Mark 16
6: እርሱ ግን፦ “አትደንግጡ፤ የተሰቀለውን የናዝሬቱን ኢየሱስን ትፈልጋላችሁ፤ ተነሥቶአል፥ በዚህ የለም፤ እነሆ እርሱን ያኖሩበት ስፍራ።
እንኳን ለጌታችን እና ለአምላካችን ለኢየሱስ ክርስቶስ የትንሳኤው መታሰቢያ በዓል በሰላም አደረሳችሁ።
መልካም በዓል!
[ @CHRIST_PICTURES ]
[ @KINE_TUBE ]
❤13
ያለኝ ድካሜ ነው
ምንም ብኖር ከሰው ተመሳስዬ
ጉድለቴን ሸፍነህ ሙሉ ሰው ተብዬ
አውቃለሁ እኔነቴን ከየት እንደሆንኩኝ
ማያከብርህን ሳሳድድ እንዳገኘኸኝ
ከባዶነት አንስተህ ሙሉ አድርገኸኝ
ከጨለማም ደግሞ ብርሃን አድርገኸኝ
እንድመላለስ በፊትህ እንዲሁ ከወደድከኝ
ከነድካሜ ወድደህ ካቀረብከኝ
ይኸው ማንነቴን ውረሰው ቤቴን
የአንተ ላድርግልህ ሰውነቴን
ያለኝን ንብረቴን አንተ የወደድከውን
በሰው እውቀት ሲሰላ ፍፁም ማይጠቅመውን
አቀርብልሃለሁ ዛሬም እንድትሰራበት
በእስሱም ተጠቅመህ ሀይልህን ግለጥበት
እንደገጣሚ ግጥሜ ወዛም ባይሆንም
የቃላት ምርጫዬ ውስጤን ባያረካውም
ግን ዝም አልልም እጄን አጣምሬው
አንተ ከመረጥከው ልትጠቀምበት ከወደድከው
ያለኝ ድካሜ ነው በፊትህ ማቀርበው
ተጠቀምበት ልብህን እንዳረካው
ኢየሱስ እወድሃለሁ
ልታርሙኝ ትችላላችሁ ☺️
ʏᴏᴜʀs ʟɪᴛᴛʟᴇ ʙʀᴏ :
🥰13❤2👏2👍1