የኀብረተሰብ ተሳትፎና በጎ ፈቃድ ማስተባበሪያ ኮሚሽን - አዲስ አበባ
818 subscribers
2.14K photos
47 videos
265 links
Download Telegram
የኅብረተሰቡ የአካባቢ ጥበቃ ተሳትፎ እየተጠናከረ መምጣቱ ተገለፀ።

የኅብረተሰብ ተሳትፎና በጎ ፈቃድ ማስተባበሪያ ኮምሽን በአዋጅ ከተሰጡት ኃላፊነቶች መካከል ኅብረተሰቡ በብሎክ አደረጃጀት ውስጥ በአካባቢ ሰላም ስራዎች እንዲሳተፍ ምቹ ሁኔታን መፍጠር ይገኝበታል።

የኅብረተሰቡ የአካባቢ ጥበቃ ተሳትፎ የቅጥር ጥበቃን ከማጠናከር ጀምሮ የፀጥታ ስጋቶችን አስቀድሞ መከላከል ፣ በመሰረተ ልማቶች ላይ የሚደርሱ ጉዳቶችን መቆጣጠር ፣ አካባቢን በሽፍት መጠበቅና ሌሎች ጉዳዮችን ያካትታል።

ኮሚሽኑ የኅብረተሰቡን የሠላም ተሳትፎ ለማሳደግም የኅብረተሰብ የአካባቢ ጥበቃ ተሳትፎ መመሪያ ቁጥር 148/2016 አዘጋጅቶ ስራ ላይ አውሏል።

መመሪያው በርካታ የመልካም አስተዳደር ችግሮችን መፍታቱንና ለሥራቸውም ምቹ ሁኔታ እንደፈጠረላቸው በአራዳ ክፍለ ከተማ ወረዳ 1 በምሽት የአካባቢ ሠላም ስራ ላይ የተሰማሩ የቅጥር ጥበቃ አባላት ገልፀዋል።

የኮሚሽኑ የደንብ መተላለፍ ቅድመ መከላከል ህዝባዊ ተሳትፎ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ገዛኸኝ ኃይሉ አዲሱን መመሪያ መሰረት በማድረግ በብሎኮች የኅብረተሰብ ጥበቃ አባላት በብዛት እየተሳተፉ መሆኑን ገልፀዋል።

የማኀበራዊ ሚዲያ አማራጮቻችን፥
ፌስቡክ - https://www.facebook.com/cpvcc.2015
ቴሌግራም - https://t.me/CommunityPVC
ቲክቶክ - https://www.tiktok.com/@voluntarismaddis16
ዩቱዩብ - https://youtube.com/@communityparticipationvolu8714
ዌብሳይት - www.volunteeraddis.et
Instagram - https://www.instagram.com/communitypv/
Twitter - https://x.com/Volunteeraddis
👍1
ለመጪው አዲስ ዓመት አብሮነትን ይበልጥ ማጠናከር የሚያስችሉ ማህበራዊና ሰብዓዊ ሥራዎች እየተከናወኑ ነው።

በአዲስ አበባ ከተማ አዲሱን ዓመት ምክንያት በማድረግ አቅመ ደካሞችን ፣ በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ የሚገኙ ነዋሪዎችንና አረጋውያንን ተጠቃሚ የሚያደርጉና አብሮነትን ይበልጥ የሚያጠናክሩ ማህበራዊና ሰብዓዊ ተግባራት እየተከናወኑ ይገኛሉ።

የአስተዳደሩ የኅብረተሰብ ተሳትፎና በጎ ፈቃድ ማስተባበሪያ ኮሚሽን እነዚህ ሰው ተኮር ተግባራት የደረሱበትን የአፈፃጸም ደረጃ ከክፍለ ከተማ የዘርፍ ኃላፊዎችና ከማዕከል አመራሮች ጋር በመገምገም ቀሪ ስራዎች በልዩ ትኩረት እንዲመሩ አቅጣጫ አስቀምጧል።

በጳጉሜን ቀናት የሚከናወኑ ሰብዓዊና ማኅበራዊ ተግባራት በየደረጃው አሰራሩን ጠብቀው እየተመሩ መሆኑ በጥንካሬ የተገመገመ ሲሆን የተቸገሩ ወገኖቻችን በዓሉን በደስታና በአብሮነት እንዲያከብሩ ሁሉም አካላት ማኅበራዊ ኃላፊነታቸውን በመወጣት የበኩላቸውን አስተዋፅዖ እንዲያደርጉ በመድረኩ ተጠይቋል።

"በጎ ፈቃደኝነት ፤ ለማኅበረሰብ ለውጥ!"
የማኀበራዊ ሚዲያ አማራጮቻችን፥
ፌስቡክ - https://www.facebook.com/cpvcc.2015
ቴሌግራም - https://t.me/CommunityPVC
ቲክቶክ - https://www.tiktok.com/@voluntarismaddis16
ዩቱዩብ - https://youtube.com/@communityparticipationvolu8714
ዌብሳይት - www.volunteeraddis.et
Instagram - https://www.instagram.com/communitypv/
Twitter - https://x.com/Volunteeraddis
👍2
በከተማችን አዲስ አበባ የመጀመሪያው የአፍሪካ ከተሞች ፎረም ከነገ ጀምሮ በዓድዋ ድል መታሰቢያ የሚካሄድ በመሆኑ ደስታችን የላቀ ነው ።

የመጀመሪያውን የአፍሪካ ከተሞች ፎረም በማዘጋጀት ከአፍሪካ ወንድሞችና እህቶቻችን ጋር ከተሞቻችንን በማዘመን፣ ለነዋሪዎች ምቹ የለውጥና የብልፅግና ማዕከል እንዲሆኑ ማድረግ እና እጅ ለእጅ ተያይዘን መስራት በምንችልባቸው መንገዶች ዙሪያ የምንመክርበት ወሳኝ መድረክ ሲሆን ለፎረሙ ስኬታማነት በርካታ ዝግጅቶችን አድርገናል::

ውድ የከተማችን ነዋሪዎች ይህን እድል ማግኘታችን ትልቅ ትርጉም አለው ፤ ተባብረን በጋራ ሰርተን ከተማችንን ለዚህ አይነት ፎረም፣ ኮንቬንሽንና የስበት ማዕከል ማድረግን አጠናክረን ይበልጥ መስራት ይኖርብናል::

እንዲህ ያሉ ሁነቶች ለከተማችን በቱሪዝም ተጨማሪ ገቢ በማስገኘትና በማስተዋወቅ በኩል ጥቅም ያላቸው በመሆኑ በተለመደው ኢትዮጵያዊ ጨዋነት በፍፁም ትህትና ፣ አፍሪካዊ ወንድማማችነትና እህትማማችነት እንዲጎለብት በማድርግ እንግዶችን በመቀበል ፣ በማስተናገድ እና በተለያዩ የግብይት ስፍራዎችም ይህንኑ ክብር እንድትሰጡ እና ፍቅራችሁን እንድትገልፁላቸው በራሴ እና በከተማ አስተዳደሩ ስም ጥሪዬን አቀርባለሁ::

ፈጣሪ ኢትዮጵያን እና ህዝቦቿን ይባርክ!

ከንቲባ አዳነች አቤቤ
👍4
የአፍሪካ ከተሞች ፎረም በአዲስ አበባ መከናወን ጀምሯል::

ውይይቱ ዘላቂ የክትመት ምጣኔ ለአፍሪካ ትራንስፎርሜሽን በሚል መሪ ቃል የሚከናወን ሲሆን ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ፣ ከንቲባ አዳነች አቤቤ ፣ የፌዴራልና የከተማ አስተዳደሩ ከፍተኛ የስራ ሃላፊዎች፣ ከ30 በላይ የተለያዩ የአፍሪካ ከተሞች የመጡ ከንቲባዎች፣ ተመራማሪዎች እና ሌሎች ባለድርሻ አካላት ይሳተፉበታል::

በአፍሪካዊያን መዲና በሆነችው አዲስ አበባ በመከናወን ላይ በሚገኘው የአፍሪካ ከተሞች ፎረም ከመላው አለም የተውጣጡ እንግዶችም በመታደም ላይ ይገኛሉ::
👍4
በሠላም እሴት ግንባታ ዙሪያ ቅንጅታዊ አሰራሮችን በማሳደግ ብሎክን ማዕከል ያደረገና ኅብረተሰቡን ያሳተፈ ስራ መስራት እንደሚገባ ተገለፀ።

የኅብረተሰብ ተሳትፎና በጎ ፈቃድ ማስተባበሪያ ኮምሽን ከዘርፉ ባለሙያዎች ፣ ከክፍለ ከተማ እና ከወረዳ ቡድን መሪዎች ጋር በ2016 በጀት ዓመት የሰላም እሴት ተግባራት አፈፃፀም እና በ2017 ዓ.ም እቅድ ዙሪያ ውይይት አካሂዷል።

የኮሚሽኑ ምክትል ኮሚሽነር ወ/ሮ ፀሐይ ኪባሞ በመድረኩ ላይ ተገኝተው ወቅቱንና ጥራቱን የጠበቀ እቅድ ማዘጋጀት እንዲሁም የአፈፃፀም ደረጃን በየጊዜው መገምገም ውጤታማነትን እንደሚያረጋግጥ ጠቁመዋል።

በሰላም እሴት ግንባታ ላይ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በመቀናጀት ቀጣይነት ያለው ስራ መሥራት እንደሚገባ ያነሱት ወ/ሮ ፀሐይ ብሎክን ማዕከል ያደረገ የልማት ፣ የሰላምና የመልካም አስተዳደር ስራ ውጤታማ እንደሚሆን ጠቁመዋል። የኅብረተሰቡን የልማትና መልካም አስተዳደር ፍላጎቶች ብሎኮችን መሰረት በማድረግ በፍጥነት መልስ መስጠት እንደሚገባም ነው ምክትል ኮምሽነሯ የተናገሩት።

ህገ ወጥነትን ለመከላከል ከፀጥታ አካላት ጋር በመቀናጀት እንዲሁም ኅብረተሰቡን በማስተባበር በግንባር ቀደምትነት እንደሚሰሩ የመድረኩ ተሳታፊዎች ገልፀዋል።

በኅብረተሰብ ተሳትፎ የተሰሩ መሠረተ ልማቶች ጉዳት እንዳይደርስባቸው መጠበቅና አዋኪ ድርጊቶችን መከታተል ፣ መቆጣጠርና መከላከል እንደሚገባም ተጠቁሟል።


የማኀበራዊ ሚዲያ አማራጮቻችን፥
ፌስቡክ - https://www.facebook.com/cpvcc.2015
ቴሌግራም - https://t.me/CommunityPVC
ቲክቶክ - https://www.tiktok.com/@voluntarismaddis16
ዩቱዩብ - https://youtube.com/@communityparticipationvolu8714
👍2
የአዲስ አበባ ኮሪደር ልማት ለኢትዮጵያ ብቻ ሳይሆን ለአፍሪካ ከተሞች መነቃቃትን የፈጠረ፤ የህዝብ እና መንግሥት ትብብር ውጤት ነው:: - ከንቲባ አዳነች አቤቤ

አዲስ አበባን ከመሰረቱ ለማደስ እና በሁለንተናዊነት ለማልማት በተጀመረው ስራ ተጨባጭ የሆኑ ማህበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ ውጤቶች እየተመዘገቡ መሆናቸውን ከንቲባ አዳነች አቤቤ በአፍሪካ ከተሞች ፎረም መክፈቻ ላይ ተናግረዋል።

በአዲስ አበባ ከተማ የዓድዋ ድል መታሰቢያ ፓን-አፍሪካን አዳራሽ በዛሬ ዕለት በተጀመረው የመጀመሪያው የአፍሪካ ከተሞች ፎረም ላይ ንግግር ያደረጉት ከንቲባ አዳነች አቤቤ የአዲስ አበባ ኮሪደር ልማት ስኬት ለኢትዮጵያ ብቻ ሳይሆን ለአፍሪካ ከተሞች መነቃቃትን የፈጠረ የህዝብ እና መንግሥት ትብብር ውጤት ነው ብለዋል።

ያለ ከተማ ፕላን የተገነቡ ያረጁና ያፈጁ ሰፈሮችን ለአኗኗር ምቹ በሆነ ደረጃ እንደገና ማደስ፣ ለሰውና ለትራንስፖርት የማይመቹ መንገዶችን ደረጃቸውን ጠብቀው መገንባት፣ እንዲሁም ሁሉም የማህበረሰብ ክፍሎች ያለ ልዩነት የሚጠቀሙበትን የህዝብ መዝናኛዎችን በማስፋፋት ረገድ ውጤታማ ስራዎች መከናወናቸውንም ከንቲባዋ ጨምረው ገልፀዋል።

ለአብነት ያህል የሳይክል መንገዶችን እና መሮጫ ትራኮችን የመገንባት ስራ፣ የውሃ፣ የመብራትና የቴሌኮም አገልግሎቶችን እርስበርሳቸው መናበብ በሚያስችላለው ሁኔታ ተደራሽ የማድረግ ስራ የኮሪደር ልማቱ ትሩፋቶች ናቸው ብለዋል።

እነዚህ መደበኛ እና ኮሪደር ልማቶች የአዲስ አበባን ውበት፣ ተወዳዳሪነትና ምቹነት ከማሳደጋቸው በተጨማሪ የነዋሪዎቻችንን ፍትሐዊና እኩል ተጠቃሚነት እውን ማድረጋቸውን ያነሱት ከንቲባዋ በከተማው ውስጥ እየተሰሩ ያሉት ፕሮጀክቶች ለብዙ ሺ ዜጎቻችን የስራ ዕድል መፍጠራቸውን እና የንግድ ተቋማትን ማነቃቃታቸውንም ጨምረው ገልጸዋል።
👍2
"ኅብር ለሁለንተናዊ ሉዓላዊነት!" በሚል መሪ ቃል የ2016 የጳጉሜን ቀናት ከነገ ጀምሮ በተለያዩ መርሀ ግብሮች ይከበራሉ።

ሀገራችን ኢትዮጵያ ከሌሎች ሀገሮች ከምትለይባቸው ጉዳዮች መካከል አንዱ የዘመን አቆጣጠሯ ሲሆን የ"13 ወራት ፀጋ" ባለቤት መሆኗ ነው። 13ኛዋ ወር የዓመቱ ማጠናቀቂያና የአዲሱ ዓመት መቀበያ በመሆኗ ሁላችንም በከፍተኛ ጉጉትና ስሜት የምንጠብቃት ናት።

ለሀገራችን ኢትዮጵያና ለመላ ህዝባችን የመሻገር ጊዜን እንመኛለን!
👍4
"የመሻገር ጥሪቶች ፣ የአዲስ ብርሃብ ወረቶች!"

ዛሬ ጳጉሜን 1 "የመሻገር ቀን" ነው። በየተሰማራንበት መስክ ውጤት በማምጣት ፤ በግብርናው ዘርፍ ምርታማነትን በማሳደግ ፣ ኢንዱስትሪውን በማሻሻል ፣ አገልግሎቱን በማቀላጠፍ ፣ የውጭ ምንዛሬ የሚያስገኙ ተኪ ምርቶችን በማስፋት ፣ ቴክኖሎጂን በመጠቀም ፣ በፍጥነትና በአጭር ጊዜ ሌትም ቀንም ሰርተን ሀገራችን ኢትዮጵያን ወደ ብልፅግና እናሻግር።

ከተማችን አዲስ አበባ የጀመረችውን ሁሉአቀፍ ለውጥ በማስቀጠል ዓለም አቀፍ የዲፕሎማሲና የቱሪዝም ስበት ማዕከል ሆና እንድትዘልቅ ፣ ለነዋሪዎቿ ምቹ እንድትሆን ፣ ሁሉም የሚመርጣት ፣ ወደ ውብና ፅዱነቷን እናረጋግጥ!
👍41
ጳጉሜን 1 የመሻገር ቀን !

አዲስ ዓመት ያለቀውን ዓመት ሸኝቶ አዲሱን ከመጀመርም ባለፈ ከአስቸጋሪው ደመናማ የዝናብ ወቅት ወደ ብሩህ ተስማሚ ወራት መሻገርን የሚያበስር፣ በአዲስ አስተሳሰብና በብሩህ ተስፋ የምንቀበለው የአዲስ ምዕራፍ መባቻ ነው።

የተገባደደው ዓመት እንደ ሀገርም ሆነ እንደ ከተማ በበርካታ መስኮች የህዝባችንን ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ እድገት የማረጋገጥ ጉልህ ፋይዳ ያላቸው ዘርፈ ብዙ ውጤቶች ያስመዘገብንበት እንዲሁም ከድህነት ወደ አስተማማኝ የብልጽግና ምዕራፍ ለመሸጋገር የሚያስችለንን መሰረት የጣልንበት አንጸባራቂ የስኬትና የእድገት ዘመን እንደነበረ ግልጽ ነው።
ይህ ዛሬ የምናከበረው የመሻገር ቀንም፣ ባለፈው ዓመት ካለፍናቸው ትላልቅ ፈተናዎችና በድል ከተሻገርናቸው እንቅፋቶች ተገቢውን ትምህርት ወስደን በዚህ ሂደት ውስጥ አቅም በፈቀደ መጠን አስተዋጾ ያደረጉና ያገዙን አካላትንና መላው ህዝባችንን ከልብ የምናመሰግንበት፣ ብሎም የቀጣዩ ዓመት የርብርባችን ማዕከል የሆነውን ብልጽግናን የማረጋጋጥና ህዝባችንን ወደ ላቀ ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ እመርታ የማሻገር ራዕይ እውን ለማድረግ በጋራ ለመትጋት ቃል የምንገባበት እለት ነው።

በመሆኑም፣ ባሳለፍናቸው የለውጥ ዓመታት በአጭር ጌዜ ያስመዘገብናቸውን ተአምራዊ የልማት ስኬቶችን ተስፋ ሰጪነት አይቶ አስፈላጊ በሆኑ ጉዳዮች ላይ ሁሉ በመሳተፍ ሲያግዘንና ሲያበረታን የነበረው ህዝባችን ላሳየን አጋርነትና ትብብር ሁሉ ልባዊ ምስጋና እያቀረብን ቀጣዩ ዓመትም ካሳለፍነው ዓመት የተሻሉ ግዙፍ ድሎችን በማስመዝገብ ህዝባችንን ወደ ብልጽግና የምናሻግርበት እንደሚሆን በመተማመን ይህን ታላቅ አገራዊ ራዕይ ለማሳካት ህዝባችን አብሮን እንዲቆም ጥሪ እናስተላልፋለን።

መልካም አዲስ አመት!!!!

ከንቲባ አዳነች አቤቤ
👍5
#ጳጉሜን_2
የሪፎርም ቀን!

ለውጥ አይቀሬ ነገር ነው። የማይለወጥ የለም። የማይለወጠው ራሱ ለውጥ ብቻ ነው። ያለለውጥ ህይወት አይጣፍጥም። መኖር አያጓጓም። የሰው ልጅ ነገን ተስፋ አድርጎ በጉጉት የሚኖረው ለውጥን አጥብቆ ስለሚሻ ነው።

የዛሬዋ ቀን የለውጥ ቀን ነች። ራሳችንን ለውጠን በአገልግሎት አሰጣጣችን መለወጥ ያስፈልገናል። ህዝባችንን በስነ ምግባር በማስተናገድ ለውጥ ማምጣት አለብን። በተመደብንበት የስራ መስክ ራሳችንን ብቁ ማድረግ ፣ ተወዳዳሪ ሆኖ መገኘት ግድ ይለናል።

እያንዳንዳችን ካልተለወጥን ሀገራችንን በሁሉም ዘርፍ ወደምንናፍቀው ብልፅግና ማድረስ አንችልም። እንለወጥ!

"ሪፎርም ለላቀ አገልግሎት!"
👍2
ዛሬ የአዋሬ አካባቢን ለማሻሻል ላለን ትልም እና ጥረት አንድ ምዕራፍ ሆኗል። የተጎዳ እና የተጎሳቆለ የነበረው አካባቢ ዛሬ ለነዋሪዎች በተለይም ለአረጋውያን ምቹ እና ለሰው ልጅ የከበረ አኗኗር የሚመረጥ ሰፈር ሆኗል። ይህ ሥራ የማኅበረሰባችንን አኗኗር ለመለወጥ ላለን ጽኑ አላማ ማሳያ ነው።

አዋሬ ጥራትን ሳያጓድሉ በፍጥነት የመገንባት መርሃችንን ያንፀባርቃል። አሁን በአዋሬ ክብር ላለው የሰው ልጅ ኑሮ የተመቸ የልጆች መጫወቻ ስፍራ፣ ለማረፊያ እና ማሰቢያ የሚሆን አረንጓዴ ስፍራ፣ ለአረጋውያን የሚመች የእግረኛ መንገድ እንዲሁም ንፁህ ከባቢን ይዟል።

ይሁንና በአዋሬ ያሳካነው ገና ጅምር ሥራ ነው። በዚህ ሥራችን ረክተን መቆም የለብንም። ብዙ ሥራ ይቀረናል። የብዙ ሚሊዮኖች ሀገር እንደመሆናችን በመላው ሀገራችን የዜጎቻችንን ሕይወት ከፍ ማድረግ ፋታ የማይሰጥ ቀጣይነት ያለው ሥራችን ነው።

መሻሻልን ሳናቋርጥ ለመቀጠል እና ጅምር ሥራውን ለማስፋፋት ከግሉ ዘርፍ እና ከየከተሞች ጋር ያለንን ትብብር ማጠናከር ይኖርብናል። አዲሱን አመት ስንቀበል ብዙዎቹን ተግዳሮቶቻችንን ተሻገረን ለልጆቻችን ጠንካራ ኢትዮጵያን እንደምንገነባ እምነቴ ጽኑ ነው።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐብይ አሕመድ
👍5