CHANNEL 29
25.2K subscribers
19.5K photos
2.93K videos
44 files
2.29K links
Download Telegram
ስለ ዴክሳሜታዞን ጉዳይ: አሁንም እንጠንቀቅ
[መድሀኒቱ ተዓምራዊ ፈውስ እንዳልሆነ ልብ እንበል]
.
ዛሬ ከእንግሊዝ አገር ስለተሰማው መልካም ዜና ብዙዎቻችን እንደሰማን እርግጠኛ ነኝ። ዜናው በአጭሩ የሚለው ዴክሳሜታዞን የሚባለው በአለም ዙሪያ በስፋት ለሌሎች አገልግሎቶች የሚውለው መድሃኒት በኮቪድ ፅኑ ህመም ላይ ላሉ ታካሚዎች ቢሰጥ የሞት ቁጥር በ1/3ኛ እነደሚቀንስ አሳይቷል።
.
ጥናቱ በበርካታ ህሙማን የተደረገና ተቀነባይነቱ ከፍተኛ ስለሆነ እጅግ ግሩም ዜና ቢሆንም ጥቂት ማብራሪያዎች ግን ልብ ማለት ያሻል:-
.
1. የጥናቱ ትኩረት የኮቪድ ሞትን መቀነስ በመሆኑ ያተኮረው የሞት አደጋ ያለባቸውን ፅኑ ሕሙማንን ነው። ጠቀሜታውም በተለይ ለእነዚህ ፅኑ ህሙማን እንጂ ለሁሉም የኮቪድ ህሙማን አይደለም። ቀላል ህመም ላላቸው ሰዎች አልተመከረም፣ እንዲሁም ለመከላከል ቢውል ከጥቅሙ ጉዳቱ ሊያመዝን ይቻላል።
.
2. ይሄም መድሃኒት ሆኑ ወንድሞቹ (steroids) ከሌሎች መድሃኒቶችም በሚልቅ መልኩ በርካታ የጎንዮሽ ጉዳት ያስከትላሉ። የሞት አፋፍ ላይ ላሉ ህሙማን ከጉዳቱ ጥቅሙ ቢያመዝንም ለሌሎች ግን ጎጂ ሊሆን ይችላል። በተጨማሪም ለብዙዎቹ ፅኑ ህሙማን ቢጠቅምም የተወሰኑትን ግን ጭራሽ አባብሶ ለሞት ሊያበቃ እንደሚችል እናስተውል:: እንዲሁም ከእነዚህ መድሃኒቶች መጥፎ የጎንዮሽ ጉዳት አንዱ የሰውነትን የመከላከያ ሃይል ማዳከም ስለሆነ ምናልባትም የህመሙ ጅማሬ ላይ ከተሰጠ ጭራሽ የቫይረሱን የመራባት አቅም አባብሶ ለአደጋ ሊዳርግ እንደሚችል መላ ምት አለ።
.
3. ይሄ መድሃኒት አገራችንን ጨምሮ በአለም ዙሪያ በስፋት የሚገኝ መሆኑ የዜናው አስደሳች ጎኑ ነው። ሌላኛው ጠቀሜታ እንዳለው የተጠቆመው ሬምዴሲቪር የተባለው መድሃኒት እጅግ ውድና ለአገራችን የማይታሰብ ነበር።
.
4. አብዛኞቹ የዜና አውታሮች ላይ ዜናው ሞቅሞቅ ተደርጎ ቢቀርብም "ተዓምራዊ ፈውስ "(miracle cure) እንዳልሆነ ልብ እንበል። በጥናቱ እንደታዬው ለምሳሌ
.
- የእስትንፋስ እገዛ ካስፈለጋቸው ሰዎች በአማካይ ከመቶ ውሰጥ አርባዎቹ የሚሞቱ ሲሆን በአንፃሩ ይሄ መድሃኒት ከተሰጣቸው ውስጥ የሚሞቱት 28ቱ ናቸው። ከመቶ ፅኑ ህሙማን 12ቱ በዚህ የተነሳ ተረፉ ማለት ነው። ቀላል አይደለም፣ ተኣምራዊ ፈውስ ግን አይደለም።
.
- የኦክስጅን እገዛ ካስፈለጋቸው ሰዎች ከመቶ 25ቱ የሚሞቱ ሲሆን፣ በዚህ መድሃኒት የሟቾች ቁጥር ወደ20 ይወርዳል። እዚህኛው ላይ ጠቀሜታው ዝቅ ያለ ነው።
.
4. ይሄ ጥራቱን የጠበቀ ምርምር እንደሆነ ቢነገረም እርግጠኛ ሆኖ መናገር የሚቻለው ሌሎች መጠነሰፊ ምርምሮች በተግባር ላይ ከዋለ በኋላ ሲያረጋግጡት ብቻ ነው። ነገርግን "ብልጥ ልጅ የሰሰጡትን ይዞ ያለቅሳል" ስለሆነ እስከዛው መልካም ዜና ነው።
.
Dr. Abiy Meaza, Internist/hospitalist
Morristown and Saint Barnabas Medical Centers, New Jersey, USA

#Hakim

|CHANNEL29----------------CHANNEL29|
ከቻነሌ ዜና እየወሰዳቹ የራሳችሁ ላይ የምትለቁ ሰዎች ለቻነሌ ክሬዲት ብትሰጡ ምንጭም ብትጠቅሱ ጥሩ ነው....

የራስህ ያልሆነን ዜና ወይም ሀሳብ እንደራስ አርጎ ማቅረብ ነውር ነው....
ይህን ምስል በጣም ብዙ ሰው እያየ ለመቀለድ ሲሞክር አንዳንዶችም ሀይሌ እኮ የሀገር ባለውለታ ነው ለምን እንደዚህ ይፈተሻል ሲሉ አየው.... በጣም የሚገርመው ደግሞ የተማረውም ያልተማረው ስለ Security protocol ምንም አለማወቃቸው ነው......

ይህ የፖሊስ አባል ስራውን በአግባብ ስለ ሰራ ሊደነቅ እንጂ ሊብጠለጠል አይገባውም...

ልክ የዛሬ አመት የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳደር ባመኑት ሰው እንደተገደለ ስንቶቻችን ዘንግተን ይሆን?

ብርጋዴር ጄኔራል አሳምነው ፅጌን ተጠሪነታቸው ለክልሉ ፕሬዝዳንት ሆኖ ለአጭር ጊዜ በቆዩበት የአማራ ክልል የጸጥታ ቢሮ ኃላፊ ሆነው እንዲያገለግሉ ሹመት ሰጥቷቸው ከነበር በኋላ ዶ/ር አምባቸውን(የወቅቱ የአማራ ክልል ፕሬዝዳንት) ገድለዋል..

👉ሀይሌ በጣጣጣም የተከበረ ሀገርን የሚወድ ሀገሩን ያስጠራ እና ምስጉን ሰው ነው።ሀይሌና አሳምነው በፍፁም ሚነፃፀሩ ሰዎች አይደሉም ምሳሌው ግን የሰጠኋቹ ሁሌም ቢሆን ጥንቃቄ ግዴታ መሆኑን እንድታውቁ ነው!

መቼም ሀይሌና ደብረፅዮን ካላቸው ግንኙነት አምባቸውና አሳምነው የነበራቸው ቅርበት በእጅጉ ይልቃል!ካለፈው ስህተት የማይማር ደግሞ ፈንጅ አምካኝ ብቻ ነው!

👉አብይ ትግራይ አይሄድም እንጂ ቢሄድ ከዚህ በላይ ይፈተሻል...

ይህ የ PROTOCOL ጉዳይ ነው እና ለምን ይፈተሻል ምናምን ብላችሁ ምታለቃቅሱ ሰዎች ምክንያታዊ ሁኑ

|CHANNEL29----------------CHANNEL29|
CHANNEL 29
EBC’s head of Tigrinya TV department resigned citing increased pressure and interference. He said he has reached a point where he couldn’t perform his duties professionally. Recently, FBC mekelle branch complained the media house is censoring news from Tigray…
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ከ 10 አመት በላይ በ EBC ያገለገለው ጋዜጠኛ ሃይለማርያም በሚደርስበት የውሸት ዜና ስራ ጫና ከሀላፍነቱን መልቀቁን ነግርያችሁ ነበር.....

አሁን EBC ውስጥ የሚደረገውን ጉድ ዘርግፎላቸዋል!

#7MB (ሙሉ ቪድዮ)

|CHANNEL29----------------CHANNEL29|
"ከትግራይ ህዝብ ይልቅ ኢሳያስ አፈወርቂ የሚቀርበው ሰው ነው ቤተ-መንግስት ውስጥ ያለው። ከኢሳያስ ጋር ግንባር ፈጥሮ ትግራይ ለመውጋት ያለው እንቅስቃሴ በቅርብ ርቀት እያየን ነው።"
ትናንት በመቐለ በተካሄደው ሽምግልና ዶ/ር ደብረፅዮን የተናገሩት

|CHANNEL29----------------CHANNEL29|
CHANNEL 29
Photo
በቃ እኔ የኢትዮጵያ ፖለቲካ አልገባኝም ማለት ነው። ጡረታ መውጣት ሳይኖርብኝ አይቀርም…


እንደራደር ተባለ። አይ ድርድሩ ሁሉንም ያካተተ ይሁን የሚል መልስ ተሰጠ። ታድያ ይሄ ሁሉ ጫጫታ ምንድን ነው? እውን ኢትዮጵያ ሐገር ዓቀፍ ውይይት (dialogue) አያሻትም? እውነት ኢትዮጵያ ሕወሐት ብቻ ነው ያለባት ችግር? ከሰሜን ጫፍ እስከ ሞያሌ ችግር እስከ አፍጢሟ ሞልቷት የለም እንዴ? ሁላችንም ተቀምጠን ችግሩን አፍረጥርጠን እንነጋገር ማለት ምኑ ነው «ሽምግልና መግፋት» የሆነው?

ሕወሐት ሌባ ናት፣ ባንዳ ናት… ምናምን እያሉ አጉል ፕሮፖጋንዳ ከመስራት ሐገር ዓቀፍ ውይይት ጠርቶ ሌብነቷን ለምን ፊትለፊቷ አትነግሯትም? ባንዳነቷን፣ የግብፅ ተላላኪነቷን እዛው ሐገር ዓቀፍ ውይይቱ ላይ በመረጃና ማስረጃ ማጋለጥ አይቻልም?


ሽምግልናው ዓላማው ዳያሎግ እንዲጀመር ነው እንጂ «በቃ አንተም ተው አንተም ተው!» ዓይነት የሰፈር ግሩፕ ፀብ ሽምግልና ነው እንዴ? ሽማግሌዎቹ ሕወሐትን ድርድር አድርጊ ሲሏት ሕወሐት «ያው የመጣችሁት ከዘገየ በኋላ ነው። ግን በቃ ውይይቱ ሰፋ ይበልና ለሕዝብም በይፋ የሚቀርብበት መንገድ ይመቻች!» ብላ መልስ ሰጠች። ታድያ ምን እንድትል ተፈልጎ ነበረ እዚህ ሰፈር ለቅሶ የበዛው?


ተነጋግረን ችግራችንን እንፍታና ወደ ውጫዊ ጠላታችን ባንድነት እንዝመት ሲባል ውይይቱን ጠልቶ፣ ራስን እንደ ብቸኛ «ለሐገር ተቆርቋሪ» ቆጥሮ ሌላውን በባንዳነት እየፈረጁ «አስጠቁን!» ምናምን ማለት ሲምፕሊ ነገር መፈለግ አይደለም እንዴ?


እንወያይ ተብሏል። Of all the people, «ችግርን በውይይት መፍታት የኛ መለያ ነው!» የምትሉ የኢዜማና ብልፅግና ደጋፊዎች ሕወሐት ለዚህ ላልለመደባት ዓመል ፈቃደኛ ሆና ምላሽ በመስጠቷ ፈጣሪን እያመሰገንን ውይይት ተደርጎ በሰላማዊ መንገድ ሐሳባችሁ እንዲያሸንፍ መዘጋጀቱ አይሻላችሁም?

#YONAS_HAGOS

|CHANNEL29----------------CHANNEL29|
በታንዛኒያ በመጭው ጥቅምት ወር የሚካሄደው ምርጫ እንደማይራዘም ፕሬዝዳንቱ ገለጹ!

የታንዛኒያው ፕሬዘዳንት ማጉፉሊ በመጭው ጥቅምት ወር ከሚካሄደው የሀገሪቱ ምርጫ ቀደም ብለው ፓርላማውን መበተናቸውን ሲጂቲኤን ዘግቧል፡፡

ፕሬዘዳንቱ የሀገሪቱ መንግስት በመሰረተ ልማት ማስፋፋት ማለትም በኤሌክትሪክ ማመንጨትና የማእድን ዘርፉን በማሻሻል ትልቅ ስራ መስራታቸውን እየገለጹ ይገኛሉ፡፡

ፕሬዘዳንት ማጉፉሊ ምስራቅ አፍሪካን በመንገድና በባቡር ለማገናኘት ያቀዱትን እቅድ ጨምሮ ሌሎች ትልል ፕሮጀክቶችን በመትለማቸው “ዘቡልዶዘር” የሚል ስያሜ ተሰጥቷቸዋል፡፡

#AlAin #CGTN

|CHANNEL29----------------CHANNEL29|
ህወሓት ላይ ያለህ አስተያየት ምንድነው ላላቹን

👉ህወሓት ወንጀል ሰርቷል ላላችሁኝ መልሴ አዎ

👉ወንጀል እንደሰራ ካመንክ ለምን እንዲታሰሩ አትፈልግም ላላችሁኝ እፈልጋለው ግን እኔ እንደናንተ በጭፍኑ አይደለም እንደዛ ምለው

የህወሓት አመራሮች ከታሰሩ አብረው ሲያሽቃብጡ የነበሩት ከጠ/ሚ አበይ ጀምሮ በሙሉ የብልፅግና አመራሮችም መታሰር አለባቸው....አብረው ስለሆነ ስራውን የሰሩት!

አለበለዝያ ግን ለህወሓት ብቻ ተብሎ የሚወጣ ህግ የለም

አብረህ ገለህ እና መዝብረህ ከሳሽ ሆነህ መቅረብ አይጥመኝም.... ማይዋጥላቹ ሰዎች ትኖራላችሁ ግን ዋጡት!

በነገራችን ላይ ሁሉም ክልል እንደ ህወሓት ጠንካራ መንግስት ቢኖረው ምኞቱ ነው ያው እሱ ሲያቅታቸው ግን ጣታቸውን መልሰው ወደ ህወሓት ይቀስራሉ..የኢትዮጵያ ፖለቲካ ኮሜዲም ትራጄዲም የተሞለበት መሆኑ ይገርመኛል

|CHANNEL29----------------CHANNEL29|
Audio

ወደ መቐለ የተጓዘው የሽምግልና ቡድን ምን ውጤት አስገኘ ?


#Ethiopia #ShegerWerewoch #መቐለ #የሽምግልና_ቡድን

|CHANNEL29----------------CHANNEL29|

የአዲስ አበባው ኢንተርኮንቲኔንታል ሆቴል ስያሜውን እንዲሰርዝ በፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ተወሰነበት፡፡

ሸገር ከፍርድ ቤቱ የውሳኔ ሰነድ እንደተረዳው የአዲስ አበባው ኢንተርኮንትኔንታል ሆቴል ስሙን ያለ ፈቃድ በመጠቀሙ፣ ለዓለም አቀፉ የኢንተርኮንትኔንታል ኮርፖሬሽን የ13 ዓመት ሮያሊቲ ወይም ስሙን በመጠቀም የሰበሰበውን ገንዘብ እንዲከፍል በፍርድ ቤት ተወስኖበታል።

አምስት ኮከብ ያለው የአዲስ አበባው ኢንተርኮንትኔንታል ሆቴል ከእንግዲህ ስያሜውን መጠቀም እንዲያቆምም ተወስኗል።

የአዲስ አበባው ኢንተርኮንትኔንታል ሆቴል እስከዛሬ ስያሜውን ያለ ፈቃድ በመጠቀሙ ሳቢያ ለዓለም አቀፉ የኢንተርኮንትኔንታል ኮርፖሬሽን ሮያሊቲ ከፍተኛ መጠን ያለው ዶላር ሊከፍል እንደሚችል ተሰምቷል።

የአዲስ አበባው ሆቴል በስሙ የከፈተውን ድረገጽ እንዲዘጋ እና ማንኛውንም ማስታወቂያዎች እንዲያነሳ መወሰኑንም ሸገር ከዓለም አቀፉ ኢንተርኮንትኔንታል ሆቴልስ ኮርፖሬሽን ጠበቃ ከአቶ ኢዮብ ሐጎስ ሰምቷል፡፡

ባለፈው ዓመት በዓለምአቀፉ ኢንተርኮንትኔንታል ኮርፖሬሽን አሸናፊነት ሆቴሉ ስያሜውን እንዲሰርዝ መወሰኑ ይታወሳል። ሆቴሉ ይግባኝ ቢጠይቅም፣ የፌደራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት የስር ፍርድ ቤቱን ውሳኔ አጽንቶታል፡፡

ዓለም አቀፉ ኢንተርኮንትኔንታል ኮርፖሬሽን ከስምንት ዓመታት በፊት በኢትዮጵያ በንግድ ምልክት ባለቤትነት መመዝገቡን ሸገር ሰምቷል፡፡

#Sheger

|CHANNEL29----------------CHANNEL29|
ታኬ አዲስ አበባ ላይ የከተማ ግብርና እየሰራነው ያለው ብሎ የለቀቀው ምስል ከውጪ የተገኘ 1 Photo ነው

እናማ ታኬ(የፎቶ ሰው) ያልሰራኸውን ሰራው ብለህ አታውራ ለፎቶ አትቸኩል

|CHANNEL29----------------CHANNEL29|
በቅርብ ግዚያት በምስራቅ አፍሪካ አዳዲስ ሀገራት ይፈጠራሉ እንኳን ባልል ትግራይ ግን እንደ ሀገረ መንግስት (De Facto state ) act ማድረግ የምትችልበት ሁኔታ ይፈጠራል:: ይህም በምስራቅ አፍሪካ ትልቅ የጂኦ ፖለቲካ ለውጥ ያመጣል::(ቃል በቃል አይደለም)

በኢትዮጵያ የምርጫ ቦርድ የተመዘገቡም ያለተመዘገቡም ሁሉም የትግራይ የፖለቲካ ፓርቲዎች ትግራይ ውስጥ በሚቋቋሙት የምርጫ ተቋማት ተመዝግበው ትግራይ በምታካህደው ምርጫ ላይ ይሳተፋሉ:: በዚህ ትግራይ ነፃ: ግልፅ እና ፍትሓዊ ምርጫ ታካህዳለች

ኣቶ ጌታቸው ረዳ

#MedhinGebreslassie

nᷡeͤwꙻsᷤ|🅲🅷🅰🅽🅽🅴🅻 29|Blᷝoⷪgᷚsᷤ
¤በከፊል ወደ ግል ለሚዛወረው ኢትዮ ቴሌኮም 4 ዐለም ዐቀፍ አማካሪ ኩባንያዎች እንደቀረቡ ፎርቹን ዘግቧል፡፡ ኧርነስት ኤንድ ያንግ አንዱ ኩባንያ ሲሆን፣ ከሌሎች ዝቅተኛ ዋጋ አቅርቧል፡፡ አሸናፊው አማካሪ ኢትዮ ቴሌኮሙ በከፊል ወደ ግል የሚዛወርባቸውን መመሪያዎች ያዘጋጃል፤ ከታክስ እና ኮንትራት ጋር የተያያዙ የሕግ ጉዳዮችንም ያከናውናል፡፡

¤የተመድ ሰብዓዊ መብቶች ካውንስል ዛሬ በአሜሪካዊያን ጥቁሮች ላይ በሚፈጸመው ዘር ተኮር የሰብዓዊ መብት ጥሰት ላይ ክርክር እንደሚያደርግ ከዲፕሎማቲክ ምንጮች ሰምተናል፡፡ በአሜሪካ እና በሌሎች ሀገራት ለሚፈጸመው ዘር ተኮር የመብት ጥሰት፣ ካውንስሉ ገለልተኛ አጣሪ ኮሚሽን እንዲያቋቋም የአፍሪካ ሀገራት ቡድን የውሳኔ ሃሳብ እንደሚያቀርብ ይጠበቃል፡፡ አሜሪካ አንዳንድ የአውሮፓ ሀገራት ግን የአፍሪካው ቡድን በውሳኔ ሃሳቡ የአሜሪካን ስም እንዳይጠቅስ ጫና እያደረጉ እንደሆነ ተሰምቷል፡፡

[ዋዜማ ራዲዮ]

nᷡeͤwꙻsᷤ|🅲🅷🅰🅽🅽🅴🅻 29|Blᷝoⷪgᷚsᷤ
ትናንት ወደ መቀሌ የተጓዘው የሀይማኖት መሪዎችና የሀገር ሽማግሌዎች ስብስብ ከፌዴራል መንግስት ጋር ለመነጋገር ጥያቄ ማቅረቡን አስታወቀ።

nᷡeͤwꙻsᷤ|🅲🅷🅰🅽🅽🅴🅻 29|Blᷝoⷪgᷚsᷤ

ጥያቄዎች ሁሉ በንግግርና በሰላም መፈታት አለባቸው በሚል ፣ በአሁኑ ወቅት በትግራይና በፌደራል መንግስት መካከል የሚስተዋለው ፍጥጫ ወደ ግጭት የማምራት አዝማሚያ በማሳየቱ ቅድሚያ እንደተሰጠው ተገልጿል
👇
https://p.dw.com/p/3dvOu?maca=amh-RED-Telegram-dwcom
🖍በህዳሴው ግድብ ላይ በሦስቱ ሀገራት ሲካሄድ የነበረው ድርድር በህጋዊ ጉዳዮች ላይ ስምምነት ሳይደረስ መጠናቀቁን ሱዳን አስታወቀች።

በሱዳን አነሳሽነት በታላቁ የህዳሴ ግድብ ዙሪያ በኢትዮጵያ ፣ ሱዳን እና ግብፅ የውሃ ሚነስትሮች መካከል ሲካሄድ በነበረው ድርድር በአብዛኛው ጉዳዮች ላይ መግባባት ቢደረስም በህጋዊ ጉዳዮች ላይ ግን መግባባት እንዳልተቻለ የሱዳን የውሃና መስኖ ሚኒስቴር ገልጿል።

ሚኒስትሩ ያሰር አባስ (ፕ/ር) ምሽት በሰጡት መግለጫ ውይይቱ በብዙ ጉዳዮች ላይ በተለይም በቴክኒክ ጉዳይ 95 በመቶ መግባባት የተደረሰበት ነው ብለዋል። መግባባት ያልተደረሰባቸው የህግ ጉዳዮች በመሪዎች ደረጃ ፖለቲካዊ እልባት እንዲሰጥባቸው ጉዳዩ ወደ ሦስቱ ሀገራት መሪዎች መላኩንም ሚኒስትሩ ገልጸዋል።

ምንጭ : አልአይን

nᷡeͤwꙻsᷤ|🅲🅷🅰🅽🅽🅴🅻 29|Blᷝoⷪgᷚsᷤ