የኀብረተሰብ ተሳትፎና በጎ ፈቃድ ማስተባበሪያ ኮሚሽን - አዲስ አበባ
814 subscribers
2.14K photos
47 videos
265 links
Download Telegram
የኮልፌ ቀራኒዮ ክፍለ ከተማ ከ52 ሚሊየን ብር በላይ ወጪ የተደረገባቸው የአካባቢ ልማት ስራዎችን አስመረቀ።

በክፍለ ከተማው ሁሉም ወረዳዎች ከ52 ሚሊየን ብር በላይ ወጪ የተደረገባቸው 25 የሚደርሱ በህብረተሰቡ ተሳትፎ የተገነቡ የተለያዩ የልማት ፕሮጀክቶች ተመርቀው ዛሬ ለአገልግሎት ክፍት ተደርገዋል፡፡

ከተሰሩ የልማት ስራዎች መካከል የሰብ ቤዝ ንጣፍ ፣ የኮብል ስቶን ንጣፍ እና ጥገና ፣ አነስተኛ ድልድይ ግንባታ ፣ የኮሙኒቲ ፖሊስ ሴንተር ፣ ካልቨርቶችና ዲቾች ፣ የቴራዞ ንጣፎች ፣ የመማሪያ ክፍሎች በአጠቃላይ 25 አይነት የልማት ስራዎች እንደሚገኙበት የክፍለ ከተማው ኮሙኒኬሽን ፅህፈት ቤት ያደረሰን መረጃ ያመለክታል፡፡

የማኀበራዊ ሚዲያ አማራጮቻችን፥
ፌስቡክ - https://www.facebook.com/cpvcc.2015
ቴሌግራም - https://t.me/CommunityPVC
ቲክቶክ - https://www.tiktok.com/@voluntarismaddis16
ዩቱዩብ - https://youtube.com/@communityparticipationvolu8714
ዌብሳይት - www.volunteeraddis.et
Instagram - https://www.instagram.com/communitypv/
Twitter - https://x.com/Volunteeraddis
👍2
ኮሚሽኑ በቢሾፍቱ ከተማ ለማራናታ የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርት ቤት ተማሪዎች 350 ደርዘን ደብተር ድጋፍ አደረገ።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የኅብረተሰብ ተሳትፎና በጎ ፈቃድ ማስተባበሪያ ኮሚሽን በወሰን የለሽ የበጎ ፈቃድ ፕሮግራም በቢሾፍቱ ከተማ ለማራናታ የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርት ቤት ተማሪዎች 350 ደርዘን ደብተር ድጋፍ አድርጓል።

የትምህርት ቁሳቁስ ድጋፉ በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ለሚገኙ የተማሪ ወላጆች እፎይታ የሚሰጥና ለተማሪዎች ውጤታማነት ከፍተኛ አስተዋፅዖ የሚያበረክት መሆኑ የተገለፀ ሲሆን ኮሚሽኑ መሰል የበጎ ፈቃድ አገልግሎቶችን በከተማዋ ሲሰጥ ይህ ለ3ኛ ጊዜ ነው።

ከዚህ በፊት ለቶኩማ የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርት ቤት እና ለቢፍቱ የመጀመሪያ ትምህርት ቤቶች የትምህርት ቁሳቁስ ድጋፎችን ጨምሮ በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ለሚገኙ የተማሪ ወላጆች የማዕድ ድጋፍ አድርጓል።

የፕሮግራሙ ዓላማ ከሚሰጠው ድጋፍ ባሻገር የአዲስ አበባን የበጎ ፈቃድ ተሞክሮ ለሌሎች ከተሞች ማስፋት እንደሆነ በኮሚሽኑ የበጎ ፈቃድ ዘርፍ ምክትል ኮሚሽነር አቶ ደረጀ ካሳ ገልፀዋል።

የትምህርት ቤቱ ተማሪዎችና አመራሮች በበኩላቸው ለተደረገላቸው ድጋፍ ለመማር ማስተማር ስራው ከፍተኛ አስተዋፅዖ እንዳለው በመግለጽ ኮሚሽኑን አመስግነዋል።

ኮሚሽኑ በማራናታ የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርት ቤት ከቢሾፍቱ ከተማና ከትምህርት ቤቱ አመራሮች እንዲሁም ከበጎ ፈቃደኞች ጋር አረንጓዴ አሻራውን አስቀምጧል።
👍5
አቶ ተንኩዌይ ጆክ ሮም የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የኅብረተሰብ ተሳትፎና በጎ ፈቃድ ማስተባበሪያ ኮሚሽን ኮሚሽነር ሆነው ተሾሙ።

ኮሚሽነር ተንኩዌይ ጆክ ሮም በጋምቤላ ክልል ከዞን አመራርነት እንዲሁም በክልል ደረጃ የተለያዩ ተቋማትን በቢሮ ኃላፊነት የመሩ ሲሆን የጋምቤላ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር በመሆን አገልግለዋል። ኮሚሽኑ ለአዲሱ ኮሚሽነር መልካም የስራ ዘመን እንዲሆንላቸው መልካም ምኞቱን ይገልፃል።

የማኀበራዊ ሚዲያ አማራጮቻችን፥
ፌስቡክ - https://www.facebook.com/cpvcc.2015
ቴሌግራም - https://t.me/CommunityPVC
ቲክቶክ - https://www.tiktok.com/@voluntarismaddis16
ዩቱዩብ - https://youtube.com/@communityparticipationvolu8714
ዌብሳይት - www.volunteeraddis.et
Instagram - https://www.instagram.com/communitypv/
Twitter - https://x.com/Volunteeraddis
👍1
የኀብረተሰብ ተሳትፎና በጎ ፈቃድ ማስተባበሪያ ኮሚሽን - አዲስ አበባ
Photo
በአዲስ አበባ በዘንድሮው የክረምት የበጎ ፈቃድ አገልግሎት እስካሁን ከ3 ነጥብ 6 ቢሊየን ብር በላይ የሚገመት አገልግሎት ተሰጥቷል።

በዘንድሮው የክረምት የበጎ ፈቃድ አገልግሎት እስካሁን ከ3 ነጥብ 6 ቢሊየን ብር በላይ የሚገመት አገልግሎት ለኅብረተሰቡ መሰጠቱን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የኅብረተሰብ ተሳትፎና በጎ ፈቃድ ማስተባበሪያ ኮሚሽን ገለጸ።

የኮሚሽኑ ምክትል ኮሚሽነር ደረጄ ካሳ እንደገለጹት በመዲናዋ በርካታ በጎ ፈቃደኞች በተለያዩ የበጎ ፈቃድ አገልግሎት ተግባራት ላይ እየተሳተፉ ነው።

የአቅመ ደካማና አረጋውያን ቤት እድሳት ፣ የክረምት የማጠናከሪያ ትምህርት ፣ ደም ልገሳና የትራፊክ አደጋን መከላከል ከሚሰጡ የበጎ ፈቃድ አገልግሎት ውስጥ ተጠቃሽ መሆናቸውን ጠቁመዋል።

ይህንንም ተከትሎ በአዲስ አበባ በክረምት የበጎ ፈቃድ አገልግሎት መርኃ-ግብር ብቻ እስካሁን ከ3 ነጥብ 6 ቢሊየን ብር በላይ የሚገመት አገልግሎት ለኅብረተሰቡ መስጠት መቻሉን ተናግረዋል።

በበጎ ፈቃደኞች ከተከናወኑ ዋና ዋና ተግባራት መካከል ማዕድ በማጋራትና ለአቅመ ደካሞች ቤት እድሳትና ግንባታ ዘርፍ ስኬታማ ሥራ ተሰርቷል ብለዋል።

ለአብነትም በተጠናቀቀው በጀት ዓመት 6 ሺህ 500 ለመገንባት ታቅዶ ወደ 6 ሺህ 730 ቤቶችን በመገንባት ለተጠቃሚዎች ማስተላለፍ መቻሉን ነው ያስረዱት።

በዘንድሮ የክረምት ወቅት የበጎ ፈቃድ አገልግሎትም 3ሺ 500 ቤት ለመገንባት እቅድ ተይዞ እስካሁን ባለው ሁኔታ ወደ 2 ሺህ 100 ቤቶችን ገንብተናል ነው ያሉት።

በተመሳሳይ በክረምት በጎ ፈቃድ ማጠናከሪያ ትምህርት እንዲሁም በጎነት በሆስፒታል በሚባሉ መርኃ- ግብሮች በርካታ በጎ ፈቃደኞች እየተሳተፉ መሆኑንም አብራርተዋል።

የመዲናዋ ነዋሪዎች፣ ወጣቶች፣ ባለኃብቶች፣ መንግሥታዊና መንግሥታዊ ያልሆኑ ተቋማት በበጎ ፈቃድ አገልግሎት ላይ የሚያደርጉት ተሳትፎ እያደገ መምጣቱን ተናግረዋል።

የበጎ ፈቃድ አገልግሎቶች በማኅበራዊና ኢኮኖሚያዊ ዕድገት ውስጥ አካታችነትን ለማረጋገጥ ሚናው የላቀ በመሆኑ ሁሉም የበኩሉን አስተዋጽዖ እንዲያደርግ ጥሪ አቅርበዋል።
👍2
ከነዋሪው ፣ ከለጋሾችና ከመንግስት የሚመደበውን የልማትና የድጋፍ በጀት በአግባቡ ማስተዳደርና ለታለመለት ዓላማ ማዋል እንደሚገባ ተገለፀ።

የኅብረተሰብ ተሳትፎና በጎ ፈቃድ ማስተባበሪያ ኮምሽን ከነዋሪው ኅብረተሰብ ፣ ከለጋሾችና ከመንግስት የሚመደበውን የድጋፍ በጀት ለማስተዳደር በተዘጋጀ የፋይናንስ መመሪያ ዙሪያ ለባለድርሻ አካላት ስልጠና ሰጥቷል።

ብሎክን ማዕከል ያደረገ የኅብረተሰብ ተሳትፎን ለማጎልበት በከተማ አስተዳደሩ የአካባቢ ልማት ፣ የሠላም እና የበጎ ፈቃድ አገልግሎት እቅዶች ነዋሪው ንቁ ተሳትፎ እንዲያደርግ ፤ ፍትሐዊ ተጠቃሚ እንዲሆንና የነዋሪውን መሥተጋብርና ትስስር በማጠናከር ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ችግሮችን በራስ አቅም ለመፍታት የፋይናን መመሪያ እንደሚያግዝ ተጠቁሟል።

የአስራር ግልፀኝነት መፈጠሩ መሬት ላይ ህጋዊ አሰራሩን የጠበቀ ስራ ለመሥራት እንደሚያግዝ የገለፁት ሰልጣኞች ለተፈፃሚነቱም በቁርጠኝነት እንደምሰሩ ተናግረዋል።

የማኀበራዊ ሚዲያ አማራጮቻችን፥
ፌስቡክ - https://www.facebook.com/cpvcc.2015
ቴሌግራም - https://t.me/CommunityPVC
ቲክቶክ - https://www.tiktok.com/@voluntarismaddis16
ዩቱዩብ - https://youtube.com/@communityparticipationvolu8714
ዌብሳይት - www.volunteeraddis.et
Instagram - https://www.instagram.com/communitypv/
Twitter - https://x.com/Volunteeraddis
👍1
የኅብረተሰቡ የአካባቢ ጥበቃ ተሳትፎ እየተጠናከረ መምጣቱ ተገለፀ።

የኅብረተሰብ ተሳትፎና በጎ ፈቃድ ማስተባበሪያ ኮምሽን በአዋጅ ከተሰጡት ኃላፊነቶች መካከል ኅብረተሰቡ በብሎክ አደረጃጀት ውስጥ በአካባቢ ሰላም ስራዎች እንዲሳተፍ ምቹ ሁኔታን መፍጠር ይገኝበታል።

የኅብረተሰቡ የአካባቢ ጥበቃ ተሳትፎ የቅጥር ጥበቃን ከማጠናከር ጀምሮ የፀጥታ ስጋቶችን አስቀድሞ መከላከል ፣ በመሰረተ ልማቶች ላይ የሚደርሱ ጉዳቶችን መቆጣጠር ፣ አካባቢን በሽፍት መጠበቅና ሌሎች ጉዳዮችን ያካትታል።

ኮሚሽኑ የኅብረተሰቡን የሠላም ተሳትፎ ለማሳደግም የኅብረተሰብ የአካባቢ ጥበቃ ተሳትፎ መመሪያ ቁጥር 148/2016 አዘጋጅቶ ስራ ላይ አውሏል።

መመሪያው በርካታ የመልካም አስተዳደር ችግሮችን መፍታቱንና ለሥራቸውም ምቹ ሁኔታ እንደፈጠረላቸው በአራዳ ክፍለ ከተማ ወረዳ 1 በምሽት የአካባቢ ሠላም ስራ ላይ የተሰማሩ የቅጥር ጥበቃ አባላት ገልፀዋል።

የኮሚሽኑ የደንብ መተላለፍ ቅድመ መከላከል ህዝባዊ ተሳትፎ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ገዛኸኝ ኃይሉ አዲሱን መመሪያ መሰረት በማድረግ በብሎኮች የኅብረተሰብ ጥበቃ አባላት በብዛት እየተሳተፉ መሆኑን ገልፀዋል።

የማኀበራዊ ሚዲያ አማራጮቻችን፥
ፌስቡክ - https://www.facebook.com/cpvcc.2015
ቴሌግራም - https://t.me/CommunityPVC
ቲክቶክ - https://www.tiktok.com/@voluntarismaddis16
ዩቱዩብ - https://youtube.com/@communityparticipationvolu8714
ዌብሳይት - www.volunteeraddis.et
Instagram - https://www.instagram.com/communitypv/
Twitter - https://x.com/Volunteeraddis
👍1
ለመጪው አዲስ ዓመት አብሮነትን ይበልጥ ማጠናከር የሚያስችሉ ማህበራዊና ሰብዓዊ ሥራዎች እየተከናወኑ ነው።

በአዲስ አበባ ከተማ አዲሱን ዓመት ምክንያት በማድረግ አቅመ ደካሞችን ፣ በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ የሚገኙ ነዋሪዎችንና አረጋውያንን ተጠቃሚ የሚያደርጉና አብሮነትን ይበልጥ የሚያጠናክሩ ማህበራዊና ሰብዓዊ ተግባራት እየተከናወኑ ይገኛሉ።

የአስተዳደሩ የኅብረተሰብ ተሳትፎና በጎ ፈቃድ ማስተባበሪያ ኮሚሽን እነዚህ ሰው ተኮር ተግባራት የደረሱበትን የአፈፃጸም ደረጃ ከክፍለ ከተማ የዘርፍ ኃላፊዎችና ከማዕከል አመራሮች ጋር በመገምገም ቀሪ ስራዎች በልዩ ትኩረት እንዲመሩ አቅጣጫ አስቀምጧል።

በጳጉሜን ቀናት የሚከናወኑ ሰብዓዊና ማኅበራዊ ተግባራት በየደረጃው አሰራሩን ጠብቀው እየተመሩ መሆኑ በጥንካሬ የተገመገመ ሲሆን የተቸገሩ ወገኖቻችን በዓሉን በደስታና በአብሮነት እንዲያከብሩ ሁሉም አካላት ማኅበራዊ ኃላፊነታቸውን በመወጣት የበኩላቸውን አስተዋፅዖ እንዲያደርጉ በመድረኩ ተጠይቋል።

"በጎ ፈቃደኝነት ፤ ለማኅበረሰብ ለውጥ!"
የማኀበራዊ ሚዲያ አማራጮቻችን፥
ፌስቡክ - https://www.facebook.com/cpvcc.2015
ቴሌግራም - https://t.me/CommunityPVC
ቲክቶክ - https://www.tiktok.com/@voluntarismaddis16
ዩቱዩብ - https://youtube.com/@communityparticipationvolu8714
ዌብሳይት - www.volunteeraddis.et
Instagram - https://www.instagram.com/communitypv/
Twitter - https://x.com/Volunteeraddis
👍2