የኀብረተሰብ ተሳትፎና በጎ ፈቃድ ማስተባበሪያ ኮሚሽን - አዲስ አበባ
809 subscribers
2.14K photos
47 videos
265 links
Download Telegram
#ደም_ሕይወት_አድን_ስጦታ
የፋኖስ ኮሚዩኒቲ ቤተሰቦች በክረምት የበጎ ፈቃድ አገልግሎት የሚተካ ደማቸውን ለማይተካው የሰው ልጅ ሕይወት ለግሰዋል።

ፋኖስ ኮሚዩኒቲ በቴክኖሎጂ ዙሪያ የጋራ አስተሳሰብ ያላቸው ወጣቶች የተሰባሰቡበት የማህበራዊ ሚዲያ ፕላትፎርም ሲሆን ማህበራዊ ሚዲያውን ለበጎ ዓላማ በመጠቀም በዛሬው ዕለት በብሔራዊ ደምና ህብረ ህዋስ ባንክ በመገኘት ለመጀመሪያ ጊዜ የደም ልገሳ አካሂዷል።

የፋኖስ ኮሚዩኒቲ አባላት ከደም ልገሳ ባሻገር በሌሎች የበጎነት ተግባራት ለመሳተፍ ፍላጎት እንዳላቸውና የበጎ ፈቃድ አገልግሎታቸውን አጠናክረው እንደሚቀጥሉ ገልፀዋል።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የኅብረተሰብ ተሳትፎና በጎ ፈቃድ ማስተባበሪያ ኮሚሽን በማህበራዊ ሚዲያ ላይ የሚሰሩ ሌሎች ወጣቶች የፋኖስ ኮሚዩኒቲን አርዓያነት በመከተል በበጎ ፈቃድ ተግባራት ላይ እንዲሳተፉ ጥሪውን ያስተላልፋል።

የማኀበራዊ ሚዲያ አማራጮቻችን፥
ፌስቡክ - https://www.facebook.com/cpvcc.2015
ቴሌግራም - https://t.me/CommunityPVC
ቲክቶክ - https://www.tiktok.com/@voluntarismaddis16
ዩቱዩብ - https://youtube.com/@communityparticipationvolu8714
ዌብሳይት - www.volunteeraddis.et
Instagram - https://www.instagram.com/communitypv/
Twitter - https://x.com/Volunteeraddis
የኀብረተሰብ ተሳትፎና በጎ ፈቃድ ማስተባበሪያ ኮሚሽን - አዲስ አበባ
Photo
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የ2016 በጀት ዓመት የስራ አፈጻጸም ግምገማ ተጠናቋል።

የከተማ አስተዳደሩ የበጀት ዓመቱ ገቢ የመሰብሰብ አቅም 44 % ማደጉ ፣ በኮሪደር ልማት ስራዎች ከተማዋን በማጽዳት እንደ ስሟ ውብ አበባ ማድረግ መቻሉ ፣ የነዋሪውን የኑሮ ጫና አቅልለው ተስፋ ያለመለሙ የበርካቶችን ሸክም ያቀለሉ ሰው ተኮር ስራዎች መከናወናቸው ፣ የአቅመ ደካሞችንና የሀገር ባለውለታዎችን እምባ አብሰው ማህበራዊ ፍትህን ያነገሱ ስራዎች መሰራታቸው እና በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ላይ የሚገኙ የህብረተሰብ ክፍሎችን ለመደጎም ከ11 ቢሊዮን ብር በላይ ስራ ላይ መዋሉ ተመላክቷል።

የከተማዋን በጀት 63% ለልማት በማዋል የህዝብን ሀብት ከምዝበራ መታደግ መቻሉ ፤ ለህዝብ ግልጋሎት ክፍት የተደረጉት ከ18 ሺሕ በላይ ፕሮጀክቶች ማንንም ወደኋላ ያልተው ፣ አካታች ልማት ሲሆኑ በመንግስት እና ህዝብ ተሳትፎ በተሰራው የአረንጓዴ አሻራ ንቅናቄም 17.5 ሚሊዮን ችግኞችን በመትከል የከተማዋን የአረንጓዴ ሽፋን ማሳደግ ተችሏል።

ፍትሃዊና ቀልጣፋ አገልግሎት መስጠት የሚያስችሉ በ10 ተቋማት ጠንካራ ሪፎርሞች እና አሰራሮችን መዘርጋት መቻሉ እንዲሁም አቅመ ደካሞችን እና የሀገር ባለውለታዎችን የመደገፍ ስራ ተከናውኗል።

ከንቲባ አዳነች አቤቤ በማኅበራዊ ሚዲያ ገፃቸው እንዳሰፈሩት "ከህዝብ ጋር ባደረግናቸው በርካታ ውይይቶች የተለዩ ችግሮችን በተለይም ሌብነት፣ ጉቦኝነት፣ ብልሹ አሰራርን እንዲሁም በአገልግሎት አሰጣጥ ዙሪያ ያለውን ውስንነት በቁርጠኝነት በማስተካከል ለህዝባችን በገባነው ቃል መሰረት የምንሰራ ይሆናል።" ሲሉ ተናግረዋል።

ባመጣናቸው አመርቂ ውጤቶች እና ለውጦች ሳንወሰድ ውስንነቶች ላይ አፋጣኝ እርማት እየወሰድን ፣ ጥንካሬዎቻችንን በማስቀጠል አሁንም አዳዲስ አሰራሮችን በመተግበር ለነዋሪዎች ምቹ የሆነች ከተማ መገንባታችንን እንቀጥላለን ብለዋል ከንቲባ አዳነች አቤቤ።

የማኀበራዊ ሚዲያ አማራጮቻችን፥
ፌስቡክ - https://www.facebook.com/cpvcc.2015
ቴሌግራም - https://t.me/CommunityPVC
ቲክቶክ - https://www.tiktok.com/@voluntarismaddis16
ዩቱዩብ - https://youtube.com/@communityparticipationvolu8714
ዌብሳይት - www.volunteeraddis.et
Instagram - https://www.instagram.com/communitypv/
Twitter - https://x.com/Volunteeraddis
👍6
የክረምት በጎ ፈቃድ አገልግሎት ከተጀመረ ወዲህ 73 ሺህ 350 ከፍለው መታከም የማይችሉ ነዋሪዎች ነፃ የህክምና አገልግሎት አግኝተዋል።

በአዲስ አበባ ነፃ ህክምና የመስጠት የበጎ ፈቃድ አገልግሎት በርካታ ከፍለው መታከም የማይችሉ ነዋሪዎች ተጠቃሚ እያደረገ ይገኛል።

በክረምት የበጎ ፈቃድ አገልግሎት ከፍለው መታከም የማይችሉ የአዲስ አበባ ነዋሪዎችን ነፃ ህክምና እያገኙ ሲሆን ጤናማ ማኅበረሰብ ለመፍጠር የሚደረገውን ጥረት ከማገዙም ባሻገር የነዋሪዎችን ተጠቃሚነት አሳድጓል።

በዛሬው ዕለት ብቻ በኮልፌ ቀራኒዮ ክፍለ ከተማ ለሦስት ሺህ ነዋሪዎች ነጻ የህክምና አገልግሎት ተሰጥቷል። የህክምና አገልግሎቱን ጤና ቢሮን ጨምሮ ምግብና መድኃኒት ባለስልጣን ያስተባበሩት ሲሆን የኢትዮጵያ የሀኪሞች ማህበር እና አለርት ሆስፒታል የህክምና ባለሙያዎችን በማሰማራት ተሳትፈዋል።

በከተማችን አዲስ አበባ የክረምቱ የበጎ ፈቃድ አገልግሎት ከተጀመረ ግንቦታ 18 ወዲህ 73 ሺህ 350 ዜጎች ነፃ የህክምና አገልግሎት አግኝተዋል።

"በጎ ፈቃደኝነት ፤ ለማኅበረሰብ ለውጥ!"
👍3
ነሐሴ 17፣ 2016 ዓ.ም በአንድ ጀምበር 600 ሚሊዮን ችግኞችን በመትከል ዓሻራችንን እናኑር::

በአንድ መንፈስ በመላው ኢትዮጵያ ዓሻራችንን እናኑር፡፡ አንድ ከሆን ከዚህም በላይ እንችላለን!

አዋቂዎች ከ20 በላይ፣ ታዳጊወች ከ10 በላይ በመትከል ለሀገር ያለንን ፍቅር፣ ለትውልድ ያለንን ስጦታ በተገቢው ስፍራ እንግለጥ፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)
👍7
#3_ቀን ቀረው!

"የምትተክል ሀገር ፤ የሚያፀና ትውልድ!" 6ኛው ሀገር አቀፍ በአንድ ጀምበር 600 ሚሊዮን ችግኞችን የመትከል ንቅናቄ 3 ቀናት ቀሩት!

በአንድነት መንፈስ አረንጓዴ አሻራችንን ለትውልድ ለማስቀመጥ እንዘጋጅ!

#GreenLegacy
#Ethiopia
#worlrecord
👍3
አገልጋይ መሪነትን የተላበሰ ባለሙያ በመፍጠር ተቋማዊ ውጤታማነትን ማሳደግ እንደሚገባ ተገለፀ።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የኅብረተሰብ ተሳትፎና በጎ ፈቃድ ማስተባበሪያ ኮሚሽን ከማዕከል እስከ ክፍለ ከተማ ለሚገኙ ባለሙያዎች አገልጋይ መሪነት ( Servant Leadership) እና የቡድን ግንባታ (Team Building) በሚሉ ርዕሰ ጉዳዮች ስልጠና ሰጥቷል።

መሪነት ወደፊት መራመድን ፣ ከምቾት ቀጠና መውጣትን ፣ ኃላፊነት መውሰድን ፣ ተግዳሮቶችን መጋፈጥን እና ቡድን በመገንባት ውጤት ማምጣትን የሚጠይቅ ሳይንስ መሆኑ በስልጠናው ተመላክቷል።

አገልጋይ መሪነትን መላበስና የቡድን ግንባታ ብቃትን ማሳደግ ተቋማዊ ውጤታማነትን ለማረጋገጥ ያግዛል ተብሏል።

የስልጠናው ተሳታፊዎች የተናጠል ስራ ለውጥ የማያመጣ መሆንና በቡድን መሥራት የተሻለ ውጤት ለማምጣት እንደሚያግዝ ከስልጠናውም መረዳታቸውን በመግለፅ ለተቋማዊ ለውጥ እንደሚሰሩ ተናግረዋል።

የማኀበራዊ ሚዲያ አማራጮቻችን፥
ፌስቡክ - https://www.facebook.com/cpvcc.2015
ቴሌግራም - https://t.me/CommunityPVC
ቲክቶክ - https://www.tiktok.com/@voluntarismaddis16
ዩቱዩብ - https://youtube.com/@communityparticipationvolu8714
ዌብሳይት - www.volunteeraddis.et
Instagram - https://www.instagram.com/communitypv/
Twitter - https://x.com/Volunteeraddis
የኀብረተሰብ ተሳትፎና በጎ ፈቃድ ማስተባበሪያ ኮሚሽን - አዲስ አበባ
Photo
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በ2016 ዓ. ም. ባደረገው የስራ አፈፃፀም ግምገማ የተገኙ ውጤታማ ጥንካሬዎችን በማላቅ የተለዩ ድክመቶችን በማረም ላይ ይገኛል:: የተጀመረውን የተቋማት ግንባታና የሪፎርም ስራዎችን አጠናክሮ ለማስቀጠል የከተማ አስተዳደሩ አዳዲስ ሹመቶችን ሰጥቷል ፣ ሽግሽግ አድርጏል እንዲሁም የተወሰኑትን ከኃላፊነት አንስቷል:: በዚህም መሰረት:-

1. አቶ አብርሃም ታደሰ - የከንቲባ የአደረጃጀት አማካሪ
2.. አቶ ይመር ከበደ- የመንግስት ልማት ድርጅቶች ባለስልጣን ሃላፊ

በከተማ ማዕከል ደረጃ የተሰጡ ሹመቶች:-

1. አቶ አደም ኑሪ - የፕላንና ልማት ቢሮ ሃላፊ
2. አቶ ቢኒያም ምክሩ - የገቢዎቸ ቢሮ ሃላፊ
3. ወ/ሮ ሀቢባ ሲራጅ- የንግድ ቢሮ ሃላፊ
4. ዶ/ር ዳዲ ወዳጆ - የከንቲባ ስትራቴጂክ ጉዳዮች አማካሪ
5. አቶ ተስፋዬ ደንድር - የሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ምክትል ቢሮ ሃላፊ
6. አቶ ማቆያ አለማየሁ - የግንባታና ዲዛይን ምክትል ቢሮ ሃላፊ
7. አቶ አስመሮም ብርሃኔ - የትራንስፖርት ምክትል ቢሮ ሃላፊ
8. አቶ ተስፋዬ ጫኔ - የሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ምክትል ቢሮ ሃላፊ
9. አቶ ዩኑስ አደም - የመሬት ልማትና አስተዳደር ምክትል ቢሮ ሃላፊ
10. አቶ አዳነ ሱሌ - የገቢዎች ቢሮ ፅ/ ቤት ሃላፊ
11. ወ/ሮ ወርቅነሽ ሰቦቃ - የገቢዎች ምክትል ቢሮ ሃላፊ
12. አቶ ዘገየ በላይነህ - የፀረ-ሙሰና ኮሚሽን ምክትል ሃላፊ
13. ወ/ሮ ፀሀይ ኪባሞ - የበጎ ፈቃድና ህዝብ ተሳትፎ ኮሚሽን ምክትል ኮሚሽነር
14. ኮ/ር አህመድ ሙሃመድ - የደንብ ማስከበር ባለስልጣን ምክትል ሃላፊ
15. ⁠አቶ ከፍያለው ታደሰ- የደንብ ማስከበር ባለስልጣን ምክትል ሃላፊ
16. ⁠አቶ ዘመኑ ታደሰ - የመብራት አገልግሎት ፅ/ ቤት ሃላፊ
17. ⁠ወ/ሮ ወይንሸት ብዛኔ - የከንቲባ ፕሬስ ሴክሬታሪያት ምክትል ሃላፊ
18. ⁠አቶ አሰፋ ቶላ - የዲዛይንና ግንባታ ማማከር ፅ/ቤት ሃላፊ

በክ/ ከተማ ደረጃ

1. ወ/ ሮ ካባ መብራቱ - የንፋስ ስልክ ላፍቶ ክ/ ከተማ ዋና ስራ አስፈፃሚ
2. ⁠ወ/ሮ አበባ እሸቴ - የልደታ ክፍለ ከተማ ዋና ስራ አስፈፃሚ
3. ⁠አቶ ጌታሁን አበራ - የአራዳ ክፍለ ከተማ ዋና ስራ አስፈፃሚ
4. ⁠አቶ መብራቱ ደሴ የንፋስ ስልክ ላፍቶ ፓርቲ ፅ/ ቤት ሃላፊ በመሆን ተሹመዋል::

የተጣለባችሁን ኃላፊነት በቅንነት፣ በታማኝነት እና በትጋት እንድትወጡ እናሳስባለን::

መልካም የስራ ዘመን!
ነሃሴ 2016 ዓ.ም
ከንቲባ ፅ/ቤት
👍5
የተቋማችን ዋና ኮሚሽነር አብርሐም ታደሰ የከንቲባ አደረጃጀት አማካሪ ሆነው ተሹመዋል።

ኮሚሽነር አብርሐም በተቋሙ ውስጥ በነበራቸው አጭር ጊዜ ውስጥ በአመራሩና በሰራተኛው መካከል ውህደት በመፍጠር ኮሚሽኑ ተቋማዊ አሰራር እንዲኖረው በማድረግ ውጤታማ የአመራር ሰጭነት ሚናቸውን ተወጥተዋል።

የኮሚሽኑ አመራሮችና ሰራተኞች መልካም የስራ ዘመን እንዲሆንላቸው ምኞታችንን በታላቅ አክብሮት እንገልፃለን።
ወ/ሮ ፀሐይ ኪባሞ የአዲስ አበባ ከተማ የኅብረተሰብ ተሳትፎና በጎ ፈቃድ ማስተባበሪያ ኮሚሽን ምክትል ኮሚሽነር ሆነው ተሾሙ።

መልካም የስራ ዘመን
👍4👏2
#ኢትዮጵያ በዛሬው ዕለት በአንድ ጀምበር 600 ሚሊዮን ችግኞችን ትተክላለች።

አዋቂዎች ከ20 በላይ እንዲሁም ህፃናት ከ10 በላይ ችግኞችን በመትከል የተቀመጠውን የችግኝ ተከላ ግብ ለማሳካት ከጥዋቱ 12:00 እስከ ምሽት 12:00 ሰዓት ድረስ ሁላችንም አሻራችንን እናስቀምጥ!

#አረንጓዴ_አሻራ
#አዲስ_አበባ
👍4
"የምትተክል ሀገር ፤ የሚያፀና ትውልድ!"

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የኅብረተሰብ ተሳትፎና በጎ ፈቃድ ማስተባበሪያ ኮሚሽን አመራሮችና ሰራተኞች በአንድ ጀምበር 600 ሚሊዮን ችግኝ የመትከል ሀገራዊ ንቅናቄ ላይ በመሳተፍ አረንጓዴ አሻራቸውን እያኖሩ ነው።

በእንጦጦ ፓርክ በተካሄደው የአረንጓዴ አሻራ ንቅናቄ ምክትል ኮሚሽነር አቶ ደረጀ ካሳ ፣ የኮሚሽኑ የፅህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ስመኘው አድነው እንዲሁም ዳይሬክተሮችና ባለሙያዎች ተሳትፈዋል።

ሀገራዊ የአረንጓዴ አሻራ ንቅናቄ በአንድ ጀምበር 600 ሚሊዮን ችግኞችን የመትከል ግብን ለማሳካት መላው ኢትዮጵያዊ በነቂስ እየተሳተፈ ሲሆን በአዲስ አበባ ዛሬ ብቻ 6 ሚሊዮን ችግኞችን ለመትከል እቅድ ተይዟል።
#234ሚሊየን

"የምትተክል ሃገር የሚያጸና ትውልድ"

" የ600 ሚሊዮን ችግኞች የአንድ ጀምበር የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር እስከ ረፋዱ 5 ሰአት 30 ድረስ 234 ሚሊየን ችግኞች ተተክለዋል፡፡"

ሰላማዊት ካሳ- የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር ዴኤታ

ሚኒስትር ዴኤታዋ የአንድ ጀምበር 600 ሚሊየን የችግኝ ተከላ በመላ ሃገሪቱ በከፍተኛ የዜጎች ተሳትፎ እየተካሄደ መሆኑን ጠቁመው በዚህ ችግኝ ተከላ እስከ ረፋዱ 5 ሰአት ከ30 ድረስ 11 ሚሊየን ዜጎች በተከላው ተሳትፈዋል፣ 93 ሺህ ሄክታር መሬት ላይ ችግኞች ተተክለዋል ብለዋል፡፡

የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር ለኢትዮጵያዊያንና ለመላው ዓለም ለሚገኙ የማህበረሰብ ክፍሎች ተደራሽ ለማድረግ ከ 2 ሺህ በላይ የመገናኛ ብዙሃን ባለሙያዎች በመላው ኢትዮጵያ መሰማራታቸውንም ተናግረዋል፡፡

ይህንን ሃገራዊ ሁነት በቀጥታ ስርጭት ለዜጎች ተደራሽ ለማድረግም ከ50 በላይ የቀጥታ ስርጭት መሳሪያዎች አገልግሎት ላይ መዋላቸውን ገልጸዋል፡፡
ከጠዋት 12:00 ጀምሮ እስካሁን 402 ሚሊየን ችግኞች ተተክለዋል - የመንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት

ከጠዋት 12:00 ጀምሮ እስካሁን 402 ሚሊየን ችግኞች መተከላቸውን የመንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር ዴኤታ ሰላማዊት ካሣ ገለጹ።

በዛሬው ዕለት እየተካሄደ ባለው በአንድ ጀንበር 600 ሚሊዮን ችግኝ የመትከል ብሔራዊ የአረንጓዴ አሻራ ንቅናቄ 19 ሚሊዮን ኢትዮጵያውያን መሳተፋቸውንም ገልጸዋል።

በዚህም 161 ሺህ ሔክታር መሬት መሸፈኑን ነው ሚኒስትር ዴኤታዋ ያስታወቁት።
የአዲስ አበባ እናቶች በዛሬው ብሔራዊ የአረንጓዴ አሻራ ንቅናቄ ላይ!

#ኢትዮጵያ
#አረንጓዴ_አሻራ