የኀብረተሰብ ተሳትፎና በጎ ፈቃድ ማስተባበሪያ ኮሚሽን - አዲስ አበባ
812 subscribers
2.14K photos
47 videos
265 links
Download Telegram
የአዲስ አበባ እናቶች በዛሬው ብሔራዊ የአረንጓዴ አሻራ ንቅናቄ ላይ!

#ኢትዮጵያ
#አረንጓዴ_አሻራ
በመዲናችን አዲስ አበባ በ11ዱም ክፍለ ከተሞች በአንድ ጀምበር ችግኞችን የመትከል ስራዉ ተጠናክሮ ቀጥሏል

"የምትተክል ሃገር የሚያፀና ትዉልድ"በሚል መሪ ቃል የከተማ አስተዳደሩ በዛሬዉ እለት ከማለዳ 12 ሰዓት ጀምሮ በመዲናችን አዲስ አበባ በ11 ክፍለ ከተሞች ህዝቡን በነቂስ በማስተባበር የአንድ ጀምበር ችግኞችን የመትከል ስራዉ ተጠናክሮ መቀጠሉ በየክፍለ ከተማዉ ያሉ መረጃዎች ያሳያሉ፡፡


በመርሃ ግብሩ ላይም ከሃገር ዉስጥ፤- ህፃናት፤ወጣት ወንዶችና ሴቶች፤ ጎልማሶች፤ አረጋዉያን፤ ነፍሰጡሮች ፤ታዋቂ ግለሰቦች እና በየደረጃዉ ያሉ መንግስታዊና መንግስታዊ ያልሆኑ የተቋማት ሰራተኞችና አመራሮች እንዲሁም የዉጪ ሀገራት ዜጎችና ዲፕሎማቶች ተሳታፊ በመሆን አሻራቸዉን አኑረዋል፡፡

ይህ የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር ለከተማችን የቱሪስት መስህብነት፤ለጥላና መዝናኛነት፤ተስማሚ የአየር ንብረት ለመፍጠር፤ለመድሃኒት፤ለምግብ ፤ለስራ እድልና ለገቢ ምንጭነት እንዲሁም ዉብ እና ለኑሮ ምቹና ተስማሚ የሆኑ ገፀ-በረከቶችን የሚያመጣ በመሆኑ መዲናዋ ከጀመረቻቸዉ ሰፋፊ የልማት ስራዎች ጋር በማስተሳሰር የአረንጓዴ መርሃ ግብርን በሁሉም ክፍለ ከተማ እየተሳለጠ መሆኑ በነቂስ ከወጣዉ የከተማዋ ህዝቡ ተሳትፎ ለመገንዘብ ተችሏል፡፡

በየክፍለ ከተማዉ አሻራቸዉን እያስቀመጡ የሚገኙት የመርሃ ግብሩ ተሳታፊዎችም የከተማችንን የአረንጓዴ አሻራ ልማት ስራ ላይ ሙሉ አቅማችንን በመጠቀም፤ሁላችንም ተረባርበን በዚህ ታሪካዊ ቀን ለትዉልድ የሚሻገር ታሪክ እየሰራን እንገኛለን ብለዋል፡፡
👍1
በአንድ ጀምበር የአረንጓዴ አሻራ መርሐ ግብር እስካሁን 594 ሚሊየን ችግኞች ተተክለዋል ።

በአንድ ጀምበር የአረንጓዴ አሻራ መርሐ ግብር ከማለዳ 12:00 ሰዓት ጀምሮ እስካሁን 594 ሚሊየን ችግኞች መተከላቸውን የመንግስት ኮሙኒኬሽን ሚኒስትር ድኤታ ሰላማዊት ካሳ አስታውቀዋል፡፡በዚህም 28 ሚሊየን ኢትዮጵያውያን ተሳትፈዋል።

የሁሉም ችግኝ መትከያ ቦታዎች መረጃ አለመጠናቀቁን የገለጹት ሚኒስትር ድኤታዋ ተከላው አሁንም ቀጥሏል ብለዋል።
እንኳን ደስ አላችሁ!

ኢትዮጵያ በአንድ ጀምበር የአረንጓዴ አሻራ መርሐ ግብር 600 ሚሊዮን ችግኞችን ከመትከል አቅዳ 615 ነጥብ 7 ሚሊየን ችግኞች በመትከል እቅዷን አሳክታለች።

የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ መልዕክት፥

የዛሬ ጀምበር ወጥታ እስክትጠልቅ ስድስት መቶ ሚሊዮን ችግኞችን ልንተክል ኢትዮጵያውያን ሁሉ አቅደን ነበር። ያሰብነውን ሳናሳካ ጀምበር የሚጠልቅብን አይደለንምና በአንድ ጀምበር 615.7 ሚሊዮን ችግኞችን መትከል ችለናል።

ህፃናት ተስፋቸውን ተክለዋል። ወጣቶች ጽናተቸውን አሳይተዋል። አረጋውያን ውርስ አኑረዋል። ኢትዮጵያውያን ከሊቅ እስከ ደቂቅ ከቤታቸው ወጥተው የማይደበዝዝ አሻራ አኑረዋል። በማበራችን እና በመጽናታችን በአለም በሌላ ስፍራ በአንድ ጀምበር ያልተደረገውን እኛ ኢትዮጵያውያን አድርገነዋል። ዛሬ ለአየር ንብረት ለውጥ ሚዛን ጥበቃ ቆመን ውለናል። የአፈር መራቆትን ለመመከት ተሰልፈን ውለናል። የምግብ ዋስትና ለማረጋገጥ ስንደክም ውለናል። ምድራችንን አረንጓዴ ለማልበስ ልምላሜን ለመመለስ ሳንበገር ሰርተናል። ፈጣሪም ረድቶን ለዛሬዋ ጀምበር ያሰብነውን አሳክተናል።

ዛሬ 29.1 ሚሊዮን ዜጎች በ318.4 ሄክታር በጂኦስፓሻል መረጃ በተገኘባቸው ስፍራዎች ላይ ችግኞችን ተክለዋል። እስካሁን በመረጃ ቋት ከተመዘገበው ውጭ የተተከሉ ችግኞች መረጃ በተከታታይ የሚገለፅ ይሆናል።

ለአስደማሚው የኢትዮጵያውያን ኅበረት እና ጽናት እነሆ ምስጋና። ለስኬታችን የእቅድ፣ የክትትል እና የመረጃ አውታር በመሆን በትጋት የሰራችሁ አመራሮች ባለሞያዎች እና የሚዲያ ተቋማት ምስጋና ይገባችኋል። ምኞት ተግባራችን ሁሉ የተሻለች ኢትዮጵያን በኅብረት ገንብቶ ማቆየት ነው። ይኽንኑ እንቀጥላለን።
👍3👏1
አዲስ አበባ በአንድ ጀምበር 6 ሚሊዮን ችግኞችን ለመትከል አቅዳ 9.9 ሚሊዮን ችግኞችን በመትከል እቅዷን አሳክታለች።

ከንቲባ አዳነች አቤቤ ባስተላለፉት የእንኳን ደስ አላችሁ መልዕክት "ኢትዮጵያውያን የዛሬ ጀምበር 600 ሚሊዮን ችግኞችን ለመትከል አቅደን 615.7 ሚሊዮን ችግኞችን መትከል የቻልን ሲሆን ከዚህም ውስጥ እንደ አዲስ አበባ 6 ሚሊዮን አቅደን 9.9 ሚሊዮን በላይ ችግኞችን ተክለናል" ብለዋል።

የከተማችን ነዋሪ የመሪችንን ጥሪ ተቀብሎ ማልዶ በመነሳት በአስደናቂ አፈፃፀም ከእቅድ በላይ ችግኞችን በመትከል ታሪክ የማይዘነጋው ታላቅ ገድል በመፈጸሙ ታላቅ አክብሮት ከምስጋና ጋር የሚገባው ሲሆን በተጨማሪም ይህ እንዲሳካ ያስተባበራችሁ እና የደከማችሁ አመራሮች እንዲሁም ሰራተኞቻችን በራሴና በከተማ አስተዳደራችን ስም ላመሰግናችሁ እወዳለሁ ብለዋል ከንቲባ አዳነች አቤቤ።

ይህ ዛሬ ያሳየነውን የተባበረ ክንድ የሚያመጣውን ለውጥ በሌሎች የልማት ስራዎች ላይ በመድገም የሃገራችንን ብልፅግና እውን እንድናደርግ ጥሪ አቅርበዋል።

የምትተክል ሀገር የሚያጸና ትውልድ!
👍5
የረዳን ፈጣሪ ይመስገን!!

እንኳን ደስ አለን! እንደ አዲስ አበባ 6 ሚሊዮን አቅደን 9.9 ሚሊዮን በላይ ችግኞችን ተክለናል::

ከንቲባ አዳነች አቤቤ
የኀብረተሰብ ተሳትፎና በጎ ፈቃድ ማስተባበሪያ ኮሚሽን - አዲስ አበባ
Photo
ኮሚሽኑ በ2016 የስራ አፈፃጸምና በ2017 በጀት ዓመት እቅድ ዙሪያ ከባለድርሻ አካላት ጋር ውይይት አክሂዷል::

በውይይት መድረኩ ላይ የተገኙት የቀድሞው የኮሚሽኑ ኮሚሽነር እና የወቅቱ በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የከንቲባ የአደረጃጀት ዘርፍ አማካሪ አቶ አብርሃም ታደሰ በተጠናቀቀው በጀት አመትከ12 ቢሊዮን ብር በላይ የበጎ ፈቃድ አገልግሎት መሰጠቱንና ከ1.9 ቢሊዮን ብር በላይ ሀብት ለአካባቢ መሰረተ ልማት ስራ ላይ መዋሉን ገልፀዋል። በ2017 በጀት አመት ስኬቶችን በማላቅ ፣ ድክመቶችንና መንስዔዎቻቸውን በማረም ለተሻለ አፈፃጸም መትጋት እንደሚገባም አቶ አብርሐም ታደሰ አሳስበዋል።

የበጎ ፈቃድ ዘርፍ ምክትል ኮሚሽነር አቶ ደረጀ ካሳ ፣ የኅብረተሰብ ተሳትፎ ዘርፍ ምክትል ኮሚሽነር ወ/ሮ ፀሐይ ኪባሞ እና የኮሚሽኑ የፅህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ስመኘው አድነው የውይይት መድረኩን መርተዋል።

የውይይቱ ተሳታፊዎች በኮሚሽኑ አስተባባሪነት የተሰሩ የኅብረተሰብ ተሳትፎና የበጎ ፈቃድ ስራዎች ለከተማዋ ሰላምና ልማት የላቀ ሚና የተጫወቱ በመሆኑ በ2017 በጀት አመት ነዋሪውን በማሳተፍ በትብብር ለመስራት መዘጋጀታቸውን ተናግረዋል።

በከተማ አስተዳደሩ የኮሚሽኑ የኅብረተሰብ ተሳትፎ ዘርፍ ምክትል ኮሚሽነር ሆነው የተሾሙት ወ/ሮ ፀሐይ ኪባሞ በመድረኩ ላይ ተገኝተው ትውውቅ በማድረግ መደበኛ ስራቸውን በይፋ ጀምረዋል።

የማኀበራዊ ሚዲያ አማራጮቻችን፥
ፌስቡክ - https://www.facebook.com/cpvcc.2015
ቴሌግራም - https://t.me/CommunityPVC
ቲክቶክ - https://www.tiktok.com/@voluntarismaddis16
ዩቱዩብ - https://youtube.com/@communityparticipationvolu8714
ዌብሳይት - www.volunteeraddis.et
Instagram - https://www.instagram.com/communitypv/
Twitter - https://x.com/Volunteeraddis
የኮልፌ ቀራኒዮ ክፍለ ከተማ ከ52 ሚሊየን ብር በላይ ወጪ የተደረገባቸው የአካባቢ ልማት ስራዎችን አስመረቀ።

በክፍለ ከተማው ሁሉም ወረዳዎች ከ52 ሚሊየን ብር በላይ ወጪ የተደረገባቸው 25 የሚደርሱ በህብረተሰቡ ተሳትፎ የተገነቡ የተለያዩ የልማት ፕሮጀክቶች ተመርቀው ዛሬ ለአገልግሎት ክፍት ተደርገዋል፡፡

ከተሰሩ የልማት ስራዎች መካከል የሰብ ቤዝ ንጣፍ ፣ የኮብል ስቶን ንጣፍ እና ጥገና ፣ አነስተኛ ድልድይ ግንባታ ፣ የኮሙኒቲ ፖሊስ ሴንተር ፣ ካልቨርቶችና ዲቾች ፣ የቴራዞ ንጣፎች ፣ የመማሪያ ክፍሎች በአጠቃላይ 25 አይነት የልማት ስራዎች እንደሚገኙበት የክፍለ ከተማው ኮሙኒኬሽን ፅህፈት ቤት ያደረሰን መረጃ ያመለክታል፡፡

የማኀበራዊ ሚዲያ አማራጮቻችን፥
ፌስቡክ - https://www.facebook.com/cpvcc.2015
ቴሌግራም - https://t.me/CommunityPVC
ቲክቶክ - https://www.tiktok.com/@voluntarismaddis16
ዩቱዩብ - https://youtube.com/@communityparticipationvolu8714
ዌብሳይት - www.volunteeraddis.et
Instagram - https://www.instagram.com/communitypv/
Twitter - https://x.com/Volunteeraddis
👍2