበጎ ፍቃድ ስራዎች መከናወናቸውን ገልጸዋል።

የቤት ዕድሳትና ግንባታ ስራዎች ትልቁን ድርሻ እንደሚይዙ ገልጸው፤ በበጀት ዓመቱ ከ2 ሺህ 280 በላይ ትላልቅ የቤት ግንባታ ሥራዎች በተለያዩ በጎ ፍቃደኛ ባለሃብቶች እየተከናወኑ እንደሚገኙ ተናግረዋል።

ሁሉም ዜጋ በጉልበቱ፣ በዕውቀቱና በገንዘቡ የበጎ ፍቃድ አገልግሎት በመስጠት ለተሻለ አገርና ትውልድ ግንባታ የድርሻውን እንዲወጣ ጠይቀዋል።

በበጀት ዓመቱ በአጠቃላይ ከ12 ቢሊዮን ብር በላይ የሚገመት የበጎ ፍቃድ አገልግሎት ለመስጠት ታቅዶ እየተሰራ መሆኑንም ጠቁመዋል።

#Ethiopia
#voluntarism
#Humanityfirst

የማኀበራዊ ሚዲያ አማራጮቻችን፥
ፌስቡክ - https://www.facebook.com/cpvcc.2015
ቴሌግራም - https://t.me/CommunityPVC
ቲክቶክ - https://www.tiktok.com/@voluntarismaddis16
ዩቱዩብ - https://youtube.com/@communityparticipationvolu8714
ዌብሳይት - www.volunteeraddis.et
Instagram - https://www.instagram.com/communitypv/
Twitter - https://x.com/Volunteeraddis
👍1
የኀብረተሰብ ተሳትፎና በጎ ፈቃድ ማስተባበሪያ ኮሚሽን - አዲስ አበባ
Photo
ኅብረተሰቡን ያሳተፉ የልማት ፣ የሠላምና የመልካም አስተዳደር ተግባራት ተጠናክረው ቀጥለዋል።

ኮሚሽኑ በተያዘው በጀት ዓመት ኅብረተሰቡ በባለቤትነት የሚሳተፍባቸው የአካባቢ ልማት ፣ የሠላምና የመልካም አስተዳደር ተግባራትን ቀርፆ ወደ ስራ የገባ ሲሆን የኮሚሽኑ ዳይሬክተሮችና ባለሙያዎች በሁሉም ክፍለ ከተሞች በኅብረተሰብ ተሳትፎ እንዲሁም በበጎ ፈቃድ ስራዎች ዙሪያ ድጋፍና ክትትል እያካሄዱ ነው።

የአካባቢ ልማቶች፣ የአካባቢ ሠላም ተግባራትና መጪውን የገና በዓል ምክንያት በማድረግ በርካታ የበጎ ፈቃድ አገልግሎቶች በኅብረተሰቡና በበጎ ፈቃደኞች ተሳትፎ ተጠናክረው ቀጥለዋል።

ለአካባቢ መሰረተ ልማት ፕሮጀክቶች የፋይናንስ አሰራሮችን የጠበቀ በቂ ሀብት መሰብሰብ በሁሉም ክፍለ ከተሞች በልዩ ትኩረት እንዲከናወን አቅጣጫ የተቀመጠ ሲሆን የህብረተሰቡን ሁለንተናዊ ተሳትፎ አጠናክሮ ማስቀጠል ይገባል ተብሏል።

"ሁሉ አቀፍ የኅብረተሰብ ተሳትፎ ለዘላቂ ልማት!"

የማኀበራዊ ሚዲያ አማራጮቻችን፥
ፌስቡክ - https://www.facebook.com/cpvcc.2015
ቴሌግራም - https://t.me/CommunityPVC
ቲክቶክ - https://www.tiktok.com/@voluntarismaddis16
ዩቱዩብ - https://youtube.com/@communityparticipationvolu8714
ዌብሳይት - www.volunteeraddis.et
Instagram - https://www.instagram.com/communitypv/
Twitter - https://x.com/Volunteeraddis
የኀብረተሰብ ተሳትፎና በጎ ፈቃድ ማስተባበሪያ ኮሚሽን - አዲስ አበባ
Photo
ምክትል ከንቲባና የኢንዱስትሪ ልማት ቢሮ ኃላፊ አቶ ጃንጥራር አባይ በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ የአቅመ ደካሞችን መኖሪያ ቤቶች ግንባታ አስጀምረዋል።

የአዲስ አበባ ከተማ ምክትል ከንቲባና የኢንዱስትሪ ልማት ቢሮ ኃላፊ አቶ ጃንጥራር አባይ በበጋ የበጎ ፈቃድ አገልግሎት በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ሁለት የአቅመ ደካሞችን መኖሪያ ቤቶች ግንባታ በዛሬው ዕለት አስጀምረዋል።

በሌላ በኩል የአዲስ አበባ ከተማ የስራና ክህሎት ቢሮ በዚሁ ክፍለ ከተማ በኢንተርፕራይዞች ተሳትፎ የአቅመ ደካሞችን የቤት ግንባታ የበጎ ፈቃድ አገልግሎት አስጀምሯል።

የአዲስ አበባ ደንብ ማስከበር ባለስልጣንም በክፍለ ከተማው በበጋ በጎ ፈቃድ አግልግሎት የሚከናወኑ መኖሪያ ቤቶችን እድሳትና ግንባታ ያስጀመረ ሲሆን አገልግሎቱ ጥራቱን ጠብቆ ባጠረ ጊዜ ውስጥ በማጠናቀቅ ለተጠቃሚዎች ለማስተላለፍ የተሟላ ድጋፍና ክትትል እንደሚደረግ ተመላክቷል።

"በጎ ፈቃደኝነት ፤ ለማኅበረሰብ ለውጥ!"

👍3