የኀብረተሰብ ተሳትፎና በጎ ፈቃድ ማስተባበሪያ ኮሚሽን - አዲስ አበባ
814 subscribers
2.14K photos
47 videos
265 links
Download Telegram
የኀብረተሰብ ተሳትፎና በጎ ፈቃድ ማስተባበሪያ ኮሚሽን - አዲስ አበባ
Photo
በአዲስ አበባ በዘንድሮው የክረምት የበጎ ፈቃድ አገልግሎት እስካሁን ከ3 ነጥብ 6 ቢሊየን ብር በላይ የሚገመት አገልግሎት ተሰጥቷል።

በዘንድሮው የክረምት የበጎ ፈቃድ አገልግሎት እስካሁን ከ3 ነጥብ 6 ቢሊየን ብር በላይ የሚገመት አገልግሎት ለኅብረተሰቡ መሰጠቱን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የኅብረተሰብ ተሳትፎና በጎ ፈቃድ ማስተባበሪያ ኮሚሽን ገለጸ።

የኮሚሽኑ ምክትል ኮሚሽነር ደረጄ ካሳ እንደገለጹት በመዲናዋ በርካታ በጎ ፈቃደኞች በተለያዩ የበጎ ፈቃድ አገልግሎት ተግባራት ላይ እየተሳተፉ ነው።

የአቅመ ደካማና አረጋውያን ቤት እድሳት ፣ የክረምት የማጠናከሪያ ትምህርት ፣ ደም ልገሳና የትራፊክ አደጋን መከላከል ከሚሰጡ የበጎ ፈቃድ አገልግሎት ውስጥ ተጠቃሽ መሆናቸውን ጠቁመዋል።

ይህንንም ተከትሎ በአዲስ አበባ በክረምት የበጎ ፈቃድ አገልግሎት መርኃ-ግብር ብቻ እስካሁን ከ3 ነጥብ 6 ቢሊየን ብር በላይ የሚገመት አገልግሎት ለኅብረተሰቡ መስጠት መቻሉን ተናግረዋል።

በበጎ ፈቃደኞች ከተከናወኑ ዋና ዋና ተግባራት መካከል ማዕድ በማጋራትና ለአቅመ ደካሞች ቤት እድሳትና ግንባታ ዘርፍ ስኬታማ ሥራ ተሰርቷል ብለዋል።

ለአብነትም በተጠናቀቀው በጀት ዓመት 6 ሺህ 500 ለመገንባት ታቅዶ ወደ 6 ሺህ 730 ቤቶችን በመገንባት ለተጠቃሚዎች ማስተላለፍ መቻሉን ነው ያስረዱት።

በዘንድሮ የክረምት ወቅት የበጎ ፈቃድ አገልግሎትም 3ሺ 500 ቤት ለመገንባት እቅድ ተይዞ እስካሁን ባለው ሁኔታ ወደ 2 ሺህ 100 ቤቶችን ገንብተናል ነው ያሉት።

በተመሳሳይ በክረምት በጎ ፈቃድ ማጠናከሪያ ትምህርት እንዲሁም በጎነት በሆስፒታል በሚባሉ መርኃ- ግብሮች በርካታ በጎ ፈቃደኞች እየተሳተፉ መሆኑንም አብራርተዋል።

የመዲናዋ ነዋሪዎች፣ ወጣቶች፣ ባለኃብቶች፣ መንግሥታዊና መንግሥታዊ ያልሆኑ ተቋማት በበጎ ፈቃድ አገልግሎት ላይ የሚያደርጉት ተሳትፎ እያደገ መምጣቱን ተናግረዋል።

የበጎ ፈቃድ አገልግሎቶች በማኅበራዊና ኢኮኖሚያዊ ዕድገት ውስጥ አካታችነትን ለማረጋገጥ ሚናው የላቀ በመሆኑ ሁሉም የበኩሉን አስተዋጽዖ እንዲያደርግ ጥሪ አቅርበዋል።
👍2
ከነዋሪው ፣ ከለጋሾችና ከመንግስት የሚመደበውን የልማትና የድጋፍ በጀት በአግባቡ ማስተዳደርና ለታለመለት ዓላማ ማዋል እንደሚገባ ተገለፀ።

የኅብረተሰብ ተሳትፎና በጎ ፈቃድ ማስተባበሪያ ኮምሽን ከነዋሪው ኅብረተሰብ ፣ ከለጋሾችና ከመንግስት የሚመደበውን የድጋፍ በጀት ለማስተዳደር በተዘጋጀ የፋይናንስ መመሪያ ዙሪያ ለባለድርሻ አካላት ስልጠና ሰጥቷል።

ብሎክን ማዕከል ያደረገ የኅብረተሰብ ተሳትፎን ለማጎልበት በከተማ አስተዳደሩ የአካባቢ ልማት ፣ የሠላም እና የበጎ ፈቃድ አገልግሎት እቅዶች ነዋሪው ንቁ ተሳትፎ እንዲያደርግ ፤ ፍትሐዊ ተጠቃሚ እንዲሆንና የነዋሪውን መሥተጋብርና ትስስር በማጠናከር ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ችግሮችን በራስ አቅም ለመፍታት የፋይናን መመሪያ እንደሚያግዝ ተጠቁሟል።

የአስራር ግልፀኝነት መፈጠሩ መሬት ላይ ህጋዊ አሰራሩን የጠበቀ ስራ ለመሥራት እንደሚያግዝ የገለፁት ሰልጣኞች ለተፈፃሚነቱም በቁርጠኝነት እንደምሰሩ ተናግረዋል።

የማኀበራዊ ሚዲያ አማራጮቻችን፥
ፌስቡክ - https://www.facebook.com/cpvcc.2015
ቴሌግራም - https://t.me/CommunityPVC
ቲክቶክ - https://www.tiktok.com/@voluntarismaddis16
ዩቱዩብ - https://youtube.com/@communityparticipationvolu8714
ዌብሳይት - www.volunteeraddis.et
Instagram - https://www.instagram.com/communitypv/
Twitter - https://x.com/Volunteeraddis
👍1
የኅብረተሰቡ የአካባቢ ጥበቃ ተሳትፎ እየተጠናከረ መምጣቱ ተገለፀ።

የኅብረተሰብ ተሳትፎና በጎ ፈቃድ ማስተባበሪያ ኮምሽን በአዋጅ ከተሰጡት ኃላፊነቶች መካከል ኅብረተሰቡ በብሎክ አደረጃጀት ውስጥ በአካባቢ ሰላም ስራዎች እንዲሳተፍ ምቹ ሁኔታን መፍጠር ይገኝበታል።

የኅብረተሰቡ የአካባቢ ጥበቃ ተሳትፎ የቅጥር ጥበቃን ከማጠናከር ጀምሮ የፀጥታ ስጋቶችን አስቀድሞ መከላከል ፣ በመሰረተ ልማቶች ላይ የሚደርሱ ጉዳቶችን መቆጣጠር ፣ አካባቢን በሽፍት መጠበቅና ሌሎች ጉዳዮችን ያካትታል።

ኮሚሽኑ የኅብረተሰቡን የሠላም ተሳትፎ ለማሳደግም የኅብረተሰብ የአካባቢ ጥበቃ ተሳትፎ መመሪያ ቁጥር 148/2016 አዘጋጅቶ ስራ ላይ አውሏል።

መመሪያው በርካታ የመልካም አስተዳደር ችግሮችን መፍታቱንና ለሥራቸውም ምቹ ሁኔታ እንደፈጠረላቸው በአራዳ ክፍለ ከተማ ወረዳ 1 በምሽት የአካባቢ ሠላም ስራ ላይ የተሰማሩ የቅጥር ጥበቃ አባላት ገልፀዋል።

የኮሚሽኑ የደንብ መተላለፍ ቅድመ መከላከል ህዝባዊ ተሳትፎ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ገዛኸኝ ኃይሉ አዲሱን መመሪያ መሰረት በማድረግ በብሎኮች የኅብረተሰብ ጥበቃ አባላት በብዛት እየተሳተፉ መሆኑን ገልፀዋል።

የማኀበራዊ ሚዲያ አማራጮቻችን፥
ፌስቡክ - https://www.facebook.com/cpvcc.2015
ቴሌግራም - https://t.me/CommunityPVC
ቲክቶክ - https://www.tiktok.com/@voluntarismaddis16
ዩቱዩብ - https://youtube.com/@communityparticipationvolu8714
ዌብሳይት - www.volunteeraddis.et
Instagram - https://www.instagram.com/communitypv/
Twitter - https://x.com/Volunteeraddis
👍1
ለመጪው አዲስ ዓመት አብሮነትን ይበልጥ ማጠናከር የሚያስችሉ ማህበራዊና ሰብዓዊ ሥራዎች እየተከናወኑ ነው።

በአዲስ አበባ ከተማ አዲሱን ዓመት ምክንያት በማድረግ አቅመ ደካሞችን ፣ በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ የሚገኙ ነዋሪዎችንና አረጋውያንን ተጠቃሚ የሚያደርጉና አብሮነትን ይበልጥ የሚያጠናክሩ ማህበራዊና ሰብዓዊ ተግባራት እየተከናወኑ ይገኛሉ።

የአስተዳደሩ የኅብረተሰብ ተሳትፎና በጎ ፈቃድ ማስተባበሪያ ኮሚሽን እነዚህ ሰው ተኮር ተግባራት የደረሱበትን የአፈፃጸም ደረጃ ከክፍለ ከተማ የዘርፍ ኃላፊዎችና ከማዕከል አመራሮች ጋር በመገምገም ቀሪ ስራዎች በልዩ ትኩረት እንዲመሩ አቅጣጫ አስቀምጧል።

በጳጉሜን ቀናት የሚከናወኑ ሰብዓዊና ማኅበራዊ ተግባራት በየደረጃው አሰራሩን ጠብቀው እየተመሩ መሆኑ በጥንካሬ የተገመገመ ሲሆን የተቸገሩ ወገኖቻችን በዓሉን በደስታና በአብሮነት እንዲያከብሩ ሁሉም አካላት ማኅበራዊ ኃላፊነታቸውን በመወጣት የበኩላቸውን አስተዋፅዖ እንዲያደርጉ በመድረኩ ተጠይቋል።

"በጎ ፈቃደኝነት ፤ ለማኅበረሰብ ለውጥ!"
የማኀበራዊ ሚዲያ አማራጮቻችን፥
ፌስቡክ - https://www.facebook.com/cpvcc.2015
ቴሌግራም - https://t.me/CommunityPVC
ቲክቶክ - https://www.tiktok.com/@voluntarismaddis16
ዩቱዩብ - https://youtube.com/@communityparticipationvolu8714
ዌብሳይት - www.volunteeraddis.et
Instagram - https://www.instagram.com/communitypv/
Twitter - https://x.com/Volunteeraddis
👍2
በከተማችን አዲስ አበባ የመጀመሪያው የአፍሪካ ከተሞች ፎረም ከነገ ጀምሮ በዓድዋ ድል መታሰቢያ የሚካሄድ በመሆኑ ደስታችን የላቀ ነው ።

የመጀመሪያውን የአፍሪካ ከተሞች ፎረም በማዘጋጀት ከአፍሪካ ወንድሞችና እህቶቻችን ጋር ከተሞቻችንን በማዘመን፣ ለነዋሪዎች ምቹ የለውጥና የብልፅግና ማዕከል እንዲሆኑ ማድረግ እና እጅ ለእጅ ተያይዘን መስራት በምንችልባቸው መንገዶች ዙሪያ የምንመክርበት ወሳኝ መድረክ ሲሆን ለፎረሙ ስኬታማነት በርካታ ዝግጅቶችን አድርገናል::

ውድ የከተማችን ነዋሪዎች ይህን እድል ማግኘታችን ትልቅ ትርጉም አለው ፤ ተባብረን በጋራ ሰርተን ከተማችንን ለዚህ አይነት ፎረም፣ ኮንቬንሽንና የስበት ማዕከል ማድረግን አጠናክረን ይበልጥ መስራት ይኖርብናል::

እንዲህ ያሉ ሁነቶች ለከተማችን በቱሪዝም ተጨማሪ ገቢ በማስገኘትና በማስተዋወቅ በኩል ጥቅም ያላቸው በመሆኑ በተለመደው ኢትዮጵያዊ ጨዋነት በፍፁም ትህትና ፣ አፍሪካዊ ወንድማማችነትና እህትማማችነት እንዲጎለብት በማድርግ እንግዶችን በመቀበል ፣ በማስተናገድ እና በተለያዩ የግብይት ስፍራዎችም ይህንኑ ክብር እንድትሰጡ እና ፍቅራችሁን እንድትገልፁላቸው በራሴ እና በከተማ አስተዳደሩ ስም ጥሪዬን አቀርባለሁ::

ፈጣሪ ኢትዮጵያን እና ህዝቦቿን ይባርክ!

ከንቲባ አዳነች አቤቤ
👍4
የአፍሪካ ከተሞች ፎረም በአዲስ አበባ መከናወን ጀምሯል::

ውይይቱ ዘላቂ የክትመት ምጣኔ ለአፍሪካ ትራንስፎርሜሽን በሚል መሪ ቃል የሚከናወን ሲሆን ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ፣ ከንቲባ አዳነች አቤቤ ፣ የፌዴራልና የከተማ አስተዳደሩ ከፍተኛ የስራ ሃላፊዎች፣ ከ30 በላይ የተለያዩ የአፍሪካ ከተሞች የመጡ ከንቲባዎች፣ ተመራማሪዎች እና ሌሎች ባለድርሻ አካላት ይሳተፉበታል::

በአፍሪካዊያን መዲና በሆነችው አዲስ አበባ በመከናወን ላይ በሚገኘው የአፍሪካ ከተሞች ፎረም ከመላው አለም የተውጣጡ እንግዶችም በመታደም ላይ ይገኛሉ::
👍4
በሠላም እሴት ግንባታ ዙሪያ ቅንጅታዊ አሰራሮችን በማሳደግ ብሎክን ማዕከል ያደረገና ኅብረተሰቡን ያሳተፈ ስራ መስራት እንደሚገባ ተገለፀ።

የኅብረተሰብ ተሳትፎና በጎ ፈቃድ ማስተባበሪያ ኮምሽን ከዘርፉ ባለሙያዎች ፣ ከክፍለ ከተማ እና ከወረዳ ቡድን መሪዎች ጋር በ2016 በጀት ዓመት የሰላም እሴት ተግባራት አፈፃፀም እና በ2017 ዓ.ም እቅድ ዙሪያ ውይይት አካሂዷል።

የኮሚሽኑ ምክትል ኮሚሽነር ወ/ሮ ፀሐይ ኪባሞ በመድረኩ ላይ ተገኝተው ወቅቱንና ጥራቱን የጠበቀ እቅድ ማዘጋጀት እንዲሁም የአፈፃፀም ደረጃን በየጊዜው መገምገም ውጤታማነትን እንደሚያረጋግጥ ጠቁመዋል።

በሰላም እሴት ግንባታ ላይ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በመቀናጀት ቀጣይነት ያለው ስራ መሥራት እንደሚገባ ያነሱት ወ/ሮ ፀሐይ ብሎክን ማዕከል ያደረገ የልማት ፣ የሰላምና የመልካም አስተዳደር ስራ ውጤታማ እንደሚሆን ጠቁመዋል። የኅብረተሰቡን የልማትና መልካም አስተዳደር ፍላጎቶች ብሎኮችን መሰረት በማድረግ በፍጥነት መልስ መስጠት እንደሚገባም ነው ምክትል ኮምሽነሯ የተናገሩት።

ህገ ወጥነትን ለመከላከል ከፀጥታ አካላት ጋር በመቀናጀት እንዲሁም ኅብረተሰቡን በማስተባበር በግንባር ቀደምትነት እንደሚሰሩ የመድረኩ ተሳታፊዎች ገልፀዋል።

በኅብረተሰብ ተሳትፎ የተሰሩ መሠረተ ልማቶች ጉዳት እንዳይደርስባቸው መጠበቅና አዋኪ ድርጊቶችን መከታተል ፣ መቆጣጠርና መከላከል እንደሚገባም ተጠቁሟል።


የማኀበራዊ ሚዲያ አማራጮቻችን፥
ፌስቡክ - https://www.facebook.com/cpvcc.2015
ቴሌግራም - https://t.me/CommunityPVC
ቲክቶክ - https://www.tiktok.com/@voluntarismaddis16
ዩቱዩብ - https://youtube.com/@communityparticipationvolu8714
👍2