@Book for all
4.37K subscribers
672 photos
4 videos
62 files
48 links
ማንበብ ማንበብ ማንበብ ‹‹ሰፊ ይለበሳል ጠባብ ይቀደዳል››
@መባ
ለማንኛውም አስተያየት
@Dasolo
Download Telegram
ኑ - ዛፎችን እንትከል 🌴🌵🎄🌴

#ETHIOPIA | ሐምሌ 22 ~ ኢትዮጵያ 200 ሚሊዮን ችግኞች በአንድ ጀምበር ትተክላለች ኑ አብረን እንትከል፡፡ 🍀🌴
@Bookfor
01√√ ጠንካራ ሰው ሁን ማለት አትወደቅ ማለት አይደለም
ወድቀህ መነሳትን ልመድ ማለት እንጂ!
02√√ ዝም በል ማለት አትናገር ማለት አይደለም
ሌሎችን ለመስማትም ጆሮ ስጥ ማለት እንጂ!
03√√ ሆዳም አትሁን ማለት አትብላ ማለት አይደለም
በሰዎች ሃቅ ላይ አትለፍ ማለት እንጂ!
04√√ አትቆጣ ማለት ስሜት አይኑርህ ማለት አይደለም
ከቁጣ ቶሎ ተመለስ ማለት እንጂ!
05√√ ይቅርታ አድርግ ማለት አልተጎዳህም ማለት አይደለም
በሆድ ቂም መያዝ ሌላ ጉዳት ስለሆነ እንጂ!
06√√ ጠላትህን ውደድ ማለት ጠላት ጥሩ ነው ማለት አይደለም
ከጥላቻ ይልቅ ፍቅር ስለሚያሸንፍ እንጂ!
07√√ ደስተኛ ሁን ማለት ሁሉ ይኑርህ ማለት አይደለም
ባለህ ነገር ደስ ይበልህ ማለት እንጂ
08√√ ስራህን ወደድ ማለት የምትሰራው ስራ ጥሩ ነው ማለት
አይደለም ነገ ጥሩ ስራ እንዲኖርህ ዛሬ የምትሰራውን ወደድ
ማለት እንጂ!
09√√ ወረኛ አትሁን ማለት አታውራ ማለት አይደለም
ምንም ስለማታውቀው ነገር አታውራ ማለት እንጂ!
10√√ ትሞታለህ ማለት አትስራ ማለት አይደለም
ምንም ቁም ነገር ሰትሳራ አትሙት ማለት እንጂ!
11√√ ብቸኛ አትሁን ማለት ሮጠህ ትዳር ያዝ ማለት አይደለም
ልብህን ጊዜህን ያለህን ሁሉ አሳልፈህ ለመስጠት ዝግጁ
ሁን ማለት እንጂ!
12√√ እውነተኛ ሁን ማለት ሰዎች ባሉበት ብቻ እውነት ተናገር ማለት
አይደለም ለራስህም የእውነት ኑሮ ኑር ማለት እንጂ!
13√√ አትጣላ ማለት ከሰው ጋር አትጋጭም ማለት አይደለም
ቂም ይዘህ አትቆይ ማለት እንጂ!
14√√ ኩራተኛ አትሁን ማለት አትዘንጥ ማለት አይደለም
ሌሎችን አትናቅ ማለት እንጂ!
15√√ ቆንጆ ነህ ማለት ከሌሎች የተሸልክ ነህ ማለት አይደለም
አምሮብሃል ማለት እንጂ!
16√√ አዋቂ ሁን ማለት እንደገና ት/ቤት ሂድ ማለት አይደለም
ብልህ ሁን ማለት እንጂ
መልካም ስብዕና ፣ ሀገር ወዳድነት አይለየን፡፡
ሰናይ ዕለተ ሰንበት ተመኘሁ፡፡
@Bookfor
# ኢትዮጵያዬ_ለምልሚ
@Bookfor
ማሰብ_ካልጀመርክ_የትኛውም_ሽቶ_የህይወትህን_መጥ
ፎ_ሽታ_ሊደብቅ_አይቻለውም (ዲዮጋን).....
ዲዮጋን እቺን ቃል የተናገራት መዋብና ማሸብረቅ ለሚወዱ ግን ማንበብና በጥልቀት ማሰብን የማይፈልግ ሰው በገጠመው ሰዓት ነበር..................ብዙዎችቻችን ስለምንጌጥበት ነገር ስለምንለብሰው ልብስ ፤ ስለምንጫማው ጫማ ፤ ስለምንከተለው ፋሽን አብዝተን እንጨነቅ ይሆናል ።
ጥያቄው ግን
* ለሚቀርብልን ጥያቄዎች፤ ለምንሰጠው ቀና ምላሽ የምንጨነቀው ስንቶቻችን እንሆን..................?
በተለይ በኛ አገር ላይ ጥሩ ፋሽን ተከታይ ባለ ጥሩ ሽቶ ግን አንደበቱ በክፋት የተሞላ እና ምንም ማነፅ የተሳነው ሰው እየበዛ የመጣው ለምንድነው ? ብለን የጠየቅን ሰዓት.. ........መልሱን ውስጣችን እናገኘዋለን .......... ማንበብ ችግራችን ለመፍታት እይታን ያሰፋል በጥልቀት ማሰብ ደግሞ መፍትሔን ያመላክታል ............ለምን
ለብሰው ልብስ እንደምንጨነቀው ሁሉ ለምናስበው ሃሳብና ለምንናገረው ቃላትም መጠበብ ይኖርብናል። አለበለዚያ የኛ አገር ጠቢባን እንደሚሉት ባዶ ገንቦ ሽፋን መሆናችን ነው።
ግሪኮችም ለዛ ነው " ጥበብን ፈልጋት ጥበብ ከሌለህ እንደ እሪያ መሆንክ ነው.................የሚሉት።
@Bookfor
@Bookfor
ለውብ ቀን!
💚💚💚

ኢትዮጵያ ሆይ፥ እኛ አንቺን ለምንል ሁሉ ከአንቺ አልጋ የመውረድን ገፊ ምኽኛት ሳናይ
ምጽኣት ይምጣ!
--------
እኔ ኢትዮጵያዊ ነኝ! የምገለጠውም ሆነ ሙሉነት የሚሰማኝ ኢትዮጵያ በያዘችውና
ባቀፈችው ሁሉ የኢትዮጵያዊነት ትርክትና ንግርት ነው።
የሃገሬ "ቅርንጫፎች ግንድ መሆን" ቢያምራቸው በቆየው ስርና ግንድ የኢትዮጵያነት ማማ
ላይ የምቆይ እንጂ ተገንጣይ ቅርንጫፎች ላይ ልወጣ ፍጹም አልሻም። በማያውቁት አዲስ
ጎጆ መውጣት ናፍቆት ነሁልለው በነጻውና ሰፊው አዳራሽ መኖር ሰልችቷቸው፣ በዘር
ማንዘራቸው ስም የቆመ ጠባብ ቀፎ አገር ናፍቋቸው፣ ከሽለመጥማጥ ያምልጥ አያምልጥ
ባላወቁት "እጭ" ውስጥ ገና ያሉ ግርር ብለው ለመብረር፣ የሚንደፋደፍ "አውራቸውን"
ጠባቂ ተፈልፋይ ተስፈኛ ንቦችን ባየሁ ጊዜ አገርን ማፍረስ ጎጆ የመቀለስን ያክል ቀለለ
እንዴ? እላለሁ።


እንዲህም እላለሁ፥ ከትናንት ዛሬ ይበልጣል፥ለብልህም ከዛሬም ነገ ይ'በጃል። ትናንት
ኢትዮጵያዊነት "እኔን አልነበረም" ላሉም ሆነ "ነበርን" ለሚሉ ነገን የተሻለ እናድርግ ቢሉ
ሁላቸውንም የምትመስል ኢትዮጵያን ለመስራት ቀኑ ዛሬ ነው።
ደግሜም እላለሁ፥
የሆነው ሁሉ የኔ ነው!! በሃገሬ ላይ የሆነውን ሁሉ ያደረገ በየዘመኑ የኖረ "በጎና መጥፎ"
ትውልድ እንጂ ማንም አደል! በጎም ይሁን መጥፎው ትውልድም የኔው ነው። በመጥፎው
በጎውን አልጥልም! በመጥፎው የትናንት ትዝታ የዛሬ ቤቴን አላቃጥልም። በትናንት በጎ
አለቅጥ ጭፈራም ዛሬን ያስጥልም ይሆናል። ብቻ በተተረክልኝ ትርክት ብስጭት የዛሬ
ወንድሞችንና እህቶቼን አልከስም፥ አልገፋም፣ አልጠላም። ዛሬን ለማበጀት ብቻ ጅማቴን
እገትራለሁ!!
በኢትዮጵያ ሰማይና መሬት የሆነው ሁሉ በእናትና አባቴ ቤት ምሰሶ ስር የሆነ ነው ብየ
አስባለሁ። በእናትና አባቴ ቤት የሆነውን ደግ ምግባር የማወሳ ቢሆን እንጂ መጥፎውን
ብለፍፈው ገመናው የማን ሊሆን? እንዲያስ ቢሆን ሰው በጻፈው ታሪክ ውስጥ በጎና መጥፎ
ተለያይተው ያውቃሉን? የገለማ ትናንትን እያኘክኩና እያማሰልኩ የቤቴን የዛሬ መልካም
ጠረን ከማበላሽ፣ በተስፋ ጠኔ ከምመታ፣ ተለዋዋጭ ለሆነው ነብሴና መንፈሴ ስለምን
አዲስ ታሪክ ዛሬ ለነገ አልጽፍም?
ኢትዮጵያ ሆይ፥ እኛ አንቺን ለምንል ሁሉ ከአንቺ አልጋ የመውረድን ገፊ ምኽኛት ሳናይ
ምጽኣት ይምጣ!

(( ያሲን መሀመድ ))💚💛

@Bookfor
እባክሽ!!!!!


ታከተኝ እምዬ
ጣና ዳር ተቀምጦ ንጹህ ውሃ መጠማት
ጥቁር አፈር ኖሮኝ
ለካናዳ ስንዴ ሰርክ እጄን መዘርጋት
ለባእዳን ደስታ
የጭንቄን ተካፋይ ወንድሜን መዋጋት
አቃተኝ ሀገሬ
ኮሽ ባለ ቁጥር በምን ሰበብ መስጋት፡፡

እናም ስጦታዬ
ክብርሽ ወዲያ ሆኖ ወዲህ ስብሰለሰል
መጥፋቴ ነውና
ህልሜን የሚጋራ አጥቼ እኔን መሰል
ማበዴን ሳትሰሚ
እባክሽ ንቂና
ተባልተን ሳናልቅ ልጆችሽ እንብሰል፡፡

@Bookfor
የተወዳጁ ደራሲ አለማየሁ ገላጋይ አዲስ መጽሐፍ ገበያ ላይ ዋለ፡፡
"ውልብታ" አሥራ ሦስተኛው መጽሐፍ ነው፡፡
****
በኢትዮጵያ ሥነ-ጽሑፍ ታሪክ በተለየ አጻጻፍ ብቅ ካሉ ደራሲዎች መካከል የሚጠቀሰውና ከፍተኛ አንባቢዎች ያሉት ደራሲና ሃያሲ አለማየሁ ገላጋይ አዲስ መጽሐፍን ገበያ ላይ አውሏል፡፡ አለማየሁ ገላጋይ ያወጣው አዲስ መጽሐፍ "ውልብታ" የሚል ርዕስ ያለው ሲሆን አሥራ ሦስተኛው ስራውም ነው፡፡
.
አጫጭር መሳጭ ታሪኮችን የያዘው ይህ አዲስ መጽሐፍ 160 ገጾች ያሉት ሲሆን በውስጡም 71 የሚሆኑ ትርካዎችን አካቷል፡፡ መጽሐፍ በ 71 ብር ዋጋ ለገበያ የቀረበ ነው፡፡
.
አለማየሁ ገላጋይ በመቶዎች የሚቆጠሩ አርቲክሎችን በተለያዩ ጋዜጦች ላይ ሲጽፍ የቆየ በሂስና በድርሰት የሚታወቅ አንጋፋ ደራሲ ሲሆን እስከአሁንም ኩርቢት፣ አጥቢያ፣ የብርሃን ፈለጎች፣ ቅበላ፣ ወሬሳ፣ በፍቅር ስምና ታለ የታባሉ ልቦለዶች መለያየት ሞት ነውና ኢህአዴግን እከሳለሁ የመሳሰሉ የወግ መጻህፍትን ጨምሮ ከአሁኑ መጽሐፍ ጋር አስራ ሦስት ድርሰቶችን ለአንባቢያን ያደረሰ ነው፡፡
@Bookfor
@Bookfor
@Bookfor
አንድ አባት እንዲህ ብለው ተናገሩ
የምታያቸውን ነገሮች ተጠንቀቃቸው ታስባቸዋለህና
የምታስባቸውን ተጠንቀቃቸው ታረጋቸዋለህና
የምታረጋቸውን ተጠንቀቃቸው ልምድህ ይሆናሉና
ልምዶችህን ተጠንቃቸው እጣፈንታህ ሆነው ይቀራሉና፡፡
እናም ሁሉም የሚጀምረው ከምታየው ነውና የምታየውን ለይ፡፡
@Bookfor
@Bookfor
ወርቃማ የስነፅሁፍ ዘመን
ታሪክ በፅሁፍ መስፈር ከጀመረበት ጀምሮ ስነፅሁፍ አሻራውን በዘመን ላይ ሲያሳርፍ ኖሯል። ዘመን መልሶ ስነፅሁፍን ይቀርፃል። ታድያ ስነፅሁፍ ቀጥ ብሎ እየጎለመሰ አልመጣም። አንዳንዴ ይገናል ሌላ ግዜ ይተናል፤ ሲያሻው ይወጣል አሊያም ይወርዳል፤ በወቅት ይረቃል በወቅት ይደቃል። የስነፅሁፍን እድገት በግራፍ ብንሰራው እየጨመረ የሚሄድ ቀጥ ያለ መስመር አይሆንም። የተወሳሰበ ዚግዛግ መስመር እንጂ።
ስነፅሁፍ አስደናቂ ከፍታ ላይ የደረሰባቸውን ዘመናት ወርቃማ እንላቸዋለን።
በአለምአቀፍ ደረጃ ለስነፅሁፍ ወርቃማ የሚባሉ ዘመኖች አሉ። የክላሲካል ግሪክ ዘመን በፍልስፍና ፣ ኤፒክ ፖትሪ ፣ ቲያትር ጫፍ ላይ የደረሰበት ዘመን ነው። ሮማውያንም ይህንኑ ስነፅሁፋዊ ዘይቤ ቀጥለውበታል። በእንግሊዝ 16ኛው ክፍለዘመን ሼክስፒርን ጨምሮ እልፍ ገጣምያን የነበሩበት ሌላ ወርቃማ ዘመን ነው። ከኢንላይትመንት እና ኢንደስትሪያል አብዮት ጋር ተያይዞ በመላው አውሮፓ የረቀቀ የስነጽሑፍ ዘይቤ ተቀጣጥሏል። በፈረንሳይ ጀርመን ሩስያ እንግሊዝ አሁን ድረስ ተነባቢነት ያላቸው ልብወለድ መፅሀፍት የተፃፉት በዚያ ዘመን ነው። በ20ኛው ክፍለዘመን አሜሪካ የመጀመሪያ ግማሽ ሌላ የስነፅሁፍ ከፍታ ግዜ ነው።
ይህንን ትሬንድ ስንመለከት ስነፅሁፍ ሌጣውን እንደማይጎለምስ ወይንም እንደማይከስም ይገለፅልናል። ኢኮኖሚያዊ መነቃቃት የባህል አብዮት መንፈሳዊ ከፍታ ለስነፅሁፍ እድገት ምቹ እርሾዎች ናቸው።
ይሄንን ይዘን ወደ ኢትዮጵያ አውድ እንምጣ። የኢትዮጵያ ዘመናዊ ስነፅሁፍ ወርቃማ ዘመን መቼ ነው? ጦቢያ የመጀመሪያው የአማርኛ ልብወለድ ነው ካልን ስነፅሁፋችን የ100 አመት ወጣት ቢሆን ነው። በዚህ ግዜ ውስጥ ጥበብ ከፍተኛ ደረጃ ላይ የደረሰው ከ50ዎቹ እስከ 70ዎቹ ባሉት ዘመን ነው። የኢትዮጵያ ታላላቅ ልብወለዶች ፣ ግጥሞች ፣ ቲያትሮች ፣ የታሪክ መፅሀፍት የተፃፉት በዚሁ ዘመን ነው። ሃዲስ አለማየሁ በፍቅር እስከ መቃብር፣ ዳኛቸው ወርቁ በአደፍርስ፣ ስብሃት በሌቱም አይነጋልኝ የተጠበቡት ያኔ ነው። ሎሬት ፀጋዬ፣ መንግስቱ ለማ ትያትሩን ከፍ አድርገው የሰቀሉት በዚያ ዘመን ነው። ግጥም በጋሽ ፀጋዬ በሰለሞን ደሬሳ የረቀቀው ከግማሽ ምእተ አመት በፊት ነው። ከስነፅሁፉ ባሻገር በስእል እና ሙዚቃም ይህ ዘይቤ ተንሰራፍቷል። አፈወርቅ ተክሌ፣ እስክንድር ቦጎስያን ፣ ገብረክርስቶስ ደስታ፣ ሙላቱ አስታጥቄ፣ ጥላሁን ገሰሰ ሁሉም ዘመኑን ከፍ ያደረጉ ከያንያን ነበሩ።
ያ ዘመን ጉምቱ ጥበበኞች ከያሉበት ተጠራርተው የተሳበሰቡበት ወርቃማ፣ አልማዛማ ፣ ፕላቲኒየማማ ግዜ ነበር!
@Bookfor
@Bookfor
የ ህይወት ትልቁ ትርጉም በሆነው ሁሉ መደሰት ነው፡፡
ያጣነውን ሳይሆን ያለንን ማየት ትልቁ መሰጠት ነው፡፡
መባ
@Bookfor
@Bookfor
የዕለቱ መልዕክት
አዋቂ ሰው ከሌሎች ስህተት ይማራል አዎ እኛ ለመማር ዕልፍ ምሳሌ አለን አጥተን ሳይሆን ካጡት ፣ ጠፍተን ሳይሆን ከጠፍት ፣ ተጣልተን ሳይሆን ከተጣሉት ፣ ፈርሰን ሳይሆን ከፈረሱት መማር አለብን፡፡ ይህ የምትመለከቱት ሊቢያ ወደ እርስ በርስ ግጭት ከማምራቷ በፊት እና ግጭቱ የፈጠረባት መከራ ነው፡
ሸጋ ቅዳሜ
በብሩህ ሰማይ ስር ፣ በንፁህ ልቦና
በአባቶችህ አገር
በእናቶችህ መንደር
ፍልቅልቅ ፍንድቅድቅ ለአዲስ የቀን ፍና
@Bookfor
@Bookfor
Audio
ግጥም ፦ እንዳለጌታ ከበደ
አቅራቢ ፦ መብረቁ ጥቁር ሰው (መባ)
@Bookfor
@Bookfor
@getem
ለመላው የእስልምና ሀይማኖት ተከታዮች እንኳን ለ1 ሺህ 440ኛው ዓመተ ሒጅራ የኢድ-አል-አድሐ (አረፋ) በዓል በሰላም አደረሳችሁ::
ኢድ ሙባረክ!!!
በዓሉ የሰላም፣ የመተሳሰብ ፣ የፍቅር እንዲሆን ምኞታችን ነው፡፡
@Bookfor
ጦብያ.pdf
845.2 KB
ውድ የ Book For all ቤተሰቦች እንዴት ናችሁ? ይህን ክረምት እየተዝናናችሁ ቁም ነገር ትቀስሙበት ዘንድ ጦቢያ የተሰኘውን የአፈወርቅ ተክለ ኢየሱስ መፅሐፍ እነሆ!
@Bookfor