የኀብረተሰብ ተሳትፎና በጎ ፈቃድ ማስተባበሪያ ኮሚሽን - አዲስ አበባ
823 subscribers
2.14K photos
47 videos
265 links
Download Telegram
"በ2016 በጀት ዓመት 12 ቢሊዮን ብር የበጎ ፈቃድ አገልግሎት ተሰጥቷል።" - ከንቲባ አዳነች አቤቤ

በ2016 በጀት ዓመት 12 ቢሊዮን ብር የበጎ ፈቃድ አገልግሎት መሰጠቱን ከንቲባ አዳነች አቤቤ ገለፁ። የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በበጀት ዓመቱ ለበጎ ፈቃድ አገልግሎት አስተዋፅዖ ላበረከቱ በጎ ፈቃደኞች ፣ ባለሀብቶችና ተቋማት እውቅና ሰጥቷል።

በእውቅና መድረኩ ላይ ተገኝተው በጎ ፈቃደኞችን ያመሰገኑት ከንቲባ አዳነች አቤቤ በበጀት ዓመቱ ልበ ቀና ባለሀብቶችን በማስተባበር 7 ሺህ 567 የአቅመ ደካሞችና አረጋውያን ቤቶች መገንባታቸውን ገልፀዋል።

1.2 ሚሊዮን ዜጎች በድግግሞሽ ማዕድ የተጋሩ መሆኑን የተናገሩት ከንቲባዋ በተከናወኑ የበጎ ፈቃድ አገልግሎቶች 1.9 ሚሊዮን ዜጎች ቀጥታ ተጠቃሚ መሆናቸውን ነው የገለፁት።

ከንቲባ አዳነች አቤቤ ለበጎነት እጃቸውን በመዘርጋት ወገኖቻቸውን ያገዙ እና ማህበራዊ ችግሮችን ያቃለሉ በጎ ፈቃደኞችን ምስጋና አቅርበዋል።
👍2
መልካም አዲስ ዓመት

ምድር አረንጓዴ ለብሳ በአደይ አበባ ስታጌጥ ፤ በተፈጥሮ ኅብር ዜማ አዕዋፋት ሲዘምሩ ፤ ልጆች አበባየሁሽ ሲጨፍሩ ፤ አዲስ አመት ፣ አዲስ ተስፋ ፣ አዲስ ህይወት ሲሰነቅ ፤ ትላንት በትውስታ ሲያልፍ ነጋችን በብርሀን ሲደምቅ ፤ እኛ ኢትዮጵያውያን አብሮነታችን ይበልጥ ይጠብቃል፡፡ የጎደለባቸውን ሞልተን ፣ የወደቁትን አንስተን ፣ የተራቡትን አጉርሰን ፣ የታረዙትን አልብሰን ተደጋግፈን የምንኖር እኛ ኢትዮጵያውያን ነን፡፡

በበጎነት ያካበትነውን ልምድ ሌትና ቀን በመስራት ከድህነት ለመላቀቅ የምንተጋበት ፣ የህብረት ፣ የሰላም ፣ የመተሳሰብና የፍቅር ዘመን ይሁንልን!

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር
የኅብረተሰብ ተሳትፎና በጎ ፈቃድ ማስተባበሪያ ኮሚሽን!
👍6
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የኅብረተሰብ ተሳትፎና በጎ ፈቃድ ማስተባበሪያ ኮሚሽን ለመላው ህዝበ ሙስሊም እንኳን ለ1 ሺህ 499ኛው የመውሊድ በዓል በሰላም አደረሳችሁ እያለ መልካም ምኞቱን ይገልፃል!

ኮሚሽኑ በዓሉን ስናከብር ምንጊዜም እንደምናደርገው ለወገኖቻችን ያለንን ፍቅር የምንገልፅባቸውን የበጎነት ፣ የልግስናና የቸርነት ተግባራትን በማከናወን ፤ አብሮነትን ፣ ወንድማማችነትንና መተሳሰብን በማጠናከር እንዲሆን ጥሪውን እያስተላለፈ ለመላው የእስልምና እምነት ተከታዮች የሰላምና የጤና በዓል ይመኛል፡፡
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ለመላው የእስልምና እምነት ተከታዮች እንኳን ለ1499ኛው የመውሊድ በዓል በሰላም አደረሳችሁ!

#Ethiopia
#addisababa
#volunteering
#ወርቃማው_ሰኞ

ጅማሬያችን ለመጨረሻችን መነሻ ነው። በመልካም መጀመር በመልካም ለማጠናቀቅ ወሳኝ ነው። የስራ መጀመሪያችን ወርቃማዋን ሰኞ የስራ መነሳሳትን በሚፈጥር መልኩ በ"ቅንነት!" መጀመር ተገቢ ነው።

በዛሬው ወርቃማ ሰኞ "ቅንነት" ለስኬታማነት ያለውን ሚና የሚያስረዳ ማብራሪያ የሰጡት የበጎ ፈቃድ ዘርፍ ምክትል ኮሚሽነር አቶ ደረጀ ካሳ ናቸው። በረዥም ጊዜ የስራ ልምዳቸው አብረዋቸው የሰሩ ቀና ሰዎች ከፍ ከፍ ብለው ስኬታማ መሆናቸውን ገልፀዋል አቶ ደረጀ።

ቀና ያልሆኑ ሰዎች መጨረሻቸው አያምርም ፤ ስኬት አያመጡም ፤ ለውጥ አልባ ናቸው። ቀና ሰዎች ደግሞ በተቃራኒው የጀመሩትን በስኬት ይጨርሳሉ ፤ ከነበሩበት ኃላፊነት ወደላቀ ደረጃ ያድጋሉ። በአጠቃላይ ለውጥ ለማምጣትና ስኬት ላይ ለመድረስ በቅንነት ማገልገል ያስፈልጋል።

በህዝብ አገልግሎት ከ12ቱ የስነ ምግባር መርሆዎች መካከል ቅንነት አንዱ ነው። እንደ መርህ በየመሥሪያ ቤታችን ግድግዳ ላይ ያስቀመጥነው "ቅንነት" ልንገዛበትና ልንተገብረው የሚገባ ህግ ነው። ህዝብን በቅንነት ማገልገል ደግሞ የምናልማትን ታላቅ ሃገር ለመገንባት ያግዛል። የኮሚሽናችን ባለሙያዎች "ቅንነትን" የሥራቸው መሰረት ፣ የሕይወታቸው ህግ በማድረግ የላቀ ውጤት ማስመዝገብ ይጠበቅባቸዋል።

ቅንነት - ለላቀ ውጤት!
መልካም የስራ ሳምንት!
👍9
የኀብረተሰብ ተሳትፎና በጎ ፈቃድ ማስተባበሪያ ኮሚሽን - አዲስ አበባ
Photo
ማኅበራዊ ሚዲያን ለሀገራዊ አንድነት ፣ ለሠላም ዕሴትና ለመልካም ገፅታ ግንባታ እንዲሁም ለበጎ ዓላማ መጠቀም እንደሚገባ ተጠቆመ።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የኅብረተሰብ ተሳትፎና በጎ ፈቃድ ማስተባበሪያ ኮሚሽን "ማኅበራዊ ሚዲያ ለበጎነት" በሚል መሪ ቃል ማኅበራዊ ሚዲያውን ለበጎ ዓላማ ለሚጠቀሙ በጎ ፈቃደኞች ስልጠና ሰጥቷል።

የስልጠና መድረኩን በንግግር የከፈቱት የኮሚሽኑ ምክትል ኮሚሽነር ወ/ሮ ፀሐይ ኪባሞ ወጣቶች በማኅበራዊ ሚዲያ ኅብረ ብሔራዊ ወንድማማችነትና እህትማማችነትን የሚያፀኑ ፣ ሀገራዊ አንድነትንና መልካም ገፅታን የሚገነቡ እንዲሁም ለሠላም ዕሴት ግንባታ ቀዳሚ ትኩረት የሚሠጡ ይዘቶችን ማጋራት እንደሚገባቸው አሳስበዋል።

ወጣቶች አዎንታዊ አጀንዳዎችን በመሸጥ የተዛቡና አንድነትን የሚሸረሽሩ አሉታዊ መረጃዎች ቦታ እንዳይኖራቸው ማድረግ ፣ የማኅበራዊ ሚዲያውን አልጎሪዝም በልማት ፣ በሠላም ፣ በዲሞክራሲ ፣ በማኅበረሰብ ለውጥና ተጠቃሚነት የበላይነት እንዲይዝ መስራት ይጠበቅባቸዋል ብለዋል ምክትል ኮሚሽነሯ።

የአሁኑ ትውልድ አሉታዊ የማኅበራዊ ሚዲያ አጠቃቀም ተፅዕኖን በመግታት ለብሔራዊ ጥቅምና ለሀገር ሉዓላዊነት መከበር የድርሻውን የሚወጣበት ጊዜ መሆኑን ያወሱት ወ/ሮ ፀሐይ በከተማችን አዲስ አበባ በየዘርፉ የተከናወኑ የልማት ፣ የበጎነትና የሠላም ስራዎች የማህበራዊ ሚዲያው ቀዳሚ አጀንዳ እንዲሆኑ በማድረግ ረገድ የወጣት በጎ ፈቃደኞች ሚና ከፍተኛ እንደነበር አውስተው ተሳትፏቸውን ይበልጥ እንዲያጠናክሩ ጠይቀዋል።

ኮሚሽኑ በክረምት በጎ ፈቃድ አገልግሎት ከተያዙ 15 ፕሮግራሞች መካከል "ማኅበራዊ ሚዲያ ለበጎነት" አንደኛው መርሀ ግብር ሲሆን ጤናማ የዲጂታል ሚዲያ አጠቃቀም ባህል እንዲጎለብት ፣ ማኅበራዊ ሚዲያ ኢትዮጵያዊ አብሮ የመኖር እሴትን በማይሸረሽር መልኩ ፣ ወንድማማችነት ፣ አብሮነትና ሠላም እንዲዳብር ለከተማዋ ወጣቶች የተለያዩ መድረኮችን በማዘጋጀት ግንዛቤዎችን ሲፈጥር ቆይቷል።

በዛሬው የስልጠና መድረክ በጎ ተፅዕኖ የሚፈጥሩ ወጣት በጎ ፈቃደኞች የተሳተፉ ሲሆን ሥልጠናው በይዘት አዘገጃጀት ፣ በእውነታ ማጣራት እንዲሁም በማህበራዊ ሚዲያ በጎ ፈቃደኝነት ላይ ትኩረት አድርጓል።

"ጤናማ የማኅበራዊ ሚዲያ አጠቃቀም የሥልጡን ዜጋ መገለጫ ነው!"

የማኀበራዊ ሚዲያ አማራጮቻችን፥
ፌስቡክ - https://www.facebook.com/cpvcc.2015
ቴሌግራም - https://t.me/CommunityPVC
ቲክቶክ - https://www.tiktok.com/@voluntarismaddis16
ዩቱዩብ - https://youtube.com/@communityparticipationvolu8714
ዌብሳይት - www.volunteeraddis.et
Instagram - https://www.instagram.com/communitypv/
Twitter - https://x.com/Volunteeraddis
👍2
👉ትላንት በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ለአቅመ ደካሞች የተገነቡ መኖሪያ ህንፃዎች በከንቲባ አዳነች አቤቤ ተመርቀው ለተጠቃሚዎች ተላልፈዋል።

👉ዊንጌት እና ገብስ ተራ አካባቢ ደሳሳና ለኑሮ የማያመቹ የነበሩ የቀበሌ ቤቶችን በማፍረስ ምቹ ተደርገው የተገነቡ ናቸው።

👉አጠቃላይ የቤቶች ብዛት 75 ሲሆኑ ባለ 5 ወለል(G+5) ሁለት ህንጻዎች ናቸው።

👉ከ375 በላይ ቤተሰቦች ያሏቸው 75 አባውራ/እማውራዎችን ተጠቃሚ ያደረጉት እነዚህ ቤቶች በአጭር ጊዜ ውስጥ የተጠናቀቁ ናቸው።

👉የመጸዳጃና የማብሰያ ቦታ ፣ ሰፋፊ ሳሎኖችና መኝታ ቤቶች ያላቸው ናቸው::

👉በዚህ የበጎ ፈቃድ አገልግሎት ላይ ብዙአየሁ ታደለ ፋውንዴሽን፣ መተባበር ለኢትዮጵያ አ/ማ ፣ ተምሳሌት በሲዳሞ ተራ አ/ማ ፣ ምዕራብ ገበያ ልማት አ/ማ ፣ ጉሊት አክሲዮን ማህበር ፣ ሸራ ተራ ብርሃን አክሲዮን እንዲሁም ጎሽ ንግድና አክሲዮን ግንባታ ማህበር ተሳትፈዋል።

👉ከንቲባ አዳነች አቤቤ በቦታው ተገኝተው "የዘመሙ ጎጆዎችን እያቃናን የሚፈሱ እንባዎች ሲታበሱ ማየት እጅግ ደስ ያሰኛል" ያሉ ሲሆን በዚህ የማኅበራዊ ኃላፊነት ስራ ላይ የተሳተፉ ተቋማትን በተጠቃሚ ነዋሪዎች እና በከተማ አስተዳደሩ ስም አመስግነዋል።

👉በመተባበር የሰው ኑሮ እና አኗኗርን በማሻሻል ሀገር እንገነባለንና ትብብራችንን አጠናክረን እንቀጥል ሲሉ ከንቲባ አዳነች አቤቤ ጥሪ አቅርበዋል።
👍2