"የመሻገር ጥሪቶች ፣ የአዲስ ብርሃብ ወረቶች!"
ዛሬ ጳጉሜን 1 "የመሻገር ቀን" ነው። በየተሰማራንበት መስክ ውጤት በማምጣት ፤ በግብርናው ዘርፍ ምርታማነትን በማሳደግ ፣ ኢንዱስትሪውን በማሻሻል ፣ አገልግሎቱን በማቀላጠፍ ፣ የውጭ ምንዛሬ የሚያስገኙ ተኪ ምርቶችን በማስፋት ፣ ቴክኖሎጂን በመጠቀም ፣ በፍጥነትና በአጭር ጊዜ ሌትም ቀንም ሰርተን ሀገራችን ኢትዮጵያን ወደ ብልፅግና እናሻግር።
ከተማችን አዲስ አበባ የጀመረችውን ሁሉአቀፍ ለውጥ በማስቀጠል ዓለም አቀፍ የዲፕሎማሲና የቱሪዝም ስበት ማዕከል ሆና እንድትዘልቅ ፣ ለነዋሪዎቿ ምቹ እንድትሆን ፣ ሁሉም የሚመርጣት ፣ ወደ ውብና ፅዱነቷን እናረጋግጥ!

👍4❤1
ጳጉሜን 1 የመሻገር ቀን !
አዲስ ዓመት ያለቀውን ዓመት ሸኝቶ አዲሱን ከመጀመርም ባለፈ ከአስቸጋሪው ደመናማ የዝናብ ወቅት ወደ ብሩህ ተስማሚ ወራት መሻገርን የሚያበስር፣ በአዲስ አስተሳሰብና በብሩህ ተስፋ የምንቀበለው የአዲስ ምዕራፍ መባቻ ነው።
የተገባደደው ዓመት እንደ ሀገርም ሆነ እንደ ከተማ በበርካታ መስኮች የህዝባችንን ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ እድገት የማረጋገጥ ጉልህ ፋይዳ ያላቸው ዘርፈ ብዙ ውጤቶች ያስመዘገብንበት እንዲሁም ከድህነት ወደ አስተማማኝ የብልጽግና ምዕራፍ ለመሸጋገር የሚያስችለንን መሰረት የጣልንበት አንጸባራቂ የስኬትና የእድገት ዘመን እንደነበረ ግልጽ ነው።
ይህ ዛሬ የምናከበረው የመሻገር ቀንም፣ ባለፈው ዓመት ካለፍናቸው ትላልቅ ፈተናዎችና በድል ከተሻገርናቸው እንቅፋቶች ተገቢውን ትምህርት ወስደን በዚህ ሂደት ውስጥ አቅም በፈቀደ መጠን አስተዋጾ ያደረጉና ያገዙን አካላትንና መላው ህዝባችንን ከልብ የምናመሰግንበት፣ ብሎም የቀጣዩ ዓመት የርብርባችን ማዕከል የሆነውን ብልጽግናን የማረጋጋጥና ህዝባችንን ወደ ላቀ ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ እመርታ የማሻገር ራዕይ እውን ለማድረግ በጋራ ለመትጋት ቃል የምንገባበት እለት ነው።
በመሆኑም፣ ባሳለፍናቸው የለውጥ ዓመታት በአጭር ጌዜ ያስመዘገብናቸውን ተአምራዊ የልማት ስኬቶችን ተስፋ ሰጪነት አይቶ አስፈላጊ በሆኑ ጉዳዮች ላይ ሁሉ በመሳተፍ ሲያግዘንና ሲያበረታን የነበረው ህዝባችን ላሳየን አጋርነትና ትብብር ሁሉ ልባዊ ምስጋና እያቀረብን ቀጣዩ ዓመትም ካሳለፍነው ዓመት የተሻሉ ግዙፍ ድሎችን በማስመዝገብ ህዝባችንን ወደ ብልጽግና የምናሻግርበት እንደሚሆን በመተማመን ይህን ታላቅ አገራዊ ራዕይ ለማሳካት ህዝባችን አብሮን እንዲቆም ጥሪ እናስተላልፋለን።
መልካም አዲስ አመት!!!!
ከንቲባ አዳነች አቤቤ

👍5
#ጳጉሜን_2
የሪፎርም ቀን!
ለውጥ አይቀሬ ነገር ነው። የማይለወጥ የለም። የማይለወጠው ራሱ ለውጥ ብቻ ነው። ያለለውጥ ህይወት አይጣፍጥም። መኖር አያጓጓም። የሰው ልጅ ነገን ተስፋ አድርጎ በጉጉት የሚኖረው ለውጥን አጥብቆ ስለሚሻ ነው።
የዛሬዋ ቀን የለውጥ ቀን ነች። ራሳችንን ለውጠን በአገልግሎት አሰጣጣችን መለወጥ ያስፈልገናል። ህዝባችንን በስነ ምግባር በማስተናገድ ለውጥ ማምጣት አለብን። በተመደብንበት የስራ መስክ ራሳችንን ብቁ ማድረግ ፣ ተወዳዳሪ ሆኖ መገኘት ግድ ይለናል።
እያንዳንዳችን ካልተለወጥን ሀገራችንን በሁሉም ዘርፍ ወደምንናፍቀው ብልፅግና ማድረስ አንችልም። እንለወጥ!
"ሪፎርም ለላቀ አገልግሎት!"

👍2
ዛሬ የአዋሬ አካባቢን ለማሻሻል ላለን ትልም እና ጥረት አንድ ምዕራፍ ሆኗል። የተጎዳ እና የተጎሳቆለ የነበረው አካባቢ ዛሬ ለነዋሪዎች በተለይም ለአረጋውያን ምቹ እና ለሰው ልጅ የከበረ አኗኗር የሚመረጥ ሰፈር ሆኗል። ይህ ሥራ የማኅበረሰባችንን አኗኗር ለመለወጥ ላለን ጽኑ አላማ ማሳያ ነው።
አዋሬ ጥራትን ሳያጓድሉ በፍጥነት የመገንባት መርሃችንን ያንፀባርቃል። አሁን በአዋሬ ክብር ላለው የሰው ልጅ ኑሮ የተመቸ የልጆች መጫወቻ ስፍራ፣ ለማረፊያ እና ማሰቢያ የሚሆን አረንጓዴ ስፍራ፣ ለአረጋውያን የሚመች የእግረኛ መንገድ እንዲሁም ንፁህ ከባቢን ይዟል።
ይሁንና በአዋሬ ያሳካነው ገና ጅምር ሥራ ነው። በዚህ ሥራችን ረክተን መቆም የለብንም። ብዙ ሥራ ይቀረናል። የብዙ ሚሊዮኖች ሀገር እንደመሆናችን በመላው ሀገራችን የዜጎቻችንን ሕይወት ከፍ ማድረግ ፋታ የማይሰጥ ቀጣይነት ያለው ሥራችን ነው።
መሻሻልን ሳናቋርጥ ለመቀጠል እና ጅምር ሥራውን ለማስፋፋት ከግሉ ዘርፍ እና ከየከተሞች ጋር ያለንን ትብብር ማጠናከር ይኖርብናል። አዲሱን አመት ስንቀበል ብዙዎቹን ተግዳሮቶቻችንን ተሻገረን ለልጆቻችን ጠንካራ ኢትዮጵያን እንደምንገነባ እምነቴ ጽኑ ነው።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐብይ አሕመድ

አዲስ አመትን በበጎ ፍቃድ መርሃ ግብር የተገነቡ 837 ቤቶች ለአቅመ ደካሞች ተላለፉ።
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የ2017 አዲስ አመትን በማስመልከት "በሁሉም ክፍለ ከተሞች በበጎ ፍቃድ መርሃ ግብር የተገነቡ 837 ቤቶችን ለአቅመ ደካሞች አስተላለፈ።
በንፋስ ስልክ ላፍቶ፣ አራዳ እና የካ ክፍለ ከተሞች የተገነቡ ቤቶችን ለተጠቃሚዎች ያስተላለፉት ከንቲባ አዳነች አቤቤ ጷጉሜን 3 የሉዓላዊነት ቀንን ስናስብ የሀገርን ዳር ድንበር ከማስከበር ጎን ለጎን በኢኮኖሚ አቅም መጠንከር እና መከበርም ይገባል ብለዋል።
ከድህነት መውጣት እና የኢኮኖሚ ሉዓላዊነትን ማስከበር የሚቻለው በመጣርና በመትጋት ላብን በማፍሰስ ነው ያሉት ከንቲባ አዳነች አቅመ ደካሞች እና ለተያዩ ማህበራዊ ችግሮች የተጋለጡ ወገኖችን ህይወት ለማሻሻል ትብብር እና ድጋፍ እያደረጉ ያሉ በጎ አድራጊዎችንም አመስግነዋል።
ባለፉት የለውጥ አመታት በአዲስ አበባ ከተማ 27ሺ የሚደርሱ ቤቶች በበጎ ፍቃድ አገልግሎት ተገንብተው ለአቅመ ደካሞች እና ለተለያዩ ማህበራዊ ችግሮች ለተጋለጡ ዜጎች መተላለፋቸውን የተናገሩት ከንቲባ አዳነች አሁንም ቢሆን ችግሩ ሰፊ በመሆኑ ሌሎች በጎ አድራጊ አካላትም የከተማዋን ገጽታ ለመቀየር እና የነዋሪዎቿን ህይወት ለማሻሻል የሚደረገውን ጥረት እንዲደግፉም ጥሪ አቅርበዋል።

👍4
በልደታ ክፍለ ከተማ በ69.5 ሚሊዮን ብር በኅብረተሰቡ ተሳትፎ የተገነቡ የመሰረተ ልማት ፕሮጀክቶች ተመረቁ፡፡
የልደታ ክፍለ ከተማ በተጠናቀቀው ዓመት በ69.5 ሚሊዮን ብር በኅብረተሰብ ተሳትፎ የገነባቸውን የአካባቢ መሰረተ ልማት ፕሮጀክቶች በዛሬው ዕለት አስመርቋል።
በምረቃ ሥነ-ስርዓቱ ላይ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የኅብረተሰብ ተሳትፎና በጎ ፈቃድ ማስተባበሪያ ኮሚሽን ምክትል ኮሚሽነር ወ/ሮ ፀሐይ ኪባሞ ተገኝተው የኅብረተሰቡን የመልካም አስተዳደርና የልማት ጥያቄዎች ለመመለስ ባለሀብቱንና ኅብረተሰቡን የማሳተፍ ስራ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ተናግረዋል።
የክፍለ ከተማው የኅብረተሰብ ተሳትፎና በጎ ፈቃድ ማስተባበሪያ ጽህፈት ቤት ኃላፊ ወ/ሮ ሔለን መሀመድ በ2016 በጀት ዓመት የተሰሩ የመሰረተ ልማት ስራዎች በ10 ወረዳዎች መመረቃቸውን ገልፀው 69 ሚሊዮን 526 ሺህ 45 ብር ወጪ እንደተደረገባቸው አስረድተዋል።
"ሁሉ አቀፍ የኅብረተሰብ ተሳትፎ ፤ ለዘላቂ ልማት!"
የማኀበራዊ ሚዲያ አማራጮቻችን፥
ፌስቡክ - https://www.facebook.com/cpvcc.2015
ቴሌግራም - https://t.me/CommunityPVC
ቲክቶክ - https://www.tiktok.com/@voluntarismaddis16
ዩቱዩብ - https://youtube.com/@communityparticipationvolu8714
ዌብሳይት - www.volunteeraddis.et
Instagram - https://www.instagram.com/communitypv/
Twitter - https://x.com/Volunteeraddis

ኢትዮጵያ የብዙ ብሔሮች፣ የብዙ ቋንቋዎች፣ የብዙ ባህሎች፣የብዙ እምነቶች፣ የብዙ ሥልጣኔዎች፣ የብዙ ጀግኖች፣ ሀገር ናት። ኢትዮጵያ ኅብር ናት።
ሁሉም የኛ በእኛ ለእኛ የተሰጡ ናቸው። ሁሉን እናከብራለን፤ በሁሉም እንኮራለን።
ኅብረ ብሔራዊነታችን መልካችን፣ አንድነታችን ደግሞ ህልውናችን ነው። እነዚህ ኅብራዊ ጸጋዎች በአንዲት ሀገር በኢትዮጵያ የሚገኙ ናቸው። ዓላማችን አንድ የፖለቲካና የኢኮኖሚ ማኅበረሰብ መገንባት ነው። ግባችን የኢትዮጵያ ብልጽግና ነው። ይህ ነው አንድነታችን።
የተበታተንን ኅብሮች አይደለንም፤ የተጨፈለቅን አንድ ዓይነቶችም አይደለንም። እኛ ኅብረ ብሔራዊ አንድነት ያለን ኢትዮጵያውያን ነን።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)

👍1
ከተማ አስተዳደሩ መጪውን አዲስ ዓመት ምክንያት በማድረግ ለ500 ሺህ የኅብረተሰብ ክፍሎች ማዕድ አጋራ።
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር መጪውን አዲስ ዓመት ምክንያት በማድረግ ከማዕከል እስከ ብሎክ በተዘጋጁ መርሃ ግብሮች ለ500 ሺህ የከተማዋ ነዋሪዎች በዛሬው ዕለት ማዕድ አጋርቷል።
በማዕከ ደረጃ በተካደው የማዕድ ማጋራት ፕሮግራም ላይ ተገኝተው መልዕክት ያስተላለፉት ከንቲባ አዳነች አቤቤ በዓሉ የበረከትና የደስታ እንዲሁም የመተሳሰብ እንዲሆን ተመኝተዋል።
የምናጋራው ማዕድ ብቻ ሳይሆን ለወገኖቻችን ያለንን ፍቅርና አክብሮትን ለማሳየት ጭምር ሲሆን ማዕድ ማጋራቱ ወገኖቻችን በዓሉን በደስታ እንዲያከብሩት የሚረዳ ያሉት ከንቲባ አዳነች አቤቤ የመንግስትን የሰው ተኮር ፖሊሲ፣ አቅጣጫ እና ጥሪ በመቀበል ሰርተው ካገኙት ለወገኖቻቸው ማካፈልን ባሕል ላደረጉ የከተማዋ ልበ ቀና ባለሀብቶች እና በጎ ፈቃደኞች አመስግነዋል::
የአዲስ አበባ ከተማ የኅብረተሰብ ተሳትፎና በጎ ፈቃድ ማስተባበሪያ ኮሚሽን ኮሚሽነር አቶ ተንኩቄይ ጆክ በበኩላቸው የማዕድ ማጋራት ዋና ዓላማ በሰዎች መካከል መተሳሰብን ፣ አብሮነትንና ፍቅርን ለመፍጠር መሆኑን ገልፀው በ2016 በጀት ዓመት 1.2 ሚሊዮን ዜጎች ማዕድ መጋራታቸውን ተናግረዋል። በዛሬው ዕለት አዲሱን ዓመትና የኅብር ቀንን በማስመልከት ከማዕከል እስከ ብሎክ ድረስ ለ500 ሺህ በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ለሚገኙ ዜጎች ማዕድ መጋራቱን ኮሚሽነሩ ገልፀዋል።
ኅብራችን ለአብሮነታችንና ለዘላቂ ሠላማችን!

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ፣ መጪውን አዲስ ዓመት ምክንያት በማድረግም፣ ዝቅተኛ ገቢ ላላቸው የጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት ሠራተኞች እና ጽሕፈት ቤቱ ለሚያሳድጋቸው ሕጻናት ማዕድ አጋርተዋል።
#PMOEthiopia
#PMOEthiopia