የኀብረተሰብ ተሳትፎና በጎ ፈቃድ ማስተባበሪያ ኮሚሽን - አዲስ አበባ
809 subscribers
2.14K photos
47 videos
265 links
Download Telegram
የኀብረተሰብ ተሳትፎና በጎ ፈቃድ ማስተባበሪያ ኮሚሽን - አዲስ አበባ
Photo
በቀጣይ ርብርብ የሚሹ የትኩረት አቅጣጫዎች በተመለከተ:-

👉  ከህዝባችን ጋር በመሆን የሕግ የበላይነትን በማረጋገጥ የከተማችንን ዘላቂ ሠላምና ደህንነት የማስጠበቅ ስራችንን አጠናክረን እንቀጥላለን፡፡

👉 የተጀመረውን ተቋማዊ ሪፎርም አጠናክሮ የማስቀጠል፣ የአመራርና ፈፃሚውን አቅም ለመገንባት በልዩ ትኩረት ይሰራል፡፡

👉 የተጀመረዉን የሲቪል ሰርቪስ ሪፎርምን በቴክኖሎጂ፣ በአሠራርና በአደረጃጀት በማስደገፍ እና ተግባራዊ በማድረግ የአገልግሎት አሰጣጥና የከተማውን  መልካም አስተዳደር በላቀ ደረጃ በማሻሻል በፕሮጀክቶች አፈፃፀም ያገኘነዉን ድል በአገልግሎት አሰጣጥ እና በመልካም አስተዳደር ለመድገም እንተጋለን፡፡

👉ሌብነትንና ብልሹ አሠራር ላይ የጀመርነዉን ትግል አጠናክረን ህዝቡንም በብቃት በማሳተፍ መሰረታዊ ለውጥ ለማምጣት ተግተን በቁርጠኝነት እንሰራለን፡፡

👉 በመሬት ልማት እና አስተዳደር ሥርዓታችን ላይ በቴክኖሎጂ በማስደገፍ መሠረታዊ ለውጥ ለማምጣት የጀመርነዉን ጥረት ይበልጥ ተጠናክሮ  ይቀጥላል፡፡

👉 በሁሉም መስክ የቴክኖሎጂ አጠቃቀማችንን በማሻሻል የንግድ ሥርዓቱን ማዘመን፣ ለኢንቨስትመንት ምቹ አካባቢን በመፍጠር  እንሰራለን ።

👉 የተጀመረዉን የትምህርት ሪፎርም በማጠናከር የትምህርት ጥራት የማረጋገጥ ቀሪ ተግባራትን በልዩ ትኩረት ይፈፀማል፣ እያደገ የመጣዉን የጤና አገልግሎት ይበልጥ የማሻሻልና የማዘመን ሥራ ተጠናክሮ ይቀጥላል።

👉 የኑሮ ውድነትን ለማረጋጋት፣ የሌማት ትሩፋትና የከተማ ግብርናን ማስፋት ተጠናክረው እንዲቀጥሉ ይደረጋል።

👉 የቤት ልማት ፕሮግራሞችን በግል ዘርፉ፣ በሕብረት ሥራ ማኅበራት፣ በመንግስትና በግል የአጋርነት ፕሮግራም በስፋት ተግባራዊ እናደርጋለን።

👉 የኪነ ጥበብ ዘርፉን በማጠናከርና የከተማችንን የቱሪስት መዳረሻ ቦታዎች ይበልጥ በማስተዋወቅ እና እንዲጎበኙ በማድረግ ከዘርፉ ከተማችን ማግኘት የሚገባትን ሁለንተናዊ ፋይዳ እንድታገኝ ይደረጋል፡፡

👉 በከተማችን ጽዳትና ውበት መስክ የተገኘዉን ስኬት በማላቅ ከምንጊዜውም በላቀ ትኩረት ማህበረሰብ አቀፍ አንዲሆን እንሰራለን።

👉 የሥራ ዕድል ፈጠራ ስራችን በተለይም የወጣቶች የሥራ እድል እና አምራች ኢንዱስትሪን የማስፋትና ተወዳዳሪነቱን የማሳደግ ስራ በልዩ ትኩረት ይከናወናል፡፡

👉 ሕብረ-ብሔራዊ ወንድማማችነትና አንድነትን በማጠናከር የከተማችንን ነዋሪ የላቀ ተሳታፊነትና ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ በትጋት እንሰራለን።

👉 በአጠቃላይ ከተማችን ለነዋሪዎቿ ምቹ፣ ሀገራዊ፤አህጉራዊና አለም አቀፍ ሚናዋን በብቃት የምትወጣ፤ስሟና ግብሯ የተናበበባት ስማርት ከተማ እንድትሆን የጀመርነዉን ልማት በጥራት፣ በስፋትና በፍጥነት አጠናክረን እንቀጥላለን፡፡
👍3
የአዲስ አበባ ከተማ የ2017 በጀት 230 ቢሊየን ብር ሆኖ ፀደቀ፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት 3ኛ ዓመት 4ኛ መደበኛ ጉባኤውን እያካሄደ ይገኛል፡፡
ምክር ቤቱ በመደበኛ በስብሰባው የአዲስ አበባ ከተማ የ2017 በጀት ዓመት ረቂቅ በጀትን ተወያይቶ አጽድቋል፡፡

በዚህም የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር አጠቃላይ በጀት 230 ነጥብ 39 ቢሊየን ብር ሁኖ ጸድቋል፡፡

ከጸደቀው በጀት ውስጥ 146 ነጥብ 48 ቢሊየን ብር ለካፒታል፣ 83 ነጥብ 91 ቢሊየን ብር ለመደበኛ ወጪ እንዲሆን አድርጎ የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት አጽድቋል፡፡

የጸደቀው በጀት ከባለፈው 2016 ተመሳሳይ በጀት ጋር ሲነጻጻር የ68 ነጥብ 3 ቢሊየን ብር ብልጫ እንዳለው ተገልጻል፡፡

በጀቱ የኮሪደር ልማት ስራዎችን ለማጠናቀቅ፣የጋራ መኖሪያ ቤቶችን ለማጠናቀቅ፣ ለመጠጥና ውሃ ፍሳሽ፣ለመንገድ መሰረተ ልማት እና ማህበራዊ እድገትን እንደሚውል በረቂቅ በጀቱ ተመላክቷል፡፡
👍5
የኮሚሽኑ አመራሮች ፣ ሰራተኞችና በጎ ፈቃደኞች አረንጓዴ አሻራቸውን አሳርፈዋል።

6ኛው ዙር የአረንጓዴ አሻራ መርሀ ግብር "የምትተክል ሀገር ፥ የሚያፀና ትውልድ!" በሚል መሪ ሀሳብ እየተካሄደ ሲሆን የአዲስ አበባ ከተማ የኀብረተሰብ ተሳትፎና በጎ ፈቃድ ማስተባበሪያ ኮሚሽን 20 ሺህ ችግኞችን ለመትከል አቅዷል።

ኮሚሽኑ በዛሬው ዕለት በእንጦጦ ፓርክ በተካሄደ የአረንጓዴ አሻራ መርሀ ግብር 3 ሺህ ችግኞች ተክሏል።

የምትተክል ሀገር ፣ የሚያጸና ትውልድ!
👍2
በጎ ልቦች ሲተባበሩ...

በጎ ልቦች ኀብረት ፈጥረው የማኀበረሰባቸውን ችግር በመፍታት ላይ ናቸው። የንፋስ ስልክ ላፍቶ በጎ ፈቃደኞች በዝቅተኛ ኑሮ ደረጃ ለሚገኙ ዜጎች የሰሩት ባለስድስት ወለል ህንፃ እየተጠናቀቀ ነው።

በዚህ የበጎነት አሻራ ውስጥ የመንግስት ሰራተኞች ፣ የንግዱ ማኀበረሰብ ፣ የመንግስት ኃላፊዎች. .. በጥቅሉ ሁሉም በጎ ልብ ያለው ተሳትፏል።

በጎ ልብ ድንበር ሲሻገር እና ለመስጠት እጃችን ሲዘረጋ ችግሮቻችን ለዘለቄታው ይወገዳሉ ፣ ብልፅግናችን ይረጋገጣል ፣ ኢትዮጵያችን ኃያል ትሆናለች!

"በጎ ፈቃደኝነት ፥ ለማኀበረሰብ ለውጥ!"
"የአሁኑ ትውልድም አረንጓዴ አሻራውን በማሳረፍ ሀገሩን ለምለም አድርጎ ለቀጣዩ ትውልድ ማሻገር አለበት።" በጎ ፈቃደኞች
በፅዱና ውብ አካባቢ የመኖር ተፈጥሯዊ መብታችን የሚረጋገጠው እያንዳንዳችን ለአካባቢያችን ውበት ሲገደን ፣ ከበካይ ተግባራት ስንቆጠብና ቆሻሻን በአግባቡ ስናስወግድ ብቻ ነው።

መኖሪያ ቤታችን አዲስ አበባን ከእኛ ሌላ የሚያፀዳልን ስለሌለ በተባበረ ክንድ ንፁህ ፣ ውብና ምቹ ከተማን እንፍጠር!

"ሁሉ አቀፍ ተሳትፏችን ፣ ለአዲስ አበባችን!"
#addisababa
#Ethiopia
#pictureoftheday
በ2017 በጀት ዓመት ከ230 ቢሊዮን ብር በላይ ግብር ለመሰብሰብ የተያዘውን እቅድ በጋራ ለማሳካት የሚያስችል የንቅናቄ መርሃ ግብር ተካሂዷል።

በመርሃ ግብሩ በ2016 ገቢ አሰባሰብ የተሳተፉ እና ለውጤታማነቱ ጉልህ አስተዋፅዖ ያበረከቱ አካላት እውቅና ተሰጥቷቸዋል።

በ2016 በጀት ዓመት 146 ቢሊዮን ብር በመሰብሰብ የህዝቡን የኑሮ ጫና የሚያቃልሉ እና የከተማዋን ገጽታ የቀየሩ 18,091 ፕሮጀክቶች ተሰርተው ለአገልግሎት ክፍት ተደርገዋል።

ከንቲባ አዳነች አቤቤ ለገቢ ቤተሰቦች ከተማችን አዲስ አበባ የምታመነጨው የገቢ አቅም ከዚህ በላይ መሰብሰብ እንደምንችል የሚያሳይ በመሆኑ ከብክነት፣ ከብልሹ አሰራር እና ከሙስና በጸዳ መንገድ በ2017 ያቀድነውን 230 ቢሊዮን ብር በመሰብሰብ በጋራ እናሳካ ሲሉ ጥሪ አቅርበዋል።

ከንቲባዋ እንደገለፁት በዚህ ዓመት ለተገልጋዮቻችን ክብር ስንል የአገልግሎት መስጫዎቻችን እና የአሰራር ስርዓታችን ላይ ማሻሻያዎችን ለማድረግ ስራዎች ትኩረት ሰጥተን የምንሰራ ይሆናል ብለዋል።
ኢትዮጵያ ወደተሟላ የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያ ትግበራ ገባች።