የኀብረተሰብ ተሳትፎና በጎ ፈቃድ ማስተባበሪያ ኮሚሽን - አዲስ አበባ
822 subscribers
2.14K photos
47 videos
265 links
Download Telegram
👉ትላንት በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ለአቅመ ደካሞች የተገነቡ መኖሪያ ህንፃዎች በከንቲባ አዳነች አቤቤ ተመርቀው ለተጠቃሚዎች ተላልፈዋል።

👉ዊንጌት እና ገብስ ተራ አካባቢ ደሳሳና ለኑሮ የማያመቹ የነበሩ የቀበሌ ቤቶችን በማፍረስ ምቹ ተደርገው የተገነቡ ናቸው።

👉አጠቃላይ የቤቶች ብዛት 75 ሲሆኑ ባለ 5 ወለል(G+5) ሁለት ህንጻዎች ናቸው።

👉ከ375 በላይ ቤተሰቦች ያሏቸው 75 አባውራ/እማውራዎችን ተጠቃሚ ያደረጉት እነዚህ ቤቶች በአጭር ጊዜ ውስጥ የተጠናቀቁ ናቸው።

👉የመጸዳጃና የማብሰያ ቦታ ፣ ሰፋፊ ሳሎኖችና መኝታ ቤቶች ያላቸው ናቸው::

👉በዚህ የበጎ ፈቃድ አገልግሎት ላይ ብዙአየሁ ታደለ ፋውንዴሽን፣ መተባበር ለኢትዮጵያ አ/ማ ፣ ተምሳሌት በሲዳሞ ተራ አ/ማ ፣ ምዕራብ ገበያ ልማት አ/ማ ፣ ጉሊት አክሲዮን ማህበር ፣ ሸራ ተራ ብርሃን አክሲዮን እንዲሁም ጎሽ ንግድና አክሲዮን ግንባታ ማህበር ተሳትፈዋል።

👉ከንቲባ አዳነች አቤቤ በቦታው ተገኝተው "የዘመሙ ጎጆዎችን እያቃናን የሚፈሱ እንባዎች ሲታበሱ ማየት እጅግ ደስ ያሰኛል" ያሉ ሲሆን በዚህ የማኅበራዊ ኃላፊነት ስራ ላይ የተሳተፉ ተቋማትን በተጠቃሚ ነዋሪዎች እና በከተማ አስተዳደሩ ስም አመስግነዋል።

👉በመተባበር የሰው ኑሮ እና አኗኗርን በማሻሻል ሀገር እንገነባለንና ትብብራችንን አጠናክረን እንቀጥል ሲሉ ከንቲባ አዳነች አቤቤ ጥሪ አቅርበዋል።
👍2
የኀብረተሰብ ተሳትፎና በጎ ፈቃድ ማስተባበሪያ ኮሚሽን - አዲስ አበባ
Photo
39ኛ መደበኛ የሚኒስትሮች ምክር ቤት ስብሰባ ውሳኔዎች፥

1. በቅድሚያ ምክር ቤቱ የተወያየው ብሔራዊ የመካከለኛ ዘመን 2017-2020 የገቢ ስትራቴጂ ላይ ነው፡፡ ስትራቴጂው የታክስ ሥርዓቱን ለማዘመን እና ለግል ኢንቨስትመንቱ ምቹ ሁኔታን ለመፍጠር የታለመ ሲሆን አጠቃላይ የታክስ ፖሊሲዎችን እና አስተዳደራዊ ሪፎርሞችን እንዲሁም ማሻሻያዎችን ለመተግበር የሚያስችል ነው፡፡ ሰትራቴጂው ከ10 ዓመቱ የልማት ዕቅድ ጋር የተጣጣመ እንዲሆን ተደርጎ ቀርቧል፡፡ ምክር ቤቱም በስትራቴጂው ላይ በዝርዝር ከተወያየበት በኋላ በምክር ቤቱ ውሳኔ ካገኘበት ቀን ጀምሮ ተግባራዊ እንዲደረግ በሙሉ ድምጽ ወስኗል፡፡

2. በመቀጠል የተወያየው የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዴሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ መንግስት ከማልታ ሪፐብሊክ መንግስት እና ከቻድ ሪፐብሊክ መንግስት ጋር የተፈረማቸውን የአየር አገልግሎት ስምምነቶችን ለማጽደቅ የቀረቡ 2 ረቂቅ አዋጆች ላይ ነው፡፡ ስምምነቶቹ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ ማንኛውም የማልታ ከተማ እና ወደ እንጃሜና ከተማ በ3ኛና 4ኛ ትራፊክ መብት የመንገደኛ እና የጭነት የበረራ ምልልስ ለማድረግ፣ ተወካይ አየር መንገዶችን በሽርክና ለማሰራት፣ በ5ኛ ትራፊክ መብት ወደ ተመረጡ መዳረሻዎች በረራ ለማድረግ የሚያስችል እና አገራችን ከሁለቱ ጋር ያላትን የሁለትዮሽ ግንኙነት ለማጠናከር፣ ለንግድና ኢንቨስትመንት፣ ለወጪ ንግድ፣ ለቱሪዝም፣ ለስራ እድል ፈጠራ እና ለውጭ ምንዛሪ ግኝት ትልቅ አስተዋጽኦ ያላቸው ስምምነቶች ናቸው፡፡ ምክር ቤቱ በረቂቅ አዋጆቹ ላይ ከተወያየ በኋላ ወደ ህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት እንዲተላለፉ ወስኗል፡፡

3. በመቀጠል የፓሪስ ኢንዱስትሪያዊ ንብረት ኮንቬንሽን ለማጽደቅ በቀረበው ረቂቅ አዋጅ ላይ ነው፡፡ የፓሪስ ኢንዱስትሪያዊ ንብረት ኮንቬንሽን በአባል አገራት መካከል ሕብረት በመፍጠር የኢንዱስትሪ ንብረትን ለመጠበቅ፣ የፈጠራ ባለቤትነት፣ የግልጋሎት ሞዴሎች፣ የኢንዱስትሪ ንድፎች፣ የንግድ ምልክቶች፣ የአገልግሎት ምልክቶች፣ የንግድ ስሞች፣ የምርቶች ምንጭ አመልካች ምልክቶች ለመጠበቅ እንዲሁም ተገቢ ያልሆነ ውድድር ለመከላከል እና ለግብርና እና ሁሉንም የተመረቱ ወይም ተፈጥሯዊ ምርቶች የሚያካትት ነው፡፡ ምክር ቤቱም በረቂቅ አዋጁ ላይ ከተወያየ በኋላ ወደ ህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት እንዲተላለፍ በሙሉ ድምጽ ወስኗል፡፡

4. ሌላው የዓለም አቀፍ ምልክቶችን ከሚመለከተው የማድሪድ ስምምነት ጋር የተዛመደውን ፕሮቶኮል ለማጽደቅ በወጣ ረቂቅ አዋጅ ላይ ነው፡፡ ፕሮቶኮሉ የንግድ እና የአገልግሎት ምልክቶች በአገር ውስጥ ሕግ ከሚደረግላቸው ጥበቃ አልፈው በዓለም አቀፍ ደረጃ ጥበቃ እንዲኖራቸው ለማድረግ የሚያስችል ከመሆኑም በተጨማሪ ምርቶችና አገልግሎቶች ያላግባብ ለሌሎች ጥቅም እንዳይውሉ በቂ ጥበቃ የሚደረግበትን ሁኔታ የሚፈጥር፣ ጥራታቸውን የጠበቁ ምርቶችና አገልግሎቶች እንዲኖሩና የሀብት ምንጭ እንዲሆኑ ትልቅ ጠቀሜታ ያለው በመሆኑ ምክር ቤቱ በፕሮቶኮሉ ላይ ከተወያየ በኋላ ወደ ህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት እንዲተላለፍ ወስኗል፡፡

5. በመጨረሻም የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት ደንብ እና የኢሚግሬሽን እና ዜግነት አገልግሎት ሰራተኞች ደንብ ላይ ነው፡፡ የጀመረውን ሪፎርም ውጤታማ ለማድረግ፣ ሪፎርሙ በተሟላ ሁኔታ እንዲተገበር ለማስቻል የአገልግሎቱን ልዩ ባህሪይ ከግምት ውስጥ ያስገባ ሰራተኞች መተዳደሪያ ደንብ ተዘጋጅቶ ቀርቧል፡፡ ምክር ቤቱም በረቂቅ ደንቦቹ ላይ በዝርዝር ከተወያየባቸው በኋላ ግብዓቶችን በማከል በነጋሪት ጋዜጣ ታትመው ከወጡበት ቀን ጀምሮ ተግባራዊ እንዲደረጉ በሙሉ ድምጽ ወስኗል፡፡
👍1
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የኅብረተሰብ ተሳትፎና በጎ ፈቃድ ማስተባበሪያ ኮሚሽን እንኳን ለ2017 ዓ.ም የኢሬቻ በዓል በሠላም አደረሳችሁ ሲል መልካም ምኞቱን ይገልፃል።

መልካም የኢሬቻ በዓል!
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ኢሬቻ የመቻቻል ፣ የአብሮነት ፣ የህብርና የሠላም ምልክት!

ቱባ ባህላዊ እሴቶቻችን ደምቀን የምናጌጥባቸውና የምንኮራባቸው የኅብራዊ መልኮቻችን ነፀብራቆች ፣ የወል ሀብቶቻችን ናቸው፡፡

በዓሉ የመተሳሰብ ፣ የአብሮነት ፣ የሠላምና የፍቅር እንዲሆን መልካም ምኞታችንን እየገለፅን በዓሉን ስናከብር ምንጊዜም እንደምናደርገው ለተቸገሩ እና የእኛን ድጋፍ ለሚሹ ሁሉ አብሮነታችን በማሳየት እንዲሆን እንጠይቃለን፡፡

መልካም በዓል!

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የኅብረተሰብ ተሳትፎና በጎ ፈቃድ ማስተባበሪያ ኮሚሽን!
👍6
ኮሚሽኑ በ2017 በጀት ዓመት በኅብረተሰብ ተሳትፎ የሚከናወኑ የልማት ፕሮጀክቶችን በነገው ዕለት በንቅናቄ ያስጀምራል።

"ሁሉ አቀፍ የኅብረተሰብ ተሳትፎ ለዘላቂ ልማት!" በሚል መሪ ቃል ነገ በንቅናቄ የሚጀመረው የኅብረተሰብ ተሳትፎ ልማት ከ13 በላይ ፕሮጀክቶች ተካተውበታል።

በ2016 በጀት ዓመት በኅብረተሰቡ የነቃ ተሳትፎና በመንግስት አጋርነት ከአንድ ነጥብ ዘጠኝ ቢሊዮን ብር በላይ የአካባቢ መሰረተ ልማት ስራ መከናወኑ ይታወሳል።
👍3👏3
አቶ ይመር ከበደ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የኅብረተሰብ ተሳትፎና በጎ ፈቃድ ማስተባበሪያ ኮሚሽን ኮሚሽነር ሆነው ተመደቡ።

ኮሚሽነር ይመር ከበደ ከቀድሞው ኮሚሽነር ተንኩዌይ ጆክ ሮም የስራ ርክክብና ከጠቅላላ ካውንስል አባላት ጋር ትውውቅ አድርገዋል።

የቀድሞው ኮሚሽነር አቶ ተንኩዌይ ጆክ የመንግስት የልማት ድርጅቶች ባለስልጣን ኃላፊ ሆነው ተመድበዋል።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የኅብረተሰብ ተሳትፎና በጎ ፈቃድ ማስተባበሪያ ኮሚሽን ለኮሚሽነር ይመር ከበደ እና ለአቶ ተንኩዌይ ጆክ መልካም የስራ ጊዜ እንዲሆንላቸው ይመኛል።
👍6
የ2017 በጀት ዓመት የበጋ በጎ ፈቃድ ፕሮግራም በነገው ዕለት ይፋ ይደረጋል።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የኅብረተሠብ ተሳትፎና በጎ ፈቃድ ማስተባበሪያ ኮሚሽን የክረምት በጎ ፈቃድ አገልግሎትን በማጠቃለል የ2017 ዓ.ም የበጋ በጎ ፈቃድ ፕሮግራምን በነገው ዕለት በይፋ ያስጀምራል።

በመርሃ ግብሩ ላይ ከ1000 በላይ በጎ ፈቃደኞችና ባለድርሻ አካላት የሚሳተፉ ሲሆን ፕሮግራሙ "በጎ ፈቃደኝነት ለማኅበረሰብ ለውጥ!" በሚል መሪ ቃል ተግባራዊ ይሆናል።

አስር ዐበይት መርሃ ግብሮችንና 13 ንዑሳን ተግባራትን ያካተተው ይህ ፕሮግራም ከአንድ ሚሊዮን በላይ በጎ ፈቃደኞች ይሳተፉበታል ተብሎ ይጠበቃል!
👏4👍1
የኀብረተሰብ ተሳትፎና በጎ ፈቃድ ማስተባበሪያ ኮሚሽን - አዲስ አበባ
Photo
አንድ ሚሊዮን በጎ ፈቃደኞች የሚሳተፉበትና ከ700 ሺህ በላይ የኅብረተሰብ ክፍሎች ተጠቃሚ የሚሆኑበት የበጋ በጎ ፈቃድ ፕሮግራም ይፋ ተደረገ።

በአዲስ አበባ ከተማ አንድ ሚሊዮን በጎ ፈቃደኞች የሚሳተፉበትና 784 ሺህ 844 የኅብረተሰብ ክፍሎችን ተጠቃሚ የሚያደርግ የበጋ በጎ ፈቃድ ፕሮግራም ዛሬ ይፋ ተደርጓል።

"በጎ ፈቃደኝነት ፤ ለማኅበረሰብ ለውጥ!" በሚል መሪ ቃል ይፋ የሆነው የ2017 ዓ.ም የበጋ በጎ ፈቃድ ፕሮግራም ከጥቅምት ጀምሮ እስከ ግንቦት 30/2017 ዓ.ም ድረስ የስምንት ወራት የቆይታ ጊዜ ይኖረዋል።

የበጋው የበጎ ፈቃድ ፕሮግራም 12 ዐበይት መርሃ ግብሮችንና 13 ንዑሳን ተግባራትን አካቷል። በእነዚህ መርሀ ግብሮች 6.5 ቢሊዮን ብር የሚገመት አገልግሎት ለመስጠት እቅድ ተይዟል።

በመድረኩ ላይ ተገኝተው ለበጎ ፈቃደኞች የስራ ስምሪት የሰጡት የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የኅብረተሰብ ተሳትፎና በጎ ፈቃድ ማስተባበሪያ ኮሚሽን ኮሚሽነር ይመር ከበደ በጎ ፈቃደኝነት መንግስት ተደራሽ ያላደረጋቸውን ተግባራት በመከወን በርካታ ማኅበራዊና ኢኮኖሚያዊ ችግሮችን እየፈታ መሆኑን ገልፀዋል።

ኮሚሽነር ይመር ከበደ ዓለም አቀፍ የዲፕሎማሲ መዲና በሆነችው ከተማችን በ2016 በጀት ዓመት ከ12 ቢሊዮን ብር በላይ የበጎ ፈቃድ አገልግሎት በመስጠትና የበርካታ ነዋሪዎችን ተስፋ ያለመለመ ፕሮግራም በመተግበር ለሀገራችን ከተሞች በምሳሌነት የሚጠቀስ ስራ ተስርቷል ብለዋል::

በበጋ የበጎ ፈቃድ ስራዎች የተከልናቸውን ችግኞች መንከባከብ ፣ በሠላም ዕሴት ግንባታ ፣ ለችግር የተጋለጡ ወገኖችን መደገፍና ማገዝ እንደሚገባ ኮሚሽነሩ አክለው ገልጸዋል።

በጎ ፈቃደኞች ማኅበራዊ ኃላፊነታቸውን በመወጣት ኅብረተሰባቸውን በቅንነት እንዲያገለግሉ የስራ አቅጣጫ የሰጡት ኮሚሽነሩ በበጋው የተያዘው ፕሮግራም ውጤታማ እንዲሆን ሁሉም ባለድርሻ አካላት እንዲረባረቡ ጥሪ አቅርበዋል።

ምክትል ኮሚሽነር ደረጄ ካሳ በበኩላቸው ለዘመናት የተከማመሩ ችግሮችን እየቀረፈች ዓለም አቀፍ የስበት ማዕከል መሆን በጀመረችው አዲስ አበባ ከተማ ማኅበራዊ ፍትህን ለማንገስ የተሰሩ የበጎ ፈቃድ ስራዎች ፍሬ ማፍራታቸውን ገልጸው በበጋ የበጎ ፈቃድ ስራዎች የበጎ ፈቃድ አገልግሎት ባህልን ከፍ የሚያደርጉ ስራዎችን ለመተግበር ዝግጅት መደረጉን ተናግረዋል።

በ2016 የክረምት በጎ ፈቃድ 5 ነጥብ 4 ቢሊዮን ብር የሚገመት አገልግሎት የተሰጠ ሲሆን ከሦስት ሚሊዮን በላይ በጎ ፈቃደኞች በድግግሞሽ ተሳትፈውበታል።

"በጎ ፈቃደኝነት ፤ ለማኅበረሰብ ለውጥ!"
የኀብረተሰብ ተሳትፎና በጎ ፈቃድ ማስተባበሪያ ኮሚሽን - አዲስ አበባ
Photo
በአዲስ አበባ ባለፈው ክረምት 5 ነጥብ 4 ቢሊዮን ብር የሚገመት የበጎ ፈቃድ አገልግሎት ተሰጥቷል።

በመዲናችን አዲስ አበባ በ2016 ዓ.ም የክረምት በጎ ፈቃድ 5 ነጥብ 4 ቢሊዮን ብር የሚገመት አገልግሎት ተሰጥቷል።

የክረምት በጎ ፈቃድ መርሃ ግብሩ ከግንቦት 1/2016 ዓ.ም እስከ መስከረም 30/2017 ዓ.ም ለተከታታይ 5 ወራት “በጎ ፈቃደኝነት ለማኅበረሰብ ለውጥ!” በሚል መሪ ቃል በ15 ፕሮግራሞች እና በ18 ንዑሳን ተግባራት ሲካሔድ ቆይቷል፡፡

በድግግሞሽ 3 ሚሊዮን በጎ ፈቃደኞች የተሳተፉ ሲሆን 764 ሺህ 256 ዜጎች በቀጥታ ተጠቃሚ ሆነውበታል፡፡

በዚኽ መርሀ ግብር 2,574 የአቅመ ደካሞች ፣ የሀገር ባለውለታዎች እና አረጋውያን ቤቶች ተገንብተዋል ፤ 12 ሺህ 870 ቤተሰቦች በቀጥታ የቤት ግንባታና እድሳት አገልግሎት ተጠቃሚ ሆነዋል።

469,176 የኅብረተሰብ ክፍሎች በበዓላትና በተለያዩ ወቅቶች ማዕድ ተጋርተዋል ፤ 89 ሺህ ከፍለው መታከም የማይችሉ የኅብረተሰብ ክፍሎች ነፃ የህክምና ድጋፍ አግኝተዋል።

በደም እጥረት ምክንያት የሚፈጠርን ሞት ለመቀነስ ከበጎ ፈቃደኛ ደም ለጋሽ ወጣቶች 32 ሺህ 648 ዩኒት ደም ተሰብስቧል፡፡

94 ሺህ ተማሪዎች የክረምት ማጠናከሪያ ትምህርትና አጫጭር የክህሎት ስልጠና ያገኙ ሲሆን 6 ሺህ 509 የመንገድ ደህንነት ትራፊኮች የትራፊክ መጨናነቅ በሚበዛባቸው አደባባዮችና መንገዶች ላይ እንቅስቃሴውን በማሳለጥ ፣ በመንገድ አጠቃቀምና በትራፊክ አደጋ ዙሪያ ግንዛቤ በመፍጠር እንዲኹም በእግረኛ መንገዶች አቅመ ደካሞችን በማሻገር ተሳትፈዋል።

ከ2 ሚሊዮን በላይ በጎ ፈቃደኞች በአረንጓዴ አሻራ ተግባር እንዲኹም 6 ሺህ 35 በጎ ፈቃደኞች አገልግሎት በሚበዛባቸው የመንግስት ተቋማት የባለጉዳይ እንግልት በመቀነስ አገልግሎት ሰጥተዋል፡፡

የማኅበረሰባችን እርስ በርስ የመረዳዳት እሴት መጠናከር ፤ በጎ ፈቃደኞች ከማኅረሰባቸው መስጠትን ፣ ልግስናን ፣ መደጋገፍን ፣ ፍቅርንና መልካም እሴቶችን መቅሰም ፤ በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ የሚገኙ የኅብረተሰብ ክፍሎች ማኅበራዊና ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነት ከፍ ማለት እና ከተማችን ለኑሮ ምቹና ተምሳሌት እንድትሆን ማስቻል በክረምት የበጎ ፈቃድ አገልግሎት የተገኙ ዋና ዋና ውጤቶች ናቸው።

ለተመዘገበው ሁሉ አቀፍ ውጤት የከተማው በየደረጃው ያለ አመራር ፣ የበጎ ፈቃደኞች ፣ የሚዲያ አካላትና የባለድርሻ ተቋማት ትብብር የአንበሳውን ድርሻ ይወስዳል። በዚኽም የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የኅብረተሰብ ተሳትፎና በጎ ፈቃድ ማስተባበሪያ ኮሚሽን ልባዊ ምስጋናውን በአክብሮት ይገልፃል።

"በጎ ፈቃደኝነት ፤ ለማኅበረሰብ ለውጥ!"

የማኀበራዊ ሚዲያ አማራጮቻችን፥
ፌስቡክ - https://www.facebook.com/cpvcc.2015
ቴሌግራም - https://t.me/CommunityPVC
ቲክቶክ - https://www.tiktok.com/@voluntarismaddis16
ዩቱዩብ - https://youtube.com/@communityparticipationvolu8714
ዌብሳይት - www.volunteeraddis.et
Instagram - https://www.instagram.com/communitypv/
Twitter - https://x.com/Volunteeraddis
የ2017 በጀት ዓመት የበጋ በጎ ፈቃድ አገልግሎት

👉መሪ ቃሉ “በጎ ፈቃደኝነት ለማህበረሰብ ለውጥ!” የሚል ነው፡፡
👉ከጥቅምት 1/2017 እስከ ግንቦት 30/2017 ዓ.ም ድረስ ለ8 ወራት ይቆያል፡፡
👉 በ12 ዋና ዋና ፕግራሞችና 13 መርሀ ግብሮች ይተገበራል፡፡
👉1 ሚሊዮን በጎ ፈቃደኞች ይሳተፉበታል፡፡
👉781,844 የሕብረተሰብ ክፍሎች ተጠቃሚ ይደረጋሉ፡፡
👉6,599,778,376 ብር የመንግስት ወጪን ይታደጋል፡፡

👏ዋና ዋና ተግባራት፣
👉780,824 የህብረተሰብ ክፍሎች ማዕድ ይጋራሉ፡፡
👉4,026 የአረጋውያንና አቅመ ደካሞች ቤቶች ይገነባሉ፡፡
👉100,000 በጎ ፈቃደኞችን በማሳተፍ የችግኝ እንክብካቤ ይደረጋል፡፡
👉12,000 በጎ ፈቃደኞች ከስኬታማ ግለሰቦች የህይወት ልምድና ተሞክሮ እንዲማሩ ይደረጋል፡፡

👉30,480 የህብረተሰብ ክፍሎች ነፃ የህክምና ድጋፍና አገልግሎት ያገኛሉ፡፡
👉ከደም ለጋሽ ወጣት በጎ ፈቃደኞች 33,352 ዩኒት ደም ይሰበሰባል፡፡
👉2,500 በጎ ፈቃደኞችን በማሳተፍ በሆስፒታሎች ህሙማንን የመንከባከብ አገልግሎት ይሰጣል፡፡
👉1965 በጎ ፈቃደኞችን አገልግሎት በሚበዛባቸው የመንግስት ተቋማት ይሰማራሉ፡፡
👉60,000 በጎ ፈቃደኞች በአደባባይ የሚከናወኑ በዓላት በሰላም እንዲጠናቀቁ ያስተባብራሉ፡፡
👉5000 ወጣቶች በማህበራዊ ሚድያው በጎ ተፅዕኖ እንዲፈጥሩ ይደረጋል፡፡
👉500 የአደጋ ተከላካይ በጎ ፈቃደኞች ወደ አገልግሎት ይገባሉ፡፡
👉1729 በጎ ፈቃደኞችን በተመረጡ ክልሎች የከተማችንን የበጎ ፈቃድ ተሞክሮ እንዲያጋሩ ይደረጋል፡፡

"በጎ ፈቃደኝነት ለማኅበረሰብ ለውጥ!"