የኀብረተሰብ ተሳትፎና በጎ ፈቃድ ማስተባበሪያ ኮሚሽን - አዲስ አበባ
809 subscribers
2.14K photos
47 videos
265 links
Download Telegram
የኀብረተሰብ ተሳትፎና በጎ ፈቃድ ማስተባበሪያ ኮሚሽን - አዲስ አበባ
Photo
"በጎነት እና አብሮነት ለከተማችን ከፍታ"

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የ2016 ዓ/ም የክረምት በጎ ፈቃድ አገልግሎትን ስኬታማ በማደረግ የህዝባችንን የመረዳዳትና የመደጋገፍ እሴት ከፍ ለማድረግ ባለድርሻ አካላት በዕቅዱ ላይ መክረዋል::

በብልፅግና ፓርቲ የአዲስ አበባ ቅ/ፅ/ቤት ምክትል ሀላፊ እና የፖለቲካ ዘርፍ ሀላፊ አቶ አለማየሁ እጅጉ በውይይቱ ላይ እንደተናገሩት የበጎ ፈቃድ አገልግሎትን ዓመቱን ሙሉ ለማከናወን ጥረት ሲደረግ መቆየቱን ገልፀው ከተማችን በበጎ ስራዎቿ በአገር አቀፍ እና በዓለም አቀፍ ደረጃ ተሞክሮ የሚቀሰምባት መሆን መጀመሯን አመላክተዋል።

በየደረጃው የሚገኘው አመራር የተደራጀ አመራር በመስጠቱ እና የህዝባችን ተሳታፊነትም ከጊዜ ወደ ጊዜ በማደጉ አበረታች ውጤት መመዝገቡን የገለፁት አቶ አለማየሁ በቀጣይም በጥበቃ ዲሲፕሊን በመምራት ለህዝባችን ኑሮ መሻሻል ያለውን አቅም መጠቀም እንደሚገባ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል።

በብልፅግና ፓርቲ የአዲስ አበባ ቅ/ፅ/ቤት የአደረጃጀት ዘርፍ ሀላፊ አቶ ይመር ከበደ በበኩላቸው ቀጣይነት ባለው መልኩ እየተከናወኑ ያሉ የበጎ ፈቃደኝነት ተግባራት ከዘላቂ ዕድገት እና ከከተማ ዕድገት ጋርም የተጣጣሙ መሆናቸውን በመጠቆም በብዛትም በጥራትም ከፍ በማድረግ ለአዲስ አበባ ማርሽ ቀያሪ መሆናቸውን ማረጋገጥ እንደሚገባ አስገንዝበዋል።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የህብረተሰብ ተሳትፎና በጎ ፈቃድ ማስተባበሪያ ኮሚሽን ኮሚሽነር አብርሃም ታደሰ የከተማ አስተዳደሩን የ2016 ዓ/ም የክረምት በጎ ፈቃድ አገልግሎት ዕቅድ ሲያቀርቡ እንደገለፁት ባለፉት ወራት ሚሊዮኖችን በበጎ ፈቃድ አገልግሎት በማንቀሳቀስ በቢሊዮን የሚገመት ሀብት በማሰባሰብ ሚሊዮኖችን ተጠቃሚ ማድረግ መቻሉን አስረድተዋል።

የዘንድሮው የክረምት ወራት የበጎ ፈቃድ አገልግሎት ክብርት ከንቲባ አዳነች አቤቤ እና ሌሎችም ከፍተኛ አመራሮች እያስተባበሩት ከግንቦት 18 ጀምሮ በተለያዩ ተግባራት እየተከናወነ መሆኑ የተጠቀሰ ሲሆን በቤት እድሳት፣ በልዩ ድጋፍ ፣ በአረንጓዴ አሻራ ፣ በአካባቢ ፅዳት ፣ በጤና ተቋማት ነፃ አገልግሎት በመስጠት ፣ በማስተማር ፣ በሰላም ፣ ማህበራዊ ሚዲያን ለበጎ ዓላማ በማዋል ፣ የህይወት ልምዴን አካፍላለሁ በሚሉና በሌሎችም 15 ፕሮግራሞች የህዝባችንን የመረዳዳት እሴት ለማጎልበት ሁሉም ባለድርሻ አካላት የተቀናጀ ጥረት ሊያደርጉ እንደሚገባ ተገልጿል።
👍92
የኀብረተሰብ ተሳትፎና በጎ ፈቃድ ማስተባበሪያ ኮሚሽን - አዲስ አበባ
Photo
በክረምት የበጎ ፈቃድ አገልግሎት በአዲስ አበባ 9 ሺህ 100 ጎልማሶችን ተጠቃሚ የሚያደርግ የጎልማሶች መሰረታዊ ትምህርት መርሃ ግብር ይፋ ተደረገ።

አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 8/2016 ዓ.ም
በአዲስ አበባ በክረምት የበጎ ፈቃድ አገልግሎት 9 ሺህ 100 ጎልማሶችን ተጠቃሚ የሚያደርግ የጎልማሶች መሰረታዊ ትምህርት ማስጀመሪያ የንቅናቄ መድረክ በዛሬው ዕለት ተካሂዷል።

በንቅናቄ መድረኩ ላይ የብልፅግና ፓርቲ አዲስ አበባ ቅርንጫፍ ፅህፈት ቤት ምክትል ኃላፊ አቶ አለማየሁ እጅጉን ጨምሮ የአዲስ አበባ ከተማ ትምህርት ቢሮ ኃላፊ ዶ/ር ዘላለም ሙላት ፣ የህብረተሰብ ተሳትፎና በጎ ፈቃድ ማስተባበሪያ ኮሚሽን ፅ/ቤት ኃላፊ አቶ ስመኘው አድነው እንዲሁም የከተማና የክፍለ ከተማ የስራ ኃላፊዎች ተገኝተዋል።

በከተማችን ማንበብና መፃፍ የማይችል አንድም ዜጋ መኖር የለበትም ያሉት የብልፅግና ፓርቲ አዲስ አበባ ቅርንጫፍ ፅህፈት ቤት ምክትል ኃላፊ አቶ አለማየሁ እጅጉ ፕሮግራሙን ስኬታማ ለማድረግ በየደረጃው ያሉ ባለድርሻ አካላት ርብርብ እንዲያደርጉና ተግባሩ በጥብቅ ዲሲፕሊን እንዲመራ አቅጣጫ አስቀምጠዋል

የከተማዋ ትምህርት ቢሮ ኃላፊ ዶ/ር ዘላለም ሙላት በበኩላቸው የአንዲት ሀገር እድገትና ለውጥ የሚለካው የተማረና የሰለጠነ ዜጋ ሲኖር መሆኑን ጠቁመው የጎልማሶች መሰረታዊ ትምህርት ትኩረት ተሰጥቶት እንደሚተገበር ተናግረዋል።

በክረምት የጎልማሶች መሰረታዊ ትምህርት 303 በጎ ፈቃደኞችንና ከ500 በላይ አመቻቾችን በማሳተፍ ለ9 ሺህ 100 ዕድሜያቸው ከ15-60 የሆኑ ጎልማሶችን ተጠቃሚ ያደርጋል።

ትምህርቱን ለ240 ሰዓት በተዘጋጁ ከ333 በላይ የጎልማሶች ትምህርት መማሪያ ጣቢያዎች ለመስጠት እቅድ መያዙ በመድረኩ ተመላክቷል።

የማህበራዊ ሚዲያ ገፆቻችን ቤተሰብ እንዲሆኑ እንጋብዛለን! አጋርነትዎን የበጎነትና የህብረተሰብ ተሳትፎ ግቦቻችን በመደገፍ ወይም ገንቢ አስተያየትዎን በመለገስ ያረጋግጡ!!

ፌስቡክ - https://www.facebook.com/cpvcc.2015
ቴሌግራም - https://t.me/CommunityPVC
ቲክቶክ - https://www.tiktok.com/@voluntarismaddis16
ዩቱዩብ - https://youtube.com/@communityparticipationvolu8714
ዌብሳይት - www.volunteeraddis.et
Instagram - https://www.instagram.com/communitypv/
Twitter - https://x.com/Volunteeraddis
👍1
የኀብረተሰብ ተሳትፎና በጎ ፈቃድ ማስተባበሪያ ኮሚሽን - አዲስ አበባ
Photo
"ያለ ህዝብ ብቁ ተሳትፎ የሚከናወን ስራ ሙሉ ሊሆን አይችልም!" ከንቲባ አዳነች አቤቤ

በመዲናዋ 11 ሺህ ምልምል የሰላም ሠራዊት አባላት ተመረቁ። የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር 11 ሺህ ምልምል የሰላም ሠራዊት አባላትን አስመርቋል።

በምረቃ መድረኩ ላይ የተገኙት የአዲስ አበባ ከንቲባ አዳነች አቤቤ ሰላማችንን ዘላቂ እና ህዝባዊ መሰረት ያለው ለማድረግ ዛሬ አሰልጥነን ያስመረቅናቸው 11 ሺሕ አዲስ ምልምል የሠላም ሠራዊት አባላትን ጨምሮ 341 ሺሕ የሠላም ሠራዊት አባላትን የከተማችን የሰላም ዘብ አድርገን አሰማርተናል ሲሉ ተናግረዋል።

ከ2013 ጀምሮ ሕዝባችንን በተደራጀ መልኩ ከጸጥታ ኃይሉ ጋር ማቀናጀት እና የሰላሙ ዋነኛ ባለቤት ማድረግ መቻላችን እስካሁን ካስገኙን ውጤታማ እና ስኬታማ ስራዎች በተጨማሪ ከተማችንን ለነዋሪዎቿ ምቹ እና ሰላማዊ ማድረግ ችለናል ያሉት ከንቲባዋ ዛሬ የተመረቃችሁ የሰላም ሰራዊት አባላት ሕዝባችን የሰላሙ እና የተሰሩ መሰረተ ልማቶች ባለቤትና ቀዳሚ ተጠቃሚ መሆኑን በመረዳት በየአካባቢያችሁ የሰላምና የመሰረተ ልማቱ ዘብ በመሆን ህዝባችሁን በፍፁም ትህትና እና ፍቅር እንድታገለግሉ አደራ ማለት እወዳለሁ ብለዋል።

የማህበራዊ ሚዲያ ገፆቻችን ቤተሰብ እንዲሆኑ እንጋብዛለን! አጋርነትዎን የበጎነትና የህብረተሰብ ተሳትፎ ግቦቻችን በመደገፍ ወይም ገንቢ አስተያየትዎን በመለገስ ያረጋግጡ!!

ፌስቡክ - https://www.facebook.com/cpvcc.2015
ቴሌግራም - https://t.me/CommunityPVC
ቲክቶክ - https://www.tiktok.com/@voluntarismaddis16
ዩቱዩብ - https://youtube.com/@communityparticipationvolu8714
ዌብሳይት - www.volunteeraddis.et
Instagram - https://www.instagram.com/communitypv/
Twitter - https://x.com/Volunteeraddis
👍4
ለመላው የእስልምና እምነት ተከታዮች እንኳን ለ1445ኛው ዓመተ ሒጅራ ኢድ-አል-አድሃ (አረፋ) በዓል በሰላም አደረሳችሁ።

በዓሉ የሰላም ፣ የፍቅር ፣ የአብሮነትና የመተሳሰብ እንዲሆንላችሁ እንመኛለን!

የህብረተሰብ ተሳትፎና በጎ ፈቃድ ማስተባበሪያ ኮሚሽን
👍4
“ቅን ልቦች”

በበጎነት ተግባራት ላይ ያተኮረ ዘጋቢ ፊልም ዛሬ ምሽት ከ3፡10 ሰዓት ጀምሮ በአዲስ ሚዲያ ኔትወርክ ይጠብቁን!
“በጎ ፈቃደኝነት ለማህበረሰብ ለውጥ!”
👍9
ዛሬ ምሽት በአዲስ ሚዲያ ኔትወርክ ሊተላለፍ የነበረው "ቅን ልቦች" ዘጋቢ ፊልም በፕሮግራም መጣበብ ምክንያት ወደሌላ ጊዜ የተሸጋገረ መሆኑን ለክቡራን ደንበኞቻችን ከይቅርታ ጋር እንገልፃለን!
👍3
የክፍት የስራ ማስታወቂያ!

መስሪያ ቤታችን የህብረተሰብ ተሳትፎና በጎ ፈቃድ ማስተባበሪያ ኮሚሽን ከዚህ በታች በተዘረዘሩ ክፍት የስራ መደቦች አመልካቾችን በቋሚነትና በኮንትራት አወዳድሮ መቅጠር ይፈልጋል።

የስራ መደቦቹን ተፈላጊ መስፈርት የምታሟሉ ስራ ፈላጊዎች ይህ ማስታዎቂያ ከወጣበት ከዛሬ ሰኔ 11/2016 ዓ.ም ጀምሮ ባሉት 5 ተከታታይ የስራ ቀናት የትምህርት ማስረጃችሁን ዋናውንና የማይመለስ ፎቶ ኮፒ በመያዝ ፒያሳ እሪ በከንቱ በሚገኘው ቢሯችን ቢቲ ታዎር 3ኛ ፎቅ የሰው ኃብት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ቢሮ ቁጥር 03-04 በአካል በመቅረብ ማመልከት ይኖርባችኋል።

ከግል ድርጅቶች ለሚቀርብ የስራ ልምድ ማስረጃ የስራ ግብር ስለመከፈሉ ከግብር ሰብሳቢው አካል ማስረጃ ማቅረብ ይጠበቃል።

በሌቭል ደረጃ ለተመረቃችሁ COC ማቅረብ ይኖርባችኋል።

የህብረተሰብ ተሳትፎና በጎ ፈቃድ ማስተባበሪያ ኮሚሽን!
👍71
"የቤት ልማትና ማስተላለፍን በሚመለከት በመንግስት አስተባባሪነት በ20/80 ፕሮግራም 2,087 ቤቶች፣ በ40/60 ፕሮግራም 2,966 ቤቶች፣ በወጪ ቆጣቢ እና በበጎ ፈቃድ 7,582 ቤቶች፣ ለኪራይ አገልግሎት 5,000 ቤቶች በአጠቃላይ 17,635 ቤቶች በመንግስት በጀት እና አስተባባሪነት ተገንብቶ ለልማት ተነሺዎች እና ለሌሎች ተጠቃሚዎች የማስተላለፍ ሥራ ተሰርቷል። "
👍21
"ከ1 ሚሊዮን በላይ በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ላይ ለሚገኙ ኅብረተሰብ ክፍሎች ማዕድ ለማጋራት ታቅዶ ለ1.2 ሚሊዮን ዜጎች ማዕድ ማጋራት የተቻለ ሲሆን በአጠቃላይ በሰው ተኮር እና በጎ ፈቃድ ሥራችን 11.1 ቢሊዮን ብር የበጎ ፈቃድ አገልግሎት ለ1.7 ሚሊዮን ዜጎች ለመስጠት ታቅዶ 12.6 ቢሊዮን ብር የበጎ ፈቃድ ተግባራት በማከናወን የከተማችንን ነዋሪዎች ተጠቃሚ ማድረግ ተችሏል።" ከንቲባ አዳነች አቤቤ
👍21
የትራፊክ ህጎችን በማክበር ራስዎን ከድንገተኛ አደጋ ይጠብቁ!

የአራዳ ክፍለ ከተማ የትራፊክ አገልግሎት በጎ ፈቃደኞች እግረኞችን መንገድ በማሻገርና የትራፊክ መጨናነቁን በማሳለጥ አገልግሎት ሲሰጡ!

"በጎ ፈቃደኝነት ለማኀበረሰብ ለውጥ!"
👍4