BrightMind21
305 subscribers
223 photos
1 video
2 files
133 links
"Stay informed and inspired! Explore short news updates, educational videos, career and job announcements, sports highlights, and amazing events from around the world. Learn practical tips, discover new knowledge
@BrightMind21_bot
Download Telegram
በሲዳማ ክልል የ2018 ዓ.ም የ6ኛ እና የ8ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ውጤት፦

የ6ኛ ክፍል ውጤት ለመመልከት👇
https://sidama6.ministry.et/#/result

የ8ኛ ክፍል ውጤት ለመመልከት 👇
https://sidama.ministry.et
https://t.me/Bright_mind21
👍1
የኢትዮጵያ መከላከያ ዩኒቨርሲቲ የላቀ ማዕከላዊ ላቦራቶሪ በዛሬው ዕለት አስመርቋል።

ማዕከላዊ ላቦራቶሪው ከተባበሩት አረብ ኤምሬትስ መንግሥት በተገኘ ድጋፍ የተገነባ መሆኑ ተገልጿል።

ማዕከሉ ዕውቀትን ወደ ሙያዊ ብቃት፣ ምርምርን ወደ ፈጠራ እንዲሁም ፈጠራን ወደ ተግባራዊ መፍትሔዎች ለመቀየር ትልቅ ፋይዳ እንደሚኖረው የመከላከያ ሚኒስትሯ አይሻ መሃመድ ገልፀዋል፡፡

የላቀ ላቦራቶሪ ማዕከሉ በውስጡ ሰባት ግዙፍ ላቦራቶሪዎችን የያዘ መሆኑ ተመላክቷል።
https://t.me/Bright_mind21
#UoG

ላለፉት ከሰባት ዓመታት በላይ የጎንደር ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት በመሆን ያገለገሉት አሥራት ዓፀደወይን (ዶ/ር) የአዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጅ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት ሆነው ተመደቡ፡፡

ለጎንደር ዩኒቨርሲቲ አዲስ ፕሬዝዳንት ተመድቦለታል፡፡

የቻለ ከበደ (ዶ/ር) ከሐምሌ 17/2018 ዓ.ም ጀምሮ የጎንደር ዩነኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት ሆነው መመደባቸውን በቀን 15/11/18 በትምህርት ሚኒስትሩ ብሀርሃኑ ነጋ (ፕ/ር) የተፈረመ የሹመት ደብዳቤ ያሳያል፡፡

አዲሱ ፕሬዝዳንት የትምህርት ሚኒስቴር የአስተዳደርና መሠረተ ልማት ዋና ስራ አስፈፃሚ ሰለሞን አብርሃ (ዶ/ር) በተገኙበት በዛሬው ዕለት የስራ ርክክብ ያደረጉ ሲሆን፤ ዩኒቨርሲቲው በትምህርት፣ በምርምር፣ በማኅበረሰብ አገልግሎት እና በተቋማዊ አስተዳደር ያስመዘገበውን ውጤት በማስቀጠል የተሻለ አፈጻጸም ለማረጋገጥ በትብብር መስራት እንደሚገባቸው ተገልጿል።

ላለፉት ከሰባት ዓመታት በላይ የጎንደር ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት በመሆን ያገለገሉት አሥራት ዓፀደወይን (ዶ/ር) የአዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጅ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት ሆነው መመደባቸው ታውቋል፡፡
https://t.me/Bright_mind21
🔥1
#ጥቆማ

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ በስሩ ለሚገኙ የቅድመ እንደኛ ደረጃ፣ እንደኛና መካከለኛ እንዲሁም 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ውስጥ ለመስራት ፍላጎትና ብቃት ያላቸው መምህራን እና ባለሙያዎችን አወዳድሮ መቅጠር ይፈልጋል።

ኦንላይን የመመዝገቢያ ሊንኮች፦

● ለ2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች 👇
https://docs.google.com/forms/d/1RRFzFMb2HEoCyRp_ye5E-joooyGYzpAMfEvFBQdbJJs/edit

● ከቅድመ አንደኛ ደረጃ እስከ 8ኛ ክፍል ላሉ ትምህርት ቤቶች 👇
https://docs.google.com/forms/d/1exSs8OJs3UzYpyzcqQ8e13-JiczbyGR1ohmYFpdHJOY/edit

(ዝርዝር መስፈርቶችን ከላይ ከተያያዘው ምስል ይመልከቱ።)
https://t.me/Bright_mind21
https://t.me/Bright_mind21
የNGAT ምዝገባ ለማድረግ በቴሌብር ክፍያ ከመፈፀም ጋር አጋጥሞ የነበረው ችግር ከትናንት ምሽት ጀምሮ መፈታቱ ተገልጿል፡፡ አሁን ላይ አገልግሎቱ በደንብ እየሠራ በመሆኑ ክፍያዎን በመፈፀም ምዝገባዎን ማድረግ ይችላሉ፡፡

ለድኅረ-ምረቃ ፕሮግራሞች የመግቢያ ፈተና (NGAT) ምዝገባ እስከ ቅዳሜ ሐምሌ 25/2018 ዓ.ም ብቻ የሚከናወን መሆኑን የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት መግለፁ ይታወቃል፡፡

ምዝገባዎን ያድርጉ 👇
https://ngat.ethernet.edu.et

ፈተናውን ለመውሰድ የፋይዳ መታወቂያ የግድ እንደሚያስፈልግ ያስታውሱ፡፡
https://t.me/Bright_mind21
👍1
#ጥቆማ
 
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የቅድመ አንደኛ እስከ የ2ኛ ደረጃ መምህራን ለመቅጠር በቀን 21/11/2018 ዓ.ም የቅጥር ማስታወቂያ ማውጣቱና በOnline እንድትመዘገቡ መደረጉ ይታወቃል፡፡
 
ይሁን እንጂ ሁሉን አቀፍ መረጃ ለማያያዝ በሚያመች መልኩ የተሻለ የመመዝገቢያ ሊንክ የተዘጋጀ በመሆኑ፤ በነባሩ ሊንክ የተመዘገባችሁም ሆነ አዲስ ለመመዝገብ ይምትፈልጉ መምህራን https://lyuhub.com/jobs ላይ በመግባት ምዝገባ እንድታደርጉ ቢሮው ጠይቋል፡፡
 
የምዝገባ ጊዜው እስከ ነሐሴ 06/2018 ዓ.ም በሥራ ቀናት ብቻ መሆኑ ተገልጿል፡፡
 
(ተጨማሪ መረጃ ከላይ ከተያያዘው ምስል ይመልከቱ፡፡)
 
https://t.me/Bright_mind21
#BoranaUniversity

ቦረና ዩኒቨርሲቲ የተቋሙ የ5ኛ ዓመት የእንስሳት ሕክምና ተማሪዎች ወደ ጊቢ መመለሻ ቀናት ሐምሌ 30 እና ነሐሴ 01 ቀን 2018 ዓ.ም መሆኑን አሳውቋል።
https://t.me/Bright_mind21
👍1
#AREB

በአማራ ክልል የ2018 ትምህርት ዘመን የ8ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ውጤት ይፋ ሆኗል።

በክልሉ 173,699 የ8ኛ ክፍል ተማሪዎች ፈተናውን የወሰዱ ሲሆን፤ 135,003 (77.72%) ተማሪዎች 50% እና በላይ ውጤት በማስመዝገብ ማለፋቸውን የክልሉ ትምህርሮ አሳውቋል።

ውጤት ለማየት 👇
https://amhara.ministry.et/#/result

አድራሻውን ከተጫኑ በኋላ የተማሪውን መለያ ቁጥር እና ስም በአማርኛ በማስገባት 'Check your result' የሚለውን በመጫን ውጤትዎን ማየት ይችላሉ፡፡

በቴሌግራም ቦት ለማየት 👇
@emacs_ministry_result_qmt_bot 

የቴሌግራም ቦት ላይ ከገቡ በኋላ Start የሚለውን ይጫኑ፣ ክፍልዎን ይምረጡ፣ ከዚያም ክልልዎን ይምረጡ፣ የምዝገባ መለያ ቁጥር እና የመጀመሪያ ስምን በማስገባት ውጤትዎን ማየት ይችላሉ።

ቅሬታ ለማቅረብ 👇 https://amhara.ministry.et/#/complaint

VPN የምትጠቀሙ ከሆነ በቅድሚያ ማጥፋት ይኖርባችኋል፡፡

በክልሉ የ2018 ዓ.ም የ6ኛ ክፍል ክልል አቀፍ ፈተና ውጤት ነገ ሐምሌ 27/2018 ዓ.ም ይፋ እንደሚደረግ ቢሮው ገልጿል።
https://t.me/Bright_mind21
https://t.me/Bright_mind21
https://t.me/Bright_mind21
#AREB

በአማራ ክልል የ2018 ትምህርት ዘመን የ6ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ውጤት ይፋ ሆኗል።

በክልሉ 194,374 የ6ኛ ክፍል ተማሪዎች ፈተናውን የወሰዱ ሲሆን፤ 165,342 (85.06%) ተማሪዎች 50% እና በላይ ውጤት በማስመዝገብ ማለፋቸውን የክልሉ ትምህርሮ አሳውቋል።

ውጤት ለማየት 👇
https://amhara6.ministry.et/#/result

አድራሻውን ከተጫኑ በኋላ የተማሪውን መለያ ቁጥር እና ስም በአማርኛ በማስገባት 'Check your result' የሚለውን በመጫን ውጤትዎን ማየት ይችላሉ፡፡

በቴሌግራም ቦት ለማየት 👇
@emacs_ministry_result_qmt_bot

የቴሌግራም ቦት ላይ ከገቡ በኋላ Start የሚለውን ይጫኑ፣ ክፍልዎን ይምረጡ፣ ከዚያም ክልልዎን ይምረጡ፣ የምዝገባ መለያ ቁጥር እና የመጀመሪያ ስምን በማስገባት ውጤትዎን ማየት ይችላሉ።

ቅሬታ ለማቅረብ 👇
https://amhara6.ministry.et/#/complaint

VPN የምትጠቀሙ ከሆነ በቅድሚያ ማጥፋት ይኖርባችኋል፡፡ በክልሉ የ8ኛ ክፍል ውጤት ትናንት መለቀቁ ይታወቃል።
https://t.me/Bright_mind21
የተፈተነውን ፈተና በሙሉ 100% ያመጣው የ8ኛ ክፍል ተማሪ
 
ተማሪ ዳዊት አማረ አለምየ ይባላል። በአማራ ክልል ሰሜን ወሎ ዳውንት ወረዳ የ2018 ዓ.ም የ8ኛ ክፍል ፈተና ወስዶ፣ ሁሉንም የትምህርት አይነቶች 100% በማምጣት በትምህርት ዘመኑ የክልሉን ከፍተኛ ውጤት አስመዝግቧል።
 
ተማሪ ዳዊት የወሰዳቸውን 6 የትምህርት አይነቶች በሙሉ 60 ከ 60 ማርክ ያመጣ ሲሆን፤ በአጠቃላይ ውጤት፣ በፐርሰንታይል እና በአማካይ 100% ማስመዝገብ ችሏል፡፡  👏👏
 
https://t.me/Bright_mind21
https://t.me/Bright_mind21
🥰2
የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የ2018 ዓ.ም የ8ኛ እና የ6ኛ ክፍል ውጤቶች ይፋ ተደርገዋል፡፡

በክልሉ የ2018 ዓ.ም የ6ኛ እና የ8ኛ ክፍል ማለፊያ ነጥብ 50 ሲሆን፤ ድጋፍ ለሚሹ ደግሞ 48 የማለፊያ ነጥብ እንደሆነ የክልሉ ትምህርት ቢሮ ኃላፊ አብዮት ደምሴ ገልፀዋል፡፡

በዚህም በክልሉ የ8ኛ ክፍል ፈተና ከወሰዱ 78,203 ተማሪዎች መካከል 47,307 ተማሪዎች (60.4%) የማለፊያ ነጥብ አምጥተዋል፡፡
 
540 ትምህርት ቤቶች ሙሉ በሙሉ ተማሪዎቻቸውን ማሳፍ ሲችሉ፤ 155 ትምህርቶች ደግሞ ምንም ተማሪ አለማሳለፋቸውን ኃላፊው ጠቁመዋል።

በተመሳሳይ በክልሉ የ6ኛ ክፍል ፈተና ከወሰዱ 126,224 ተማሪዎች መካከል 110,566 ተማሪዎች (63.8%) የማለፊያ ነጥብ አምጥተዋል፡፡
 
የ6ኛ ክፍል ፈተና ያስፈተኑ 476 ትምህርት ቤቶች ሙሉ በሙሉ ተማሪዎቻቸውን ሲያሳልፉ፤ 81 ትምህርት ቤቶች ምንም ተማሪ አላሳለፉም ብለዋል።

የ8ኛ ክፍል ውጤት ለማየት 👇
https://se.ministry.et/#/result

የ6ኛ ክፍል ውጤት ለማየት 👇
https://se6.ministry.et/#/result
 
https://t.me/Bright_mind21
https://t.me/Bright_mind21