የኀብረተሰብ ተሳትፎና በጎ ፈቃድ ማስተባበሪያ ኮሚሽን - አዲስ አበባ
809 subscribers
2.14K photos
47 videos
265 links
Download Telegram
የኀብረተሰብ ተሳትፎና በጎ ፈቃድ ማስተባበሪያ ኮሚሽን - አዲስ አበባ
Photo
"ያለ ህዝብ ብቁ ተሳትፎ የሚከናወን ስራ ሙሉ ሊሆን አይችልም!" ከንቲባ አዳነች አቤቤ

በመዲናዋ 11 ሺህ ምልምል የሰላም ሠራዊት አባላት ተመረቁ። የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር 11 ሺህ ምልምል የሰላም ሠራዊት አባላትን አስመርቋል።

በምረቃ መድረኩ ላይ የተገኙት የአዲስ አበባ ከንቲባ አዳነች አቤቤ ሰላማችንን ዘላቂ እና ህዝባዊ መሰረት ያለው ለማድረግ ዛሬ አሰልጥነን ያስመረቅናቸው 11 ሺሕ አዲስ ምልምል የሠላም ሠራዊት አባላትን ጨምሮ 341 ሺሕ የሠላም ሠራዊት አባላትን የከተማችን የሰላም ዘብ አድርገን አሰማርተናል ሲሉ ተናግረዋል።

ከ2013 ጀምሮ ሕዝባችንን በተደራጀ መልኩ ከጸጥታ ኃይሉ ጋር ማቀናጀት እና የሰላሙ ዋነኛ ባለቤት ማድረግ መቻላችን እስካሁን ካስገኙን ውጤታማ እና ስኬታማ ስራዎች በተጨማሪ ከተማችንን ለነዋሪዎቿ ምቹ እና ሰላማዊ ማድረግ ችለናል ያሉት ከንቲባዋ ዛሬ የተመረቃችሁ የሰላም ሰራዊት አባላት ሕዝባችን የሰላሙ እና የተሰሩ መሰረተ ልማቶች ባለቤትና ቀዳሚ ተጠቃሚ መሆኑን በመረዳት በየአካባቢያችሁ የሰላምና የመሰረተ ልማቱ ዘብ በመሆን ህዝባችሁን በፍፁም ትህትና እና ፍቅር እንድታገለግሉ አደራ ማለት እወዳለሁ ብለዋል።

የማህበራዊ ሚዲያ ገፆቻችን ቤተሰብ እንዲሆኑ እንጋብዛለን! አጋርነትዎን የበጎነትና የህብረተሰብ ተሳትፎ ግቦቻችን በመደገፍ ወይም ገንቢ አስተያየትዎን በመለገስ ያረጋግጡ!!

ፌስቡክ - https://www.facebook.com/cpvcc.2015
ቴሌግራም - https://t.me/CommunityPVC
ቲክቶክ - https://www.tiktok.com/@voluntarismaddis16
ዩቱዩብ - https://youtube.com/@communityparticipationvolu8714
ዌብሳይት - www.volunteeraddis.et
Instagram - https://www.instagram.com/communitypv/
Twitter - https://x.com/Volunteeraddis
👍4
ለመላው የእስልምና እምነት ተከታዮች እንኳን ለ1445ኛው ዓመተ ሒጅራ ኢድ-አል-አድሃ (አረፋ) በዓል በሰላም አደረሳችሁ።

በዓሉ የሰላም ፣ የፍቅር ፣ የአብሮነትና የመተሳሰብ እንዲሆንላችሁ እንመኛለን!

የህብረተሰብ ተሳትፎና በጎ ፈቃድ ማስተባበሪያ ኮሚሽን
👍4
“ቅን ልቦች”

በበጎነት ተግባራት ላይ ያተኮረ ዘጋቢ ፊልም ዛሬ ምሽት ከ3፡10 ሰዓት ጀምሮ በአዲስ ሚዲያ ኔትወርክ ይጠብቁን!
“በጎ ፈቃደኝነት ለማህበረሰብ ለውጥ!”
👍9
ዛሬ ምሽት በአዲስ ሚዲያ ኔትወርክ ሊተላለፍ የነበረው "ቅን ልቦች" ዘጋቢ ፊልም በፕሮግራም መጣበብ ምክንያት ወደሌላ ጊዜ የተሸጋገረ መሆኑን ለክቡራን ደንበኞቻችን ከይቅርታ ጋር እንገልፃለን!
👍3
የክፍት የስራ ማስታወቂያ!

መስሪያ ቤታችን የህብረተሰብ ተሳትፎና በጎ ፈቃድ ማስተባበሪያ ኮሚሽን ከዚህ በታች በተዘረዘሩ ክፍት የስራ መደቦች አመልካቾችን በቋሚነትና በኮንትራት አወዳድሮ መቅጠር ይፈልጋል።

የስራ መደቦቹን ተፈላጊ መስፈርት የምታሟሉ ስራ ፈላጊዎች ይህ ማስታዎቂያ ከወጣበት ከዛሬ ሰኔ 11/2016 ዓ.ም ጀምሮ ባሉት 5 ተከታታይ የስራ ቀናት የትምህርት ማስረጃችሁን ዋናውንና የማይመለስ ፎቶ ኮፒ በመያዝ ፒያሳ እሪ በከንቱ በሚገኘው ቢሯችን ቢቲ ታዎር 3ኛ ፎቅ የሰው ኃብት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ቢሮ ቁጥር 03-04 በአካል በመቅረብ ማመልከት ይኖርባችኋል።

ከግል ድርጅቶች ለሚቀርብ የስራ ልምድ ማስረጃ የስራ ግብር ስለመከፈሉ ከግብር ሰብሳቢው አካል ማስረጃ ማቅረብ ይጠበቃል።

በሌቭል ደረጃ ለተመረቃችሁ COC ማቅረብ ይኖርባችኋል።

የህብረተሰብ ተሳትፎና በጎ ፈቃድ ማስተባበሪያ ኮሚሽን!
👍71
"የቤት ልማትና ማስተላለፍን በሚመለከት በመንግስት አስተባባሪነት በ20/80 ፕሮግራም 2,087 ቤቶች፣ በ40/60 ፕሮግራም 2,966 ቤቶች፣ በወጪ ቆጣቢ እና በበጎ ፈቃድ 7,582 ቤቶች፣ ለኪራይ አገልግሎት 5,000 ቤቶች በአጠቃላይ 17,635 ቤቶች በመንግስት በጀት እና አስተባባሪነት ተገንብቶ ለልማት ተነሺዎች እና ለሌሎች ተጠቃሚዎች የማስተላለፍ ሥራ ተሰርቷል። "
👍21
"ከ1 ሚሊዮን በላይ በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ላይ ለሚገኙ ኅብረተሰብ ክፍሎች ማዕድ ለማጋራት ታቅዶ ለ1.2 ሚሊዮን ዜጎች ማዕድ ማጋራት የተቻለ ሲሆን በአጠቃላይ በሰው ተኮር እና በጎ ፈቃድ ሥራችን 11.1 ቢሊዮን ብር የበጎ ፈቃድ አገልግሎት ለ1.7 ሚሊዮን ዜጎች ለመስጠት ታቅዶ 12.6 ቢሊዮን ብር የበጎ ፈቃድ ተግባራት በማከናወን የከተማችንን ነዋሪዎች ተጠቃሚ ማድረግ ተችሏል።" ከንቲባ አዳነች አቤቤ
👍21
የትራፊክ ህጎችን በማክበር ራስዎን ከድንገተኛ አደጋ ይጠብቁ!

የአራዳ ክፍለ ከተማ የትራፊክ አገልግሎት በጎ ፈቃደኞች እግረኞችን መንገድ በማሻገርና የትራፊክ መጨናነቁን በማሳለጥ አገልግሎት ሲሰጡ!

"በጎ ፈቃደኝነት ለማኀበረሰብ ለውጥ!"
👍4
የኀብረተሰብ ተሳትፎና በጎ ፈቃድ ማስተባበሪያ ኮሚሽን - አዲስ አበባ
Photo
በቀጣይ ርብርብ የሚሹ የትኩረት አቅጣጫዎች በተመለከተ:-

👉  ከህዝባችን ጋር በመሆን የሕግ የበላይነትን በማረጋገጥ የከተማችንን ዘላቂ ሠላምና ደህንነት የማስጠበቅ ስራችንን አጠናክረን እንቀጥላለን፡፡

👉 የተጀመረውን ተቋማዊ ሪፎርም አጠናክሮ የማስቀጠል፣ የአመራርና ፈፃሚውን አቅም ለመገንባት በልዩ ትኩረት ይሰራል፡፡

👉 የተጀመረዉን የሲቪል ሰርቪስ ሪፎርምን በቴክኖሎጂ፣ በአሠራርና በአደረጃጀት በማስደገፍ እና ተግባራዊ በማድረግ የአገልግሎት አሰጣጥና የከተማውን  መልካም አስተዳደር በላቀ ደረጃ በማሻሻል በፕሮጀክቶች አፈፃፀም ያገኘነዉን ድል በአገልግሎት አሰጣጥ እና በመልካም አስተዳደር ለመድገም እንተጋለን፡፡

👉ሌብነትንና ብልሹ አሠራር ላይ የጀመርነዉን ትግል አጠናክረን ህዝቡንም በብቃት በማሳተፍ መሰረታዊ ለውጥ ለማምጣት ተግተን በቁርጠኝነት እንሰራለን፡፡

👉 በመሬት ልማት እና አስተዳደር ሥርዓታችን ላይ በቴክኖሎጂ በማስደገፍ መሠረታዊ ለውጥ ለማምጣት የጀመርነዉን ጥረት ይበልጥ ተጠናክሮ  ይቀጥላል፡፡

👉 በሁሉም መስክ የቴክኖሎጂ አጠቃቀማችንን በማሻሻል የንግድ ሥርዓቱን ማዘመን፣ ለኢንቨስትመንት ምቹ አካባቢን በመፍጠር  እንሰራለን ።

👉 የተጀመረዉን የትምህርት ሪፎርም በማጠናከር የትምህርት ጥራት የማረጋገጥ ቀሪ ተግባራትን በልዩ ትኩረት ይፈፀማል፣ እያደገ የመጣዉን የጤና አገልግሎት ይበልጥ የማሻሻልና የማዘመን ሥራ ተጠናክሮ ይቀጥላል።

👉 የኑሮ ውድነትን ለማረጋጋት፣ የሌማት ትሩፋትና የከተማ ግብርናን ማስፋት ተጠናክረው እንዲቀጥሉ ይደረጋል።

👉 የቤት ልማት ፕሮግራሞችን በግል ዘርፉ፣ በሕብረት ሥራ ማኅበራት፣ በመንግስትና በግል የአጋርነት ፕሮግራም በስፋት ተግባራዊ እናደርጋለን።

👉 የኪነ ጥበብ ዘርፉን በማጠናከርና የከተማችንን የቱሪስት መዳረሻ ቦታዎች ይበልጥ በማስተዋወቅ እና እንዲጎበኙ በማድረግ ከዘርፉ ከተማችን ማግኘት የሚገባትን ሁለንተናዊ ፋይዳ እንድታገኝ ይደረጋል፡፡

👉 በከተማችን ጽዳትና ውበት መስክ የተገኘዉን ስኬት በማላቅ ከምንጊዜውም በላቀ ትኩረት ማህበረሰብ አቀፍ አንዲሆን እንሰራለን።

👉 የሥራ ዕድል ፈጠራ ስራችን በተለይም የወጣቶች የሥራ እድል እና አምራች ኢንዱስትሪን የማስፋትና ተወዳዳሪነቱን የማሳደግ ስራ በልዩ ትኩረት ይከናወናል፡፡

👉 ሕብረ-ብሔራዊ ወንድማማችነትና አንድነትን በማጠናከር የከተማችንን ነዋሪ የላቀ ተሳታፊነትና ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ በትጋት እንሰራለን።

👉 በአጠቃላይ ከተማችን ለነዋሪዎቿ ምቹ፣ ሀገራዊ፤አህጉራዊና አለም አቀፍ ሚናዋን በብቃት የምትወጣ፤ስሟና ግብሯ የተናበበባት ስማርት ከተማ እንድትሆን የጀመርነዉን ልማት በጥራት፣ በስፋትና በፍጥነት አጠናክረን እንቀጥላለን፡፡
👍3
የአዲስ አበባ ከተማ የ2017 በጀት 230 ቢሊየን ብር ሆኖ ፀደቀ፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት 3ኛ ዓመት 4ኛ መደበኛ ጉባኤውን እያካሄደ ይገኛል፡፡
ምክር ቤቱ በመደበኛ በስብሰባው የአዲስ አበባ ከተማ የ2017 በጀት ዓመት ረቂቅ በጀትን ተወያይቶ አጽድቋል፡፡

በዚህም የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር አጠቃላይ በጀት 230 ነጥብ 39 ቢሊየን ብር ሁኖ ጸድቋል፡፡

ከጸደቀው በጀት ውስጥ 146 ነጥብ 48 ቢሊየን ብር ለካፒታል፣ 83 ነጥብ 91 ቢሊየን ብር ለመደበኛ ወጪ እንዲሆን አድርጎ የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት አጽድቋል፡፡

የጸደቀው በጀት ከባለፈው 2016 ተመሳሳይ በጀት ጋር ሲነጻጻር የ68 ነጥብ 3 ቢሊየን ብር ብልጫ እንዳለው ተገልጻል፡፡

በጀቱ የኮሪደር ልማት ስራዎችን ለማጠናቀቅ፣የጋራ መኖሪያ ቤቶችን ለማጠናቀቅ፣ ለመጠጥና ውሃ ፍሳሽ፣ለመንገድ መሰረተ ልማት እና ማህበራዊ እድገትን እንደሚውል በረቂቅ በጀቱ ተመላክቷል፡፡
👍5
የኮሚሽኑ አመራሮች ፣ ሰራተኞችና በጎ ፈቃደኞች አረንጓዴ አሻራቸውን አሳርፈዋል።

6ኛው ዙር የአረንጓዴ አሻራ መርሀ ግብር "የምትተክል ሀገር ፥ የሚያፀና ትውልድ!" በሚል መሪ ሀሳብ እየተካሄደ ሲሆን የአዲስ አበባ ከተማ የኀብረተሰብ ተሳትፎና በጎ ፈቃድ ማስተባበሪያ ኮሚሽን 20 ሺህ ችግኞችን ለመትከል አቅዷል።

ኮሚሽኑ በዛሬው ዕለት በእንጦጦ ፓርክ በተካሄደ የአረንጓዴ አሻራ መርሀ ግብር 3 ሺህ ችግኞች ተክሏል።

የምትተክል ሀገር ፣ የሚያጸና ትውልድ!
👍2