የኀብረተሰብ ተሳትፎና በጎ ፈቃድ ማስተባበሪያ ኮሚሽን - አዲስ አበባ
820 subscribers
2.14K photos
47 videos
265 links
Download Telegram
ከተማ አስተዳደሩ መጪውን አዲስ ዓመት ምክንያት በማድረግ ለ500 ሺህ የኅብረተሰብ ክፍሎች ማዕድ አጋራ።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር መጪውን አዲስ ዓመት ምክንያት በማድረግ ከማዕከል እስከ ብሎክ በተዘጋጁ መርሃ ግብሮች ለ500 ሺህ የከተማዋ ነዋሪዎች በዛሬው ዕለት ማዕድ አጋርቷል።

በማዕከ ደረጃ በተካደው የማዕድ ማጋራት ፕሮግራም ላይ ተገኝተው መልዕክት ያስተላለፉት ከንቲባ አዳነች አቤቤ በዓሉ የበረከትና የደስታ እንዲሁም የመተሳሰብ እንዲሆን ተመኝተዋል።

የምናጋራው ማዕድ ብቻ ሳይሆን ለወገኖቻችን ያለንን ፍቅርና አክብሮትን ለማሳየት ጭምር ሲሆን ማዕድ ማጋራቱ ወገኖቻችን በዓሉን በደስታ እንዲያከብሩት የሚረዳ ያሉት ከንቲባ አዳነች አቤቤ የመንግስትን የሰው ተኮር ፖሊሲ፣ አቅጣጫ እና ጥሪ በመቀበል ሰርተው ካገኙት ለወገኖቻቸው ማካፈልን ባሕል ላደረጉ የከተማዋ ልበ ቀና ባለሀብቶች እና በጎ ፈቃደኞች አመስግነዋል::

የአዲስ አበባ ከተማ የኅብረተሰብ ተሳትፎና በጎ ፈቃድ ማስተባበሪያ ኮሚሽን ኮሚሽነር አቶ ተንኩቄይ ጆክ በበኩላቸው የማዕድ ማጋራት ዋና ዓላማ በሰዎች መካከል መተሳሰብን ፣ አብሮነትንና ፍቅርን ለመፍጠር መሆኑን ገልፀው በ2016 በጀት ዓመት 1.2 ሚሊዮን ዜጎች ማዕድ መጋራታቸውን ተናግረዋል። በዛሬው ዕለት አዲሱን ዓመትና የኅብር ቀንን በማስመልከት ከማዕከል እስከ ብሎክ ድረስ ለ500 ሺህ በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ለሚገኙ ዜጎች ማዕድ መጋራቱን ኮሚሽነሩ ገልፀዋል።

ኅብራችን ለአብሮነታችንና ለዘላቂ ሠላማችን!
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ፣ መጪውን አዲስ ዓመት ምክንያት በማድረግም፣ ዝቅተኛ ገቢ ላላቸው የጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት ሠራተኞች እና ጽሕፈት ቤቱ ለሚያሳድጋቸው ሕጻናት ማዕድ አጋርተዋል።

#PMOEthiopia
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በ2016 በጀት ዓመት ለበጎ ፈቃድ አገልግሎት የላቀ አስተዋፅዖ ላበረከቱ አካላት ከጥቂት ደቂቃዎች በኋላ "የበጎነት እውቅና" ይሰጣል።

"በኅብር እንቆማለን ፤ የነገ ትልሞችን እናሳካለን!"
"በ2016 በጀት ዓመት 12 ቢሊዮን ብር የበጎ ፈቃድ አገልግሎት ተሰጥቷል።" - ከንቲባ አዳነች አቤቤ

በ2016 በጀት ዓመት 12 ቢሊዮን ብር የበጎ ፈቃድ አገልግሎት መሰጠቱን ከንቲባ አዳነች አቤቤ ገለፁ። የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በበጀት ዓመቱ ለበጎ ፈቃድ አገልግሎት አስተዋፅዖ ላበረከቱ በጎ ፈቃደኞች ፣ ባለሀብቶችና ተቋማት እውቅና ሰጥቷል።

በእውቅና መድረኩ ላይ ተገኝተው በጎ ፈቃደኞችን ያመሰገኑት ከንቲባ አዳነች አቤቤ በበጀት ዓመቱ ልበ ቀና ባለሀብቶችን በማስተባበር 7 ሺህ 567 የአቅመ ደካሞችና አረጋውያን ቤቶች መገንባታቸውን ገልፀዋል።

1.2 ሚሊዮን ዜጎች በድግግሞሽ ማዕድ የተጋሩ መሆኑን የተናገሩት ከንቲባዋ በተከናወኑ የበጎ ፈቃድ አገልግሎቶች 1.9 ሚሊዮን ዜጎች ቀጥታ ተጠቃሚ መሆናቸውን ነው የገለፁት።

ከንቲባ አዳነች አቤቤ ለበጎነት እጃቸውን በመዘርጋት ወገኖቻቸውን ያገዙ እና ማህበራዊ ችግሮችን ያቃለሉ በጎ ፈቃደኞችን ምስጋና አቅርበዋል።
👍2
መልካም አዲስ ዓመት

ምድር አረንጓዴ ለብሳ በአደይ አበባ ስታጌጥ ፤ በተፈጥሮ ኅብር ዜማ አዕዋፋት ሲዘምሩ ፤ ልጆች አበባየሁሽ ሲጨፍሩ ፤ አዲስ አመት ፣ አዲስ ተስፋ ፣ አዲስ ህይወት ሲሰነቅ ፤ ትላንት በትውስታ ሲያልፍ ነጋችን በብርሀን ሲደምቅ ፤ እኛ ኢትዮጵያውያን አብሮነታችን ይበልጥ ይጠብቃል፡፡ የጎደለባቸውን ሞልተን ፣ የወደቁትን አንስተን ፣ የተራቡትን አጉርሰን ፣ የታረዙትን አልብሰን ተደጋግፈን የምንኖር እኛ ኢትዮጵያውያን ነን፡፡

በበጎነት ያካበትነውን ልምድ ሌትና ቀን በመስራት ከድህነት ለመላቀቅ የምንተጋበት ፣ የህብረት ፣ የሰላም ፣ የመተሳሰብና የፍቅር ዘመን ይሁንልን!

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር
የኅብረተሰብ ተሳትፎና በጎ ፈቃድ ማስተባበሪያ ኮሚሽን!
👍6
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የኅብረተሰብ ተሳትፎና በጎ ፈቃድ ማስተባበሪያ ኮሚሽን ለመላው ህዝበ ሙስሊም እንኳን ለ1 ሺህ 499ኛው የመውሊድ በዓል በሰላም አደረሳችሁ እያለ መልካም ምኞቱን ይገልፃል!

ኮሚሽኑ በዓሉን ስናከብር ምንጊዜም እንደምናደርገው ለወገኖቻችን ያለንን ፍቅር የምንገልፅባቸውን የበጎነት ፣ የልግስናና የቸርነት ተግባራትን በማከናወን ፤ አብሮነትን ፣ ወንድማማችነትንና መተሳሰብን በማጠናከር እንዲሆን ጥሪውን እያስተላለፈ ለመላው የእስልምና እምነት ተከታዮች የሰላምና የጤና በዓል ይመኛል፡፡
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ለመላው የእስልምና እምነት ተከታዮች እንኳን ለ1499ኛው የመውሊድ በዓል በሰላም አደረሳችሁ!

#Ethiopia
#addisababa
#volunteering
#ወርቃማው_ሰኞ

ጅማሬያችን ለመጨረሻችን መነሻ ነው። በመልካም መጀመር በመልካም ለማጠናቀቅ ወሳኝ ነው። የስራ መጀመሪያችን ወርቃማዋን ሰኞ የስራ መነሳሳትን በሚፈጥር መልኩ በ"ቅንነት!" መጀመር ተገቢ ነው።

በዛሬው ወርቃማ ሰኞ "ቅንነት" ለስኬታማነት ያለውን ሚና የሚያስረዳ ማብራሪያ የሰጡት የበጎ ፈቃድ ዘርፍ ምክትል ኮሚሽነር አቶ ደረጀ ካሳ ናቸው። በረዥም ጊዜ የስራ ልምዳቸው አብረዋቸው የሰሩ ቀና ሰዎች ከፍ ከፍ ብለው ስኬታማ መሆናቸውን ገልፀዋል አቶ ደረጀ።

ቀና ያልሆኑ ሰዎች መጨረሻቸው አያምርም ፤ ስኬት አያመጡም ፤ ለውጥ አልባ ናቸው። ቀና ሰዎች ደግሞ በተቃራኒው የጀመሩትን በስኬት ይጨርሳሉ ፤ ከነበሩበት ኃላፊነት ወደላቀ ደረጃ ያድጋሉ። በአጠቃላይ ለውጥ ለማምጣትና ስኬት ላይ ለመድረስ በቅንነት ማገልገል ያስፈልጋል።

በህዝብ አገልግሎት ከ12ቱ የስነ ምግባር መርሆዎች መካከል ቅንነት አንዱ ነው። እንደ መርህ በየመሥሪያ ቤታችን ግድግዳ ላይ ያስቀመጥነው "ቅንነት" ልንገዛበትና ልንተገብረው የሚገባ ህግ ነው። ህዝብን በቅንነት ማገልገል ደግሞ የምናልማትን ታላቅ ሃገር ለመገንባት ያግዛል። የኮሚሽናችን ባለሙያዎች "ቅንነትን" የሥራቸው መሰረት ፣ የሕይወታቸው ህግ በማድረግ የላቀ ውጤት ማስመዝገብ ይጠበቅባቸዋል።

ቅንነት - ለላቀ ውጤት!
መልካም የስራ ሳምንት!
👍9