የኀብረተሰብ ተሳትፎና በጎ ፈቃድ ማስተባበሪያ ኮሚሽን - አዲስ አበባ
809 subscribers
2.14K photos
47 videos
265 links
Download Telegram
የኀብረተሰብ ተሳትፎና በጎ ፈቃድ ማስተባበሪያ ኮሚሽን - አዲስ አበባ
Photo
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በ2016 ዓ. ም. ባደረገው የስራ አፈፃፀም ግምገማ የተገኙ ውጤታማ ጥንካሬዎችን በማላቅ የተለዩ ድክመቶችን በማረም ላይ ይገኛል:: የተጀመረውን የተቋማት ግንባታና የሪፎርም ስራዎችን አጠናክሮ ለማስቀጠል የከተማ አስተዳደሩ አዳዲስ ሹመቶችን ሰጥቷል ፣ ሽግሽግ አድርጏል እንዲሁም የተወሰኑትን ከኃላፊነት አንስቷል:: በዚህም መሰረት:-

1. አቶ አብርሃም ታደሰ - የከንቲባ የአደረጃጀት አማካሪ
2.. አቶ ይመር ከበደ- የመንግስት ልማት ድርጅቶች ባለስልጣን ሃላፊ

በከተማ ማዕከል ደረጃ የተሰጡ ሹመቶች:-

1. አቶ አደም ኑሪ - የፕላንና ልማት ቢሮ ሃላፊ
2. አቶ ቢኒያም ምክሩ - የገቢዎቸ ቢሮ ሃላፊ
3. ወ/ሮ ሀቢባ ሲራጅ- የንግድ ቢሮ ሃላፊ
4. ዶ/ር ዳዲ ወዳጆ - የከንቲባ ስትራቴጂክ ጉዳዮች አማካሪ
5. አቶ ተስፋዬ ደንድር - የሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ምክትል ቢሮ ሃላፊ
6. አቶ ማቆያ አለማየሁ - የግንባታና ዲዛይን ምክትል ቢሮ ሃላፊ
7. አቶ አስመሮም ብርሃኔ - የትራንስፖርት ምክትል ቢሮ ሃላፊ
8. አቶ ተስፋዬ ጫኔ - የሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ምክትል ቢሮ ሃላፊ
9. አቶ ዩኑስ አደም - የመሬት ልማትና አስተዳደር ምክትል ቢሮ ሃላፊ
10. አቶ አዳነ ሱሌ - የገቢዎች ቢሮ ፅ/ ቤት ሃላፊ
11. ወ/ሮ ወርቅነሽ ሰቦቃ - የገቢዎች ምክትል ቢሮ ሃላፊ
12. አቶ ዘገየ በላይነህ - የፀረ-ሙሰና ኮሚሽን ምክትል ሃላፊ
13. ወ/ሮ ፀሀይ ኪባሞ - የበጎ ፈቃድና ህዝብ ተሳትፎ ኮሚሽን ምክትል ኮሚሽነር
14. ኮ/ር አህመድ ሙሃመድ - የደንብ ማስከበር ባለስልጣን ምክትል ሃላፊ
15. ⁠አቶ ከፍያለው ታደሰ- የደንብ ማስከበር ባለስልጣን ምክትል ሃላፊ
16. ⁠አቶ ዘመኑ ታደሰ - የመብራት አገልግሎት ፅ/ ቤት ሃላፊ
17. ⁠ወ/ሮ ወይንሸት ብዛኔ - የከንቲባ ፕሬስ ሴክሬታሪያት ምክትል ሃላፊ
18. ⁠አቶ አሰፋ ቶላ - የዲዛይንና ግንባታ ማማከር ፅ/ቤት ሃላፊ

በክ/ ከተማ ደረጃ

1. ወ/ ሮ ካባ መብራቱ - የንፋስ ስልክ ላፍቶ ክ/ ከተማ ዋና ስራ አስፈፃሚ
2. ⁠ወ/ሮ አበባ እሸቴ - የልደታ ክፍለ ከተማ ዋና ስራ አስፈፃሚ
3. ⁠አቶ ጌታሁን አበራ - የአራዳ ክፍለ ከተማ ዋና ስራ አስፈፃሚ
4. ⁠አቶ መብራቱ ደሴ የንፋስ ስልክ ላፍቶ ፓርቲ ፅ/ ቤት ሃላፊ በመሆን ተሹመዋል::

የተጣለባችሁን ኃላፊነት በቅንነት፣ በታማኝነት እና በትጋት እንድትወጡ እናሳስባለን::

መልካም የስራ ዘመን!
ነሃሴ 2016 ዓ.ም
ከንቲባ ፅ/ቤት
👍5
የተቋማችን ዋና ኮሚሽነር አብርሐም ታደሰ የከንቲባ አደረጃጀት አማካሪ ሆነው ተሹመዋል።

ኮሚሽነር አብርሐም በተቋሙ ውስጥ በነበራቸው አጭር ጊዜ ውስጥ በአመራሩና በሰራተኛው መካከል ውህደት በመፍጠር ኮሚሽኑ ተቋማዊ አሰራር እንዲኖረው በማድረግ ውጤታማ የአመራር ሰጭነት ሚናቸውን ተወጥተዋል።

የኮሚሽኑ አመራሮችና ሰራተኞች መልካም የስራ ዘመን እንዲሆንላቸው ምኞታችንን በታላቅ አክብሮት እንገልፃለን።
ወ/ሮ ፀሐይ ኪባሞ የአዲስ አበባ ከተማ የኅብረተሰብ ተሳትፎና በጎ ፈቃድ ማስተባበሪያ ኮሚሽን ምክትል ኮሚሽነር ሆነው ተሾሙ።

መልካም የስራ ዘመን
👍4👏2
#ኢትዮጵያ በዛሬው ዕለት በአንድ ጀምበር 600 ሚሊዮን ችግኞችን ትተክላለች።

አዋቂዎች ከ20 በላይ እንዲሁም ህፃናት ከ10 በላይ ችግኞችን በመትከል የተቀመጠውን የችግኝ ተከላ ግብ ለማሳካት ከጥዋቱ 12:00 እስከ ምሽት 12:00 ሰዓት ድረስ ሁላችንም አሻራችንን እናስቀምጥ!

#አረንጓዴ_አሻራ
#አዲስ_አበባ
👍4
"የምትተክል ሀገር ፤ የሚያፀና ትውልድ!"

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የኅብረተሰብ ተሳትፎና በጎ ፈቃድ ማስተባበሪያ ኮሚሽን አመራሮችና ሰራተኞች በአንድ ጀምበር 600 ሚሊዮን ችግኝ የመትከል ሀገራዊ ንቅናቄ ላይ በመሳተፍ አረንጓዴ አሻራቸውን እያኖሩ ነው።

በእንጦጦ ፓርክ በተካሄደው የአረንጓዴ አሻራ ንቅናቄ ምክትል ኮሚሽነር አቶ ደረጀ ካሳ ፣ የኮሚሽኑ የፅህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ስመኘው አድነው እንዲሁም ዳይሬክተሮችና ባለሙያዎች ተሳትፈዋል።

ሀገራዊ የአረንጓዴ አሻራ ንቅናቄ በአንድ ጀምበር 600 ሚሊዮን ችግኞችን የመትከል ግብን ለማሳካት መላው ኢትዮጵያዊ በነቂስ እየተሳተፈ ሲሆን በአዲስ አበባ ዛሬ ብቻ 6 ሚሊዮን ችግኞችን ለመትከል እቅድ ተይዟል።
#234ሚሊየን

"የምትተክል ሃገር የሚያጸና ትውልድ"

" የ600 ሚሊዮን ችግኞች የአንድ ጀምበር የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር እስከ ረፋዱ 5 ሰአት 30 ድረስ 234 ሚሊየን ችግኞች ተተክለዋል፡፡"

ሰላማዊት ካሳ- የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር ዴኤታ

ሚኒስትር ዴኤታዋ የአንድ ጀምበር 600 ሚሊየን የችግኝ ተከላ በመላ ሃገሪቱ በከፍተኛ የዜጎች ተሳትፎ እየተካሄደ መሆኑን ጠቁመው በዚህ ችግኝ ተከላ እስከ ረፋዱ 5 ሰአት ከ30 ድረስ 11 ሚሊየን ዜጎች በተከላው ተሳትፈዋል፣ 93 ሺህ ሄክታር መሬት ላይ ችግኞች ተተክለዋል ብለዋል፡፡

የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር ለኢትዮጵያዊያንና ለመላው ዓለም ለሚገኙ የማህበረሰብ ክፍሎች ተደራሽ ለማድረግ ከ 2 ሺህ በላይ የመገናኛ ብዙሃን ባለሙያዎች በመላው ኢትዮጵያ መሰማራታቸውንም ተናግረዋል፡፡

ይህንን ሃገራዊ ሁነት በቀጥታ ስርጭት ለዜጎች ተደራሽ ለማድረግም ከ50 በላይ የቀጥታ ስርጭት መሳሪያዎች አገልግሎት ላይ መዋላቸውን ገልጸዋል፡፡
ከጠዋት 12:00 ጀምሮ እስካሁን 402 ሚሊየን ችግኞች ተተክለዋል - የመንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት

ከጠዋት 12:00 ጀምሮ እስካሁን 402 ሚሊየን ችግኞች መተከላቸውን የመንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር ዴኤታ ሰላማዊት ካሣ ገለጹ።

በዛሬው ዕለት እየተካሄደ ባለው በአንድ ጀንበር 600 ሚሊዮን ችግኝ የመትከል ብሔራዊ የአረንጓዴ አሻራ ንቅናቄ 19 ሚሊዮን ኢትዮጵያውያን መሳተፋቸውንም ገልጸዋል።

በዚህም 161 ሺህ ሔክታር መሬት መሸፈኑን ነው ሚኒስትር ዴኤታዋ ያስታወቁት።
የአዲስ አበባ እናቶች በዛሬው ብሔራዊ የአረንጓዴ አሻራ ንቅናቄ ላይ!

#ኢትዮጵያ
#አረንጓዴ_አሻራ
በመዲናችን አዲስ አበባ በ11ዱም ክፍለ ከተሞች በአንድ ጀምበር ችግኞችን የመትከል ስራዉ ተጠናክሮ ቀጥሏል

"የምትተክል ሃገር የሚያፀና ትዉልድ"በሚል መሪ ቃል የከተማ አስተዳደሩ በዛሬዉ እለት ከማለዳ 12 ሰዓት ጀምሮ በመዲናችን አዲስ አበባ በ11 ክፍለ ከተሞች ህዝቡን በነቂስ በማስተባበር የአንድ ጀምበር ችግኞችን የመትከል ስራዉ ተጠናክሮ መቀጠሉ በየክፍለ ከተማዉ ያሉ መረጃዎች ያሳያሉ፡፡


በመርሃ ግብሩ ላይም ከሃገር ዉስጥ፤- ህፃናት፤ወጣት ወንዶችና ሴቶች፤ ጎልማሶች፤ አረጋዉያን፤ ነፍሰጡሮች ፤ታዋቂ ግለሰቦች እና በየደረጃዉ ያሉ መንግስታዊና መንግስታዊ ያልሆኑ የተቋማት ሰራተኞችና አመራሮች እንዲሁም የዉጪ ሀገራት ዜጎችና ዲፕሎማቶች ተሳታፊ በመሆን አሻራቸዉን አኑረዋል፡፡

ይህ የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር ለከተማችን የቱሪስት መስህብነት፤ለጥላና መዝናኛነት፤ተስማሚ የአየር ንብረት ለመፍጠር፤ለመድሃኒት፤ለምግብ ፤ለስራ እድልና ለገቢ ምንጭነት እንዲሁም ዉብ እና ለኑሮ ምቹና ተስማሚ የሆኑ ገፀ-በረከቶችን የሚያመጣ በመሆኑ መዲናዋ ከጀመረቻቸዉ ሰፋፊ የልማት ስራዎች ጋር በማስተሳሰር የአረንጓዴ መርሃ ግብርን በሁሉም ክፍለ ከተማ እየተሳለጠ መሆኑ በነቂስ ከወጣዉ የከተማዋ ህዝቡ ተሳትፎ ለመገንዘብ ተችሏል፡፡

በየክፍለ ከተማዉ አሻራቸዉን እያስቀመጡ የሚገኙት የመርሃ ግብሩ ተሳታፊዎችም የከተማችንን የአረንጓዴ አሻራ ልማት ስራ ላይ ሙሉ አቅማችንን በመጠቀም፤ሁላችንም ተረባርበን በዚህ ታሪካዊ ቀን ለትዉልድ የሚሻገር ታሪክ እየሰራን እንገኛለን ብለዋል፡፡
👍1
በአንድ ጀምበር የአረንጓዴ አሻራ መርሐ ግብር እስካሁን 594 ሚሊየን ችግኞች ተተክለዋል ።

በአንድ ጀምበር የአረንጓዴ አሻራ መርሐ ግብር ከማለዳ 12:00 ሰዓት ጀምሮ እስካሁን 594 ሚሊየን ችግኞች መተከላቸውን የመንግስት ኮሙኒኬሽን ሚኒስትር ድኤታ ሰላማዊት ካሳ አስታውቀዋል፡፡በዚህም 28 ሚሊየን ኢትዮጵያውያን ተሳትፈዋል።

የሁሉም ችግኝ መትከያ ቦታዎች መረጃ አለመጠናቀቁን የገለጹት ሚኒስትር ድኤታዋ ተከላው አሁንም ቀጥሏል ብለዋል።
እንኳን ደስ አላችሁ!

ኢትዮጵያ በአንድ ጀምበር የአረንጓዴ አሻራ መርሐ ግብር 600 ሚሊዮን ችግኞችን ከመትከል አቅዳ 615 ነጥብ 7 ሚሊየን ችግኞች በመትከል እቅዷን አሳክታለች።

የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ መልዕክት፥

የዛሬ ጀምበር ወጥታ እስክትጠልቅ ስድስት መቶ ሚሊዮን ችግኞችን ልንተክል ኢትዮጵያውያን ሁሉ አቅደን ነበር። ያሰብነውን ሳናሳካ ጀምበር የሚጠልቅብን አይደለንምና በአንድ ጀምበር 615.7 ሚሊዮን ችግኞችን መትከል ችለናል።

ህፃናት ተስፋቸውን ተክለዋል። ወጣቶች ጽናተቸውን አሳይተዋል። አረጋውያን ውርስ አኑረዋል። ኢትዮጵያውያን ከሊቅ እስከ ደቂቅ ከቤታቸው ወጥተው የማይደበዝዝ አሻራ አኑረዋል። በማበራችን እና በመጽናታችን በአለም በሌላ ስፍራ በአንድ ጀምበር ያልተደረገውን እኛ ኢትዮጵያውያን አድርገነዋል። ዛሬ ለአየር ንብረት ለውጥ ሚዛን ጥበቃ ቆመን ውለናል። የአፈር መራቆትን ለመመከት ተሰልፈን ውለናል። የምግብ ዋስትና ለማረጋገጥ ስንደክም ውለናል። ምድራችንን አረንጓዴ ለማልበስ ልምላሜን ለመመለስ ሳንበገር ሰርተናል። ፈጣሪም ረድቶን ለዛሬዋ ጀምበር ያሰብነውን አሳክተናል።

ዛሬ 29.1 ሚሊዮን ዜጎች በ318.4 ሄክታር በጂኦስፓሻል መረጃ በተገኘባቸው ስፍራዎች ላይ ችግኞችን ተክለዋል። እስካሁን በመረጃ ቋት ከተመዘገበው ውጭ የተተከሉ ችግኞች መረጃ በተከታታይ የሚገለፅ ይሆናል።

ለአስደማሚው የኢትዮጵያውያን ኅበረት እና ጽናት እነሆ ምስጋና። ለስኬታችን የእቅድ፣ የክትትል እና የመረጃ አውታር በመሆን በትጋት የሰራችሁ አመራሮች ባለሞያዎች እና የሚዲያ ተቋማት ምስጋና ይገባችኋል። ምኞት ተግባራችን ሁሉ የተሻለች ኢትዮጵያን በኅብረት ገንብቶ ማቆየት ነው። ይኽንኑ እንቀጥላለን።
👍3👏1
አዲስ አበባ በአንድ ጀምበር 6 ሚሊዮን ችግኞችን ለመትከል አቅዳ 9.9 ሚሊዮን ችግኞችን በመትከል እቅዷን አሳክታለች።

ከንቲባ አዳነች አቤቤ ባስተላለፉት የእንኳን ደስ አላችሁ መልዕክት "ኢትዮጵያውያን የዛሬ ጀምበር 600 ሚሊዮን ችግኞችን ለመትከል አቅደን 615.7 ሚሊዮን ችግኞችን መትከል የቻልን ሲሆን ከዚህም ውስጥ እንደ አዲስ አበባ 6 ሚሊዮን አቅደን 9.9 ሚሊዮን በላይ ችግኞችን ተክለናል" ብለዋል።

የከተማችን ነዋሪ የመሪችንን ጥሪ ተቀብሎ ማልዶ በመነሳት በአስደናቂ አፈፃፀም ከእቅድ በላይ ችግኞችን በመትከል ታሪክ የማይዘነጋው ታላቅ ገድል በመፈጸሙ ታላቅ አክብሮት ከምስጋና ጋር የሚገባው ሲሆን በተጨማሪም ይህ እንዲሳካ ያስተባበራችሁ እና የደከማችሁ አመራሮች እንዲሁም ሰራተኞቻችን በራሴና በከተማ አስተዳደራችን ስም ላመሰግናችሁ እወዳለሁ ብለዋል ከንቲባ አዳነች አቤቤ።

ይህ ዛሬ ያሳየነውን የተባበረ ክንድ የሚያመጣውን ለውጥ በሌሎች የልማት ስራዎች ላይ በመድገም የሃገራችንን ብልፅግና እውን እንድናደርግ ጥሪ አቅርበዋል።

የምትተክል ሀገር የሚያጸና ትውልድ!
👍5
የረዳን ፈጣሪ ይመስገን!!

እንኳን ደስ አለን! እንደ አዲስ አበባ 6 ሚሊዮን አቅደን 9.9 ሚሊዮን በላይ ችግኞችን ተክለናል::

ከንቲባ አዳነች አቤቤ