Dildiy - (ድልድይ)
1.38K subscribers
401 photos
85 videos
1 file
116 links
Dildiy - Whispers of the soul, echoes of the universe. 

A space where mysticism meets quantum wonder, where love, presence, and oneness awaken us. 

Thoughts, poems, and reflections for the seekers of light and the questioners of truth.

Bridge.
Download Telegram
ዝንብን ያቆሸሻት ተፈጥሮዋ አይደለም፣ ውሎዋ እንጂ።

____

@bridgethoughts
👍105👌5
ግትርነት የሚያውቁትን መላ ላለመተግበር፣ የማያውቁትን ብልሃት ላለመጠየቅ የሚያዝ አቋም ነው።

____

@bridgethoughts
10👍4👌2
ልብ ያላሉ ልቦች


የትናንቱ አዳም...

ከጥልቅ ሰመመኑ - ከእንቅልፉ ቢነቃ
ስጦታ ጠበቀው - ከነፍሱ ጠበቃ፤

የዕድሜ ልክ እውነቱ - ተከፍላ ካ’ጥንቱ
ከጎኑ አገኛት - ስጋ ደም አምሳሉ፤


                                          
እናም ያኔ...


የታደለች ሔዋን - ዓይን አዋጅ ሳይገላት
ዕድለኛው አዳም - መስፈርት ሳይበዛበት
ያለ አማራጭ ... መጥተው
እርሷ - ለእርስ ... ኖረው
አለፉ ተባዝተው!


                                          
ይብላኝ ለዛሬ አዳም - ይብላኝ ለሔዋኑ
ከዕልፍ እንስቶች መሃል - ለጠፋች መጠኑ
እኒህ ሁሉ ተባዕት - ዓይኖቿን ላልሞሉ


                                          
እርሱ...

ዓይኑ ውበት ሲያሳድድ
ፈራሽ ገላ ማርኮት፣

                                          
እርሷ...

ልቧ ‘ብር...’ ስትል
ንዋይ ቀልቧን ነስቷት፤

 
ይኸው አሉ ዛሬም - የኔ ’ሚሉት አጥተው
ልብን ከልብ ውስጥ - አላሳድር ብለው፡፡

 
____


[ይህች ግጥም ከተጫረች ትንሽ ቆየች፤ ሰሞኑን ብዙ እየተነገረለት ያለውን 'Materialists' የተሰኘ ፊልም ሳይ ድንገት ትዝ ብላኝ ተጋራሁዋችሁ... በዚህ አጋጣሚ ፊልሙን እንድታዩት እመክራችኋለሁ...]

____

@bridgethoughts
8👌4🙏1
.
.
.

ከቅኔ ወርቁን ላዋልድ - የሰሙን ሽፋን ጠርጌ
የዘመን ስልቱን ላወጋ - ከ[አ]ደባባይ ሸሽጌ፤

.

ለእኔዬ እኔው ልናገር - እኔዬን እኔው [ላ]ርቀው
ከወዳጅ አልፎ ሂያጅ ሃሜት - ቢያተርፈኝ ላስጠነቅቀው፤

.


'ካለቃ ምንዝር ግርግር - ከአስመሳይ ሌጣ ፈገግታ
ከተንኮል ከክፋት ግብሩ - ከሰው ልጅ የአፍ ወለምታ

መዳኛ - ላወጋው መላ
ልሰጠው - ጋሻ ከለላ

ላርቀው - ከነገር ጠለል
ላመጥቀው - በጠቢብ ብሂል

እኔዬን - እኔው ላድነው
ከቦታው - ድንገት ብነቅለው

.
.
.

እኔዬን ከኔ አጣሁት - ለኔዬ ማን ይናገረው?

___

@bridgethoughts
3👍2🥰2
.
.
.

ባለፍሽበት መንገድ የረጨሽው ሽቱ ቅንጣቱ አልሳሳም - በሄድሽበት ስሄድ 'ውድህ በዚህ አለች' የሚል ጣፋጭ ጠረን ደርሶ ያጅበኛል...


የፃፍሽልኝ ደብዳቤ ሃሳብ ዛሬም አልደበዘዘም - አጠገቤ እንዳለሽ ሁሉ በፍቅር ቃና ያወጋኛል... 


የሰማናቸው ዜማዎች ለዛ በየማለዳው አዲስ ነው... ከርመው ልክ እንደ ወይን ሁሌም ይጥሙኛል... 


የሳቅሽ ገደል ማሚቶ በሕዋው ላይ እንደታዘለ ንፋስ ነው - በሄድኩበት ሁሉ ሲስረቀረቅ ይሰማኛል...


ዓይኖችሽን የተዋሱ ከዋክብት በየመዳረሻዬ ያበራሉ - በሌለሽበት ጎዳና ምሽቴን ይጋሩኛል...


ያኔ የተቀመጥሽበት ሶፋ ቅድም እንደተውሽው ሁሉ ሙቀቱ ይሰማኛል... 


የግቢያችን ውሻ ስትመጪ እንዳየ ጭራውን ይቆላል...


የማዕድቤቱ ሽታ እንዳበሰልሽ ሁሉ መዓዛው ያውዳል... 


ከመስታወቱ ውስጥ ፊትሽን አያለሁ - ፊቴን ብቻ ማየት ድሮ አቁሜያለሁ...


ለስላሳ ኮቴሽን ዛሬም እሰማለሁ - ድምጹን ተከትዬ ዞር ብዬ አያለሁ...


ሻይ ያልቀዳሁበት ብርጭቆሽ ይሞቃል - በእንፋሎቱ መሃል ከንፈርሽ ይሳላል...


በጉዞዬ መሃል ጥላሽ ይታየኛል - ሳይቀድም ሳይከተል መንገድ ያጋፋኛል...


የምትወጂው መጽሐፍ ከፊቴ ይታየኛል - እያነበብሽው ነው? በዓይኖችሽ ሲገለጥ ድምጹ ይሰማኛል...


ከመተኛሽ በኩል ትራሱ ጎድጉዷል - ዓይኔ ባያይሽም ተኝተሽበታል...


____


እንደ ሰው ኖረሽ ብታልፊም ዳሩ ፍጥረትሽ የመልዓክ ነው - ሳትታይ መድመቅ፣ አለሽ ሲሉ መርቀቅ ተሰጥቶሻልና...

____

ዓይኑ ሌላ አያይም ለሚሉኝ መልሴ አንቺ ነሽ...


ባትኖሪም - አለሽ!!

____

@bridgethoughts
11🥰2
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
.
.
.



ገጣሚ - ሎሬት ጸጋዬ ገ/መድህን



አንባቢ - ገጣሚ ነብይ መኮንን



ርዕስ - እንኳን ለዓመት ጉድ አበቃን!

___

@bridgethoughts
🔥63
.
.
.

'በቤትህ መስኮት በኩል ወጨፎ እየገባ ካስቸገረህ፣ ውሽንፍር ካፏጨብህ፣ ብርድ ካርገፈገፈህ... መስኮቱን መዝጋትህ የግድ ነው... ምንም እንኳ የውጭው ገጽታ ያማረ ቢሆንም...' ይላሉ...


በመኖር ውስጥም እንዲሁ ነው... 


ኑረት ብዙ ዓይነት ገጽታ ያላቸው ነገሮችን ከፊትለፊታችን ትገልጣለች... ሆኖም መስኮታችን መዘጋቱ ግድ ሊሆን ይችላል...  ገጽታቸው የሚያስጠላ ስለሆነ ግን አይደለም - ቀዝቃዛው ንፋስ ነባር ሰላማችንን እንዳያጎድል ስለምንሰጋ እንጂ...


አንዳንዴ የደስታ ምንጮቻችንንም እንደፍናለን... ጣፋጭ ስላልሆኑ ግን አይደለም - በጣዕማቸው ውስጥ የሸሸጉት ምሬት የኖረንን ጥፍጥና እንዳያጎድል እንጂ...


አንዳንድ ድልቀቃዎችን ባሉበት እንተዋለን... ዋጋቸውን ስለማንችል ግን አይደለም - ጤናና ክብራችንን ስለሚያጎድሉ እንጂ...


አንዳንድ ወዳጅነቶች ሳቢ ሊሆኑ ይችላሉ... ሃሴታችንን ግን ሊያጎድሉ ይችላሉ... 


አንዳንድ ስራዎች የክብር ምንጭ ሊሆኑ ይችላሉ... ግን ደግሞ መንፈሳችንን የሚቀይዱ ሊሆኑ ይችላሉ... 


ልምምዳችን ቅጽበታዊ ደስታን ይቸር ይሆናል... መንፈሳችንን ግን እያጠለሸ ይሆናል...


አንዳንድ በሮች ሳይከፈቱ ሊቀሩ ይገባ ይሆናል... ለአንድ ትልቅ አዳራሽ መከፈት ምክንያት ስለማይሆኑ ግን አይደለም - ምናልባት አዳራሹ የባዶነት፣ ያለመስከን፣ የጥፋት አዳራሽ ስለሚሆን እንጂ...


አንዳንድ ጊዜ በወርቅ የተጌጡ ጠረጴዛዎችን ትተን እንነሳ ይሆናል... ምግቡ መራር ስለሆነ ግን አይደለም - ምናልባት የማዕዱ ዋጋ የአዕምሮአችን ሰላም ማጣት ስለሚሆን እንጂ...


ዓለም ብዙ ለጆሮ ጣፋጭ የሆኑ ዝማሬዎች የሞላት ልትሆን ትችላለች... ልብን የሚመርዝ ሰንኮፍ የላትም ማለት ግን አይደለም...


እንደ ጸሐይ የሚያበራ ፈገግታ በዙሪያችን ሞልቶ ይሆናል... ምናልባት ግን ሲቀርቡት እንደ እሳት የሚያነድ ሊሆን ይችላል...

.
.
.

____

ጠቢብነት እያንዳንዱን ውበት ማሳደድ አይደለም - የትኛው ውበት ምን ዓይነት ወጀብ ውስጡ እንዳቋተ መለየት እንጂ...


ብልሁ ሰው - አማላይ፣ ቀዝቃዛና ነፋሻማ ከሆነው የውጭ ገጽታ መስኮቱን ዘግቶ የሚርቀው የውብ ገጽታው ጥላ ሆኖ ወደ ቤቱ ከሚገባ ስቃይ ለመዳን ነው...

____

ብስለት እያንዳንዱ ብርሃን ሙቀት እንዳልሆነ መማር ነው... ሁሉም ውበት በረከት እንዳልሆነ ማወቅ ነው... ከየትኛው እሳት ዳር መቀመጥ፣ ከየትኛው ደግሞ መራቅ እንዳለብን መገንዘብ ነው...


[ምክንያቱም የአዕምሮ ሰላም ከውጭ ከምናየው ገጽታ በላይ ውብ ነው...]


የኋላ ኋላ - በኑረታችን ውስጥ ልዩነት የሚፈጥረው በስንት ዓይነት ውበት መራጨታችን ሳይሆን በምንያህል የልቡና ሰላም ሩጫችንን መቋጨታችን ነው...

____

@bridgethoughts
❤‍🔥63🙏3👏2🔥1
.
.
.

ያልገለጽኩት ፍቅር እንደተዳፈነ እሳት ነው... ውስጥ ውስጡን በጸጥታ ያኝከኛል... መንደርተኛው ፍሜን አያይም፣ ምክንያቱም ማንደጃው ያለው ከልቤ ውስጥ ነው...

-

ይቅርታ ያልጠየቅሁበት ስህተት እንደ ሃረግ ቅጠል ነው... በሃሳቤ ላይ ተንጠላጥሎ ይመነደጋል... ጸጥ ረጭ ባለ ለሊት ሳይቀር የምሬት እንጉርጉሮውን እያመላለሰ ይረብሸኛል...

-

ያልገለጽኩት ምስጋና የደረቀ ምንጭ ይመስላል... ካዳፈንኩት ቦታ መውጫ አጥቶ በጊዜ ብዛት ጣዕም አጥቷል... በመንገዴ ላይ አኮቴት የሚገባቸው ቢኖሩም ንፉግ ሆኜ እታያለሁ...

-

በአንድ ወቅት የቀበርኩት እውነት በጎድኖቼ መሃል እረፍት እንዳጣች ወፍ ይርገበገባል... ክንፎቹን እያማታ ክፍቱን ሰማይ ይናፍቃል... የውስጤ ህመም ቢበረታም ሃፍረት እንዳነቀኝ አለሁ...

-

የሰሰትኩት ጉልበት እንደ ድንጋይ ይከብደኛል... ብልጥ የሆንኩ መስሎኝ ስለግም ድልብ አድርጎ  ያመኛል... ልቤን ሲያፍናት መተንፈስ ጭንቄ ነው...

-

የነፈግሁት ርህራሔ ጸሐይ እንዳጣ ፍሬ ወይቧል... የጨከንኩባቸው ዓይኖች ሳይኖሩ ያዩኛል... ብቻዬን ብሆንም መንፈሴን የሚያድን አሳዳጅ አጥቼ አላውቅም...

-

በሌሎች ላይ ያዘነብኩት ጉዳት ከቀብር እንደሸሸ መንፈስ በሕልሜ አውድ ይቅበዘበዛል... በቁርና ሃሩር መሃል ያነጉደኛል... የበዳይነት ሕመም ዘልቆ ይሰማኛል...

-

የሰው ልጅ በብዙ የጦር አውዶች የሚባትል መደበኛ ተዋጊ ነው...

.
.
.

ይቅርታ የማድረግ ጦር ሜዳ - የበደሉን እጆች መተው፣ ጉዳታቸው ባልሻረበት እንኳ ሁኔታ...


እውነትን የመናገር ጦር ሜዳ - ዝምታ የደህንነት ምልክት በሚመስልበት ጊዜ ሁሉ...


ደግ ሆኖ የመዝለቅ ጦር ሜዳ - መራርነት ምቹ መንገድ በሆነ ጊዜ ጭምር...


የአሁናዊነት ጦር ሜዳ - እልፊት እያፏጨ በሚያጸጽትበት፣ መፃዒ እየጠራ በሚያሰጋበት ጊዜ ሳይቀር...


የመተው ጦር ሜዳ - የማይመለስ አመድ፣ የማይመጣ ዘመድ፣ መሆኑን ሳይመዝኑ ጭምር...


ዳግም በወዳጅነት የማመን ጦር ሜዳ - ቃል በተበላበት፣ እምነት በተናደበት ጊዜ እንኳን...


ተስፋን ሕያው የማድረግ ጦር ሜዳ - ጨለማ የመዳሰስ ያህል በገዘፈበት ጊዜ ሳይቀር...

____

እስኪ ንገሩኝ... 

[ሰው በምድር ላይ ቆሞ ይሄድ ዘንድ ስንት የጦር ሜዳ ነው ማሸነፍ ያለበት?... በልቡና ውስጥ ያለ ሰይፍ በእጅ ከጨበጡት በላይ አይወጋምን?... በሕሊና ውስጥ ያለስ ጦርነት በገሃድ ካለው አይልቅምን?...]

____

@bridgethoughts
11🔥3👌1
እንጂ
___

ማፍቀር አይደለም
ድንቁ፥
እንጂ
አፍቅሮ ማፍቀርን ማወቁ፥

መፈቀር መች ሁኖ ብልሃቱ
እንጂ እውቀቱ
ሲፈቀሩ፥ ፍቅር መሰማቱ፥

እውቀት አይደለም
ቁም ነገሩ፥
ጉዱ
እንዳወቁ ማወቁ።

___

ሰለሞን ዴሬሳ
/ዘበት እልፊቱ/
___

@bridgethoughts
8❤‍🔥3🔥3👍1
.
.
.

[ግራ እየገባኝ ስሄድ አንድ ነገር እየተማርኩ እንደሆነ አውቃለሁ... ምናልባትም ለመንገዴ አንድ ተጨማሪ የብርሃን አምድ እየተተከለች ይሆናል...]

.
.
.

አንዳንዴ ተራ ብዬ ባቃለልኩት ነገር ውስጥ ተቆጥሮ የማያልቅ መደነቅ ይወርሰኛል... ሌላ ጊዜ ደግሞ ድንቅ ያልኩትን ሳሳድድ ከእጄ ያለውን ውበት አጣና ሃዘን ይከበኛል...


[ወደላይ ብቻ የሚያዩ ከእግሮቻቸው ስር ያለውን የምድር ሃብት አይረዱም... አዘቅዝቀው የሚመለከቱም ከበላያቸው ያለውን ንጽህና አይገነዘቡም...]

___

አንዳንዴ ብዙ አለኝ ያልኩትን ጊዜ በአልባሌ ነገር ሞልቼ አባክነዋለሁ... አጠረኝ ያልኩትን ደግሞ ከበድ ባሉ ስራዎች አጭቄ ሳልጠቀም ፈጀዋለሁ...


በሁለቱ መካከል የሚተርፈኝ አንዳች የለም - ከጭንቀትና እረፍት አልባነት ውጭ...


[ነገ ይሆንልኛል እያሉ የሚጠብቁ ዛሬን አያጣጥሙም... ዛሬ ካልሞላልኝ ብለው ሙጥኝ የሚሉም ከነግ ተስፋ አይገናኙም...]

___


አንዳንድ ቀን በፍቅር እንደተጥለቀለቅሁ ይሰማኛል - ሆኖም ወዲያው በእውር ድንብር አስረክቤው ዝምታ ይውጠኛል... ሌላ ጊዜ ደግሞ ፍቅር አጣሁ ብዬ ፍለጋ እወጣለሁ - ይሁንና ቅንስናሽ ማንነቴን በየቦታው ተቀምጦ ሳገኘው እደነግጣለሁ...


በዚህ ሰበብ የሃሳብ ድካም ያናውዘኛል... ውርሱ ሃዘን የሆነ ዘር በውስጤ ያጎነቁላል...


[መፈቀርን ብቻ የሚሻ መስጠትን ሳይማር ያልፋል... ፍቅር ሲሰጥ ብቻ የኖረም የመቀበል ቆምታን ይተላለፋል...]

___


የሕይወት መትረፍረፍ በተሰማኝ ማግስት ራሴን የሚጠፋ ጥላ ሲያሳድድ አገኘዋለሁ... ኑረት በጉድለት ስሜት ስትከበኝ ደግሞ ጫፍ በሌለው ምኞት ሸክሟን አበዛዋለሁ...

በዚህ ሰበብ ባዶነት ይወርሰኛል... ተስፋቢስነት ይጫነኛል...


[መድረሻውን ብቻ የሚያይ ጉዞውን ይረሳል... መንገዱን ብቻ ሙጥኝ ያለ አድማሱን ይዘነጋል...]

___


ነፃ የሆንኩ ይመስለኛል - ግና ራሴን የማገኘው በምርጫዎች ሰንሰለት ታብቶ ነው... ነፃ እንዳልሆንኩ አስባለሁ - ግና ውስጤ የማየው የግዞት ጫና የማይታከካቸውን ዕልፍ ቦታዎች ነው...


በዚህ ሰበብ ቀልቤን ቅዥት ሞልቶት ያታልለኝና የምር ትግል ውስጥ እገባለሁ...


[ነፃነትን የሚፈሩ የራሳቸው አዕምሮ እስረኛ ከመሆን አይድኑም... ነፃነትን ያለአግባብ የሚጠቀሙ የምኞቶቻቸው ባሪያ ከመሆን አይቀሩም...]

___

እንደነገርኳችሁ ነው...


ግራ እየገባኝ ስሄድ አንድ ነገር እየተማርኩ እንደሆነ አውቃለሁ... 

___

@bridgethoughts
9🔥5🥰5💊1
.
.
.

የዛሬ ስንት ዓመት በእናትና አባቴ ጠያቂነት ምድሪቱ ከነገረ ስሪቷ የቆነጠረችውን ሥጋ በኪራይ አስረክባኝ በዚህች ውብ ዓለም ውስጥ ተከሰትኩ...


[የኑረት ስሌትህ እየገፋ ሲመጣ አባቶችህ ያስረከቡህን ስንቅ ቅርጥፍ አድርገህ ብትበላም ለልጅህ የምታቆየው ውርስ እጅህ ላይ አለመቅረቱ ስለሚያሳፍርህ ዕድሜህን አትናገርም...]


በኖርኩባቸው ዓመታት ሳቅና ለቅሶዬ ተላቁጧል... ደስታና ሃዘኔ ተጋምዷል... አክብሮት ንቀቴ ተሳስሯል... ፍቅር ጥላቻዬ ተቀይጧል... ማግኘት ማጣቴም ተዛንቋል...


እጅግ የረዘሙ ለሊቶች በጎጆ ጓዳዬ አቀርዝዘው ያውቃሉ... እጅግ አስደሳች ወቅቶችም በኑሮ ደጄ ተመላልሰው አልፈዋል... እጅግ የከፉ ሰዎች ሆዴን አሻክረው ያውቃሉ... እጅግ ልዩ ሰዎች ልቤን በሃሴት ሞልተዋል...


[የብዙ ሰዎች መዋጮ ነኝ...] 


ቆጥሬ የማልጨርሳቸው ሰዎች ቃላት የማይገዳደሩትን ውለታ እየዋሉልኝ ነው እዚህ የደረስኩት... ማወቅ ሳይገዳቸው እጅ የዘረጉልኝ፣ ስስት ሳይፈትናቸው በር የከፈቱልኝ፣ ምላሽ ሳይጠብቁ እልፍ የለገሱኝ - ብዙ ናቸው... ['የኔ የምለው አንዳች የለኝም' የምለው ለዚህ ነው]...


[መልካምነቴን እንጃ - እንጂ እኔም ብሆን ለሃዘናቸው ሰበብ፣ ለእንባቸው ምክንያት የሆንኳቸው አይጠፉም...]


ከደረሰብኝ ያልተናገርኩት ይንዛዛል... [ካልተናገርኩት የዘነጋሁት ይበዛል፣ ከተረፈው ውስጥ 'ይቅር' ያሟሟው ይገዝፋል]...


ያም ሆኖ...


እንቆቆ የጋቱኝ ማርነቴን አላጠፉትም... አይዞህ ያላሉኝ ብርታቴን አልነኩትም...


የገፉኝ ከገደል ወለል አልጣሉኝም፣ ወለል የጣሉኝ መውጫዬን መዝጋት አልቻሉም፣ ለመዝጋት ቋጥኝ ያኖሩ መብረሪያ ክንፌን አላዩም...


ሳይረዱኝ ለቀሩ ሰዎች ራሴን ላብራራ መድከሜ ያናድደኛል... ሳልረዳቸው ቀርቼ ያዘኑብኝን ሳስብ ይጸጽተኛል... [መተው ባይኖር - ከስረን ነበር]


የለመንኳቸው ሰዎች የተለማመጥኳቸው እንደመስላቸው ሲገባኝ ብስጭቴ ብቅ ትላለች... [ለመኖር ብዬ ግን አልተናነስም - ለመኗኗር ካልሆነ በቀር]... 


ግማሽ መንገድ ሊመጡ ሲገባቸው አልፌ የጠበኩዋቸው ሰዎች ግዴታዬ እንደሆነ ማሰባቸው ከገባኝ ድጋሚ አላገኛቸውም... በፍቅር ካደረጉት ግን እንደ ውለታ አልቆጥረውም...


ዝምታዬን ከሞኝነት፣ አንገት መድፋቴን ከሃፍረት ሲቆጥሩ በልቤ የናቅሁዋቸው አይጠፉም... ብልጣብልጥ መስዬ ከመንገዳቸው ግን አልወደቅሁም...


የአንዳንድ ሰዎች ክፋት አይሎ 'እንኳን አውላላ ላይ ጣሉኝ' አስብሎኝ ያውቃል... ምክንያቱም አማራጭ እንድፈልግ፣ አዲስ ሰው እንዳውቅ አድርጎኛልና...


___


የሆነስ ሆነና...


[ከመኖር ምን ተማርኩ?...]


መተው! [እርግፍ አድርጎ መተው!]

የኖረ ሁሉ ይሞታል! [ከውቅያኖሱ ላይ ወደላይ የወጣች የውሃ ጠብታ መልሳ ወደ ውቅያኖሱ ትቀላቀላለች]

ይህም ያልፋል! [መፈራረቅ የገጽታ ደንቡ ነው]


___


እንኳንም ተወለድኩ... 


[ዛሬ የወጣችውን ፀሐይ ማን በእኔ አንፃር ያያት ነበር?...]

____

@bridgethoughts
19🥰7
ያገኙሽ ሁሉ በአንቺ ምክንያት የውበት መለኪያ ሚዛናቸው ተደነቃቀፈ... ትናንት 'የውበት ጥግ' ካሏት ጋር ሲያነፃጽሩሽ አልደራረስ አልሽና - አልቀው ሰቀሉሽ... 


በእውነት ከዚህ ከፍታ ላይ ሌላ ሴት አይደለም አንቺ ራስሽም መድረስሽን እጠራጠራለሁ...


ውበትሽ ምን እንደሆን ታውቂያለሽ?...


መረዳትሽ!!

___

@bridgethoughts
9🥰6
.
.
.

ዘወትር እሁድ ምሽት ከሩቅ የሚሰማኝ አንድ ሙዚቃ አለ... የሚስረቀረቅ፣ የሚስለመለም፣ የሚያባባ ዓይነት... 


ግጥም የለውም... ዘፋኝ የለውም... የመሳሪያ ብቻ ሙዚቃ ነው... የጊታር፣ የክራር፣ የዋሽንት፣ የሳክስ፣ የቫዮሊን... [ቆይ ተውት - የመሳሪያውን ስም አላወቅሁትም...] 


ስሰማው እንባዬ ይመጣል... ባር ባር ይለኛል... ጭብጥ እላለሁ... ድምጹ የሩቅ ነው... አንዳንዴ ወደ ደጅ ወጥቼ የድምጹን አቅጣጫ አስሳለሁ... ግራና ቀኝ ከጎረቤት - አይደለም... ሽቅብ ሰማይ ቁልቁል መሬት - አይደለም... ምንጩ የት ነው?...


ዛሬም እንዲሁ ሆነ... 


አልጋዬ ላይ ጋደም ብዬ እየሰማሁት ቁልቁል እንባዬ ወረደ... እንደተለመደው ወጥቼ ከበሬ ቆምኩ... ጆሮዬን አዟዙሬ ቀሰርኩ... ምንጩን አላወቅሁትም... ከግቢ ወጥቼ ዞርዞር አልኩ... ስልኬን አውጥቼ Shazam ላደርግ ሞከርኩ... ሞባይሌ ድምጹ አልተሰማትም... [ሙዚቃውን ላገኝ አልቻልኩም] አለችኝ...


ወደ ቤቴ ገባሁ... 


የዚህ ሙዚቃ ምንጭ የት ነው?... ማድመጤን ቀጠልኩ... ዜማው አልተለወጠም... ውበቱ ግን አይሰለችም... ጣዕሙ ሁሌም አዲስ ነው...


ግራ ሲገባኝ ጆሮዬን ደፈንኩ... ግጥም አድርጌ በትራስ አፈንኩት... የሙዚቃው ጥራት ጨመረ... ጆሮዬን ከግንዱ ጋር ጨቆንኩ... ድምጹ ጭራሽ እየጎላ መጣ... 


በዚህ መሃል አንድ ድምጽ በሙዚቃው ስልት ውስጥ ሆኖ በለሆሳስ አናገረኝ...


ድምጹን አውቀዋለሁ... ያንተ ያለህ!... የራሴ ድምጽ ነው...


አንድ ቃል ብቻ ነው ደጋግሞ የሚነገረኝ...


'ትተኸኛል'... 

'ትተኸኛል'...

'ትተኸኛል'...


እንደ ሰማሁት ሲያውቅ እየሳሳ ሄደ... እየራቀ... እየራቀ...

____

ለራሳችሁ ጊዜ ከሰጣችሁ ስንት ጊዜ ሆነ?... ከራሳችሁ ጋር ቁጭ ካላችሁ ስንት ጊዜ አለፈ?... በወግ ካወጋችሁ፣ ከተደማመጣችሁ፣ ሰከን ብላችሁ ከመከራችሁ - ምን ያህል ዓመት ሆነ?...

____

“Nowhere you can go is more peaceful—more free of interruptions—than your own soul.” ~ Marcus Aurelius

___

@bridgethoughts
🥰8🔥42🙏2
🌿

🌿

🌿

ፍቅሬን እንዴት ማሳየት እንዳለብኝ ተለማምጄ ሳልጨርስ ሄደች...


በልቤ ውስጥ ያለው ነበልባል በቃል ተሰርቶ ወደጆሮዋ ሊፈስ ይቃትት ነበር... የመውደዴ ብርታት በቃል አክናፍ በርሮ እዝነ ልቡናዋን ሊያንኳኳ ይጓጓ ነበር... ጎርፍ የመውረጃ ፈለጉን እንደሚያስስ... ሕፃን የእናቱን ጡት ፍለጋ በጨለማ እንደሚዳብስ...


በውስጤ የታመቁት ቃላት ከውክብክቡ ዓለም አይደሉምና በተራ ድምጽ አይወከሉም - በጸጥታ ይነግሳሉ እንጂ... መሻቴ ከአፍዓ ገጽዋ አልተቀዱምና ለሙገሳ የተሰሩ ፊደላት አልሰጠሁዋትም - በጥልቅ ዝምታዬ ውስጥ የሚጓደዱትን እንጂ... 


[በቅጽበታት መሃል እንደሚገኝ ትንፋሽ... ነፍሶች እንደሚያወጉበት ድምጽ የሌለው ፈሳሽ...]


አዎን - እኔ ይህን ጸጥታ ወደ ቋንቋ መለወጥ ገና አልተማርኩም ነበር... እርሷም እንዲህ ዓይነት ቋንቋ ሰምታ አታውቅም ነበር...


ሄደች... 


እውነቱን ከመግለጼ በፊት ተጨለጠች... 


[ፍቅር] 


የምሰጣት - የኔ 'ምለው፣ የምትነፍገኝ - የእርሷ የሆነው እንዳልሆነ ሳልነግራት በነነች...


የዘላለማዊው ኃይል መስታወት፣ በሁለንታ ላይ የሚፈስ የኃይል ዥረት መሆኑን ሳላስታውሳት ዱካዋን አጠፋች... ዳናዋን ሰወረች...


ሄደች... የአካል ኑረቷን ከለለች...


[አዎን ሄዳለች - ግን ደግሞ አልሄደችም...] 


መቅረቷ በሌላ ቅርጽ መኖር ሆኖ ቀጥሏል... አካሏን እንጂ በኔ ዓለም ውስጥ ያነቃችውን ፍቅር በቀላሉ ማጥፋት ስላልተቻላት በመንፈስ ነብራለች... 

 🌿

ፍቅሯ ወደ ኁልቆ አልባው ዓለም ሲያሻግረኝ ከፈራሽ ገላዋ ብፋታም በእርስዋ ሰበብ የተሰጠኝ ማሕተም የሃገሩን ኬላ ሁሉ የሚያሻግር አርነት ሰጥቶኛል... 


[በእውኑ የተወኝ ምኗ ነው?...]

___

@bridgethoughts
🥰53❤‍🔥2
ባስነጠሰ ቁጥር ፈሱ የሚያመልጠው ሰውና የወር ደሞዝተኛ ኑሮ አንድ ናቸው... 

Just saying...

___

@bridgethoughts
🥴93🤔1🆒1