Dildiy - (ድልድይ)
1.38K subscribers
401 photos
85 videos
1 file
116 links
Dildiy - Whispers of the soul, echoes of the universe. 

A space where mysticism meets quantum wonder, where love, presence, and oneness awaken us. 

Thoughts, poems, and reflections for the seekers of light and the questioners of truth.

Bridge.
Download Telegram
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
A Beautiful Mind (2001)

Directed by Ron Howard, starring Russell Crowe as John Nash, with Jennifer Connelly in a supporting role.

_

The film is based on the life of the Nobel Prize-winning mathematician John Nash and explores his struggles with schizophrenia and his remarkable contributions to mathematics.

___

@bridgethoughts
🔥5🥰21
.
.
.

'የኔ ሁኚ' የማልልሽ የኔ በመሆን የምታጭው [የሚመስለኝን] ሁሉ ስለማስብ ነው... አብሮነትን የማልጠይቅሽ ማግስት የሚነጥቅሽ [የሚመስለኝን] ሁሉ እያብሰለሰልኩ ነው...


(የሚመስለኝ ያልኩሽ - በእኔ ልብ ውስጥ ያለውን እምነት እንጂ አንቺ ዘንድ ያለውን ጥንካሬ ስለማላውቅ ነው...)


ከልቤ እልፍኝ ያልጋበዝኩሽ ስለማልፈቅድሽ አይደለም... መንገዴን ያላጋራሁሽ ስለማልወድሽ አይደለም... ይልቁን ስለምጠነቀቅልሽ ነው... [የኔ በመሆን የምትከፍይው ዋጋ እንዳይኖር በመስጋት... ወይም በጥሬ ቃል 'ደስታዋን ስለ አብሮነታችን ሰውታ ብታዝንብኝስ?' ብዬ በመፍራት...]


[እንግዳ ነገር ይመስላል አይደል?... 'የነገን እግዜር ያውቃል' በሚል ተስፈኛ ሕዝብ መሐል በቅሎ 'ነገ ብትከፋብኝስ?' ብሎ ማሰብ ይገርማል አይደል?...]

____


[የነግ ፍርሃት እያጠየመብኝ እንጂ እኮ...]


ልብሽ ለኔ ያላትን ቦታ እረዳለሁ - [ልብሽን እንዳልሰብራት ደግሞ እፈራለሁ...]


ስታገኚኝ የፊትሽ ጸዳል ለልቤ እንዲያበራ አውቃለሁ - [የኔ አድርጌሽ ሳቅሽን እንዳልነጥቅሽ እያልኩ ግን እፈራለሁ...]


ጨዋታሽ ደዌ ሲፈውስ፣ ቃላትሽ ለነፍስ ሲደርስ፣ ፈገግታሽ መንፈስ ሲያድስ አውቃለሁ - [አብሮነታችን ስሜትሽን እንዳያጎሸው ግን ሁሌም እሰጋለሁ...]


[ግን ደግሞ ሰው አይደለሁ?...]


ዛሬ የገባኝ ሁሉ ከነፃነትሽ ላለመወለዱ፣ ዛሬ የወደድኩት ሁሉ ነገም ለመራመዱ እርግጠኝነት እንዲከበኝ እሻለሁ...



[እናም በልቤ እጠይቅሻለሁ...]



የመጣሁበት መንገድ አያዝልሽም?... የምደርስበት ነገ አያስከፋሽም?... እርጅናዬ ውስጥ ልትኖሪ ትሺያለሽ?... በጉዞዬ ልታብሪኝ በቂ አቅም አለሽ?... [ይኸውልሽ ማሬ፣ ፊቴ ላይ የማታነቢው ምሬት ከውስጤ ሊኖር ይችላል...]


ውድቀቴ ተስፋ አያስቆርጥሽም?... ድህነቴ አያስፈራሽም?... ቀርነቴስ አያሳቅቅሽም?... [ከዘመነኞችሽ ጋር ያለኝን መልከ ብዙ ልዩነትና ርቀት አውቀዋለሁ...]


ፍቅሬ ይበቃሻል?... ቤቴስ ይስብሻል?...

ህመሜን አትጠየፊውም?... ድካሜንስ አትሰቀቂውም?...

[ይሄ ሁሉ ይቅር...] 

ስለ ውሳኔሽ አትጸጸቺም???...

___

ጣፋጯ...

ለነዚህ ጥያቄዎች የአዎንታ ልብ ከሌለሽ 'ና' አትበይኝ... እኔም 'ምጪልኝ' ብዬ አላስጨንቅሽም...


የወደድኩሽ የማትፈልጊውን እንድትኖሪ ከመጨከን ጋር ስላልሆነ ምርጫሽን አከብራለሁ... ግን አትርሺ - ስላላበርን ፍቅሬ ፈጽሞ አይቀየርም... 


___

ይህን ግን ለምን ፃፍኩልሽ?...


ራስ ወዳድ እንዳልሆንኩ እንድታውቂ ይሆናል... [ምናልባት ደግሞ ነፃነትሽን ላስታውስሽ ብዬም ይሆናል...]


[አየሽ... ሰው በገዛ ልቡ ውስጥ ስላለች የፍቅር ኩራዝ እንጂ በሌላኛው ሰው ልብ ውስጥ ስለተዘጋጀለት እቶን መውደድ በቀላሉ እርግጠኝነት አይሰማውም... በመኖር ካልፈተነው በቀር...]


ሁሌም ግን እወድሻለሁ 💞

___

@bridgethoughts
26🥰4
.
.
.


ከምከፍተው ሙዚቃ ይልቅ፣ እንዳልረብሽ የማደርገው ጥንቃቄ ከፍ ብሎ ይሰማል... ይገርማል!!


ከምጠቀመው ውሃ በላይ፣ ላለማባከን የማደርገው ጥረት ትኩረት ስቦ ያስከፋል... ምን ይባላል??


ከማበራት አምፑል በላይ፣ የመቆጠብ ልምዴ ጠያቂ ይጎትታል... ያሳቅቃል!!


ገላ ለመታጠብ 'ሻወር ቤት' ብመርጥም፣ ድንገት የገባሁ'ለት -  አንኳኪ አላጣም...


በወር የምከፍለው ቁጥሩ ባይናቅም፣ 'የጨምር' ዕድገቱ አንዴም ቆሞ አያቅም... 


አታምሽ ያሉኝ ፈሪ በጊዜ ብሰፍርም፣ ቤት መዋል ሲያምረኝ ግን ገላማጭ አላጣም...

.
.
.

ምክንያቱም...

👇

ያለሁት ኪራይ ቤት ነው!!

___

የአንዳንድ አከራዮች የመጀመሪያ ተግባር እንደ ሰው የሚገባህን ክብር መንጠቅ ነው... ይህንንም የሚያደርጉት ተከራይነትህን እንዳትረሳ ነው...


___


በመሰረቱ ሁላችንም ተከራይ ነን... ሰውነታችን ኪራይ ቤት ነው፣ ዓለም ኪራይ ቤት ናት፣ ተፈጥሮም እንደዚያው... አንድም ቋሚ ነገር የለም!!... 


በአጭሩ - ትተነው እስከሄድን ድረስ ሁሉም ነገር ኪራይ 'ቤት' ነው... 


[ታዲያ ለምንድነው - የኔ የሚባል ሳይኖርህ 'የኔ' የሚለው 'የሌለውን' የምትገፋው?...]

___


@bridgethoughts
16👌3🔥1🤔1
.
.
.

ውዴ
_

ሞትሽ በልቤ ውስጥ ያለውን መውደድ አልገደለውም፤ 
መለየትሽ ከነፍሴ የታተመውን ፍቅር አልፋቀውም፤ 
_

አብረሽኝ ባትሆኚ አብሮኝ የሚኖረውን አክብሮት የሚነጥቀኝ የለም፤
በስጋ ባናብርም በመንፈስ የምንቆራኝበትን እውነት አልተሰረቅንም፤ 
_

በአካል ባናወራም በቀልባችን የምንግባባበትን አቅም ሜዳ አልጣልኩም፤ 
በድምጽ ባልሰማሽም ከዕዝነ-ልቡናዬ ታትሞ በየመዓልቱ የሚያዜም ቀናነትሽን ዝም አላስባልኩም፤
_

ዕጣሽ ዕጣዬ ሆኖ እስክንመሳሳል የአካል ንጥለትሽን ጉዳት በመንፈስ ተቋልፎሽ ውበት እያደስኩ እኖራለሁ።
_

የኔ ውድ 🌺

____

@bridgethoughts
7🥰2
.
.
.

___

ከፍ ባልን ቁጥር... 'ከስር የሚገፉን አልያም ከላይ የሚስቡን ስላሉ ነው' ብለን አስበን እናውቃለን?

'ከትናንት የተሻለ ዕይታ የኖረን - በተሸካሚዎቻችን ትከሻ ስለተንጠላጠልን እንጂ በራሳችን ጉልበት ስለቆምን አልነበረም' ብለን እናውቃለን?

ከእጅ ያለው - የኖረን፣ የደረስንበት - የተገባን፣ ጉድፍ ይሁን እልፍ -  የከበበን፣ ደቆም ይሁን ልቆ - ያደመቀን... ሌሎች ስለነበሩ ነው ብለንስ እናውቃለን?
__

የእውነት ይህ ጉድለታችን ነው!!...

__

ስንቴ... 

           የተራዱንን እጆች ገፋን?

ስንቴስ...

           ከፍ ያደረጉንን ትከሻዎች ረገጥን?

ምን ያህል ጊዜ...

           ያጎሉንን ሃሳብ ባለቤቶች አደበዘዝን?

ለስንተኛ ጊዜስ...

           ተሻግረን ስናበቃ ያሻገረንን ድልድይ ሰበርን?

___

"Someone is sitting in the shade today because someone planted a tree a long time ago" ~ Warren Buffet

___

@bridgethoughts
👏5❤‍🔥4👌1
.
.
.

"Mankind must put an end to war before war puts an end to mankind." ~ John F. Kennedy

___

የሰው ልጅ የውድቀቱ ጥግ፣ የድንዛዜው ቁንጮ፣ የኋላቀርነቱ መስታወት...


ጦርነት!!!


"I know not with what weapons World War III will be fought, but World War IV will be fought with sticks and stones." ~ Albert Einstein


ሰልጥነን እንደ ሰየጠን፣ ዘምነን እንደ ጎመዘዝን የሚናገርብን እውነት... 

በቁስ ተጊጠን በመንፈስ እንደነጠፍን የሚያሳብቅ ገጽታ....

በሳይንስ ተራቀን በሞራል እንደቀነጨርን መስካሪ ሃቂቃ...


ጦርነት!!...


የሰው ልጅ የትኛውንም ዓይነት አመክንዮ ቢደረድር፣ የትኛውንም ዓይነት ሰበብ ቢያግተለትል ልክ የማይሆንበት ተግባሩ የጦርነት ግብሩ ነው...


ድህነት ጦርነት አይቀሰቅስም - የሌጣ አዕምሮ ግልፍተኝነት ግን ጠብ ጭሮ ሌማት ያራቁታል...


'የድንበር መገፋት' ጦር አያሳብቅም - የብልሃት አልባ ችኩል ግብር ግን የእግር መቆሚያ ይነጥቃል...


የሃሳብ ልዩነት ሳንጃ አያማዝዝም - የአምባገነን ግትር አቋም ግን የቂም እርሾ ይወልዳል...


ኢጎህን መግደል አቅቶህ ሰው መግደል የቀለለህ ዕለት ያኔ አንተ ቀለሃል!... 


እናም - እነሆ ቃል...


ማኔ - ቴቄል - ፋሬስ!!

__

"The greatest victory is that which requires no battle." ~ Sun Tzu 'The Art of War'

__


'የዘመነ' የጦር መሳሪያ መስራትህ ዘመናዊ አያደርግህም - ከንቱነትህን ያሳብቅ እንደሁ እንጂ...



ራስን የማሸነፊያ ብስለት ስለሌለህ ሌሎችን የምታጠቃበት ሰይፍ መሳልህ ጠቢብ አያደርግህም - ጦረኛ እንጂ...



በጠብመንጃህ ነድተህ የፈጠርከውን ጠብ ቢሸሽ ፈሪ አይባልም - ስሜት ከሚነዳው ጋር የማይታገል ብልህ እንጂ...



ፍርሃትህን የምትገራበት መላ ስለሌለህ ሌሎችን በፍርሃት ውስጥ የሚከት ጠብመንጃ ታከማቻለህ...



በራስህ ዓለም የሁልጊዜ ባለስልጣን የመሆን ክህሎት ሲያጥጥህ - ተሰባሪ ወንበር ለማስጠበቅ ለጋ ሕልም ትሰብራለህ...

____

No More War!!

I do not like war—  
I know what it makes us:  
Children lost to the storm,  
Mothers weeping in vain.  

Houses turned to ash,  
Hope a fleeting spark,  
Future crushed to dust,  
Revenge left in the dark.  

Power feeds the flame,  
Lives cut short, unnamed—  
This is my plea, my cry,  
No more war—we don’t deserve to die.  

(Humble words from one who sees,  
A world aching for peace.)

____

@bridgethoughts
👍65🙏2🕊2👏1
ዝንብን ያቆሸሻት ተፈጥሮዋ አይደለም፣ ውሎዋ እንጂ።

____

@bridgethoughts
👍105👌5
ግትርነት የሚያውቁትን መላ ላለመተግበር፣ የማያውቁትን ብልሃት ላለመጠየቅ የሚያዝ አቋም ነው።

____

@bridgethoughts
10👍4👌2
ልብ ያላሉ ልቦች


የትናንቱ አዳም...

ከጥልቅ ሰመመኑ - ከእንቅልፉ ቢነቃ
ስጦታ ጠበቀው - ከነፍሱ ጠበቃ፤

የዕድሜ ልክ እውነቱ - ተከፍላ ካ’ጥንቱ
ከጎኑ አገኛት - ስጋ ደም አምሳሉ፤


                                          
እናም ያኔ...


የታደለች ሔዋን - ዓይን አዋጅ ሳይገላት
ዕድለኛው አዳም - መስፈርት ሳይበዛበት
ያለ አማራጭ ... መጥተው
እርሷ - ለእርስ ... ኖረው
አለፉ ተባዝተው!


                                          
ይብላኝ ለዛሬ አዳም - ይብላኝ ለሔዋኑ
ከዕልፍ እንስቶች መሃል - ለጠፋች መጠኑ
እኒህ ሁሉ ተባዕት - ዓይኖቿን ላልሞሉ


                                          
እርሱ...

ዓይኑ ውበት ሲያሳድድ
ፈራሽ ገላ ማርኮት፣

                                          
እርሷ...

ልቧ ‘ብር...’ ስትል
ንዋይ ቀልቧን ነስቷት፤

 
ይኸው አሉ ዛሬም - የኔ ’ሚሉት አጥተው
ልብን ከልብ ውስጥ - አላሳድር ብለው፡፡

 
____


[ይህች ግጥም ከተጫረች ትንሽ ቆየች፤ ሰሞኑን ብዙ እየተነገረለት ያለውን 'Materialists' የተሰኘ ፊልም ሳይ ድንገት ትዝ ብላኝ ተጋራሁዋችሁ... በዚህ አጋጣሚ ፊልሙን እንድታዩት እመክራችኋለሁ...]

____

@bridgethoughts
8👌4🙏1
.
.
.

ከቅኔ ወርቁን ላዋልድ - የሰሙን ሽፋን ጠርጌ
የዘመን ስልቱን ላወጋ - ከ[አ]ደባባይ ሸሽጌ፤

.

ለእኔዬ እኔው ልናገር - እኔዬን እኔው [ላ]ርቀው
ከወዳጅ አልፎ ሂያጅ ሃሜት - ቢያተርፈኝ ላስጠነቅቀው፤

.


'ካለቃ ምንዝር ግርግር - ከአስመሳይ ሌጣ ፈገግታ
ከተንኮል ከክፋት ግብሩ - ከሰው ልጅ የአፍ ወለምታ

መዳኛ - ላወጋው መላ
ልሰጠው - ጋሻ ከለላ

ላርቀው - ከነገር ጠለል
ላመጥቀው - በጠቢብ ብሂል

እኔዬን - እኔው ላድነው
ከቦታው - ድንገት ብነቅለው

.
.
.

እኔዬን ከኔ አጣሁት - ለኔዬ ማን ይናገረው?

___

@bridgethoughts
3👍2🥰2
.
.
.

ባለፍሽበት መንገድ የረጨሽው ሽቱ ቅንጣቱ አልሳሳም - በሄድሽበት ስሄድ 'ውድህ በዚህ አለች' የሚል ጣፋጭ ጠረን ደርሶ ያጅበኛል...


የፃፍሽልኝ ደብዳቤ ሃሳብ ዛሬም አልደበዘዘም - አጠገቤ እንዳለሽ ሁሉ በፍቅር ቃና ያወጋኛል... 


የሰማናቸው ዜማዎች ለዛ በየማለዳው አዲስ ነው... ከርመው ልክ እንደ ወይን ሁሌም ይጥሙኛል... 


የሳቅሽ ገደል ማሚቶ በሕዋው ላይ እንደታዘለ ንፋስ ነው - በሄድኩበት ሁሉ ሲስረቀረቅ ይሰማኛል...


ዓይኖችሽን የተዋሱ ከዋክብት በየመዳረሻዬ ያበራሉ - በሌለሽበት ጎዳና ምሽቴን ይጋሩኛል...


ያኔ የተቀመጥሽበት ሶፋ ቅድም እንደተውሽው ሁሉ ሙቀቱ ይሰማኛል... 


የግቢያችን ውሻ ስትመጪ እንዳየ ጭራውን ይቆላል...


የማዕድቤቱ ሽታ እንዳበሰልሽ ሁሉ መዓዛው ያውዳል... 


ከመስታወቱ ውስጥ ፊትሽን አያለሁ - ፊቴን ብቻ ማየት ድሮ አቁሜያለሁ...


ለስላሳ ኮቴሽን ዛሬም እሰማለሁ - ድምጹን ተከትዬ ዞር ብዬ አያለሁ...


ሻይ ያልቀዳሁበት ብርጭቆሽ ይሞቃል - በእንፋሎቱ መሃል ከንፈርሽ ይሳላል...


በጉዞዬ መሃል ጥላሽ ይታየኛል - ሳይቀድም ሳይከተል መንገድ ያጋፋኛል...


የምትወጂው መጽሐፍ ከፊቴ ይታየኛል - እያነበብሽው ነው? በዓይኖችሽ ሲገለጥ ድምጹ ይሰማኛል...


ከመተኛሽ በኩል ትራሱ ጎድጉዷል - ዓይኔ ባያይሽም ተኝተሽበታል...


____


እንደ ሰው ኖረሽ ብታልፊም ዳሩ ፍጥረትሽ የመልዓክ ነው - ሳትታይ መድመቅ፣ አለሽ ሲሉ መርቀቅ ተሰጥቶሻልና...

____

ዓይኑ ሌላ አያይም ለሚሉኝ መልሴ አንቺ ነሽ...


ባትኖሪም - አለሽ!!

____

@bridgethoughts
11🥰2
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
.
.
.



ገጣሚ - ሎሬት ጸጋዬ ገ/መድህን



አንባቢ - ገጣሚ ነብይ መኮንን



ርዕስ - እንኳን ለዓመት ጉድ አበቃን!

___

@bridgethoughts
🔥63
.
.
.

'በቤትህ መስኮት በኩል ወጨፎ እየገባ ካስቸገረህ፣ ውሽንፍር ካፏጨብህ፣ ብርድ ካርገፈገፈህ... መስኮቱን መዝጋትህ የግድ ነው... ምንም እንኳ የውጭው ገጽታ ያማረ ቢሆንም...' ይላሉ...


በመኖር ውስጥም እንዲሁ ነው... 


ኑረት ብዙ ዓይነት ገጽታ ያላቸው ነገሮችን ከፊትለፊታችን ትገልጣለች... ሆኖም መስኮታችን መዘጋቱ ግድ ሊሆን ይችላል...  ገጽታቸው የሚያስጠላ ስለሆነ ግን አይደለም - ቀዝቃዛው ንፋስ ነባር ሰላማችንን እንዳያጎድል ስለምንሰጋ እንጂ...


አንዳንዴ የደስታ ምንጮቻችንንም እንደፍናለን... ጣፋጭ ስላልሆኑ ግን አይደለም - በጣዕማቸው ውስጥ የሸሸጉት ምሬት የኖረንን ጥፍጥና እንዳያጎድል እንጂ...


አንዳንድ ድልቀቃዎችን ባሉበት እንተዋለን... ዋጋቸውን ስለማንችል ግን አይደለም - ጤናና ክብራችንን ስለሚያጎድሉ እንጂ...


አንዳንድ ወዳጅነቶች ሳቢ ሊሆኑ ይችላሉ... ሃሴታችንን ግን ሊያጎድሉ ይችላሉ... 


አንዳንድ ስራዎች የክብር ምንጭ ሊሆኑ ይችላሉ... ግን ደግሞ መንፈሳችንን የሚቀይዱ ሊሆኑ ይችላሉ... 


ልምምዳችን ቅጽበታዊ ደስታን ይቸር ይሆናል... መንፈሳችንን ግን እያጠለሸ ይሆናል...


አንዳንድ በሮች ሳይከፈቱ ሊቀሩ ይገባ ይሆናል... ለአንድ ትልቅ አዳራሽ መከፈት ምክንያት ስለማይሆኑ ግን አይደለም - ምናልባት አዳራሹ የባዶነት፣ ያለመስከን፣ የጥፋት አዳራሽ ስለሚሆን እንጂ...


አንዳንድ ጊዜ በወርቅ የተጌጡ ጠረጴዛዎችን ትተን እንነሳ ይሆናል... ምግቡ መራር ስለሆነ ግን አይደለም - ምናልባት የማዕዱ ዋጋ የአዕምሮአችን ሰላም ማጣት ስለሚሆን እንጂ...


ዓለም ብዙ ለጆሮ ጣፋጭ የሆኑ ዝማሬዎች የሞላት ልትሆን ትችላለች... ልብን የሚመርዝ ሰንኮፍ የላትም ማለት ግን አይደለም...


እንደ ጸሐይ የሚያበራ ፈገግታ በዙሪያችን ሞልቶ ይሆናል... ምናልባት ግን ሲቀርቡት እንደ እሳት የሚያነድ ሊሆን ይችላል...

.
.
.

____

ጠቢብነት እያንዳንዱን ውበት ማሳደድ አይደለም - የትኛው ውበት ምን ዓይነት ወጀብ ውስጡ እንዳቋተ መለየት እንጂ...


ብልሁ ሰው - አማላይ፣ ቀዝቃዛና ነፋሻማ ከሆነው የውጭ ገጽታ መስኮቱን ዘግቶ የሚርቀው የውብ ገጽታው ጥላ ሆኖ ወደ ቤቱ ከሚገባ ስቃይ ለመዳን ነው...

____

ብስለት እያንዳንዱ ብርሃን ሙቀት እንዳልሆነ መማር ነው... ሁሉም ውበት በረከት እንዳልሆነ ማወቅ ነው... ከየትኛው እሳት ዳር መቀመጥ፣ ከየትኛው ደግሞ መራቅ እንዳለብን መገንዘብ ነው...


[ምክንያቱም የአዕምሮ ሰላም ከውጭ ከምናየው ገጽታ በላይ ውብ ነው...]


የኋላ ኋላ - በኑረታችን ውስጥ ልዩነት የሚፈጥረው በስንት ዓይነት ውበት መራጨታችን ሳይሆን በምንያህል የልቡና ሰላም ሩጫችንን መቋጨታችን ነው...

____

@bridgethoughts
❤‍🔥63🙏3👏2🔥1
.
.
.

ያልገለጽኩት ፍቅር እንደተዳፈነ እሳት ነው... ውስጥ ውስጡን በጸጥታ ያኝከኛል... መንደርተኛው ፍሜን አያይም፣ ምክንያቱም ማንደጃው ያለው ከልቤ ውስጥ ነው...

-

ይቅርታ ያልጠየቅሁበት ስህተት እንደ ሃረግ ቅጠል ነው... በሃሳቤ ላይ ተንጠላጥሎ ይመነደጋል... ጸጥ ረጭ ባለ ለሊት ሳይቀር የምሬት እንጉርጉሮውን እያመላለሰ ይረብሸኛል...

-

ያልገለጽኩት ምስጋና የደረቀ ምንጭ ይመስላል... ካዳፈንኩት ቦታ መውጫ አጥቶ በጊዜ ብዛት ጣዕም አጥቷል... በመንገዴ ላይ አኮቴት የሚገባቸው ቢኖሩም ንፉግ ሆኜ እታያለሁ...

-

በአንድ ወቅት የቀበርኩት እውነት በጎድኖቼ መሃል እረፍት እንዳጣች ወፍ ይርገበገባል... ክንፎቹን እያማታ ክፍቱን ሰማይ ይናፍቃል... የውስጤ ህመም ቢበረታም ሃፍረት እንዳነቀኝ አለሁ...

-

የሰሰትኩት ጉልበት እንደ ድንጋይ ይከብደኛል... ብልጥ የሆንኩ መስሎኝ ስለግም ድልብ አድርጎ  ያመኛል... ልቤን ሲያፍናት መተንፈስ ጭንቄ ነው...

-

የነፈግሁት ርህራሔ ጸሐይ እንዳጣ ፍሬ ወይቧል... የጨከንኩባቸው ዓይኖች ሳይኖሩ ያዩኛል... ብቻዬን ብሆንም መንፈሴን የሚያድን አሳዳጅ አጥቼ አላውቅም...

-

በሌሎች ላይ ያዘነብኩት ጉዳት ከቀብር እንደሸሸ መንፈስ በሕልሜ አውድ ይቅበዘበዛል... በቁርና ሃሩር መሃል ያነጉደኛል... የበዳይነት ሕመም ዘልቆ ይሰማኛል...

-

የሰው ልጅ በብዙ የጦር አውዶች የሚባትል መደበኛ ተዋጊ ነው...

.
.
.

ይቅርታ የማድረግ ጦር ሜዳ - የበደሉን እጆች መተው፣ ጉዳታቸው ባልሻረበት እንኳ ሁኔታ...


እውነትን የመናገር ጦር ሜዳ - ዝምታ የደህንነት ምልክት በሚመስልበት ጊዜ ሁሉ...


ደግ ሆኖ የመዝለቅ ጦር ሜዳ - መራርነት ምቹ መንገድ በሆነ ጊዜ ጭምር...


የአሁናዊነት ጦር ሜዳ - እልፊት እያፏጨ በሚያጸጽትበት፣ መፃዒ እየጠራ በሚያሰጋበት ጊዜ ሳይቀር...


የመተው ጦር ሜዳ - የማይመለስ አመድ፣ የማይመጣ ዘመድ፣ መሆኑን ሳይመዝኑ ጭምር...


ዳግም በወዳጅነት የማመን ጦር ሜዳ - ቃል በተበላበት፣ እምነት በተናደበት ጊዜ እንኳን...


ተስፋን ሕያው የማድረግ ጦር ሜዳ - ጨለማ የመዳሰስ ያህል በገዘፈበት ጊዜ ሳይቀር...

____

እስኪ ንገሩኝ... 

[ሰው በምድር ላይ ቆሞ ይሄድ ዘንድ ስንት የጦር ሜዳ ነው ማሸነፍ ያለበት?... በልቡና ውስጥ ያለ ሰይፍ በእጅ ከጨበጡት በላይ አይወጋምን?... በሕሊና ውስጥ ያለስ ጦርነት በገሃድ ካለው አይልቅምን?...]

____

@bridgethoughts
11🔥3👌1
እንጂ
___

ማፍቀር አይደለም
ድንቁ፥
እንጂ
አፍቅሮ ማፍቀርን ማወቁ፥

መፈቀር መች ሁኖ ብልሃቱ
እንጂ እውቀቱ
ሲፈቀሩ፥ ፍቅር መሰማቱ፥

እውቀት አይደለም
ቁም ነገሩ፥
ጉዱ
እንዳወቁ ማወቁ።

___

ሰለሞን ዴሬሳ
/ዘበት እልፊቱ/
___

@bridgethoughts
8❤‍🔥3🔥3👍1
.
.
.

[ግራ እየገባኝ ስሄድ አንድ ነገር እየተማርኩ እንደሆነ አውቃለሁ... ምናልባትም ለመንገዴ አንድ ተጨማሪ የብርሃን አምድ እየተተከለች ይሆናል...]

.
.
.

አንዳንዴ ተራ ብዬ ባቃለልኩት ነገር ውስጥ ተቆጥሮ የማያልቅ መደነቅ ይወርሰኛል... ሌላ ጊዜ ደግሞ ድንቅ ያልኩትን ሳሳድድ ከእጄ ያለውን ውበት አጣና ሃዘን ይከበኛል...


[ወደላይ ብቻ የሚያዩ ከእግሮቻቸው ስር ያለውን የምድር ሃብት አይረዱም... አዘቅዝቀው የሚመለከቱም ከበላያቸው ያለውን ንጽህና አይገነዘቡም...]

___

አንዳንዴ ብዙ አለኝ ያልኩትን ጊዜ በአልባሌ ነገር ሞልቼ አባክነዋለሁ... አጠረኝ ያልኩትን ደግሞ ከበድ ባሉ ስራዎች አጭቄ ሳልጠቀም ፈጀዋለሁ...


በሁለቱ መካከል የሚተርፈኝ አንዳች የለም - ከጭንቀትና እረፍት አልባነት ውጭ...


[ነገ ይሆንልኛል እያሉ የሚጠብቁ ዛሬን አያጣጥሙም... ዛሬ ካልሞላልኝ ብለው ሙጥኝ የሚሉም ከነግ ተስፋ አይገናኙም...]

___


አንዳንድ ቀን በፍቅር እንደተጥለቀለቅሁ ይሰማኛል - ሆኖም ወዲያው በእውር ድንብር አስረክቤው ዝምታ ይውጠኛል... ሌላ ጊዜ ደግሞ ፍቅር አጣሁ ብዬ ፍለጋ እወጣለሁ - ይሁንና ቅንስናሽ ማንነቴን በየቦታው ተቀምጦ ሳገኘው እደነግጣለሁ...


በዚህ ሰበብ የሃሳብ ድካም ያናውዘኛል... ውርሱ ሃዘን የሆነ ዘር በውስጤ ያጎነቁላል...


[መፈቀርን ብቻ የሚሻ መስጠትን ሳይማር ያልፋል... ፍቅር ሲሰጥ ብቻ የኖረም የመቀበል ቆምታን ይተላለፋል...]

___


የሕይወት መትረፍረፍ በተሰማኝ ማግስት ራሴን የሚጠፋ ጥላ ሲያሳድድ አገኘዋለሁ... ኑረት በጉድለት ስሜት ስትከበኝ ደግሞ ጫፍ በሌለው ምኞት ሸክሟን አበዛዋለሁ...

በዚህ ሰበብ ባዶነት ይወርሰኛል... ተስፋቢስነት ይጫነኛል...


[መድረሻውን ብቻ የሚያይ ጉዞውን ይረሳል... መንገዱን ብቻ ሙጥኝ ያለ አድማሱን ይዘነጋል...]

___


ነፃ የሆንኩ ይመስለኛል - ግና ራሴን የማገኘው በምርጫዎች ሰንሰለት ታብቶ ነው... ነፃ እንዳልሆንኩ አስባለሁ - ግና ውስጤ የማየው የግዞት ጫና የማይታከካቸውን ዕልፍ ቦታዎች ነው...


በዚህ ሰበብ ቀልቤን ቅዥት ሞልቶት ያታልለኝና የምር ትግል ውስጥ እገባለሁ...


[ነፃነትን የሚፈሩ የራሳቸው አዕምሮ እስረኛ ከመሆን አይድኑም... ነፃነትን ያለአግባብ የሚጠቀሙ የምኞቶቻቸው ባሪያ ከመሆን አይቀሩም...]

___

እንደነገርኳችሁ ነው...


ግራ እየገባኝ ስሄድ አንድ ነገር እየተማርኩ እንደሆነ አውቃለሁ... 

___

@bridgethoughts
9🔥5🥰5💊1