በሰሜን ተራሮች ውዳችን አለቀ
እሳት አመድ ወልዶ ክብራችን ወደቀ
ውሃ ከአገር ጠፋ እሳቱም ጨከነ
መኩሪያችን ተማግዶ ስማችንን መነነ
መፈናቀል በሰው ልምድ ሆኖ በአገሬ
እንስሳቱን እሳት ያሳድዳል ዛሬ
እንደምን እንጠብቅ እሳት እንዲራራ
ጁብዱ አርጓት ወገኔ ገድሎ እየተኩራራ
ከዚህስ የሚበልጥ ምን ሊኖር ምልክት
ካስተዋልን ይህ ነው እንደ ሃገር ትምህርት
ይልቅ እንነሳ በአንድ ላይ እንውጣ
ከሰሜን ተራሮች በድል እንድንመጣ
ዘር ብሔር ሳንለይ ሆ ብለን እንውጣ
በቃል ኪዳን ድልን አውጀን እንምጣ
ብንለያይ እንጂ እሳት መች ጀግኖ
ጭድ ሆነን ነው እኛ ልባችን ጨክኖ
በአመድ አይጻፍ ታሪክ በእሳት ተፈትነን
መጠየቅ አለና በታሪክ ተወቅሰን።
ይልቅ እንነሳ በአንድ ላይ እንውጣ
ከሰሜን ተራሮች በድል እንድንመጣ።
በአንዳርጌ አሰፋ
@Bookfor
እሳት አመድ ወልዶ ክብራችን ወደቀ
ውሃ ከአገር ጠፋ እሳቱም ጨከነ
መኩሪያችን ተማግዶ ስማችንን መነነ
መፈናቀል በሰው ልምድ ሆኖ በአገሬ
እንስሳቱን እሳት ያሳድዳል ዛሬ
እንደምን እንጠብቅ እሳት እንዲራራ
ጁብዱ አርጓት ወገኔ ገድሎ እየተኩራራ
ከዚህስ የሚበልጥ ምን ሊኖር ምልክት
ካስተዋልን ይህ ነው እንደ ሃገር ትምህርት
ይልቅ እንነሳ በአንድ ላይ እንውጣ
ከሰሜን ተራሮች በድል እንድንመጣ
ዘር ብሔር ሳንለይ ሆ ብለን እንውጣ
በቃል ኪዳን ድልን አውጀን እንምጣ
ብንለያይ እንጂ እሳት መች ጀግኖ
ጭድ ሆነን ነው እኛ ልባችን ጨክኖ
በአመድ አይጻፍ ታሪክ በእሳት ተፈትነን
መጠየቅ አለና በታሪክ ተወቅሰን።
ይልቅ እንነሳ በአንድ ላይ እንውጣ
ከሰሜን ተራሮች በድል እንድንመጣ።
በአንዳርጌ አሰፋ
@Bookfor
# የጅራፍ_ንቅሳት
(ኤፍሬም ስዩም)
=====//=====
ከጀርባህ ላይ ያለው የጅራፍ ንቅሳት
እኛን የመውደድህ የዘላለም ምትራት
የፋሬስ የሳዶቅ ያለማመን ደባ
የጲላጦስ ግርፊያ የሄሮድስ ካባ
ከፊትህ የወጣው የደም ጎርፍ እና እንባ
ላንተ ስቃይ ናቸው ለኛ ግን ደስታ
መከራህ ነውና የመዳን አለኝታ
ጅራፍ እና ቡጢ ምራቅና ሃሞት
ለአይን ደስ የማይል የስቃይ ደምግባት
በደም የተረጩ ቅዱሳት አልባሳት
እኒህ ናቸው ውበት የጌታ ደምግባት
የመዳን አለኝታ የዘላለም ምትራት
ውዴን ያላያችሁ
እኔ ልንገራችሁ
ፍቅሩን ላሳያችሁ
ድምጹን ላሰማችሁ
ምራቅ ተቀብቷል
ቡጢ ተቀብሏል
ኃጢዓት ተሸክሟል
በቁንዳለው መሃል የደም ጎርፍ ይፈሳል
የፍቅር ንጉስ ነው የእሾህ አክሊል ደፍቷል
ውዴን ያላያችሁ
ድምጹን ያልሰማችሁ
ፍቅሩን ልንገራችሁ
ዐይኑ ፍቅር ያለቅሳል
ጎኑ ደም ይረጫል
ፅህሙ ተነጭቷል
ልብሱ ሜዳ ወድቋል
በቃሉ ቅዱስ ነው ይቅርታን ይሰዋል
ከፍቅር ትከሻው የዓለም ደዌን አዝሏል
ከጀርባው ላይ ያለው የጅራፍ ንቅሳት
እኛን የመውደዱ የዘላለም ምትራት
ለእሱ ስቃይ ናቸው ለኛ ግን ደስታ
መከራው ነውና የመዳን አለኝታ
ይህ ሁሉ ቢሆንም
ይህ ሁሉ ቢሆንም
የሰው ልጆች ድፍረት ክብሩን አይቀንስም
ስለሰው መድከሙም ኃይሉን አያወርድም
ስሙ እግዚአብሔር ነው
ስሙ ይቅርታ ነው
ስሙ መሀሪ ነው
የፈረሱን ብርታት ብቃቴ ነው የሚል
ብዛቱን ተማምኖ የሚታበይ ልዑል
በ'ሱ ስም ይወድቃል በስሙ ይጣላል
ስሙ ሁሉን ቻይ ነው ሁሉንም አድራጊ
ታላቁን የሚጥል ለታናሽ ተዋጊ
ውዴን ያላያችሁ
ድምጹን ላሰማችሁ
እኔ ልንገራችሁ
ፍቅሩን ላሳያችሁ
ከጀርባው ላይ ያለው የጅራፍ ንቅሳት
እኛን የመውደዱ የዘላለም ምትራት
ለርሱ ስቃይ ናቸው ለኛ ግን ደስታ
መከራው ነውና የመዳን አለኝታ
እናም ጌታችን ሆይ...
ያመኑት ይፅናኑ የወጉህም ይዩህ
በደም የተረጩ ልብሶችህን ለብሰህ
አሜን ጌታችን ሆይ ናልን ተመልሰህ።
@Bookfor
(ኤፍሬም ስዩም)
=====//=====
ከጀርባህ ላይ ያለው የጅራፍ ንቅሳት
እኛን የመውደድህ የዘላለም ምትራት
የፋሬስ የሳዶቅ ያለማመን ደባ
የጲላጦስ ግርፊያ የሄሮድስ ካባ
ከፊትህ የወጣው የደም ጎርፍ እና እንባ
ላንተ ስቃይ ናቸው ለኛ ግን ደስታ
መከራህ ነውና የመዳን አለኝታ
ጅራፍ እና ቡጢ ምራቅና ሃሞት
ለአይን ደስ የማይል የስቃይ ደምግባት
በደም የተረጩ ቅዱሳት አልባሳት
እኒህ ናቸው ውበት የጌታ ደምግባት
የመዳን አለኝታ የዘላለም ምትራት
ውዴን ያላያችሁ
እኔ ልንገራችሁ
ፍቅሩን ላሳያችሁ
ድምጹን ላሰማችሁ
ምራቅ ተቀብቷል
ቡጢ ተቀብሏል
ኃጢዓት ተሸክሟል
በቁንዳለው መሃል የደም ጎርፍ ይፈሳል
የፍቅር ንጉስ ነው የእሾህ አክሊል ደፍቷል
ውዴን ያላያችሁ
ድምጹን ያልሰማችሁ
ፍቅሩን ልንገራችሁ
ዐይኑ ፍቅር ያለቅሳል
ጎኑ ደም ይረጫል
ፅህሙ ተነጭቷል
ልብሱ ሜዳ ወድቋል
በቃሉ ቅዱስ ነው ይቅርታን ይሰዋል
ከፍቅር ትከሻው የዓለም ደዌን አዝሏል
ከጀርባው ላይ ያለው የጅራፍ ንቅሳት
እኛን የመውደዱ የዘላለም ምትራት
ለእሱ ስቃይ ናቸው ለኛ ግን ደስታ
መከራው ነውና የመዳን አለኝታ
ይህ ሁሉ ቢሆንም
ይህ ሁሉ ቢሆንም
የሰው ልጆች ድፍረት ክብሩን አይቀንስም
ስለሰው መድከሙም ኃይሉን አያወርድም
ስሙ እግዚአብሔር ነው
ስሙ ይቅርታ ነው
ስሙ መሀሪ ነው
የፈረሱን ብርታት ብቃቴ ነው የሚል
ብዛቱን ተማምኖ የሚታበይ ልዑል
በ'ሱ ስም ይወድቃል በስሙ ይጣላል
ስሙ ሁሉን ቻይ ነው ሁሉንም አድራጊ
ታላቁን የሚጥል ለታናሽ ተዋጊ
ውዴን ያላያችሁ
ድምጹን ላሰማችሁ
እኔ ልንገራችሁ
ፍቅሩን ላሳያችሁ
ከጀርባው ላይ ያለው የጅራፍ ንቅሳት
እኛን የመውደዱ የዘላለም ምትራት
ለርሱ ስቃይ ናቸው ለኛ ግን ደስታ
መከራው ነውና የመዳን አለኝታ
እናም ጌታችን ሆይ...
ያመኑት ይፅናኑ የወጉህም ይዩህ
በደም የተረጩ ልብሶችህን ለብሰህ
አሜን ጌታችን ሆይ ናልን ተመልሰህ።
@Bookfor
ለመላው የ Book for all የክርስትና እምነት ተከታይ ቤተሶቦች እንኳን ለጌታችን መድሐኒታችን እየሱስ ክርስቶስ የስቅለት በዓል በሰላም አደረሳችሁ ፡፡
@Bookfor
@Bookfor
ፍቅር እስከ መቃብር
ሁለት ወጣት ኢትዮጵያውያን ከሃገራቸው ብዙ ርቀት እየሩሳሌም ላይ ተገናኙ።
ወጣቱ ሃገራቸውን በዲፕሎማትነት ሊያገለግሉ በ1937 በእየሩሳሌም ከትመው
ነበር። በግዜው እየሩሳሌም በእንግሊዝ ግዛት አስተዳደር ስር ነበረች። ወጣቱም
በዛ የኢትዮጵያ ቆንሲል ሆኑ። በቆይታቸው አንዲት ውብ ኢትዮጵያዊት ተዋወቁ።
ኢትዮጵያዊቷ ኢትዮጵያ ውስጥ ተወልዳ በሁለት አመቷ ወደ እየሩሳሌም
መጣች። አያቷ ለመመንኮስ ወደ እየሩሳሌም ሲመጡ ነበር ህፃኗን ይዘው
የመጡት። ህፃኗ በእየሩሳሌም በአያቷ መልካም አስተዳደግ ውብ ወጣት ሆነች።
ሁለቱ ወጣቶች ወዲያውኑ ተጋቡ። ምንም እንኳን ፍሬ ለማየት ባይታደሉም
ደስተኛ እና የሚያስቀኑ ጥንዶች ነበሩ።
ሁለቱ ባለትዳሮች በባልየው ስራ ምክንያት አውሮፓ እና አሜሪካ በሚዘዋወሩበት
ወቅት እንኳን ተለያይተው አያውቁም። በ1954 ግን ኃያሉ ሞት ለያቸው።
ወይዘሮዋ በህመም አረፉ። አርፈው አስከሬናቸው አያታቸው ወደ አሉበት ቅድስት
እየሩሳሌም ባለቤታቸው ወስደው በጌቴሰማኒ የመጨረሻው እንዲሆን አደረጉ፡፡
ጎልማሳው ብርቱ ሃዘን ገባቸው። በአዲስአበባ የሚገኘውን መኖሪያ ቤታቸውን
በባለቤታቸው ስም ለተሰየመ በአዲስአበባ ከተማ ምክር ቤት ለሚተዳደር
የልጆች ማሳደጊያ በስጦታ ሰጡ።
ጎልማሳው ዳግመኛ አላገቡም። አርባ አመት በብቸኝነት ኖረው በ1995 አረፉ።
ባለታሪኮቹ ሃዲስ አለማየሁ እና ክበበ―ጸሐይ በላይ ነበሩ። ፍቅራቸውም እስከ
መቃብር ነበር!
@Bookfor
ሁለት ወጣት ኢትዮጵያውያን ከሃገራቸው ብዙ ርቀት እየሩሳሌም ላይ ተገናኙ።
ወጣቱ ሃገራቸውን በዲፕሎማትነት ሊያገለግሉ በ1937 በእየሩሳሌም ከትመው
ነበር። በግዜው እየሩሳሌም በእንግሊዝ ግዛት አስተዳደር ስር ነበረች። ወጣቱም
በዛ የኢትዮጵያ ቆንሲል ሆኑ። በቆይታቸው አንዲት ውብ ኢትዮጵያዊት ተዋወቁ።
ኢትዮጵያዊቷ ኢትዮጵያ ውስጥ ተወልዳ በሁለት አመቷ ወደ እየሩሳሌም
መጣች። አያቷ ለመመንኮስ ወደ እየሩሳሌም ሲመጡ ነበር ህፃኗን ይዘው
የመጡት። ህፃኗ በእየሩሳሌም በአያቷ መልካም አስተዳደግ ውብ ወጣት ሆነች።
ሁለቱ ወጣቶች ወዲያውኑ ተጋቡ። ምንም እንኳን ፍሬ ለማየት ባይታደሉም
ደስተኛ እና የሚያስቀኑ ጥንዶች ነበሩ።
ሁለቱ ባለትዳሮች በባልየው ስራ ምክንያት አውሮፓ እና አሜሪካ በሚዘዋወሩበት
ወቅት እንኳን ተለያይተው አያውቁም። በ1954 ግን ኃያሉ ሞት ለያቸው።
ወይዘሮዋ በህመም አረፉ። አርፈው አስከሬናቸው አያታቸው ወደ አሉበት ቅድስት
እየሩሳሌም ባለቤታቸው ወስደው በጌቴሰማኒ የመጨረሻው እንዲሆን አደረጉ፡፡
ጎልማሳው ብርቱ ሃዘን ገባቸው። በአዲስአበባ የሚገኘውን መኖሪያ ቤታቸውን
በባለቤታቸው ስም ለተሰየመ በአዲስአበባ ከተማ ምክር ቤት ለሚተዳደር
የልጆች ማሳደጊያ በስጦታ ሰጡ።
ጎልማሳው ዳግመኛ አላገቡም። አርባ አመት በብቸኝነት ኖረው በ1995 አረፉ።
ባለታሪኮቹ ሃዲስ አለማየሁ እና ክበበ―ጸሐይ በላይ ነበሩ። ፍቅራቸውም እስከ
መቃብር ነበር!
@Bookfor
ኢትዮጵያን የቀረጹ መፅሀፍት
★ ኢትዮጵያን በሃይማኖት በፍልስፍና በህግ በግብረገብ በስነልቡና በፖለቲካዊ
እና ማህበራዊ እሳቤ የቀረፁ መፅሀፍት
★ መፅሀፍቱ በከፊል በግለሰብ ደረጃ የአስተሳሰብ ለውጥ ሲያመጡ የተቀሩት
እንደ ሃገር ተፅእኖ አሳርፈዋል፤ህዝብንና መንግስትን በየፈርጁ ቀይረዋል
★ ብዙዎቹ ለበጎ አላማ ሲያነሳሱ ጥቂቶች እኩይ ተፅእኖ ነበራቸው
★ ብዙዎቹ ፈር ቀዳጅና በየዘርፋቸው አንጋፋ የሚባሉ ስራዎች ናቸው
★ ከትውልድ ትውልድ እየተሸጋገሩ ብዙዎች ጋር በመድረስ ዘመን አይሽሬ
ሆነዋል
※※※ሃይማኖታዊ(9)
መፅሀፍ ቅዱስ―(ትርጉም አብርሃም ሩሚ 1840)
መጫፈ ቁልቁሉ―(ትርጉም ኦነሲሞስ ነሲብ)
የትግርኛ መፅሀፍ ቅዱስ―(ትርጉም አለቃ ተወልደመድህን ገብሩ እና
ተወልደብርሃን ገብረመድህን)
ቅዱስ ቁርአን―(ትርጉም እጨጌ እንባቆም)
ክብረ ነገሥት
ስንክሳር
አቡሻክር
ሃይማኖተ አበው
ፍትሐ ነገስት
※※※ልብወለድ(29)
ፍቅር እስከ መቃብር―ሃዲስ አለማየሁ
አልወለድም―አቤ ጉበኛ
የጉለሌው ሰካራም―ተመስገን ገብሬ
ማህሌት―አዳም ረታ
አስኮ ጌታሁን―ጃርሶ ኪሩቤል
መስከረም―ታደሰ ሊበን
ኦሮማይ―በአሉ ግርማ
ሌቱም አይነጋልኝ―ስብሐት ገብረእግዚአብሔር
አደፍርስ―ዳኛቸው ወርቁ
ከአድማስ ባሻገር―በአሉ ግርማ
ግራጫ ቃጭሎች―አዳም ረታ
ከቡስካ በስተጀርባ―ፍቅረማርቆስ ደስታ
ታሪክና ምሳሌ―ከበደ ሚካኤል
ሰመመን―ሲሳይ ንጉሱ
ቆንጆዎቹ―ሰርቅ ዳ
የስንብት ቀለማት―አዳም ረታ
እፍታ(አምስት ቅጾች)―አርታኢ ተስፋዬ ገብረአብ
እንደወጣች ቀረች―አሰፋ ገብረማርያም
ፀሐይ መስፍን―መኮንን እንዳልካቸው
አንድ ለናቱ―አቤ ጉበኛ
የቡርቃ ዝምታ―ተስፋዬ ገብረአብ
የታንጉት ሚስጥር―ብርሃኑ ዘርይሁን
ጉንጉን―ኃይለመለኮት መዋእል
አምስት ስድስት ሰባት―ስብሐት ገብረእግዚአብሔር
ሰንሰለት―ሻምበል ፈቃደ ዮሃንስ
አባኮስትር―አበራ ጀንበሬ
አሉላአባ ነጋ―ማሞ ውድነህ
ዳር እስከ ዳር―አንዳርጌ መስፍን
ዶሰኛው―የሺጥላ ኮከብ
ጦቢያ―አፈወርቅ ገብረየሱስ
አብዮት―ብርሃኑ ዘርይሁን
ልጅነት ተመልሶ አይመጣም―በእምነት ገብረማርያም
The Thirteenth Sun―Danyachew Worku
The Case of the Socialist Witchdoctor―Hama Tuma
Notes from the Hynea's Belly―Nega Mezlekia
※※※ትያትር(11)
አፋጀሽኝ―ዮፍታሄ ንጉሴ
ቴዎድሮስ―ግርማቸው ተክለሃዋርያት
ሀሁ በስድስት ወር―ፀጋዬ ገብረመድህን
እናት አለም ጠኑ―ፀጋዬ ገብረመድህን
ጴጥሮስ ያቺን ሰአት―ፀጋዬ ገብረመድህን
ባልቻ አባ ነፍሶ―ብርሃኑ ዘርይሁን
አልቃሽና ዘፋኝ―ፍስሐ በላይ ይማም
ውበትን ፍለጋ―ጌትነት እንየው
ጠልፎ በኪሴ―መንግስቱ ለማ
ያላቻ ጋብቻ―መንግስቱ ለማ
Oda Oka Oracle―Tsegaye Gebremedhin
※※※ታሪክ(25)
የአህመድ ግራኝ ወረራ―ተክለፃድቅ መኩሪያ
የኤርትራ ጉዳይ―ዘውዴ ረታ
የኢትዮጵያ ታሪክ ከ1868 እስከ 1966—ባህሩ ዘውዴ
አጼ ቴዎድሮስ—አለቃ ዘነበ
የኢትዮጲያ ታሪክ በአስራስድስተኛው ክፍለ ዘመን—ይልማ ደሬሳ
አፄ ቴዎድሮስ እና የኢትዮጵያ አንድነት
አፄ ዮሐንስ እና የኢትዮጵያ አንድነት
አፄ ምኒልክ እና የኢትዮጵያ አንድነት―ተክለፃድቅ መኩሪያ
የኢትዮጲያና የኢጣሊያ ጦርነት ፓውሎስ ኞኞ
ሕይወቴና የኢትዮጵያ እርምጃ―ቀዳማዊ ሃይለስላሴ
የአደዋ ጦርነትና የአፄ ምኒሊክ አነሳስ―(ተርጓሚ ዳኘው ወልደ ስላሴ)
አጤ ምኒሊክ ነጋድራስ ገብረህይወት ባይከዳኝ
ያ ትውልድ(The Generation―3 vols.)―ክፍሉ ታደሰ
የኮሎኔል መንግስቱ ኃይለማርያም ትዝታዎች―ገነት አየለ አንበሴ
Tower in the Sky―ህይወት ተፈራ
የትውልድ እልቂት(To kill a generation)―ባቢሌ ቶላ
የአባ ባህሪይ ድርሰቶች—(ትርጉም ጌታቸው ሃይሌ)
ተራሮችን ያምቀጠቀጠ ትውልድ(ቅፆች)
ነበር―ገስጥ ተጫኔ
ጄኔራሎቹ
አሰብ የማን ናት?
አጤ ምኒልክ―ጳውሎስ ኞኞ
የታሪክ ማስታወሻ―ደጃዝማች ከበደ ተሰማ
ትዝታ―ሃዲስ አለማየሁ
ጥንታዊ የኢትዮጵያ ታሪክ―መሪራስ አማን በላይ
ዝክረ ነገር―ማህተመስላሴ ወልደመስቀል
ቄሳርና አብዮት―ተስፋዬ ዲንቃ
ትቤ አክሱም መኑ አንተ―አስረስ የኔሰው
A History of Modern Ethiopia,1855 -1974―Bahru Zewde
Church and State in Ethiopia―Tadesse Tamrat
Ancient and Medieval History of Ethiopia―Sergew
Hableselassie
※※※ስነግጥም(16)
እሳት ወይ አበባ―ፀጋዬ ገብረመድህን
የባለቅኔ ምህላ―ሙሉጌታ ተስፋዬ
የቅኔ አዝመራ―ከበደ ሚካኤል
እንጉርጉሮ―መስፍን ወልደማርያም
የብርሃን ፍቅር―ደበበ ሰይፉ
ልጅነት—ሰለሞን ደሬሳ
የግጥም ጉባኤ—መንግስቱ ለማ
ኗሪ አልባ ጎጆዎች—በእውቀቱ ስዩም
አፈር ያነሳ ስጋ—ሰይፉ መታፈሪያ
ፍንዳታ—ኅይሉ ገብረ ዮሐንስ(ገሞራው)
መንገድ ስጡኝ ሰፊ—ገብረክርስቶስ ደስታ
እስቲ ተጠየቁ—ዮሐንስ አድማሱ
ትንቢተ ሼህ ሁሴን ጅብሪል―ቦጋለ ተፈሪ በዙ
በረከተ መርገም―ሃይሉ ዮሐንስ(ገሞራው)
ባሻ አሸብር በአሜሪካ―መንግስቱ ለማ
ከበደች ተክለአብ―የት ነው
ሻምበል አፈወርቅ ዮሃንስ―ስሜታዊ ግጥሞች
※※※ፖለቲካዊ እሳቤ(5)
መንግስት እና የህዝብ አስተዳደር―ገብረሕይወት ባይከዳኝ
ኢትዮጵያ ምን አይነት አስተዳደር
ያስፈልጋታል―ሃዲስ አለማየሁ
ኢትዮጵያ ከየት ወደየት―መስፍን ወልደማርያም
ነፃ ያልወጡ ነፃ አውጪዎች―አንዳርጋቸው ፅጌ
የነፃነት ጎህ ሲቀድ―ብርሃኑ ነጋ
መክሸፍ እንደ ኢትዮጲያ ታሪክ―መስፍን ወልደማርያም
※※※ወግ(3)
የቡና ቤት ስእሎች―መስፍን ሃብተማርያም
እንጨዋወት―ኤፍሬም እንዳለ
እግረ መንገድ―ስብሃት ገብረእግዚአብሔር
※※※የሕይወት ታሪክ(5)
ማስታወሻ―ስብሐት ገብረእግዚአብሔር
ኦቶባዮግራፊ (የሕይወቴ ታሪክ)―ተክለሃዋርያት ተክለማሪያም
መጽሐፈ ትዝታ - ዘአለቃ ለማ ኃይሉ ወልደ ታሪክ―መንግስቱ ለማ
ደማሙ ብዕረኛ―መንግስቱ ለማ
ሰምና ወርቁ ተሰማ እሸቴ―ይድነቃቸው ተሰማ
ቀኝ ጌታ ዩፍታሄ ንጉሴ―ዮሐንስ አድማሱ
ቀዳማዊ ሃይለስላሴ―መርስኤ ሃዘን ወልደ ቂርቆስ
በአሉ ግርማ ህይወቱና ስራዎቹ―እንዳለጌታ ከበደ
※※※ተረት(3)
ተረት ተረት የመሰረት―ሃዲስ አለማየሁ
አለቃ ገብረሐና እና አስቂኝ ቀልዶቻቸው―አረፈአይኔ ሃጎስ
እንቅልፍ ለምኔ―ማህተመ ስላሴ ወልደመስቀል
※※※ስነልቡና(2)
ወዳጄ ልቤ―ብላቴንጌታ ህሩይ ወልደስላሴ
ለልጅ ምክር ላባት መታሰቢያ―ኅሩይ ወልደስላሴ
※※※ትርጉም(25)
የራሴላስ መስፍን ኢትዮጵያ ታሪክ―(ትርጉም ሲራክ ህሩይ ወልደስላሴ)
አንድ ሺህ አንድ ሌሊት―(ትርጉም ለማ በላይነህ)
ታቦተ ጽዮንን ፍለጋ
እሪ በይ ሃገሬ―(ትርጉም አማረ ማሞ)
አፍንጮ/ፒኖኪዮ―(ትርጉም ለማ ፈይሳ)
ላፎንቴን―(ትርጉም ለማ ፈይሳ)
ወንጀልና ቅጣት―(ትርጉም ካሳ ገብረሕይወት)
ታራስ ቡልባ―(ትርጉም በካፋ ሃይለእየሱስ)
እንደ ሰው በምድር እንደ አሳ በባህር―(ትርጉም በካፋ ሃይለእየሱስ)
የተራራው ምርኮኞች
ዋናው ተቆጣጣሪ―አሰፋ ገብረማርያም ተሰማ
የአና ማስታወሻ―(ትርጉም አዶኒስ)
ብርቅርቅታ―(ትርጉም
ጠብታ ማር―(ትርጉም ባሴ ሃብቴ)
ጣዝማ ማር―(ትርጉም ደጀኔ ጥላሁን)
እናት―ግእዛን የማነ
የሁለት ከተሞች ወግ፣መከረኞቹ፣እምዩ―ሳህለሥላሴ ብርሃነማርያም
ምፅአተ እስራኤል―ማሞ ውድነህ
የውበት ወጥመድ፣ህሊና ሲታወር፣ምንዱባን―ዮሃንስ ገብረፃድቅ
ሳቤላ―ሃይለስላሴ መኃሪ
ካፒታል ቅፅ ፩
ነገም ሌላ ቀን ነው―ነብይ መኮንን
መልክዐ ኡመር―(ትርጉም ተስፋዬ ገሰሰ)
ያንገት ጌጡ―(ትርጉም አውግቸው ተረፈ)
እፎይታ―(ትርጉም ተሾመ ዳምጠው)
ካፖርቱ፣ሽማግሌውና ባህሩ፣የመጨረሻዋ ቅጠል ፣የቬ
★ ኢትዮጵያን በሃይማኖት በፍልስፍና በህግ በግብረገብ በስነልቡና በፖለቲካዊ
እና ማህበራዊ እሳቤ የቀረፁ መፅሀፍት
★ መፅሀፍቱ በከፊል በግለሰብ ደረጃ የአስተሳሰብ ለውጥ ሲያመጡ የተቀሩት
እንደ ሃገር ተፅእኖ አሳርፈዋል፤ህዝብንና መንግስትን በየፈርጁ ቀይረዋል
★ ብዙዎቹ ለበጎ አላማ ሲያነሳሱ ጥቂቶች እኩይ ተፅእኖ ነበራቸው
★ ብዙዎቹ ፈር ቀዳጅና በየዘርፋቸው አንጋፋ የሚባሉ ስራዎች ናቸው
★ ከትውልድ ትውልድ እየተሸጋገሩ ብዙዎች ጋር በመድረስ ዘመን አይሽሬ
ሆነዋል
※※※ሃይማኖታዊ(9)
መፅሀፍ ቅዱስ―(ትርጉም አብርሃም ሩሚ 1840)
መጫፈ ቁልቁሉ―(ትርጉም ኦነሲሞስ ነሲብ)
የትግርኛ መፅሀፍ ቅዱስ―(ትርጉም አለቃ ተወልደመድህን ገብሩ እና
ተወልደብርሃን ገብረመድህን)
ቅዱስ ቁርአን―(ትርጉም እጨጌ እንባቆም)
ክብረ ነገሥት
ስንክሳር
አቡሻክር
ሃይማኖተ አበው
ፍትሐ ነገስት
※※※ልብወለድ(29)
ፍቅር እስከ መቃብር―ሃዲስ አለማየሁ
አልወለድም―አቤ ጉበኛ
የጉለሌው ሰካራም―ተመስገን ገብሬ
ማህሌት―አዳም ረታ
አስኮ ጌታሁን―ጃርሶ ኪሩቤል
መስከረም―ታደሰ ሊበን
ኦሮማይ―በአሉ ግርማ
ሌቱም አይነጋልኝ―ስብሐት ገብረእግዚአብሔር
አደፍርስ―ዳኛቸው ወርቁ
ከአድማስ ባሻገር―በአሉ ግርማ
ግራጫ ቃጭሎች―አዳም ረታ
ከቡስካ በስተጀርባ―ፍቅረማርቆስ ደስታ
ታሪክና ምሳሌ―ከበደ ሚካኤል
ሰመመን―ሲሳይ ንጉሱ
ቆንጆዎቹ―ሰርቅ ዳ
የስንብት ቀለማት―አዳም ረታ
እፍታ(አምስት ቅጾች)―አርታኢ ተስፋዬ ገብረአብ
እንደወጣች ቀረች―አሰፋ ገብረማርያም
ፀሐይ መስፍን―መኮንን እንዳልካቸው
አንድ ለናቱ―አቤ ጉበኛ
የቡርቃ ዝምታ―ተስፋዬ ገብረአብ
የታንጉት ሚስጥር―ብርሃኑ ዘርይሁን
ጉንጉን―ኃይለመለኮት መዋእል
አምስት ስድስት ሰባት―ስብሐት ገብረእግዚአብሔር
ሰንሰለት―ሻምበል ፈቃደ ዮሃንስ
አባኮስትር―አበራ ጀንበሬ
አሉላአባ ነጋ―ማሞ ውድነህ
ዳር እስከ ዳር―አንዳርጌ መስፍን
ዶሰኛው―የሺጥላ ኮከብ
ጦቢያ―አፈወርቅ ገብረየሱስ
አብዮት―ብርሃኑ ዘርይሁን
ልጅነት ተመልሶ አይመጣም―በእምነት ገብረማርያም
The Thirteenth Sun―Danyachew Worku
The Case of the Socialist Witchdoctor―Hama Tuma
Notes from the Hynea's Belly―Nega Mezlekia
※※※ትያትር(11)
አፋጀሽኝ―ዮፍታሄ ንጉሴ
ቴዎድሮስ―ግርማቸው ተክለሃዋርያት
ሀሁ በስድስት ወር―ፀጋዬ ገብረመድህን
እናት አለም ጠኑ―ፀጋዬ ገብረመድህን
ጴጥሮስ ያቺን ሰአት―ፀጋዬ ገብረመድህን
ባልቻ አባ ነፍሶ―ብርሃኑ ዘርይሁን
አልቃሽና ዘፋኝ―ፍስሐ በላይ ይማም
ውበትን ፍለጋ―ጌትነት እንየው
ጠልፎ በኪሴ―መንግስቱ ለማ
ያላቻ ጋብቻ―መንግስቱ ለማ
Oda Oka Oracle―Tsegaye Gebremedhin
※※※ታሪክ(25)
የአህመድ ግራኝ ወረራ―ተክለፃድቅ መኩሪያ
የኤርትራ ጉዳይ―ዘውዴ ረታ
የኢትዮጵያ ታሪክ ከ1868 እስከ 1966—ባህሩ ዘውዴ
አጼ ቴዎድሮስ—አለቃ ዘነበ
የኢትዮጲያ ታሪክ በአስራስድስተኛው ክፍለ ዘመን—ይልማ ደሬሳ
አፄ ቴዎድሮስ እና የኢትዮጵያ አንድነት
አፄ ዮሐንስ እና የኢትዮጵያ አንድነት
አፄ ምኒልክ እና የኢትዮጵያ አንድነት―ተክለፃድቅ መኩሪያ
የኢትዮጲያና የኢጣሊያ ጦርነት ፓውሎስ ኞኞ
ሕይወቴና የኢትዮጵያ እርምጃ―ቀዳማዊ ሃይለስላሴ
የአደዋ ጦርነትና የአፄ ምኒሊክ አነሳስ―(ተርጓሚ ዳኘው ወልደ ስላሴ)
አጤ ምኒሊክ ነጋድራስ ገብረህይወት ባይከዳኝ
ያ ትውልድ(The Generation―3 vols.)―ክፍሉ ታደሰ
የኮሎኔል መንግስቱ ኃይለማርያም ትዝታዎች―ገነት አየለ አንበሴ
Tower in the Sky―ህይወት ተፈራ
የትውልድ እልቂት(To kill a generation)―ባቢሌ ቶላ
የአባ ባህሪይ ድርሰቶች—(ትርጉም ጌታቸው ሃይሌ)
ተራሮችን ያምቀጠቀጠ ትውልድ(ቅፆች)
ነበር―ገስጥ ተጫኔ
ጄኔራሎቹ
አሰብ የማን ናት?
አጤ ምኒልክ―ጳውሎስ ኞኞ
የታሪክ ማስታወሻ―ደጃዝማች ከበደ ተሰማ
ትዝታ―ሃዲስ አለማየሁ
ጥንታዊ የኢትዮጵያ ታሪክ―መሪራስ አማን በላይ
ዝክረ ነገር―ማህተመስላሴ ወልደመስቀል
ቄሳርና አብዮት―ተስፋዬ ዲንቃ
ትቤ አክሱም መኑ አንተ―አስረስ የኔሰው
A History of Modern Ethiopia,1855 -1974―Bahru Zewde
Church and State in Ethiopia―Tadesse Tamrat
Ancient and Medieval History of Ethiopia―Sergew
Hableselassie
※※※ስነግጥም(16)
እሳት ወይ አበባ―ፀጋዬ ገብረመድህን
የባለቅኔ ምህላ―ሙሉጌታ ተስፋዬ
የቅኔ አዝመራ―ከበደ ሚካኤል
እንጉርጉሮ―መስፍን ወልደማርያም
የብርሃን ፍቅር―ደበበ ሰይፉ
ልጅነት—ሰለሞን ደሬሳ
የግጥም ጉባኤ—መንግስቱ ለማ
ኗሪ አልባ ጎጆዎች—በእውቀቱ ስዩም
አፈር ያነሳ ስጋ—ሰይፉ መታፈሪያ
ፍንዳታ—ኅይሉ ገብረ ዮሐንስ(ገሞራው)
መንገድ ስጡኝ ሰፊ—ገብረክርስቶስ ደስታ
እስቲ ተጠየቁ—ዮሐንስ አድማሱ
ትንቢተ ሼህ ሁሴን ጅብሪል―ቦጋለ ተፈሪ በዙ
በረከተ መርገም―ሃይሉ ዮሐንስ(ገሞራው)
ባሻ አሸብር በአሜሪካ―መንግስቱ ለማ
ከበደች ተክለአብ―የት ነው
ሻምበል አፈወርቅ ዮሃንስ―ስሜታዊ ግጥሞች
※※※ፖለቲካዊ እሳቤ(5)
መንግስት እና የህዝብ አስተዳደር―ገብረሕይወት ባይከዳኝ
ኢትዮጵያ ምን አይነት አስተዳደር
ያስፈልጋታል―ሃዲስ አለማየሁ
ኢትዮጵያ ከየት ወደየት―መስፍን ወልደማርያም
ነፃ ያልወጡ ነፃ አውጪዎች―አንዳርጋቸው ፅጌ
የነፃነት ጎህ ሲቀድ―ብርሃኑ ነጋ
መክሸፍ እንደ ኢትዮጲያ ታሪክ―መስፍን ወልደማርያም
※※※ወግ(3)
የቡና ቤት ስእሎች―መስፍን ሃብተማርያም
እንጨዋወት―ኤፍሬም እንዳለ
እግረ መንገድ―ስብሃት ገብረእግዚአብሔር
※※※የሕይወት ታሪክ(5)
ማስታወሻ―ስብሐት ገብረእግዚአብሔር
ኦቶባዮግራፊ (የሕይወቴ ታሪክ)―ተክለሃዋርያት ተክለማሪያም
መጽሐፈ ትዝታ - ዘአለቃ ለማ ኃይሉ ወልደ ታሪክ―መንግስቱ ለማ
ደማሙ ብዕረኛ―መንግስቱ ለማ
ሰምና ወርቁ ተሰማ እሸቴ―ይድነቃቸው ተሰማ
ቀኝ ጌታ ዩፍታሄ ንጉሴ―ዮሐንስ አድማሱ
ቀዳማዊ ሃይለስላሴ―መርስኤ ሃዘን ወልደ ቂርቆስ
በአሉ ግርማ ህይወቱና ስራዎቹ―እንዳለጌታ ከበደ
※※※ተረት(3)
ተረት ተረት የመሰረት―ሃዲስ አለማየሁ
አለቃ ገብረሐና እና አስቂኝ ቀልዶቻቸው―አረፈአይኔ ሃጎስ
እንቅልፍ ለምኔ―ማህተመ ስላሴ ወልደመስቀል
※※※ስነልቡና(2)
ወዳጄ ልቤ―ብላቴንጌታ ህሩይ ወልደስላሴ
ለልጅ ምክር ላባት መታሰቢያ―ኅሩይ ወልደስላሴ
※※※ትርጉም(25)
የራሴላስ መስፍን ኢትዮጵያ ታሪክ―(ትርጉም ሲራክ ህሩይ ወልደስላሴ)
አንድ ሺህ አንድ ሌሊት―(ትርጉም ለማ በላይነህ)
ታቦተ ጽዮንን ፍለጋ
እሪ በይ ሃገሬ―(ትርጉም አማረ ማሞ)
አፍንጮ/ፒኖኪዮ―(ትርጉም ለማ ፈይሳ)
ላፎንቴን―(ትርጉም ለማ ፈይሳ)
ወንጀልና ቅጣት―(ትርጉም ካሳ ገብረሕይወት)
ታራስ ቡልባ―(ትርጉም በካፋ ሃይለእየሱስ)
እንደ ሰው በምድር እንደ አሳ በባህር―(ትርጉም በካፋ ሃይለእየሱስ)
የተራራው ምርኮኞች
ዋናው ተቆጣጣሪ―አሰፋ ገብረማርያም ተሰማ
የአና ማስታወሻ―(ትርጉም አዶኒስ)
ብርቅርቅታ―(ትርጉም
ጠብታ ማር―(ትርጉም ባሴ ሃብቴ)
ጣዝማ ማር―(ትርጉም ደጀኔ ጥላሁን)
እናት―ግእዛን የማነ
የሁለት ከተሞች ወግ፣መከረኞቹ፣እምዩ―ሳህለሥላሴ ብርሃነማርያም
ምፅአተ እስራኤል―ማሞ ውድነህ
የውበት ወጥመድ፣ህሊና ሲታወር፣ምንዱባን―ዮሃንስ ገብረፃድቅ
ሳቤላ―ሃይለስላሴ መኃሪ
ካፒታል ቅፅ ፩
ነገም ሌላ ቀን ነው―ነብይ መኮንን
መልክዐ ኡመር―(ትርጉም ተስፋዬ ገሰሰ)
ያንገት ጌጡ―(ትርጉም አውግቸው ተረፈ)
እፎይታ―(ትርጉም ተሾመ ዳምጠው)
ካፖርቱ፣ሽማግሌውና ባህሩ፣የመጨረሻዋ ቅጠል ፣የቬ
ኒሱ ነጋዴ፣ንጉስ
ሊር―መስፍን አለማየሁ
ሮሜዮና ዡልየት―(ትርጉም ከበደ ሚካኤል)
ሃምሌት፣ማክቤዝ፣ኦቴሎ―(ትርጉም ፀጋዬ ገብረመድህን)
※※※ቋንቋ እና ትምህርት(18)
የከፍተኛ ትምህርት ዘይቤ―እጓለ ገብረዮሐንስ
የአማርኛ ሰዋሰው―ባዬ ይማም
ያማርኛ መዝገበ ቃላት―የኢትዮጵያ ቋንቋዎች አካዳሚ
ያማርኛ ፈሊጦች―አምሳሉ አክሊሉ ዳኛቸው ወርቁ
የስነጽሑፍ መሰረታውያን―ዘሪሁን አስፋው
ቴዎድሮስ ገብሬ―በይነ-ዲሲፕሊናዊ የሥነጽሑፍ ንባብ
ምሁሩ―ዶ/ር አለማየሁ ረዳ
የሻው ተሰማ―ልሳነ ብዕር ከመ ልሳነ ሰብዕ
መፅሀፈ ሰዋሰው ወግስ ወመዝገበቃላት―አለቃ ኪዳነወልድ ክፍሌ
ዐዲስ ያማርኛ መ ቃላት―ደስታ ተክለወልድ
ከሳቴብርሃን ተሰማ መ ቃላት―ተሰማ ሀብተሚካኤል ግፅው
ያማርኛ ሰዋሰው―መርስኤ ሃዘን ወልደ ቂዮርቂስ
የድርሰት አብነት―አለማየሁ ሞገስ
የአማርኛ የቤተክርስቲያን መዝገበ ቃላት―ስርግው ሃብለስላሴ
ስእላዊ መዝገበ ቃላት
የሳይንስና ቴክኖሎጂ መዝገበ ቃላት
የመፅሀፍ ቅዱስ መዝገበ ቃላት
የማርክሲዝም ሌኒኒዝም መዝገበ ቃላት
የግዕዝ ቅኔያት ንባብና ትርጓሜ
English Amharic Dictionary―Amsalu Aklilu and J. P. Mosback
Amharic English Dictionary―Amsalu Aklilu
※※※ፍልስፍና(10)
መፅሀፈ ጨዋታ ስጋዊ ወመንፈሳዊ―አለቃ ዘነብ ኢትዮጵያዊ
አንጋረ ፈላስፋ―ሞገስ እቁበ ጊዮርጊስ
የፍልስፍና ትምህርት―የማነ ገብረማርያም
Gorfu contra Nietzsche―ገብረእየሱስ ጎርፉ
ሐተታ ዘርዐ ያዕቆብ ወሐተታ ወልደ ሕይወት
ጃፓን እንደምን ሰለጠነች―ከበደ ሚካኤል
የካም መታሰቢያ―አስረስ የኔሰው
አውቀን እንታረም―ዐቢይ አበበ
ባህረ ሃሳብ―ጌታቸው ሃይሌ
ደቂቀ እስጢፋኖስ―ጌታቸው ሃይሌ
ምንጭ: ቴዎድሮስ ሸዋንግዛው
@Bookfor
ሊር―መስፍን አለማየሁ
ሮሜዮና ዡልየት―(ትርጉም ከበደ ሚካኤል)
ሃምሌት፣ማክቤዝ፣ኦቴሎ―(ትርጉም ፀጋዬ ገብረመድህን)
※※※ቋንቋ እና ትምህርት(18)
የከፍተኛ ትምህርት ዘይቤ―እጓለ ገብረዮሐንስ
የአማርኛ ሰዋሰው―ባዬ ይማም
ያማርኛ መዝገበ ቃላት―የኢትዮጵያ ቋንቋዎች አካዳሚ
ያማርኛ ፈሊጦች―አምሳሉ አክሊሉ ዳኛቸው ወርቁ
የስነጽሑፍ መሰረታውያን―ዘሪሁን አስፋው
ቴዎድሮስ ገብሬ―በይነ-ዲሲፕሊናዊ የሥነጽሑፍ ንባብ
ምሁሩ―ዶ/ር አለማየሁ ረዳ
የሻው ተሰማ―ልሳነ ብዕር ከመ ልሳነ ሰብዕ
መፅሀፈ ሰዋሰው ወግስ ወመዝገበቃላት―አለቃ ኪዳነወልድ ክፍሌ
ዐዲስ ያማርኛ መ ቃላት―ደስታ ተክለወልድ
ከሳቴብርሃን ተሰማ መ ቃላት―ተሰማ ሀብተሚካኤል ግፅው
ያማርኛ ሰዋሰው―መርስኤ ሃዘን ወልደ ቂዮርቂስ
የድርሰት አብነት―አለማየሁ ሞገስ
የአማርኛ የቤተክርስቲያን መዝገበ ቃላት―ስርግው ሃብለስላሴ
ስእላዊ መዝገበ ቃላት
የሳይንስና ቴክኖሎጂ መዝገበ ቃላት
የመፅሀፍ ቅዱስ መዝገበ ቃላት
የማርክሲዝም ሌኒኒዝም መዝገበ ቃላት
የግዕዝ ቅኔያት ንባብና ትርጓሜ
English Amharic Dictionary―Amsalu Aklilu and J. P. Mosback
Amharic English Dictionary―Amsalu Aklilu
※※※ፍልስፍና(10)
መፅሀፈ ጨዋታ ስጋዊ ወመንፈሳዊ―አለቃ ዘነብ ኢትዮጵያዊ
አንጋረ ፈላስፋ―ሞገስ እቁበ ጊዮርጊስ
የፍልስፍና ትምህርት―የማነ ገብረማርያም
Gorfu contra Nietzsche―ገብረእየሱስ ጎርፉ
ሐተታ ዘርዐ ያዕቆብ ወሐተታ ወልደ ሕይወት
ጃፓን እንደምን ሰለጠነች―ከበደ ሚካኤል
የካም መታሰቢያ―አስረስ የኔሰው
አውቀን እንታረም―ዐቢይ አበበ
ባህረ ሃሳብ―ጌታቸው ሃይሌ
ደቂቀ እስጢፋኖስ―ጌታቸው ሃይሌ
ምንጭ: ቴዎድሮስ ሸዋንግዛው
@Bookfor
በቂም የጠለሹ............... ፤
ከአንድነት ሸሽተው ለሆዳቸው ሲያድሩ
ትግስት ጣራን አልፎ ደም ሆነ ሀገሩ
ብሔር ገደብ አልፎ ግፍ ሲፈስ ባገሩ
ዘር ከሰውነት በልጦ .................
ሀገር አለቀሰች እልፎች ተቀበሩ።
አምላኬ ሆይ የቃል ኪዳን ምድርህን አንተ ጠብቃት ፣ ለህቦቿ ቅን ልቦናን እና
የጣልነውን የሰውነት መንፈስ መልስልን፡፡
መባ(ጥቁር ሰው)
@Bookfor
ከአንድነት ሸሽተው ለሆዳቸው ሲያድሩ
ትግስት ጣራን አልፎ ደም ሆነ ሀገሩ
ብሔር ገደብ አልፎ ግፍ ሲፈስ ባገሩ
ዘር ከሰውነት በልጦ .................
ሀገር አለቀሰች እልፎች ተቀበሩ።
አምላኬ ሆይ የቃል ኪዳን ምድርህን አንተ ጠብቃት ፣ ለህቦቿ ቅን ልቦናን እና
የጣልነውን የሰውነት መንፈስ መልስልን፡፡
መባ(ጥቁር ሰው)
@Bookfor
# ረመዳን ከሪም
.
.
.
እንኳን ለታላቁ ለረመዳን ፆም በሰላም አደረሳችሁ ለእዝበ ሙስሊም በሙሉ
ፆሙ ለኢትዮጵያ፦ ሰላም ፣ ፍቅር ፣ መከባበርን ፣ መተሳሰብን ... ወዘ ተረፈ
ያድርግልን ዘንድ እመኛለሁ!!
@Bookfor
.
.
.
እንኳን ለታላቁ ለረመዳን ፆም በሰላም አደረሳችሁ ለእዝበ ሙስሊም በሙሉ
ፆሙ ለኢትዮጵያ፦ ሰላም ፣ ፍቅር ፣ መከባበርን ፣ መተሳሰብን ... ወዘ ተረፈ
ያድርግልን ዘንድ እመኛለሁ!!
@Bookfor