የኀብረተሰብ ተሳትፎና በጎ ፈቃድ ማስተባበሪያ ኮሚሽን - አዲስ አበባ
815 subscribers
2.14K photos
47 videos
265 links
Download Telegram
ከነዋሪው ፣ ከለጋሾችና ከመንግስት የሚመደበውን የልማትና የድጋፍ በጀት በአግባቡ ማስተዳደርና ለታለመለት ዓላማ ማዋል እንደሚገባ ተገለፀ።

የኅብረተሰብ ተሳትፎና በጎ ፈቃድ ማስተባበሪያ ኮምሽን ከነዋሪው ኅብረተሰብ ፣ ከለጋሾችና ከመንግስት የሚመደበውን የድጋፍ በጀት ለማስተዳደር በተዘጋጀ የፋይናንስ መመሪያ ዙሪያ ለባለድርሻ አካላት ስልጠና ሰጥቷል።

ብሎክን ማዕከል ያደረገ የኅብረተሰብ ተሳትፎን ለማጎልበት በከተማ አስተዳደሩ የአካባቢ ልማት ፣ የሠላም እና የበጎ ፈቃድ አገልግሎት እቅዶች ነዋሪው ንቁ ተሳትፎ እንዲያደርግ ፤ ፍትሐዊ ተጠቃሚ እንዲሆንና የነዋሪውን መሥተጋብርና ትስስር በማጠናከር ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ችግሮችን በራስ አቅም ለመፍታት የፋይናን መመሪያ እንደሚያግዝ ተጠቁሟል።

የአስራር ግልፀኝነት መፈጠሩ መሬት ላይ ህጋዊ አሰራሩን የጠበቀ ስራ ለመሥራት እንደሚያግዝ የገለፁት ሰልጣኞች ለተፈፃሚነቱም በቁርጠኝነት እንደምሰሩ ተናግረዋል።

የማኀበራዊ ሚዲያ አማራጮቻችን፥
ፌስቡክ - https://www.facebook.com/cpvcc.2015
ቴሌግራም - https://t.me/CommunityPVC
ቲክቶክ - https://www.tiktok.com/@voluntarismaddis16
ዩቱዩብ - https://youtube.com/@communityparticipationvolu8714
ዌብሳይት - www.volunteeraddis.et
Instagram - https://www.instagram.com/communitypv/
Twitter - https://x.com/Volunteeraddis
👍1
የኅብረተሰቡ የአካባቢ ጥበቃ ተሳትፎ እየተጠናከረ መምጣቱ ተገለፀ።

የኅብረተሰብ ተሳትፎና በጎ ፈቃድ ማስተባበሪያ ኮምሽን በአዋጅ ከተሰጡት ኃላፊነቶች መካከል ኅብረተሰቡ በብሎክ አደረጃጀት ውስጥ በአካባቢ ሰላም ስራዎች እንዲሳተፍ ምቹ ሁኔታን መፍጠር ይገኝበታል።

የኅብረተሰቡ የአካባቢ ጥበቃ ተሳትፎ የቅጥር ጥበቃን ከማጠናከር ጀምሮ የፀጥታ ስጋቶችን አስቀድሞ መከላከል ፣ በመሰረተ ልማቶች ላይ የሚደርሱ ጉዳቶችን መቆጣጠር ፣ አካባቢን በሽፍት መጠበቅና ሌሎች ጉዳዮችን ያካትታል።

ኮሚሽኑ የኅብረተሰቡን የሠላም ተሳትፎ ለማሳደግም የኅብረተሰብ የአካባቢ ጥበቃ ተሳትፎ መመሪያ ቁጥር 148/2016 አዘጋጅቶ ስራ ላይ አውሏል።

መመሪያው በርካታ የመልካም አስተዳደር ችግሮችን መፍታቱንና ለሥራቸውም ምቹ ሁኔታ እንደፈጠረላቸው በአራዳ ክፍለ ከተማ ወረዳ 1 በምሽት የአካባቢ ሠላም ስራ ላይ የተሰማሩ የቅጥር ጥበቃ አባላት ገልፀዋል።

የኮሚሽኑ የደንብ መተላለፍ ቅድመ መከላከል ህዝባዊ ተሳትፎ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ገዛኸኝ ኃይሉ አዲሱን መመሪያ መሰረት በማድረግ በብሎኮች የኅብረተሰብ ጥበቃ አባላት በብዛት እየተሳተፉ መሆኑን ገልፀዋል።

የማኀበራዊ ሚዲያ አማራጮቻችን፥
ፌስቡክ - https://www.facebook.com/cpvcc.2015
ቴሌግራም - https://t.me/CommunityPVC
ቲክቶክ - https://www.tiktok.com/@voluntarismaddis16
ዩቱዩብ - https://youtube.com/@communityparticipationvolu8714
ዌብሳይት - www.volunteeraddis.et
Instagram - https://www.instagram.com/communitypv/
Twitter - https://x.com/Volunteeraddis
👍1
ለመጪው አዲስ ዓመት አብሮነትን ይበልጥ ማጠናከር የሚያስችሉ ማህበራዊና ሰብዓዊ ሥራዎች እየተከናወኑ ነው።

በአዲስ አበባ ከተማ አዲሱን ዓመት ምክንያት በማድረግ አቅመ ደካሞችን ፣ በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ የሚገኙ ነዋሪዎችንና አረጋውያንን ተጠቃሚ የሚያደርጉና አብሮነትን ይበልጥ የሚያጠናክሩ ማህበራዊና ሰብዓዊ ተግባራት እየተከናወኑ ይገኛሉ።

የአስተዳደሩ የኅብረተሰብ ተሳትፎና በጎ ፈቃድ ማስተባበሪያ ኮሚሽን እነዚህ ሰው ተኮር ተግባራት የደረሱበትን የአፈፃጸም ደረጃ ከክፍለ ከተማ የዘርፍ ኃላፊዎችና ከማዕከል አመራሮች ጋር በመገምገም ቀሪ ስራዎች በልዩ ትኩረት እንዲመሩ አቅጣጫ አስቀምጧል።

በጳጉሜን ቀናት የሚከናወኑ ሰብዓዊና ማኅበራዊ ተግባራት በየደረጃው አሰራሩን ጠብቀው እየተመሩ መሆኑ በጥንካሬ የተገመገመ ሲሆን የተቸገሩ ወገኖቻችን በዓሉን በደስታና በአብሮነት እንዲያከብሩ ሁሉም አካላት ማኅበራዊ ኃላፊነታቸውን በመወጣት የበኩላቸውን አስተዋፅዖ እንዲያደርጉ በመድረኩ ተጠይቋል።

"በጎ ፈቃደኝነት ፤ ለማኅበረሰብ ለውጥ!"
የማኀበራዊ ሚዲያ አማራጮቻችን፥
ፌስቡክ - https://www.facebook.com/cpvcc.2015
ቴሌግራም - https://t.me/CommunityPVC
ቲክቶክ - https://www.tiktok.com/@voluntarismaddis16
ዩቱዩብ - https://youtube.com/@communityparticipationvolu8714
ዌብሳይት - www.volunteeraddis.et
Instagram - https://www.instagram.com/communitypv/
Twitter - https://x.com/Volunteeraddis
👍2
በከተማችን አዲስ አበባ የመጀመሪያው የአፍሪካ ከተሞች ፎረም ከነገ ጀምሮ በዓድዋ ድል መታሰቢያ የሚካሄድ በመሆኑ ደስታችን የላቀ ነው ።

የመጀመሪያውን የአፍሪካ ከተሞች ፎረም በማዘጋጀት ከአፍሪካ ወንድሞችና እህቶቻችን ጋር ከተሞቻችንን በማዘመን፣ ለነዋሪዎች ምቹ የለውጥና የብልፅግና ማዕከል እንዲሆኑ ማድረግ እና እጅ ለእጅ ተያይዘን መስራት በምንችልባቸው መንገዶች ዙሪያ የምንመክርበት ወሳኝ መድረክ ሲሆን ለፎረሙ ስኬታማነት በርካታ ዝግጅቶችን አድርገናል::

ውድ የከተማችን ነዋሪዎች ይህን እድል ማግኘታችን ትልቅ ትርጉም አለው ፤ ተባብረን በጋራ ሰርተን ከተማችንን ለዚህ አይነት ፎረም፣ ኮንቬንሽንና የስበት ማዕከል ማድረግን አጠናክረን ይበልጥ መስራት ይኖርብናል::

እንዲህ ያሉ ሁነቶች ለከተማችን በቱሪዝም ተጨማሪ ገቢ በማስገኘትና በማስተዋወቅ በኩል ጥቅም ያላቸው በመሆኑ በተለመደው ኢትዮጵያዊ ጨዋነት በፍፁም ትህትና ፣ አፍሪካዊ ወንድማማችነትና እህትማማችነት እንዲጎለብት በማድርግ እንግዶችን በመቀበል ፣ በማስተናገድ እና በተለያዩ የግብይት ስፍራዎችም ይህንኑ ክብር እንድትሰጡ እና ፍቅራችሁን እንድትገልፁላቸው በራሴ እና በከተማ አስተዳደሩ ስም ጥሪዬን አቀርባለሁ::

ፈጣሪ ኢትዮጵያን እና ህዝቦቿን ይባርክ!

ከንቲባ አዳነች አቤቤ
👍4
የአፍሪካ ከተሞች ፎረም በአዲስ አበባ መከናወን ጀምሯል::

ውይይቱ ዘላቂ የክትመት ምጣኔ ለአፍሪካ ትራንስፎርሜሽን በሚል መሪ ቃል የሚከናወን ሲሆን ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ፣ ከንቲባ አዳነች አቤቤ ፣ የፌዴራልና የከተማ አስተዳደሩ ከፍተኛ የስራ ሃላፊዎች፣ ከ30 በላይ የተለያዩ የአፍሪካ ከተሞች የመጡ ከንቲባዎች፣ ተመራማሪዎች እና ሌሎች ባለድርሻ አካላት ይሳተፉበታል::

በአፍሪካዊያን መዲና በሆነችው አዲስ አበባ በመከናወን ላይ በሚገኘው የአፍሪካ ከተሞች ፎረም ከመላው አለም የተውጣጡ እንግዶችም በመታደም ላይ ይገኛሉ::
👍4
በሠላም እሴት ግንባታ ዙሪያ ቅንጅታዊ አሰራሮችን በማሳደግ ብሎክን ማዕከል ያደረገና ኅብረተሰቡን ያሳተፈ ስራ መስራት እንደሚገባ ተገለፀ።

የኅብረተሰብ ተሳትፎና በጎ ፈቃድ ማስተባበሪያ ኮምሽን ከዘርፉ ባለሙያዎች ፣ ከክፍለ ከተማ እና ከወረዳ ቡድን መሪዎች ጋር በ2016 በጀት ዓመት የሰላም እሴት ተግባራት አፈፃፀም እና በ2017 ዓ.ም እቅድ ዙሪያ ውይይት አካሂዷል።

የኮሚሽኑ ምክትል ኮሚሽነር ወ/ሮ ፀሐይ ኪባሞ በመድረኩ ላይ ተገኝተው ወቅቱንና ጥራቱን የጠበቀ እቅድ ማዘጋጀት እንዲሁም የአፈፃፀም ደረጃን በየጊዜው መገምገም ውጤታማነትን እንደሚያረጋግጥ ጠቁመዋል።

በሰላም እሴት ግንባታ ላይ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በመቀናጀት ቀጣይነት ያለው ስራ መሥራት እንደሚገባ ያነሱት ወ/ሮ ፀሐይ ብሎክን ማዕከል ያደረገ የልማት ፣ የሰላምና የመልካም አስተዳደር ስራ ውጤታማ እንደሚሆን ጠቁመዋል። የኅብረተሰቡን የልማትና መልካም አስተዳደር ፍላጎቶች ብሎኮችን መሰረት በማድረግ በፍጥነት መልስ መስጠት እንደሚገባም ነው ምክትል ኮምሽነሯ የተናገሩት።

ህገ ወጥነትን ለመከላከል ከፀጥታ አካላት ጋር በመቀናጀት እንዲሁም ኅብረተሰቡን በማስተባበር በግንባር ቀደምትነት እንደሚሰሩ የመድረኩ ተሳታፊዎች ገልፀዋል።

በኅብረተሰብ ተሳትፎ የተሰሩ መሠረተ ልማቶች ጉዳት እንዳይደርስባቸው መጠበቅና አዋኪ ድርጊቶችን መከታተል ፣ መቆጣጠርና መከላከል እንደሚገባም ተጠቁሟል።


የማኀበራዊ ሚዲያ አማራጮቻችን፥
ፌስቡክ - https://www.facebook.com/cpvcc.2015
ቴሌግራም - https://t.me/CommunityPVC
ቲክቶክ - https://www.tiktok.com/@voluntarismaddis16
ዩቱዩብ - https://youtube.com/@communityparticipationvolu8714
👍2
የአዲስ አበባ ኮሪደር ልማት ለኢትዮጵያ ብቻ ሳይሆን ለአፍሪካ ከተሞች መነቃቃትን የፈጠረ፤ የህዝብ እና መንግሥት ትብብር ውጤት ነው:: - ከንቲባ አዳነች አቤቤ

አዲስ አበባን ከመሰረቱ ለማደስ እና በሁለንተናዊነት ለማልማት በተጀመረው ስራ ተጨባጭ የሆኑ ማህበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ ውጤቶች እየተመዘገቡ መሆናቸውን ከንቲባ አዳነች አቤቤ በአፍሪካ ከተሞች ፎረም መክፈቻ ላይ ተናግረዋል።

በአዲስ አበባ ከተማ የዓድዋ ድል መታሰቢያ ፓን-አፍሪካን አዳራሽ በዛሬ ዕለት በተጀመረው የመጀመሪያው የአፍሪካ ከተሞች ፎረም ላይ ንግግር ያደረጉት ከንቲባ አዳነች አቤቤ የአዲስ አበባ ኮሪደር ልማት ስኬት ለኢትዮጵያ ብቻ ሳይሆን ለአፍሪካ ከተሞች መነቃቃትን የፈጠረ የህዝብ እና መንግሥት ትብብር ውጤት ነው ብለዋል።

ያለ ከተማ ፕላን የተገነቡ ያረጁና ያፈጁ ሰፈሮችን ለአኗኗር ምቹ በሆነ ደረጃ እንደገና ማደስ፣ ለሰውና ለትራንስፖርት የማይመቹ መንገዶችን ደረጃቸውን ጠብቀው መገንባት፣ እንዲሁም ሁሉም የማህበረሰብ ክፍሎች ያለ ልዩነት የሚጠቀሙበትን የህዝብ መዝናኛዎችን በማስፋፋት ረገድ ውጤታማ ስራዎች መከናወናቸውንም ከንቲባዋ ጨምረው ገልፀዋል።

ለአብነት ያህል የሳይክል መንገዶችን እና መሮጫ ትራኮችን የመገንባት ስራ፣ የውሃ፣ የመብራትና የቴሌኮም አገልግሎቶችን እርስበርሳቸው መናበብ በሚያስችላለው ሁኔታ ተደራሽ የማድረግ ስራ የኮሪደር ልማቱ ትሩፋቶች ናቸው ብለዋል።

እነዚህ መደበኛ እና ኮሪደር ልማቶች የአዲስ አበባን ውበት፣ ተወዳዳሪነትና ምቹነት ከማሳደጋቸው በተጨማሪ የነዋሪዎቻችንን ፍትሐዊና እኩል ተጠቃሚነት እውን ማድረጋቸውን ያነሱት ከንቲባዋ በከተማው ውስጥ እየተሰሩ ያሉት ፕሮጀክቶች ለብዙ ሺ ዜጎቻችን የስራ ዕድል መፍጠራቸውን እና የንግድ ተቋማትን ማነቃቃታቸውንም ጨምረው ገልጸዋል።
👍2
"ኅብር ለሁለንተናዊ ሉዓላዊነት!" በሚል መሪ ቃል የ2016 የጳጉሜን ቀናት ከነገ ጀምሮ በተለያዩ መርሀ ግብሮች ይከበራሉ።

ሀገራችን ኢትዮጵያ ከሌሎች ሀገሮች ከምትለይባቸው ጉዳዮች መካከል አንዱ የዘመን አቆጣጠሯ ሲሆን የ"13 ወራት ፀጋ" ባለቤት መሆኗ ነው። 13ኛዋ ወር የዓመቱ ማጠናቀቂያና የአዲሱ ዓመት መቀበያ በመሆኗ ሁላችንም በከፍተኛ ጉጉትና ስሜት የምንጠብቃት ናት።

ለሀገራችን ኢትዮጵያና ለመላ ህዝባችን የመሻገር ጊዜን እንመኛለን!
👍4