BrightMind21
305 subscribers
223 photos
1 video
2 files
133 links
"Stay informed and inspired! Explore short news updates, educational videos, career and job announcements, sports highlights, and amazing events from around the world. Learn practical tips, discover new knowledge
@BrightMind21_bot
Download Telegram
#ጥቆማ
 
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የቅድመ አንደኛ እስከ የ2ኛ ደረጃ መምህራን ለመቅጠር በቀን 21/11/2018 ዓ.ም የቅጥር ማስታወቂያ ማውጣቱና በOnline እንድትመዘገቡ መደረጉ ይታወቃል፡፡
 
ይሁን እንጂ ሁሉን አቀፍ መረጃ ለማያያዝ በሚያመች መልኩ የተሻለ የመመዝገቢያ ሊንክ የተዘጋጀ በመሆኑ፤ በነባሩ ሊንክ የተመዘገባችሁም ሆነ አዲስ ለመመዝገብ ይምትፈልጉ መምህራን https://lyuhub.com/jobs ላይ በመግባት ምዝገባ እንድታደርጉ ቢሮው ጠይቋል፡፡
 
የምዝገባ ጊዜው እስከ ነሐሴ 06/2018 ዓ.ም በሥራ ቀናት ብቻ መሆኑ ተገልጿል፡፡
 
(ተጨማሪ መረጃ ከላይ ከተያያዘው ምስል ይመልከቱ፡፡)
 
https://t.me/Bright_mind21
#BoranaUniversity

ቦረና ዩኒቨርሲቲ የተቋሙ የ5ኛ ዓመት የእንስሳት ሕክምና ተማሪዎች ወደ ጊቢ መመለሻ ቀናት ሐምሌ 30 እና ነሐሴ 01 ቀን 2018 ዓ.ም መሆኑን አሳውቋል።
https://t.me/Bright_mind21
👍1
#AREB

በአማራ ክልል የ2018 ትምህርት ዘመን የ8ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ውጤት ይፋ ሆኗል።

በክልሉ 173,699 የ8ኛ ክፍል ተማሪዎች ፈተናውን የወሰዱ ሲሆን፤ 135,003 (77.72%) ተማሪዎች 50% እና በላይ ውጤት በማስመዝገብ ማለፋቸውን የክልሉ ትምህርሮ አሳውቋል።

ውጤት ለማየት 👇
https://amhara.ministry.et/#/result

አድራሻውን ከተጫኑ በኋላ የተማሪውን መለያ ቁጥር እና ስም በአማርኛ በማስገባት 'Check your result' የሚለውን በመጫን ውጤትዎን ማየት ይችላሉ፡፡

በቴሌግራም ቦት ለማየት 👇
@emacs_ministry_result_qmt_bot 

የቴሌግራም ቦት ላይ ከገቡ በኋላ Start የሚለውን ይጫኑ፣ ክፍልዎን ይምረጡ፣ ከዚያም ክልልዎን ይምረጡ፣ የምዝገባ መለያ ቁጥር እና የመጀመሪያ ስምን በማስገባት ውጤትዎን ማየት ይችላሉ።

ቅሬታ ለማቅረብ 👇 https://amhara.ministry.et/#/complaint

VPN የምትጠቀሙ ከሆነ በቅድሚያ ማጥፋት ይኖርባችኋል፡፡

በክልሉ የ2018 ዓ.ም የ6ኛ ክፍል ክልል አቀፍ ፈተና ውጤት ነገ ሐምሌ 27/2018 ዓ.ም ይፋ እንደሚደረግ ቢሮው ገልጿል።
https://t.me/Bright_mind21
https://t.me/Bright_mind21
https://t.me/Bright_mind21
#AREB

በአማራ ክልል የ2018 ትምህርት ዘመን የ6ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ውጤት ይፋ ሆኗል።

በክልሉ 194,374 የ6ኛ ክፍል ተማሪዎች ፈተናውን የወሰዱ ሲሆን፤ 165,342 (85.06%) ተማሪዎች 50% እና በላይ ውጤት በማስመዝገብ ማለፋቸውን የክልሉ ትምህርሮ አሳውቋል።

ውጤት ለማየት 👇
https://amhara6.ministry.et/#/result

አድራሻውን ከተጫኑ በኋላ የተማሪውን መለያ ቁጥር እና ስም በአማርኛ በማስገባት 'Check your result' የሚለውን በመጫን ውጤትዎን ማየት ይችላሉ፡፡

በቴሌግራም ቦት ለማየት 👇
@emacs_ministry_result_qmt_bot

የቴሌግራም ቦት ላይ ከገቡ በኋላ Start የሚለውን ይጫኑ፣ ክፍልዎን ይምረጡ፣ ከዚያም ክልልዎን ይምረጡ፣ የምዝገባ መለያ ቁጥር እና የመጀመሪያ ስምን በማስገባት ውጤትዎን ማየት ይችላሉ።

ቅሬታ ለማቅረብ 👇
https://amhara6.ministry.et/#/complaint

VPN የምትጠቀሙ ከሆነ በቅድሚያ ማጥፋት ይኖርባችኋል፡፡ በክልሉ የ8ኛ ክፍል ውጤት ትናንት መለቀቁ ይታወቃል።
https://t.me/Bright_mind21
የተፈተነውን ፈተና በሙሉ 100% ያመጣው የ8ኛ ክፍል ተማሪ
 
ተማሪ ዳዊት አማረ አለምየ ይባላል። በአማራ ክልል ሰሜን ወሎ ዳውንት ወረዳ የ2018 ዓ.ም የ8ኛ ክፍል ፈተና ወስዶ፣ ሁሉንም የትምህርት አይነቶች 100% በማምጣት በትምህርት ዘመኑ የክልሉን ከፍተኛ ውጤት አስመዝግቧል።
 
ተማሪ ዳዊት የወሰዳቸውን 6 የትምህርት አይነቶች በሙሉ 60 ከ 60 ማርክ ያመጣ ሲሆን፤ በአጠቃላይ ውጤት፣ በፐርሰንታይል እና በአማካይ 100% ማስመዝገብ ችሏል፡፡  👏👏
 
https://t.me/Bright_mind21
https://t.me/Bright_mind21
🥰2
የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የ2018 ዓ.ም የ8ኛ እና የ6ኛ ክፍል ውጤቶች ይፋ ተደርገዋል፡፡

በክልሉ የ2018 ዓ.ም የ6ኛ እና የ8ኛ ክፍል ማለፊያ ነጥብ 50 ሲሆን፤ ድጋፍ ለሚሹ ደግሞ 48 የማለፊያ ነጥብ እንደሆነ የክልሉ ትምህርት ቢሮ ኃላፊ አብዮት ደምሴ ገልፀዋል፡፡

በዚህም በክልሉ የ8ኛ ክፍል ፈተና ከወሰዱ 78,203 ተማሪዎች መካከል 47,307 ተማሪዎች (60.4%) የማለፊያ ነጥብ አምጥተዋል፡፡
 
540 ትምህርት ቤቶች ሙሉ በሙሉ ተማሪዎቻቸውን ማሳፍ ሲችሉ፤ 155 ትምህርቶች ደግሞ ምንም ተማሪ አለማሳለፋቸውን ኃላፊው ጠቁመዋል።

በተመሳሳይ በክልሉ የ6ኛ ክፍል ፈተና ከወሰዱ 126,224 ተማሪዎች መካከል 110,566 ተማሪዎች (63.8%) የማለፊያ ነጥብ አምጥተዋል፡፡
 
የ6ኛ ክፍል ፈተና ያስፈተኑ 476 ትምህርት ቤቶች ሙሉ በሙሉ ተማሪዎቻቸውን ሲያሳልፉ፤ 81 ትምህርት ቤቶች ምንም ተማሪ አላሳለፉም ብለዋል።

የ8ኛ ክፍል ውጤት ለማየት 👇
https://se.ministry.et/#/result

የ6ኛ ክፍል ውጤት ለማየት 👇
https://se6.ministry.et/#/result
 
https://t.me/Bright_mind21
https://t.me/Bright_mind21
የሪሚዲያል ፕሮግራም ተፈታኞች ቅሬታ

በ2018 ዓ.ም አገር አቀፍ የሪሚዲያል ፕሮግራም ፈተና የወሰዱ ተማሪዎች ውጤት ሳይገለፅ በመዘግየቱ ቅሬታቸውን እያቀረቡ ነው።

"ፈተናውን ወስደን ከጨረስን ድፍን ሁለት ወራት ሊሞላን ነው" ያሉት ተማሪዎቹ፤ "ይህን ያህል ጊዜ ውጤት ሳይገለፅ መቆየቱ ተገቢ አይደለም" ሲሉ ቅሬታቸውን አቅርበዋል።

"ውጤት ሳይገለፅ 57 ቀናት ማለፉ ተገቢ አይደለም፣ ለድባቴና ያልተገባ ጫና ተዳርገናል" ያሉት ተማሪዎቹ፤ "መንግሥት በአስቸኳይ ውጤታችንን ያሳውቀን" ሲሉ ተደጋጋሚ ቅሬታቸውን ለቲክቫህ ዩኒቨርሲቲ አድርሰዋል።

ቲክቫህ የሪሚዲያል ፈተና ወጤት መቼ ይለቀቃል ሲል የሚመለከታቸውን የመንግሥት አካላት ለመጠየቅ ያደረገው ሙከራ አልተሳካም።

የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት እንዲሁም ትምህርት ሚኒስቴር ከሪሚዲያል ፈተና ውጤት ጋር የተያያዘ የሚያወጡትን መረጃ የምናደርሳችሁ ይሆናል።

53 ሺህ በላይ ተፈታኞች ከግንቦት 27/2018 ዓ.ም እስከ ሰኔ 03/2018 ዓ.ም የተሰጠውን የሪሚዲያል ፈተና መውሰዳቸውን ይታወቃል።
 
https://t.me/Bright_mind21
https://t.me/Bright_mind21
👍1
#ጥቆማ
 
በ2019 የትምህርት ዘመን ወደ ሸገር ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት (SIT) ለመግባት ያመልክቱ!
 
የማመልከቻ ጊዜው እስከ ነሐሴ 24/2018 ዓ.ም መራዘሙን ኢንስቲትዩቱ ገልጿል።
 
የትምህርት መስኮች
● Electrical Engineering
● Biotechnology
● Space Science
● Mechanical Engineering
● AI
● Nuclear engineering

ያመልክቱ 👇
https://sitedu.info/admission/application

መስፈርቶች
● የ11ኛ እና 12ኛ ክፍል አማካኝ ውጤት 90%
● የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ውጤት 95 ፐርሰንታይል
● ከ500-700 ቃላት የግል መግለጫ መጻፍ ይኖርብዎታል
● የድጋፍ ደብዳቤ ከ2ኛ ደረጃ መምህርዎ/ሜንተርዎ ማጻፍ
● የማኅበረሰብ በጎ አገልግሎት የሰጡት ካለ ቢያይዙ ጥሩ ነው
 https://t.me/Bright_mind21
https://t.me/Bright_mind21
#ጥቆማ

ትምህርት ሚኒስቴር በ2018 ዓ.ም ትምህርት መስጠት በጀመረባቸው አምስት የፌዴራል ልዩ አዳሪ 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች በ2019 ዓ.ም ተጨማሪ የ10ኛ ክፍል ተማሪዎችን ተቀብሎ ለማስተማር ዝግጅት እያደረገ እንደሚገኝ ገልጿል።

የተማሪዎች ምዝገባ በቅርቡ እንደሚጀመር ሚኒስቴሩ አሳውቋል።

የምዝገባ መስፈርቶች፣ የምዝገባ ጊዜ እና ሌሎች መረጃዎች በቅርቡ ይፋ የሚደረግ መሆኑ የተገለፀ ሲሆን ዝግጅት እያደረጋችሁ እንድትጠብቁ ተብሏል።
https://t.me/Bright_mind21
1
#ጥቆማ
#EthiopianAirlines

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ብቁ የሆኑ ተለማማጅ የበረራ አስተናጋጅ  (Trainee Cabin Crew) አወዳድሮ መቅጠር ይፈልጋል፡፡

➤ የሥራ መደብ፦ ET SPONSORED Trainee Cabin Crew
➤ ተፈላጊ የትምህርት ደረጃ፦ የዩኒቨርሲቲ መግቢያ ፈተና ሰርተፊኬት ቢያንስ 200 ውጤት ያለው/ያላት
➤ ዕድሜ፦ ከ 21-30
➤ ቁመት፦ 1.58ሜ እና በላይ ለሴት (የክንድ ርዝማኔ 212ሴ.ሜ. ፤ 1.70ሜ እና በላይ ለወንድ
➤ ክብደት፦ ከቁመት ጋር ተመጣጣኝ የሆነ
➤ ቋንቋ፦ የእንግሊዝኛ ቋንቋ ክህሎት ደረጃ III (ሌሎች ቋንቋዎች መቻልም ጥሩ ነው)
 
የምዝገባ ቀናት፦
ከነሐሴ 04-08/2018 ዓ.ም


የምዝገባ ቦታዎች፦


➫ አዲስ አበባ፦ በኦንላይን (የማመልከቻ ሊንክ በምዝገባ ቀናት አክቲቭ ይሆናል)
➫ አዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ፣ አዳማ
➫ አምቦ ዩኒቨርሲቲ፣ አምቦ
➫ አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ፣ አርባ ምንጭ
➫ አሶሳ ዩኒቨርሲቲ፣ አሶሳ
➫ ባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ፣ ባህር ዳር
➫ ወሎ ዩኒቨርሲቲ፣ ደሴ
➫ ድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ፣ ድሬዳዋ
➫ ጋምቤላ ዩኒቨርሲቲ፣ ጋምቤላ
➫ ጎንደር ዩኒቨርሲቲ፣ ጎንደር
➫ ሐረማያ ዩኒቨርሲቲ፣ ሐረር ካምፓስ፣ ሐረር
➫ ሀዋሳ ኤርፖርት፣ ሀዋሳ
➫ ጅግጅጋ ዩኒቨርሲቲ፣ ጅግጅጋ
➫ ጅማ ዩኒቨርሲቲ፣ ጅማ
➫ መደ ወላቡ ዩኒቨርሲቲ፣ ሮቤ
➫ መቐለ ዩኒቨርሲቲ፣ መቐለ
➫ ወለጋ ዩኒቨርሲቲ፣ ነቀምቴ
➫ ሰመራ ዩኒቨርሲቲ፣ ሰመራ
➫ ወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ፣ ወልቂጤ
➫ ቦረና ዩኒቨርሲቲ፣ ያቤሎ
➫ ነገሌ ቦረና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ፣ ነገሌ

🔔 ምዝገባ ሲያደርጉ የአስፈላጊ ሰነዶችዎንና የትምህርት ማስረጃዎችዎን (የ8ኛ ክፍል ሚኒስትሪ ካርድ፣ የልደት ሰርተፊኬት፣ የ12ኛ ክፍል ሰርተፊኬት፣ የቀበሌ መታወቂያ) ዋናውንና ኮፒውን መያዝ ይጠበቅብዎታል፡፡

ከላይ የተገለፁ መስፈርቶችን ማሟላትዎን ያረጋግጡ፡፡ በሐሰተኛ መረጃ ለመመዝገብ ከሞከሩ ወዲያውኑ ከቅጥር ሂደቱ የሚወገዱ ይሆናል፡፡
https://t.me/Bright_mind21
https://t.me/Bright_mind21
❤️ በዚህ የቴሌግራም ቻናል ባለቤቶችን ወደ Inside Ad እጋብዛለሁ፡፡ ለእድገትና ለገንዘብ ማግኘት ጥቅም ላይ ማዋል የሚችሉ ስልት!

https://t.me/InsideAds_bot/open?startapp=r_1372541129
🔥1
#ጥቆማ

የጅማ ዩኒቨርሲቲ ልዩ 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት በ2018 ዓ.ም የ8ኛ ክፍል መልቀቂያ ክልላዊ ፈተና ተፈትናችሁ ከፍተኛ ውጤት ያስመዘገባችሁ ተማሪዎችን ለ2019 ዓ.ም ባለው ክፍት ቦታ አወዳድሮ መቀበል ይፈልጋል፡፡

መስፈርቶች፦
➻ የ8ኛ ክፍል ክልላዊ ፈተና አመካይ ውጤት ለወንድ 83% ፤ ለሴት 80%
➻ የ7ኛ-8ኛ ክፍል ትራንስክሪፕት አማካይ ውጤት ለወንድ 85% ፤ ለሴት 75%
➻ የ7ኛ-8ኛ ክፍል ትራንስክሪፕት የእንግሊዘኛ እና ሒሳብ ትምህርት አይነቶች አማካይ ውጤት ለወንድ 75% ፤ ለሴት 70%

ለምዝገባ የሚያስፈልጉ፦
➻ የ8ኛ ክፍል ውጤት ሰርቲፊኬት
➻ የ7ኛ-8ኛ ክፍል ትራንስክሪፕት

የምዝገባ ቀናት፦
ከነሐሴ 05-12/2018 ዓ.ም ባሉት የሥራ ቀናት

የምዝገባ ቦታ፦
በጅማ ዩኒቨርሲቲ ልዩ 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት

የመግቢያ ፈተና የሚሰጥበት ቀን እና ቦታ ወደፊት ይገለጻል ተብሏል። (ትምህርት ቤቱ አዳሪ ትምህርት ቤት አይደለም።)
https://t.me/Bright_mind21
#ጥቆማ

የአዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ የማኅበረሰብ ትምህርት ቤት (ASTU-Community School) ከቅድመ 1ኛ ደረጃ እስከ 12ኛ ክፍል ተማሪዎች የ2019 የትምህርት ዘመን የመደበኛ ተማሪዎች ምዝገባ ከነሐሴ 06-15/2018 ዓ.ም መሆኑን ገልጿል፡፡

(የክፍያ ሁኔታ እና ሌሎች ተጨማሪ መረጃዎችን ከላይ ከተያያዘው ምስል ይመልከቱ፡፡)
https://t.me/Bright_mind21
https://t.me/Bright_mind21
ትምህርት ሚኒስቴር በፌዴራል ልዩ አዳሪ 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች የ9ኛ እና የ10ኛ ክፍል ተማሪዎችን ተቀብሎ በነፃ ማስተማር ይፈልጋል።

🔔 ሙሉ የትምህርት ክፍያ ሽፋን እንዲሁም ነፃ የመኝታ እና የምግብ አገልግሎት በነፃ ትምህርት ዕድሉ ይሰጣል፡፡

9ኛ ክፍል ብቻ የሚቀበሉ ልዩ አዳሪ ትምህርት ቤቶች
● አርባ ምንጭ ልዩ አዳሪ ትምህርት ቤት
● ድሬዳዋ ልዩ አዳሪ ትምህርት ቤት
● አሶሳ ልዩ አዳሪ ትምህርት ቤት
● ባህር ዳር ልዩ አዳሪ ትምህርት ቤት

9ኛ እና 10ኛ ክፍል የሚቀበሉ ልዩ አዳሪ ትምህርት ቤቶች
● ቡኢ ልዩ አዳሪ ትምህርት ቤት
● ጅግጅጋ ልዩ አዳሪ ትምህርት ቤት
● ጋምቤላ ልዩ አዳሪ ትምህርት ቤት
● ወሊሶ ልዩ አዳሪ ትምህርት ቤት
● ቦንጋ ልዩ አዳሪ ትምህርት ቤት

ለ9ኛ ክፍል የመመዝገቢያ መስፈርቶች
● በ8ኛ ክፍል ሚኒስትሪ ፈተና 85 እና በላይ አማካኝ ውጤት ያመጣ/ያመጣች
● በሂሳብ እና እንግሊዝኛ የትምህርት ዓይነቶች 80 እና በላይያመጣ/ያመጣች
● ጥሩ ስነ-ምግባር ያለው/ያላት

ለ10ኛ ክፍል የመመዝገቢያ መስፈርቶች
● በ2017 ዓ.ም በ8ኛ ክፍል ሚኒስትሪ ፈተና 70 እና በላይ አማካኝ ውጤት ያመጣ/ያመጣች
● በ9ኛ ክፍል ትራንስክሪፕት 95 እና በላይ አማካኝ ውጤት ያመጣ/ያመጣች
● በሂሳብ እና እንግሊዝኛ የትምህርት ዓይነት 80 እና በላይ ያመጣ/ያመጣች
● ጥሩ ስነ-ምግባር ያለው/ያላት

ኦንላይን ይመዝገቡ 👇
https://sbs.moe.gov.et/apply

የመመዝገቢያ ጊዜ 👇
እስከ ነሐሴ 15/2018 ዓ.ም

ለፈተና የሚቀርቡ ተማሪዎች ዝርዝር እና የፈተና ጊዜ ወደፊት ይገለፃል፡፡ የመግቢያ ፈተናውን የሚያልፉ ተማሪዎች በሚደቡበት ልዩ አዳሪ ትምህርት ቤት ለመማር ፈቃደኛ የሆኑ መሆን አለባቸው ተብሏል፡፡
https://t.me/Bright_mind21
#AREB

የአማራ ክልል ትምህርት ቢሮ በ2019 የትምህርት ዘመን በክልሉ በሚገኙ ልዩ አዳሪ ትምህርት ቤቶች ለሚገቡ ተማሪዎች የምዝገባ ጥሪ አድርጓል፡፡

የይሁኔ ወልዱ መታሰቢያ አዳሪ ትምህርት ቤት - ደሴ፣ የክቡር ዶ/ር ሐዲስ አለማየሁ - ደብረማርቆስ፣ እንዲሁም አዲስ የተገነቡ የደብረ ታቦር እና የሰቆጣ አዳሪ ትምህርት ቤቶች አዲስ ተማሪዎችን ተቀብለው ለማስተማር ዝግጅት በማድረግ ላይ ይገኛሉ።

በመሆኑም በ2018 ዓ.ም በክልሉ ከሚገኙ የመንግሥት እንዲሁም የግል ትምህርት ቤቶች ተምራችሁ፣ ክልላዊ ፈተና የወሰዳችሁና የተቀመጡ መስፈርቶችን የምታሟሉ ተማሪዎች በትምህርት ቤቶቹ ምዝገባ እንድታደርጉ የክልሉ ትምህርት ቢሮ ጥሪ አስተላልፏል፡፡

መሰፈርቶች
● የ8ኛ ክፍል ክልላዊ ፈተና አማካይ ውጤት ለሴቶች 80% እና ለወንዶች 82%
● የ7ኛ እና የ8ኛ ክፍል ትራንስክሪፕት አማካይ ውጤት ለሴቶች 83% እና ለወንዶች 85%

የምዝገባ ጊዜ 👇
ከነሐሴ 06-15/2018 ዓ.ም

የምዝገባ ቦታ 👇
በአማራ ክልል በሚገኙ በሁሉም የወረዳ/ከተማ አስተዳደር ትምህርት ጽ/ቤቶች

የመግቢያ ፈተና በዞን ዋና ከተሞች ነሐሴ 25/ 2018 ዓ.ም ይሰጣል ተብሏል፡፡ (ተጨማሪ መረጃ ከላይ ከተያያዘው ምስል ይመልከቱ፡፡)
https://t.me/Bright_mind21
https://t.me/Bright_mind21
👍1