ድልድይ | Dildiy | Bridge
1.45K subscribers
417 photos
87 videos
1 file
117 links
DILDIY

Whispers of the soul. Echoes of the universe.

Exploring consciousness, love, interconnectedness, and the mystery of existence through philosophy, mysticism & science.

Every thought is a bridge. Every question is a path. Every soul is connected.
Download Telegram
_

የቤቲ ሼርን አልበም ሰምተን ስናበቃ የምጋብዛትን ሙዚቃ ርዕስ ጠየቀችኝ... ብዙ ጊዜ አዲስ አልበም ሲወጣ ተመሳሳይ ልማድ አለን...

"አካልዬ" አልኳት... እውነቴን ነበር፣ እርሷን እያሰብኩ ነው ያደመጥኩት...

ዝም አለችኝ...

"ያንቺስ ግብዣ ምንድነው?" ድርሻዬን ጠየቅሁዋት

"ቻው ቻው" አለችኝ...

በተራዬ ዝም አልኩ...

__


ጊዜና የሰው ልጅ እንደ ሙዚቃ አልበም ናቸው... ውስጣቸው መንታ ስሜት ባላቸው 'ስልቶች' የታጨቀ ስለሆነ መቼ የቱን "ሙዚቃቸውን" እንደሚጋብዙህ አታውቅም...

___


@bridgethoughts
6🥰6🔥2🕊1
📌

.
.
.

በውዳሴ ወቅት የምታሳየው ፈንጠዝያ፣ በወቀሳ ጊዜ ለመሰበር ያለህን ፍጥነት አመልካች ነው... ለሙገሳ ፈጥኖ እጅ የሚሰጥ ሰው በውግዘት ወቅት በፍጥነት ይፈራርሳል... 


ብልህ ሰው ግን ሲያሞግሱት በዝምታ ያልፋል - ከቁምነገር አይጽፈውም... ሲያወግዙትም አንዳች ሳይረበሽ ጸንቶ ይጓዛል - በግሉ አይወስደውም... 


ዓለሚቱን ጠንቅቆ ስለሚያውቅ፣ ሰውንም ከእጁ መዳፍ በላይ በማንበብ ስለሚራቀቅ እያንዳንዱ አጋጣሚ በቀላሉ አሻራውን የሚያትምበት የመንገድ ላይ ሸራ ከመሆን ነፃ ወጥቷል...


ስለምን ቢሉ... ብልህ መሆን ማለት  "ይህም ያልፋል!!" ይሉትን ብሂል መገንዘብ ነውና...

___


The moment you are disturbed by insult or pleased by praise, you are still slave ~ Osho


___

@bridgethoughts
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
14🔥3
.
.
.

ታክሲ ውስጥ ነኝ... ኋላ ወንበር ላይ ቁጭ ብያለሁ... ክ/ሃገር ለመሄድ ነው ወደ አውቶብስ ተራ የሚወስዱኝን ጎማዎች የምከተለው...


አጠገቤ አንድ ጎልማሳ ተቀምጧል...


በተሽከርካሪ መጓዝ ምቾት የሚነሳኝ ዓይነት ሰው ስለሆንኩ በመዳረሻዬ ላይ እንጂ በመጓጓዣዬ ሁነት ብዙ አልመሰጥም... በዚህ ምክንያት ወሬ አልሰማም - ወይም ሲያወሩኝ አልወድም...


ሰውየው ግን ጆሮ እንዳለኝ እንጂ ሁኔታ መርጬ እንደምገለገለው አያውቅም... ስናወጋ እንደቆየን ሁሉ ከመሐል ጀምሮ ማውራት ጀመረ... ምናልባት በውስጡ የሚመላለሰው ሃሳብ ከአፉ ድንገት አፈትልኮ ሊሆን ይችላል... ሆኖም ቀልቤን መግዛት አልተሳነውም... ብርቱ ቃል ያሸንፈኛል - ደካማ ጎኔ ነው...


[ቀጥሎ የምታነቡዋቸው መስመሮች ክልበ-ቢስ ልቤ የተንጠባጠቡ የማላውቀው መንገደኛ ተብሰልስሎቶች ናቸው...]

.
.
.


"... እኔ እርሷን የምወድበት አቅም፣ እርሷ ገንዘብን ከምታመልክበት ጉልበት ጋር ሲነፃጸር መቶ እጥፍ ያንስ ነበር...


እናም ተውኳት!!...


መውደዴን ሳይሆን ፍለጋዎቼን ተውኩ... ማፍቀሬ ላይ ሳይሆን መከተሌ ላይ አመጽኩ...


አውቃለሁ ፍቅርን የሚስተካከል ሐብት እንደሌለ... አውቃለሁ መውደዴን ገንዘብ እንደማያክለው... ይህ ግን ለኔ እንጂ ለእርሷ የሚዋጥ አይደለም...


እውነት ለመናገር ገንዘብ ፍለጋ መሄድ እችል ነበር... በሃቅ ወይ በረቂቅ ሐብት ማካበት እችል ነበር - ሆኖም ምርጫዬ አላደረኩትም... ፍቅሯን በማጣት ላይ ፈርጄ ግን አልነበረም - ራሴን አጥቼ እርሷን ባገኝ እርባን የለውም ብዬ እንጂ... ቀልቧን እንጂ ልቧን ለማግኘት ዋስትና አይደለም ብዬ እንጂ... 


ደግሞስ... 


በገንዘብ ያገኙት ልብ በገንዘብ እንዳይሄድ መቋጠሪያው ምንድነው?... ባለኝ እንጂ በሆንኩት ላይ ያልቆመ አብሮነት ጽናት ምኑ ነው?...


አዎን... 


የማይጠረቃን የንዋይ ጥንወት በመውደድ እጆች ማስካድ አይቻልም... 


ገንዘብ እያሳዩ የሚስቧት ሴት አጥንት እያሳዩ ከሚጎትቱት ቡችላ በምን ትለያለች?...


ስለዚህ... ተውኳት!!..."

.
.
.

___


"ወራጅ አለ"


ድንገት ጮኸ... ሁላችንም ደነገጥን... ሰውዬው ድንገቴ ነገር ነው... በተለመደው የተግባቦትና የንግግር ደንቦች አይዳኝም... ይህ ግን የአድማጭ ጆሮ ከመማረክ አላገደውም...


ከልቤ አሳዘነኝ...


ተውኳት ሲል የማይተው ተቆጣጥሮት ቢሆንስ?... እንደ ታክሲው 'ወራጅ አለ' ያላለው የሆነ ዓይነት ነገር ተጣብቶት ቢሆንስ?...

___


መንገደኛው በየራሱ መንገድ የጎልማሳውን ጉዳይ ይበልት ገባ... እኔ ወዲህ በ Buddha ቃል ተወስጄ ነበር...


"Anger will never disappear so long as thoughts of resentment are cherished in the mind"

___


@bridgethoughts
9👌1🤝1💘1
When we have lived with a problem for a long time, the first thing that exposes the problem may appear to be the cause of the problem.

.
.
.

እንደምታውቀው ጥርሱን ሳይፍቅ/ ሳይቦርሽ ለረጅም ጊዜ የቆየ ሰው የአፉ ጠረን እንደሚያስቀይም ለመረዳት ሩቅ ነው... 


እንዲህ ዓይነት ሰው ለተወሰኑ ቀናት የጥርስ ሳሙና መጠቀም ቢጀምርና መልሶ ቢተዉ እንኳ የአፉን ሽታ በተለየ መንገድ ለማስተዋል ዕድል ስለሚያገኝ 'በምን ምክንያት ነው ይህ ሽታ የተፈጠረብኝ?' ብሎ መጠየቁ አይቀርም...


ሁኔታው በቅርብ ከጀመረው የጥርስ መቦረሽ ጉዳይ ጋር ስለሚያያዝበት ወደ አዕምሮው ቶሎ የሚመጣለት ድምዳሜ ‘የጥርስ ሳሙና አፍ ያሸታል’ የሚል ነው…
 

ስለምን?...
 

ነገሩ ወዲህ ነው...


ብሩሽ ከመጠቀሙ በፊት የአፉን መጥፎ ጠረን ተላምዶት ስለቆየ ‘አፍህ ይሸታል’ ቢሉት እንኳ አይሰማም ነበር… ወይም ደግሞ እንደ ችግር ለመቀበል ይከብደው ነበር... ብሩሹ ካለመደው ንጽህና በኋላ ግን የትኛውንም ሽታ መረዳትና መለየት ስለሚጀምር፣ ሽታውን እንደ አዲስ ክስተት ወስዶ ሰበቡ 'አዲሱ እንግዳ ነው' በሚል የጥርስ ሳሙናን ለማውገዝ አንደኛ ይሆናል… 


"Sometimes the thing that disturbs your comfort is the thing that restores your clarity."



በአጭሩ...


እንከን ጠቋሚው ከእንከን በሚጸዳበት ወቅት የነበረውን አጋርነት አይረዳም…



ይሄ አዲስ ዕውቀት አይደለም...


አፍንጫ ሊቆርጥ በሚደርስ መጥፎ ጠረን የተቀላቀልከው መጸዳጃ ቤት እንኳ ትንሽ ስትቆይበት 'ሽታ የለም' አስብሎ ሊያስክድህ ይችላል... መላመድ ክፉ አባዜ ነው...

__


የሆነስ ሆነና...


ጠረን እንድትለይ የረዱህን ‘ብሩሾች’ ስንቴ ‘አፍ ያሸታሉ’ ብለህ ጣልክ?… ስንቴስ ከእድፍ ያላቀቁህን ሳሙናዎች 'ጥርስ ያሳድፋሉ' ብለህ አወገዝክ?... ስንቴ ወደ ቀደመ ሽታህ ለመመለስ ተንደረደርክ?… ስንቴስ ለልማድ አጎበደድክ?...

__

ተገንዝቦት (Awareness) ሁሌም ጅምሩ አስደሳች ነው ብዬ ልሞግትህ አልደፍርም... ምክንያቱም የተገንዝቦት የመጀመሪያ ግብ ልናይ የማንሻቸውን ነገሮች ማስተዋወቅ ነውና...

በምሳሌ ብናየው...

የመስታወት ግብር የቆዳህን ሽብሽብ መፍጠር አይደለም - ገልጦ ማሳየት እንጂ፣

የላምባዲና ድርሻ አቧራ መውለድ አይደለም - መጠቆም እንጂ፣

የመምህር ግቡ ድንቁርናን መስጠት አይደለም - ዕውቀት የሚያሻውን ክፍተት መጠቆም እንጂ፣

አዎን እነዚህን ማየት አያስደስት ይሆናል... ጥያቄው ግን 'ጉድለትን ሳያውቁት እንዴት ይሞሉታል?' የሚለው ነው...

___

ብዙ የሚፈትኑን ነገሮች እርግጥም እየረዱን ይሆናል... ቀጥተኛ መምህራን፣ ሕመም የተሞሉ ልምምዶች፣ ለመቀበል የከበደን ሃቅ፣ ምቾት የነሳን የወዳጅ አስተያየት... ብዙ ነገሮች፤

ነገሩን ከኢጎ ሳንጸዳ ካየነው "ለምንድነው ሰላም የሚነሱኝ?" ያስብለናል...

በለውጥ ውስጥ ሆነን ስንረዳው ግን "አስቀድሜ ላየው ያልቻልኩትን ችግር እንድገነዘብ ስላደረግኸኝ አመሰግናለሁ" ለማለት እንደፍራለን...

___


"The first enemy of transformation is not the problem itself; it is our attachment to what has become familiar. We often reject the hand that cleanses us because cleanliness makes us aware of the dirt we had learned to ignore."

___

የመዳን መጀመሪያ ስለ ቁስልህ ጠንቅቆ ማወቅ ነው!!...
___


@bridgethoughts
11🔥2👌1
የተስፋ ነገር...

.
.
.


"The mature person does not abandon hope for tomorrow, nor abandon responsibility for today."


ተስፋ የአወሳሰድ ምጣኔው እንደማይታወቅ መድኃኒት ነው... እንደ ፈውስነቱ ሊያድንህ፣ እንደ dose ምጣኔው ሊያጠፋህ ይችላል...


እርግጥ ነው ተስፋ ጠቃሚ ነገር ነው... ሕይወትን አጨልሞ ከመመልከት ይታደግሃል፣ ደስ በማያሰኙ ሁኔታዎች ውስጥ በጽናት እንድትቆም ያደርግሃል፣ ከማይመቹና ለጸጸት ከሚዳርጉ ውሳኔዎች ይጋርድሃል... ወዘተ፤


ተስፋ የሌለው ሰው ለራሱም ሆነ ለሌሎች አይጠቅምም... ለትውልድ አያስብም፣ ለስብዕናው አይጠነቀቅም፣ ርሕራሔና ፍቅር አያውቅም...  በግልጽ ቋንቋ ተስፋ-ቢስ ሰው ጨካኝ ነው...


"A person who has completely abandoned hope may lose the motivation to care, create, or protect."



ስለዚህ የሰው ልጅ የተስፋ ነዳጅ ያስፈልገዋል...


በሌላ በኩል ግን ተስፋ፣ ዓይኖችህን ከዛሬ ላይ አንስተህ ባልተጨበጠ 'ነግ' ላይ እንድትተክል የሚያደርግ አደንዛዥ ዕጽ ነው... እውን (Real) በሆነውና በምናባዊው (Imagined) ሁኔታ መሐል ያለውን ልዩነት ያፈርስብሃል...


ነገ የተሻለ ግንኙነት እመሰርታለሁ፣ ነገ የተሻለ ስራ አገኛለሁ፣ ነገ የተሻለ ቀን ይመጣል... ወዘተ እያልክ ተጨባጭ ከሆነው የዛሬ እውነታህ የሚፈነጥቁ የብርሃን ቅንጣቶችን ከማሳደግ ይልቅ በማይመጣ ነገ ውስጥ የሳልከውን የሚንቦገቦግ ዥረት እያሰብክ ዕድሎችህን እንድታመክን ሊያደርግህ ይችላል...


ነገ ምን ውብ ዛፍ ቢሆን የዛሬ መደብ ላይ ከምትዘራው ዘር የለጠቀ እንጂ በተዓምራት የቆመ ሊሆን አይችልም...


ለነገሩ ተስፋ ስለ ነገ ብቻ አይደለም - ስለ ዛሬም ነው... 'ነገ ምን እንደያዘ ባላውቅም ዛሬ መልካም ማድረግ አለብኝ' ብሎ ተስፋ ማድረግ አለ... ደግሞ እንደ Victor Frankl እጅግ አሰቃቂ ግፍና መከራ በሚወርድበት የናዚ ካምፕ ውስጥ ሆኖ እንኳ መኖርን የሚያስቀጥል የሕይወት ትርጉም ማግኘት አለ...


ብርቱ ገበሬ የሚዘራት እያንዳንዷ ዘር ነገ ዛፍ ሆና ፍሬ እንደምትሰጠው ያምናል... አበው "ገበሬን የሚያህል አማኝ የለም" የሚሉትም ለዚሁ ነው... አፈር ላይ የጣላት ነቁጥ ጥሬ ለእልፍ ፍራፍሬ ምክንያት እንደምትሆን ያውቃል... በዚህም ምክንያት ዕለት ዕለት ለዘሯ የሚያስፈልገውን ሁሉ ያደርጋል... 'የነግ ተስፋ' አሸንፎት ግን ድርስ አዝመራ ወይም ሙሉ ጎተራ፣ የደለበ ከብት ወይም የመና በረከት ቁጭ ብሎ አይጠብቅም...


ነገሩን በመንፈሳዊ ዕሳቤ ውስጥ ካየነው፣ ገበሬው ችግኝ የሚተክለው እኔ እጠቀምበታለሁ ብሎ ብቻ ላይሆን ይችላል... እርሱ እንኳ ባይኖር ለሌሎች ጥላ እንዲሆን አስቦም ጭምር እንጂ... 

___

ነገሩን ለማጠቃለል...


ተስፋ ከዛሬ (ከተጨባጩ እውነት) እስካፋታህ ድረስ ጤናማ አይደለም - ይልቁንም ለቅዠት ይቀርባል... የነገ ውጤትህን አሁንህ ላይ እያየህ እንድትበረታ ሲያደርግ ግን ጉልበት ነው...


ስለዚህ... 


ለሰው ልጅ የእውነታ ስርም፣ የምናብ ክንፍም ያስፈልገዋል... ክንፍ ያጣ ስር እስረኛ እንደሚያደርግ ሁሉ፣ ስር የሌለው ክንፍም ቅዠታም ያደርጋል... ሁለቱን ማዛነቅ ግን ጥበብ ነው...


መድኃኒትም ቢሆን በአወሳሰድ ምክንያት መርዝ ሊሆን ይችላልና!!

___

"Hope should not be a place where we hide from today. It should be the light that helps us walk through today."


____

@bridgethoughts
9🔥3👍1🥰1
👀
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
🤔7
ጨረርና ጸሐይ

.
.
.

ለህይወቴ ትርጉም የሚሰጣት አዲስ ነገር ለመሆን መባዘኔ አይደለም... ቀድሞውኑ የሆንኩትን ማንነቴን ማስታወሴ እንጂ…


በየማለዳው የምነቃው በጸጥታና በድንቅ ስሜት ነው… ከዋክብትን የሚያንቀሳቅሰው፣ አበቦችን የሚያፈካውና ወንዞችን የሚያስጉዘው ያው ታላቅ ኃይል፣ በእኔም ውስጥ እንደሚተነፍስ በማሰብ…


በየቀኑ የሚቀስቅሰኝ ብርታት በዚህ ጽንፈ ዓለም ውስጥ እንግዳ ወይንም ከህልውና ጋር ብቻዬን የምታገል ንጡል ነፍስ እንዳልሆንኩ ማወቄ ነው… እኔ የውቅያኖሱ ማዕበል አካል፣ የጽንፈ ዓለሙ ቅንብር ዜማ፣ የህላዌ ዛፍ አንድ ቅጠል ነኝ…


ለዚህ ነው - በስራ፣ በምኞት፣ በስኬትና በውድቀት ጩኸት መካከል፣ ማንነትዋን በመዘንጋት ለምትንገላታዋ ነፍሴ ደጋግሜ እንዲህ የምላት፡


‘እኔ የምልዓቱ አንድ ክፍል ነኝ - ሙሉውም የእኔ አካል ነው…’


ህይወትን ድል ለመንሳት፣ ከእሷ ለማምለጥ፣ ወይም ሙሉ በሙሉ ለመረዳት እዚህ አልተገኘሁም… እዚህ የመጣሁት በህልውና ውዝዋዜ ውስጥ በንቃት፣ በፍቅርና በሙሉ ልብ ለመሳተፍ ብቻ ነው…


አዎን...


ከዋክብት ከኔ የራቁ ግዑዝ ነገሮች አይደሉም… እንጅላቶቼ እንጂ…  ጽንፈ ዓለም ከውጪ ቆሞ የሚታዘበኝ ባዕድ አይደለም… በእኔ አይኖች በኩል ራሱን የሚመለከት ህያው እንጂ… ወንዞች በደሜ ውስጥ ይፈሳሉ… ምድር በሰውነቴ ውስጥ ትራመዳለች…. 


ስለዚህ ተግባሬ እጅግ ቀላል ነው…


👉 ህላዌ በጸጥታ ውስጥ ሲያወራ ለመስማት መንቃት…

👉 ራሴን በሌሎች ውስጥ አይቼ እስክመሰክር መውደድ…

👉 ህይወት ያለ ምንም ተቃውሞ በእኔ ውስጥ እንድትፈስ ራሴን ፍጹም ባዶ ማድረግ…

👉 እያንዳንዱ እንቅስቃሴ ከሚፈልቅበት ከዚያ ታላቅ ምልዓት ሳልለይ መኖር…

.
.
.

ግና እንደማንኛውም ሰው በየመሐሉ ይህን ተግባሬን እዘነጋለሁ... ወደ ንቃቴ ስመለስ ደግሞ መልሼ እንዲህ እላለሁ:


‘እኔ መንፈሳዊ ጉዞን በመለማመድ ላይ ያለሁ ተራ ሰው አይደለሁም… "እኔ" በሚባል አጭርና ውብ ቅጽበት ውስጥ ራሱን እያወቀና እያስተዋለ የሚገኝ ጽንፈ ዓለም እንጂ…’


ለዚህም ነው 'በህይወት ውስጥ የተለየ ግብና ዓላማ የለኝም - የተለየ ኃላፊነት እንጂ' የምለው…


"የመነጠል" ከሚመስል የቅዠት እንቅልፍ መንቃት ብሎም በሁለንተና መልክ ለሚገለጠው ለዚያ ለ"አንዱ ህይወት" መታያ ሆኖ መኖር…

ፀሐይ ለሁሉ እንደምትፈነጥቀው ሁሉ ያለስስት መውደድ…

በአለቶች መሃል መንገዱን እንደሚፈልግ ወንዝ መፍሰስ…

ብሎም... 

ቀድሞውኑ ወደቆምኩበት እውነተኛ ስፍራ መድረስ… ይህ ነው የኔ ኃላፊነት...

.
.
.

በአጭሩ…


ለህይወቴ ትርጉም የሚሰጣት፣ ከህልውና የተለየሁ እንዳልሆንኩ ማስታወሴ ነው… በየቀኑ ብርታት የሚሆነኝ፣ ጋላክሲዎችን የሚያንቀሳቅሰው ያው ጥበብ በልቤ ውስጥ እንደሚመታ ማወቄ ነው…


'አንተ በውቅያኖስ ውስጥ ያለች አንዲት ጠብታ አይደለህም… ራሱን በጠብታ መልክ የሚገልጠው ያንኑ ውቅያኖስ ነህ እንጂ' እያልኩ ዘወትር ራሴን አሳስበዋለሁ…


ከህይወት የተለየሁ እንዳልሆንኩ ማስታወሴ ደግሞ ለህይወቴ ትርጉም ይሰጣታል…


ጋላክሲዎችን የሚያሽከረክረው፣ ውቅያኖሶችን የሚያናውጠውና ደኖችን የሚያለመልመው ያው እውቀት በልቤ በኩል እንደሚመታና በሳምባዎቼ በኩል እንደሚተነፍስ ማወቄ በየቀኑ ያበረታኛል…


በዚህ ጽንፈ ዓለም ውስጥ - በስራ፣ በስኬትና በትግል መካከል እንደ ተራ የሚያልፍ እንግዳ እንዳልሆንኩ ማወቄ ያተጋኛል…


እኔ - "እኔ" በሚባል ጊዜያዊ መልክ ራሱን እያወቀ ያለ ጽንፈ ዓለሙን ራሱን ነኝ…


የእኔ ተግባር ሙሉ መሆን አይደለም… ይልቁንም ከቶውንም ቢሆን ከሙሉው ተለይቼ እንደማላውቅ ማስታወስ እንጂ…


❗️ ማዕበሉ ውቅያኖሱን ፍለጋ ህይወቱን ሙሉ ይባዝናል… በመጨረሻ ግን ቀድሞውኑ ውሃ እንደነበረ ይደርስበታል…

 .
.
.

(ማስታወሻ: ይህ ጽሑፍ ለገጹ እንዲስማማ ከመሸራረፉ ውጪ ለአንዲት ወዳጄ የነፍስ ጥያቄ በውስጥ መስመር የተላከ ጨዋታ ነው)

____

@bridgethoughts
10🥰3🔥1
👍

ከመስበቅዎ በፊት...


የተወረወረ ጦር የሚያውቀው አንድ አቅጣጫ ብቻ ነው፤ ንግግር ግን መሄድን ብቻ ሳይሆን መመላለስንም ያውቃል...


ሰሞኑን አንድ ፊልም እያየሁ ነበር… "Man of War" የተሰኘ የ 2026 የጦርነት ፊልም ነው…

 
ፊልሙ በሩሲያና ዩክሬን ጦርነት መሃል በቅጥረኛ ወታደሮች የታገተችን እንስት ለማዳን በጦርነት ቀውስ ውስጥ ወደምትገኘው ዩክሬን የተጓዘን አንድ ጡረተኛ የአሜሪካ ልዩ ኃይል (Special Forces) ወታደርን ጀብዱ ያትታል…

 
ፊልሙ ሲጀምር - ቀደም ሲል በተሰማራባቸው የጦር ሜዳዎች  የደከመውን፣ በከባድ የስነ-ልቦና ቀውስ (Trauma) ውስጥ የሚገኘውን እና ራሱን የማጥፋት ሃሳብ የሚታገለውን ሰው እናያለን... ይህ ሰው ጡረተኛው የባህር ኃይል ልዩ ተዋጊ (Navy SEAL) እና የ CIA ወኪል ማይክል ኮነር ሲሆን በአፓርታማው ውስጥ በከፍተኛ የስካር መንፈስ ውስጥ ሆኖ እንደተቀመጠ ይቀላቀለናል…

 
ኮነር (በመዝገብ ስሙ LaMonica Garrett) ራሱን ለማጥፋት በሚዳዳበት ቅጽበት በዩክሬን ካርኪቭ በሚገኝ የህፃናት ማሳደጊያ ውስጥ ረዳት ሰራተኛ ሆና ከምትሰራውና የማደጎ ልጁ ከሆነችው ራይሊ አስቸኳይ የቪዲዮ ጥሪ ይደርሰዋል…. የተጨነቀች ሴት ድምጽ፣ በፍርሃት የተዋጠች እንስት ፊት፣ በፈንጂዎች የምትናጥ ከተማ ድምጽ…


"Mike, I'm in trouble. I need your help."


"I'm still in Kharkiv."


"I couldn't leave them, Mike. The Russians just crossed the border. They're bombing the city."

 
ኮነር የሚወዳት ራይሊ፣ ኮኒየቭ በተባለ ጨካኝ የቅጥረኛ ጦር አዛዥ ታግታ ስትወሰድ በስልኩ ስክሪን ላይ እያየ ምንም ማድረግ ካለመቻል በሚፈጠር ሕመም ይጨሳል…

 
ያ ከደቂቃዎች በፊት ራሱን ለማጥፋት ሲጣጣር የነበረ ሰው፣ ድንገት የመኖሪያ ምክንያትና የሕላዌ ትርጉም እንዳገኘ ሁሉ ከሚገኝበት ባርሴሎና ወደ ዩክሬን በድብቅ የመግባት ሃሳብ ወጥኖ በቀድሞ ወዳጆቹ አመቻችነት ጉዞ ይጀምራል…

 
ከዚህ በኋላ ያለው ታሪክ ለተመልካች የሚተው ነው… ጦርነት የሚያመጣቸውን ሰቆቃዎች ሁሉ በፊልሙ ውስጥ ታያላችሁ… ስደት፣ መፈናቀል፣ አስገድዶ መደፈር፣ የሕፃናት - የእናቶችና የአዛውንቶች ሰቆቃ፣ የከተሞች መድቀቅ፣ የመሰረተ ልማት መውደም - ምኑ ቅጡ…

.
.
.

ዛሬ ስለዚህ ፊልም እንዳወራ የገፋፋኝ በታሪኩ ዋና ገጸ-ባሕሪ አማካይነት በፊልሙ መካከል ለዩክሬንያዊው መንገድ መሪ የተነገረ ሸንቋጭ ንግግር ነው… እንዲህ ይላል…

 
“War is a monster that chews up everything in its path.” ~ Connor

 
 
 ደጋግሜ ሰማሁት...

____ 


አዎን... War is a monster...


ጦርነት አውሬ ነው... መቼም ቢሆን አይጠረቃም... ለስግብግብነቱ ልክ፣ ለሆዱም እምብርት የለውም... ባለጠብመንጃውንም ሆነ ሰላማዊውን አኩል ይሰለቅጣል... ሕፃናት አድገው ሰው እንዳይሆኑ፣ ፍቅረኞች ተጋብተው ጎጆ እንዳይሰሩ፣ ሕልሞች ተወልደው እውን እንዳይሆኑ በአጭር ይቀጫል...


War is a monster...


የአበባ መስኮችን ወደ መቃብር፣ መኖሪያ ቤቶችን ወደ ፍርስራሽ፣ ታላላቅ ከተሞችን ወደ ትዝታነት እስኪቀየሩ ድረስ ያጋያቸዋል... ጦርነት ተስፋን ያገረጣል፣ የነገን ብርሃን ይነጥቃል፣ ሳቅና ጨዋታ በተመላለሰባቸው ቀዬዎች ላይ አስፈሪ ጭጭታን ትቶ ያልፋል... ጦርነት መቼም ቢሆን ሆዱን አሸንፎ አያውቅም... የሚበላው ነገር ሁሉ አልቆ ባዶነት ራሱ ባዶ እስኪቀር መቦጨቁንና መዋጡን አያቆምም…


War is a monster...


ለእርሱ ልዩ ልጅ፣ የተመረጠ ሕዝብ፣ ወይም ብቸኛ ተበዳይ የለም - ሁሉንም ያደቃል... አስቀድሞ ሥጋን - በመቀጠል እምነትን ይበላል... አስቀድሞ ሕንፃዎችን - በመቀጠል የጥሪት ባለቤትነትን ያፈርሳል... አስቀድሞ ታሪክን - ከዚያም ማንነትን ይበላል... ምድርን በቁስል የተሞላች፣ ነዋሪን በድንጋጤ የታወከ፣ የሞቱትንም በወዳጆቻቸው ልብ ውስጥ ባልተፈጸመ ሕልም ሜዳ እንደቀሩ ብኩኖች ይስላል... ስግብግብነቱ ለመሬት ወይም ለሥልጣን ሳይሆን፣ ሰው ያደረገንን መልካም ነገር ሁሉ ለማጥፋት ነው…


War is a monster...


የጦርነት አስፈሪው ነገር ገዳይነቱ ብቻ አይደለም የተስፋን ዕድልና የመጻኢ ሕይወትን ሙሉ በሙሉ ማጨለሙም እንጂ... በጦርነት የምትወድቅ እያንዳንዷ ነፍስ - ያልተጻፈ ግጥም፣ ያልተከፈተ መድኃኒት፣ ያልተወለደ ልጅ፣ ያልተጠናቀቀ ሙዚቃ፣ ያልተነገረ "እወድሃለሁ/እወድሻለሁ"፣ ያልተመሠረተ ወዳጅነት፣ ያልተተከለ ድንግል ጫካ፣ እና መቼም ቢሆን ሊመጣ የማይችል ጣፋጭ ትዝታዎችን ሁሉ ይዛ ትቀበራለች… የወግ ቀብር እንኳ አያውቃትም...

.
.
.

አውቃለሁ ለሃገሬ ይህ ሃቅ አይጠፋትም... የሆነችውን ሁሉ የሆነችው በጦር ወዳድ ልጆቿ ሰበብ ነው... ይህ ግን ጦርነትን ቤተኛዋ ከመሆን አላስቀረውም... መዝገብ ከሚያውቀው የ3 ሺህ ዓመት ዕድሜዋ እንኳ 9/10ኛው ገጽ የተያዘው በዚሁ አውሬ የውድመት ታሪክ ነው... 'ከባዕዳን' የጥይት አረርም ሆነ ከአብራኳ ክፋዮች ሳንጃ መሞሻለቅ እፎይ ብላ አታውቅም...


ግን ዛሬም እዚያው ናት... ዛሬም ጎራዴ ከማርዘም፣ ሰይፍ ከመቆልመም አልወጣችም... ከሰማይ በራሪ እስከ ምድር ተሽከርካሪ ከማጠራቀም አልወጣችም... የጓዳዋን ችግር እንኳ በበጎ ቃል ሕብር መፍታት አልቻለችም... የልጆቿ እብሪት፣ መናናቅ እና ጥላቻ በባሩድ ሽታ እንጂ በንግግር ፋታ ሲረግብ ታይቶ አይታወቅም...


[አንድ ላይ ብንሆንም ፈጽሞ አንድነት የለንም...]

.
.
.

ይህ በዓለም ዙሪያም የምናየው እብደት ነው... 'ሰልጥነናል፣ ዘመናዊ ሆነናል፣ ሰማያትን መርምረናል' ወዘተ የሚሉን እንኳ ሳይቀሩ ቋንቋቸው አረር ብቻ ነው... 


[እውነት ለመናገር የሰለጠነው አስተሳሰባችን አይደለም - ማሽኖቻችን ብቻ እንጂ...]


እውነት ለመናገር የዚህ ትውልድና አስተሳሰቡ አካል መሆን በጭራሽ አያኮራም!!...

____

የሃገሬ ልጆች ግን እረፉ!!...


ጦር የምትስሉት የመለያየት ተስፋ-ቢስ ምናባችሁ ከአንድ የሰው ልጅነታችሁ እውነት በላይ ገዝፎ ስለሚታያችሁ ነው...

ግን አስታውሱ...

'ከጠላታችሁ' ሳንባ የሚወጣው አየር፣ እናንተን በህይወት የሚያቆየው ያው አየር ነው... 

'ከጠላታችሁ' አካል የሚፈሰው ደም በእናንተም ውስጥ የሚፈሰው ያው ቀይ ወንዝ ነው... 

ጦርነት የሚጀምረው ሰውነታችሁ ሲደበዝዝ፣ መወገናችሁ ሲጎላና የሰውነት መልክ አጥታችሁ አውሬያዊነት ስትላበሱ ነው...


እናም እረፉ - የጦር ክንዳችሁን እጠፉ!!

____

🦢ሰላም በምድራችን ላይ ይስፈን!!🦢

____


📩 [ይህን መልዕክት የሰው ልጆችን ሰላም ለሚሹ ወዳጆችዎ አጋሩልኝ - አመሰግናለሁ]

____


@bridgethoughts
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
12🕊7🫡2👍1🔥1
.
.
.

ኢትዮጵያ ውስጥ የተሽከርካሪ ትርፍ መጫን የሚነገርህ ሲገለበጥ ብቻ ነው... 

___

[አዎን - ይህ ሃሳብ ስለ ሕዝብ ማመላለሻ አይደለም]

___

@bridgethoughts
6👌3🔥2
⭐️

[[ማምለጥ ስላልቻለ የቆየ እስረኛ ታማኝ አይባልም...]]

.
.
.


ማሕበረሰባችን ውስጥ መተማመን ላልቷል... ታማኝነት በእጅጉ ሳስቷል... ምክንያቱ ብዙ ቢሆንም ይህ ዘመን ልዩ ቀለሙ በቃል አለመገኘት ነው... ለሕሊና ጀርባ መስጠት፣ ለስሜት ነውጥ ፊት ማሳየት፣ ቃልኪዳንን ማተናነስ፣ በየኩርባው ማነቀፍና ማንከስ ጉልህ ምልክቱ ነው...


[ይህ ጉዳይ በተለይ በግንኙነት ውስጥ እጅግ ከባዱ ፈተና ይመስለኛል...]


እርግጥ ነው - በሰዎች ዕለታዊ መስተጋብር ውስጥ ግንኙነትን እንደ ይዞታ የማሰብ አዝማሚያ መኖሩን መካድ አይቻልም... 'እከሊት የእንትና ናት'፣ 'እከሌ የእኔ ነው'፣ 'እርሷ የኔ ናት' እያልን ሰውነትን እንደ ቁስ ለመቁጠር መዳዳታችን እውቅ ነው... ጥንዶች ለየብቻ ሕይወት እንደሌላቸው ሁሉ የአንድ ሰው እስረኛ እንደሆኑ አድርገን እናስባለን... ይህ ግን ፍቅር አይደለም...


ይልቅ እርሷ ሁሌም ነፃ ሆና እርሱን ትመርጣለች - ሌላ ምርጫ ባላት ጊዜም ቢሆን... እርሱ ሁሌም ነፃ ሆኖ እርሷን ይላል - ብዙ ሴቶች ዙሪያው ሳሉም ጭምር... [ልዩነቱ ግልጽ ነው...]


ማምለጥ ስላልቻለ የቆየ እስረኛ ታማኝ አይባልም... የመተው ምርጫ እያለው ሁሌም በዚያ ያለ ሰው ግን እርሱ ፍቅርን ያውቃታል...


[ይህ በእንዲህ እንዳለ - ይላል ራዲዮን...]


ፍቅርን የሚያዘልቁት ከባዱን ዳገት መርጠው እንጂ ቀላሉን ቁልቁለት አቋርጠው አይደለም... ስለዚህ መታመን ጥንካሬን ይፈልጋል... ጽናትን ይፈልጋል... ምርጫ ነፃነት ቢሆንም ዳሩ በማንኛውም ሁኔታ ውስጥ ለቃል ማደር ብርታትን ይጠይቃል... ሲታዩም ሳይታዩም ለአቋም መገዛት የሞራል ልዕልናን ይፈልጋል... 


እኔና እርሷ 'ሚጋራና 'ሚከለከለውን ካለየን... 'ሚገለጥ 'ሚሸፈነውን ካልመረጥን... በነ'ከሌ ድርሻና በራስ ሰው ድብቅ ላይ - ድንበር ካላኖርን ታማኝነት ውሉን ይስታል... ስብዕና ይተናነሳል...


ያም ብቻ አይደለም፣ እኔ 'ጨዋ ነው ቀሚሷ' ለማለት ሳመነታ፣ እርሷ 'ልቡ የኔ ብቻ ናት' ለማለት ድፍረት ታጣለች... 


[ይሄኔ... ያልታሰረ ልብ ይዞ ጣትን በቀለበት የማሰር ልማድ ትርጉም ያጣል...]


"... ማተብን ቢያጠብቁ - የአንጀት ፍቅር ሽረው
በቁርባን ቢጋቡ - ቃልኪዳን ሸርሽረው
ለአፍ ዓመል ካልሆነ - ማ'ላው ከምን ሊያስጥል
በቀለበት ታስሮስ - ፍቅር ምን ሊቀጥል..." እንዲል ከያኒው


እንደ ሰው ማሕበራዊ ተጋልጦ (Exposure) ቢኖረንም እንደ ቤተሰብ ደግሞ የማይነካ ግዛት አለን... ካርታ ባይኖረውም ቅሉ ቤተሰብ ሃገር ነው፣ የማይቆረስ ስስ ገላ - የሚከለል እውነት፣ የማይደራደሩበት ልዓላዊነት አለው...


[ለቤት ከምንገልጠው ገጽ ላይ ገመና ባይኖረንም ለውጭ ከምንጋራው ላይ ግን ደስታና ሃዘናችንም ቁጥብ ነው...]


ከገበያ ብንሸምትም የምናበስለውን የምናውቀው እኛ ነን... (የሸመትነውን ያወቀ ሁሉ የበላነውን መለየት የለበትም!)... ከአደባባይ ብንውልም አዳር የሁለታችን ብቻ ምስጢር ነው... (ያገኘን ሁሉ ልባችንን ማግኘት የለበትም)...


[ከሳቅም ሸርፈው ይስቁታል፣ ከቃልም መርጠው ያወጉታል...]


ለባልሽ ብቻ የምትስቂውን ሳቅ የምትስቂለት እስካለ ድረስ ታማኝነትሽ ከንቱ ነው... ለሚስትህ ብቻ በሚመጥን ቃል የምታወራት እስካለች ድረስ ሴሰኛነትህ ግልጽ ነው...

____

"Lust is a strong need. Love is not a need but a longing. When you love, you settle down – nothing more is needed." ~ Sadhguru


_


@bridgethoughts
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
12🔥4👏1
.
.
.

ብዙ ሰዎች ገደብ አልባ ምርጫን 'ከነፃነት' ጋር፣ ልክ የሌለው ትኩረትን ደግሞ 'ከፍቅር' ጋር ያምታታሉ... በዚህም ምክንያት ከእጃቸው ላይ ያለውን በረከት በማይጨበጥ ቅዥት ሲያዘርፉ ይኖራሉ...

.
.
.

[የቆምንበትን ስንተው...]


ሁሌም ቢሆን ካንተ ሚስት 'የምትበልጥ' ሴት በዚያ አለች... አንተ ግን የሁሏም አትሆንም... የትም ቢሆን ከባልሽ 'የሚሻሉ' ወንዶች ይኖራሉ... ሚስትነትሽን ግን አይጋሩም...


እርግጥ ነው...


'የምትበልጥ' ወይም 'የሚሻል' የምንለው በስሜት ከባቢያችን ውስጥ የሚመላለሰውን ስሁት መስፈሪያ እንጂ አግባቢ መለኪያ አይደለም...


መቼም እንደ መዝለቂያ ምክንያታችን ሁሉ መግቢያና መግባቢያ በራችንም ልዩ ልዩ ነው...


ወንዶች - አካላዊ ውበት መግቢያችን፣ መላመድና መጣጣም መክረሚያችን ሊሆን ይችላል... ሆኖም ግን እኛ ካየነው ውበት 'የሚልቅ ውበት' ያላቸው ሌሎች ሴቶች በየትም አሉ...

[በግንኙነት ውስጥ ግን ልባችን የሚዳረው ለአንዷ ብቻ ነው...]


ሴቶች - ኢኮኖሚያዊ አቅም ማንኳኩያቸው፣ ቁምነገርና ብስለት መሻገሪያቸው ሊሆን ይችላል... ከሚያውቁት ወንድ የሚበልጥ ሃብት ያለው ወንድ ግን በየትም አለ... 

[በግንኙነት ውስጥ ግን የልብ አዳር የሚሰምረው አንዱ ጋ ብቻ ነው...]



"A river gains its power not because it flows everywhere, but because it accepts its banks and moves toward its destination."



አዎን... ሁሌም ቢሆን እጃችን ላይ ካለው 'የሚበልጥ' ነገር ከማዶም ከባሻገርም አለ... ልባችንን የሚያቀልጥ ግን ላይሆን ይችላል... የትም ቢሆን የምርጫ መስፈርታችንን የሚያስንቅ እልፍ አለ... ነፍሳችንን የሚዘልቅ ግን ላይሆን ይችላል...


ውበት ይስብ ይሆናል - መሰረት የሚቆመው ግን ስብዕና ላይ ነው... ቅብጥብጥ ስሜት ግንኙነትን ሊያስጀምር ይችላል - የሚዘልቀው ግን ጥልቀት ላይ ነው... 


'ቆንጆ' ሴት በዓይንህ ትገባለች፣ ትርጉም ያላቷ ግን ነፍስህን ትዘልቃለች... ብራም ወንድ ቀልብሽን ይወስዳል፣ የሚረዳሽ ግን ለግብሽ ያዋጣል...


በነገራችን ላይ...


ችግሩ ያለው 'የተሻለ' ማየታችን ላይ አይደለም - ማመናችን ውስጥ እንጂ... የሆነ ነገር 'የተሻለ ነው' ማለት የግድ ትርጉም የሚሰጥ ነው ማለት አይደለም... አንድ ሰው ከሚስቱ 'በላይ' ቆንጆ ሲያገኝ የበለጠ ዋጋ ያላት አገኘ ማለት እንዳልሆነው ሁሉ...


ሌላም እውነት አለ...


'የተሻለ' ማየት እስከጀመርን ድረስ የቀደመውን 'አፍቅረናል' ማለት አንችልም... ዘግይቶ የሚረታን እስከመጣ ድረስ የቆየው ቦታ ይዞ ነበር አይባልም... ሁሌም 'የተሻለ' እስካለን ድረስ ፍለጋው በቅቶናል አያስብልም...


ትርጉም ያለው ግንኙነት - የመምረጥ ብልሃትን ይፈልጋል... መምረጥ - ኁልቆ መሳፍርት አማራጮችን መተውን ይሻል...


"Freedom means consciously choosing what deserves your devotion."


Relationship - አስቦ የመምረጥ፣ መርጦም የመዝለቅ ጉዳይ ነው... ያም ሆኖ ግን ከበር ያላስተዋሉት እንከን ከቤት አይጎትትም ማለት አይቻልም... በዋዜማ ያልተገለጠ ጸባይ በማግስት አይፀኸይም ሊባል አይችልም...


[አብሮነት በማትፈታው ቋጠሮ ቁርቋሬ ምቾት ማጣት አይደለም - ልታቻችል በምትችለው ክፍተት ላይ መሸካከም እንጂ...]

____


@bridgethoughts
13🔥3🙏3👍1
➡️

.
.
.


በጦርነት ምድር ቀድሞ የሚሞተው እውነት ወይም ህይወት አይደለም፤ 'የእርሱ ህመም እንደኔ ህመም ያለ ነው፣ የእርሷ ስቃይ እንደኔ ዓይነት ስቃይ ነው' የሚለው እውቅና እንጂ...


እያንዳንዱ ጥይት ኢላማውን ሁለት ጊዜ ይመታል - አንዴ አካልን ቀስፎ፣ ደግሞም የአካሉን ባለቤት ውብ ነገዎችን ገድሎ...


ጦርነት - ባልተፈፀመ ኑረት የደም ቀለምነት ክፉ ታሪክ የሚፃፍበት የመከራ ደብተር ነው...


ጦርነት 'ድል ላደረጉ' ህያዋን የክብር አክሊል ሲጭንላቸው፣ የሞቱትን ተስፋና ነገ ግን ከመሬት ስር ይደብቃል... የውጊያ ሜዳ ነግ ሳይወለድ የሚቀበርበት መቃብር ነው... ጦርነት አንድን ህይወት ብቻ አይቀስፍም፣ ከዚያ ህይወት ሊያብብ የሚችለውን የነገውን ትውልድ ጭምር እንጂ...


በጦርነት ውስጥ ጎልቶ የሚሰማው ድምፅ የቦምብ ፍንዳታ አይደለም፣ ወጥቶ የቀረ ክፋያቸውን በሚጠብቁ አፍቃሪዎች ጎጆ ውስጥ የሚረበው ጭጭታ እንጂ... 


ጦርነት ሲያበቃ የመሳሪያዎች አፍ ይዘጋል፣ ድምፃቸውም ይፀጥታል፣ በህፃናት ልብ ውስጥ ያለው ጩኸት ገደል ማሚቶ ግን ለዘላለም ይኖራል...


በጦርነት አንድም የሚያሸንፍ ህዝብ የለም፣ የአንዳንዶች 'ድል' ከሌሎቹ ኪሳራ አንፃር ኁልቆ አልባ ከመሆኑ ውጪ...


ምድር መቼም ቢሆን ደም እንድንረጫት ጠይቃን አታውቅም፣ ደም የሚጠማው የሰው ልጅ አእምሮ ብቻ ነው...


ጦርነት የሌላው ሰው ሞት ለኔ ህይወት ይሆናል ብሎ እራስን የሚያታልሉበት ቅዠት ነው... 


ጦርነት የሌላው አካል መቁሰል፣ ለኛ ፈውስ እንደሚሆን የምናስብበት የውሸት ተስፋ ነው...


ጦርነት ማለት...


[ብቻ ይደክማል...]

____


@bridgethoughts
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
🕊96🔥1
👣

መስተሃልያችን ጥንተ አብሶ አለባት... በአንድ በኩል ከአንድ ሰው ጋር ጥልቅ የሆነ ትስስር ትፈልጋለች... በዚያው ሁኔታ ውስጥ በብዙ ሌሎች መደነቅን ደግሞ ታሻትታለች...

.
.
.

በሁሉ መወደድ ይርበናል... በሁሉ መወደስ ይናፍቀናል... በምናውቀውም በማናውቀውም አንደበት መደነቅ ያጓጓናል... በምናገኘውም በማናገኘውም ልብ ውስጥ ማደር ይከይፈናል... 


'የኔ' ያልካት ጎንህ ኖራም ያንተ ያልሆነችው እንድትወድህ ከመሆን አትቦዝንም - ቢያንስ መሳቧን አታወግዘውም... ውዱ ባልሽ ቤት ቢኖርም የውጭው ወደድኩ ባይ እንዲያደንቅሽ ከመሆን አትሰንፊም - ቢያንስ ጨከን ብለሽ 'ሰው እንዳለሽ' አትነግሪውም...


Social media ላይ የምናየው የእዩኝና ውደዱኝ ሽሚያ የዚህ ስሜት ተቀጥላ ነው... 


አብዛኞቹ የመድረኩ ሰዎች የሚሰጡን ሃሳብ፣ የሚያሳዩን ፈጠራ፣ የሚጋሩን ቁምነገር የላቸውም... ሆኖም እዩን ለማለት እርቃን አደባባይ ከመቆም አይመለሱም... አንዳች ኖሯቸው ብናይ፣ ፍሬ ቋጥረው ብንሰይ ባልከፋን... የኑሮን ብልሃት አቀብለው፣ ለጠብ አተካራው መፍትሔ ሰንቀው መስኮታችንን ቢሞሉ ባልቸገረን... ግና 'እዩ' የሚሉን ወቅት የሚገድበውን፣ ዕድሜ 'ሚያፈርሰውን ነው...


ያም ሆኖ ግን አወዳሽና አንጋሹ ብዙ ነው... አንዳንዱ ከልቡ ያለው የውዴታ ልክ ባይታወቅም Virtual መውደዱን አይነሳም፤ ሌላው በአካል ወድቀው ቢያገኝ ሊያነሳቸው መፍቀዱን ባናውቅም የለጠፉትን ማየት አይሰለችም... 


ይህ በተራው ቅዠታዊ የመፈለግ ስሜት በማንበሩ ብዙ ሰዎች በንፋስ ዓለም ለፈጠሩት ባዶ ዓለም ቅድሚያ የመስጠትና አካላዊውን መፈላለግ የመተው ሁኔታ ውስጥ የገቡ ይመስላል... አብሮነት፣ ፍቅር፣ ጋብቻና ጓደኝነት የሚመዘንበት መንገድም ከጠየመ ከራርሟል...


በሌላ በኩል ደግሞ 'የሁሉም ሁን' የሚመስል ያልታወጀ ማሕበረሰባዊ ስምምነት እየተፈጠረ ይመስላል...


ይህ ጉዳይ ዝም ብሎ መላምት አይደለም...


ሴት አርቲስቶች ካገቡ በኋላ Cast የመደረግ ዕድላቸው የመነመነ እንደሆነ ሰምተናል... ለሞዴሎች 'በጊዜያቸው' ግንኙነት መመስረት ቢዝነሳቸው እንደማይፈቅድላቸው ሲነገር አድምጠናል... ለትላልቅ ሆቴልና ባር አስተናጋጆች ግንኙነት ውስጥ መኖር እንጀራቸውን የሚያሳጣ ነገር መሆኑን አስተውለናል... 'የቲክቶክ ዕይታ' ሳይቀር በትዳር ማግስት ሳስቶ እጃችንን በአፍ አስጭኖናል...


አንዲት ዘፋኝ ከወራት በፊት በቲቪ መስኮት በሰጠችው ቃለ-መጠይቅ የሙዚቃ ባለሙያ ሴቶች ትዳር ከያዙ በኋላ ለክለብ መድረክ የሚኖራቸው ተፈላጊነት በከፍተኛ ደረጃ እንደሚወርድ ስትናገር ሰምተናል... 


ይህ የሚነግረን ምንድነው?... ተጠቃሚው፣ ዘፋኟ 'የሁሉም' መሆን እንደማትችል ቢያውቅም 'የእከሌ ናት' ተብሎ ተስፋ ከሚቆርጥ 'የማንም አይደለችም' ብሎ እየነሆለለ ቢዘልቅ፣ አልያም 'አንድ ቀን አገኛት ይሆናል' በሚል ተስፋ እየናወዘ ቢቀልጥ እንደሚመርጥ ነው...


[ይህ ግን የምር የምሩን ስናወራ በሽታ እንጂ ሌላ ስም የለውም...]


ነገሩ በዚህ ብቻ አይቆምም...


በሁሉ የመወደድ [የመፈለግ] አምሮት ያላቸው ሰዎች መብዛት ውሎ አድሮ የማንም ሳይሆኑ የሚያረጁ ላጤዎችን እያበዛው እንዳይሄድ ያሰጋል... 


አንዳንድ በበዛወርቅ ስልት:


"... አይሻልም ወይ መኖር - የማንም ሳይሆኑ
ልብ የፈቀደውን - እስኪለግስ ቀኑ..."


የሚሉን ወዳጆቻችን ሳይቀር 'ልብ የሚፈቅደውን' የሚያገኘው መች እንደሆነ ሳይነግሩን በዓይናችን ፊት እንዳረጁ - በምርጫ እንደባጁ አሉ... 


የመፈቀድ ረሃብ የሴቶች ብቻ አይደለም... የሰው ልጅ ሁሉ ነው... ወንድም ቢሆን በሀብቱ፣ በደረጃውና በሙያ ስኬቱ በኩል በሁሉ መፈለግን ይፈልጋታል... ዘመነኛው ኢጎ ጾታ አልባ ነው...


[በነገራችን ላይ ትዳር አለመፈለግ ችግር ነው የሚል እሳቤ የለኝም - ምርጫ እንጂ... እንዲያውም እነዚህ መስመሮች ለብቻ የመሆን መሻት (Solitude) ከብቸኝነት (Loneliness) ጋር ለማይምታታባቸው፣ ግንኙነት ውስጥ ባይኖሩም ምሩና ቅዠቱ ላልተደባለቀባቸው ሰዎች አያገለግሉም...]



ግና ምርጫችን - 'ሁሉ አማረሽ ሆኖ ገበያ መውጣትን'፣ 'መራጭ ሆኖ ከርሞ ከምራጭ መውደቅን'፣ ልብ እየፈለገ ሃሳብ አልረጋ ብሎ 'ቆሞ መቅረትን' ካስከተለ ልክ ነበር አያስብልም...

.
.
.


ነገሩ ሲጠቀለል...


እኔና አንተ/ቺ በዘመን ንብርብር ውስጥ እየተዥጎረጎርን፣ በመጭ ሂያጅ ፋሽን ቋሚ ቀለም እያጣን፣ ከልብ ወግ ይልቅ ለጭንቅላት ሃሳብ እጅ እየሰጠን - ቁምነገር ጠፍቶብናል ለማለት ያህል ነው...


____


@bridgethoughts
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
10🥰2🔥1👏1
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
6🥰1🙏1
😵‍💫

የዓመቱን የመጨረሻ እሁድ እንዴት ለማሳለፍ አቅዳችኋል?


ፍልስፍና፣ በተለይም የሩቅ ምስራቅና ዐፍሪካዊ ነጽሮተ ዓለም የስራዎቹ ማጠንጠኛ በማድረግ የምታውቁት ደራሲና ገጣሚ O' Pulto (ኦታም ፑልቶ) በ 92ተኛው የአውደ ፋጎስ መርሃግብር ላይ እንገናኝ ብሏችኋል...


በሙያ Landscape Architect (የመልክዓ ምድር ነዳፊ) የሆነው ደራሲው በዚህ ዕለት ሁለት አዳዲስ መፃሕፍቱን ያስተዋውቃል...


🤩ዑቡንቱ ዕና ፑልቶ” እና “የፕሌቶ ኃጢአት” 


መፃሕፍቱ ለማስተዋወቅ የሚሞክሩት ዐብሮኛዊ ፍልስፍና መልክዐምድርን እንደ ቅኔ ያያል... ቅኔ ደግሞ የተለያዩ ነበባዎችንና ትርጓሜዎችን ይፈቅዳል... 


እናም ይጠይቃል....


የቤተክርስቲያን ሥነ-ዕነጻ እንደመንፈሳዊ ጉዞ ካርታ ሊነበብ ይችላል? 

የግል መንፈሳዊ ጉዞን ብቻ ሳይሆን የሰው ዘርን የሥልጣኔ ጉዞ ዕምርታዎችንስ ሊያሳይ ይችላል?


ዝግጅቱ - የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያናትን ክበባዊ የቦታ አወቃቀሮችን እንደግላዊ የመንፈሳዊ ንቃት ካርታ፣ እንደ ሰው ዘር ሥልጣኔያዊ ዕመርታ ደረጃዎች እያሰናኘ ያቀርባል... በዐፍሪቃዊው ፍልስፍና ውስጥ የሚኖረውን መሠረታዊ ቦታም ባጭሩ ያስቃኛል... 


🔔 በነገራችን ላይ...


መድረኩ በዐፍሪቃ ዕጣፈንታ ቅኔያዊ ቅኝት፣ እና በፍልስፍናዊ ዕንስልስላት አማካኝነት በቅርቡ የሚጀመረውን ዐለምዐቀፍ የዐፍርቃ ፍልስፍናዊ ንቅናቄ በጋራ እንድንጀምረውና እንድንመራው ጭምር ይጋብዛል... 


በተለይ ደግሞ - ለወጣት ጸሐፍት፣ ስክሪን ራይተርስ፣ የፊልም ባለሙያዎች፣ የባህል አዋቂዎች፣ እና የቴክኖሎጂ ሰዎች ለዓመታት የሚዘልቁ ልዩ ዕድሎችን ለመጀመሪያ ጊዜ ያስተዋውቃል...


🔑 በቦታው ተገኝታችሁ የውይይቱና የዕድሎቹ ተሳታፊ ሁኑ።


📩 ይህን መልዕክት ለወዳጅዎ ያጋሩዋቸው

____

🗓️ ቀን - ዕሁድ - ጳጉሜ 01/2018

ሰዓት - ከቀኑ 8:00 ሰዓት

📍 ቦታ - ወመዘክር 

____

የደራሲውን ስራዎች ለመከታተል ይህን አዲስ ገጽ ይቀላቀሉ ⬇️

https://t.me/OPultoSinkneh
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
9🔥21🙏1
.
.
.

😵‍💫

በኖርንበት ጊዜ ሁሉ ሁሉንም አዲስ ዓመቶች የጀመርነው በበጎ ምኞትና በብዙ ምርቃቶች ነበር...


ስለ ሰላም

ስለ ብልጽግና

ስለ መተሳሰብ

ስለ መፋቀር

.
.
.

ስለ ብዙ ጥሩ ነገሮች በዕድሜ ዘመናችን ጸልየናል... በተነገረ ቅጽበት ሁሉ ለምርቃት አሜንታ ሰጥተናል... እጃችንን ዘርግተን፣ ድምፃችንን አጉልተን ይሁንልህ ይሁንልሽ ብለናል... 


መሬት ላይ ያለው እውነት ግን በተቃራኒው ነው... 


ሰው ከሌላው ጋር ቀርቶ ከራሱም ጋር ሰላም የለውም፤

ከቤቱ በረከት ከማዕዱ ረድኤት አያውቀውም፤

በመንገዱ እረፍት፣ በቀዬው ደህንነት አይሰማውም፤

ከመዝሙራችን በተቃራኒ ሃገር ሰላም ብርቋ ነው፤

ከልፋፌያችን በስተኋላ ወጥቶ መግባት በዕጣ ነው፤


ብቻ - መኖር በብዙ ሕመም የተሞላ አሰልቺ ጉዞ ነው!!


እኔ ላንተ ደስታ አላዋጣም... አንተ ለእርሷ መሳቅ ምክንያት አትሆንም... እነርሱ ለእነዚያ የስጋት ምንጭ ናቸው... እኛ ለነከሌ የምቾት ጠንቅ ነን...



የሆነ የተሳሳተ ነገር እንዳለ አይሰማችሁም?... ከኑረት Equation ውስጥ ያነጠብነው የሆነ ቁልፍ ማስሊያ እንዳለ አታስቡም?... ያላችሁበት ሁኔታ ተስማምቷችኋል?...


ግማሽ ምዕተ ዓመት የሞላው የ “Exodus” (1977) ድምጽ ዛሬም ይጮሃል...


“Open your eyes and look within. 
Are you satisfied with the life you're living?”~ Bob Marley



ስለ ሰላም በምንሰብከው ልክ ግንኙነታችን ውስጥ ሰላም አለን?... ስለ ፍቅር በምናወራው ልክ ሰዎች የመወደድ ስሜት እንዲሰማቸው እናደርጋለን?... ስለ ሕብረት በምንደሰኩረው ከፍታ የተለየ ሃሳብ  የማስተናገድ ቀናነት አለን?...


“Be the change that you wish to see in the world.” ~ Mahatma Gandhi



[ልንሆነው ባንፈቅድም መልካሙን በመመኘት አንደኛ ነን...]


⭐️ በልባችን ጥላቻ ሞልቶም ሃገር ሰላም እንድትሆን ከመፈለግ አንቦዝንም...

⭐️ የሌሎችን ስቃይ ባይሰማንም ርሕራሔን ከመስበክ አንታቀብም... 

⭐️ በጥቅማችን ሲመጣ ቃልአባይ ብንሆንም ታማኝነትን መደስኮር አንዘልም... 

⭐️ 'እኛ' እና 'እነርሱ' ከማለት ባንቦዝንም ስለ አንድነት ማውራት አንሰለችም...


[ከቶ ለበጎነት መዋጮአችን ምንድነው?...]


"Transformation begins with oneself before it radiates outward." ~ Lao Tzu (Tao Te Ching)


እርግጥ ቃላችን ላይ ላይሆን ይችላል ችግሩ ያለው... ይልቁንም በድንዛዜ የተሞላው ተሳትፎአችን ላይ እንጂ... 


ማለቴ...


እንደ ግለሰብ ሰላምን ብንመኝም ከንቃት በተፋታ ጉዞ በቁጣ እንመላለሳለን... እንደ ወላጅ ታማኝ ልጆች እንዲኖሩን ብንመኝም በዝንጋኤ ከፊታቸው እንዋሻለን... እንደማሕበረሰብ ኢፍትሐዊነት ብንቃወምም ጠቅሞን ሲገኝ ፍትሕ እንነፍጋለን...


አኗኗራችን ቃላችንን አይመስልም... ቀና መሻታችን ተግባራችንን አያክልም...  


“Everyone thinks of changing the world, but no one thinks of changing himself.” ~ Leo Tolstoy


አዎን...


ምርቃቱ ሙሉ ነው...
የበጎ ቃል ድርድሩ አልጎደለም...
የመልካም ምኞት ግትልትሉ ዛሬም አልተለየም...


በአካል ብንርቅም...


ተደዋውሎ መጠያየቅ፣ 
Text ልኮ ቃል መጠበቅ፣ 
በ Emoji ሃሳብ ማርቀቅ - ብዙ አልደበዘዘም...


ግና ከቃል የዘለለ እውነት፣ ከመሬት ጠብ ያለ ምልክት፣ በአብሮነት የተገለጸ ብርታት አልታደልንም...


የሚያፈላልግ ፊት፣ የሚያስተሳስብ ሰውነት፣ የሚያከባብር ቀናነት እያየን አይደለም...


ያም ሆኖ አንጠይቅም...



መልካም ነገር ከአፋችን እንጂ ከልባችን ባይኖርስ?... ለማለት ያህል እንጂ ከነፍሳችን እያልነው ባይሆንስ?... ለጨዋታው ድምቀት፣ ለልማድ አበርክቶት ብቻ እየተመሳሰልን ቢሆንስ?...


ወይ ደግሞ አንጠረጥርም....



ከእኛ ጋር አብሮ 'አሜን' የማይል ይኖር ይሆን እንዴ?... ከበጎ ምኞታችን Package ውስጥ የጎደለ ነገር ይኖር ይሆን እንዴ?... መፈለጋችን ውስጥ የአፈላለግ ጥይመት፣ መጠየቃችን ውስጥ የአጠያቅ ዝንፈት ይኖር ይሆን እንዴ?...


'ከትናንት' የሚሻል 'ዛሬ' ከሌለን በመሻሻል ውስጥ ነን ልንል አንችልም... ከቁስ ሃብትና ከረብጣ ልቃሚ የሚበልጠውን የመንፈስ ልዕልና ማየት ሳንጀምር ሰላም አለን አንልም...


አዎን - ሁሉም ዓመት በበጎ ቃልና በመልካም ምኞት ነው ሲጀመር የኖረው... በሰላም፣ በፍቅር፣ በብልጽግና መሻት ነው መሠረቱ የተዋቀረው... ምኞትና ተግባር ግን በየዓመቱ እልፍ ክንድ እንደተራራቁ ናቸው... 


ይልቅ በዚህ 'አዲስ' ዓመት ይህን ኮስተር ብለን እንጠይቅ...


የጎደለን ምንድነው?...

____


@bridgethoughts
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
10👌21🔥1
.
.
.


ትዝታማ አለሽ
የለኝም ብትይኝ  እኔም አላምንሽም፣

በህይወት መንገድ ላይ
ተራምደሽ ሳታልፊ ዛሬ ላይ አልቆምሽም፤


ህይወት ያለ ታሪክ
ቀን ያለ ጨለማ መች ቶሎ ይመሻል፣

ሰዉ ስለሆንሽ ብቻ 
ለሰዉ ምታወጊዉ ቅፅበት ይኖርሻል።

_

@yeesua_queen
10🔥1🥰1