Bonga University
6.87K subscribers
4.52K photos
30 videos
5 files
83 links
Together We Can
Download Telegram
10ኛው የመንግስት ከፍተኛ ት/ት ተቋማት የስፖርት ፌስቲቫል በደማቅ ሁኔታ ተጀመረ።

**ጥር 17/2018 ዓ.ም.*

ቦንጋ ዩኒቨርሲቲን ጨምሮ ሁሉም የመንግስት ከፍተኛ የት/ት ተቋማት የሚሳተፉበት ሀገር ዓቀፉ የስፖርት ውድድር ዛሬ በጅማ ዩኒቨርሲቲ በደማቅ ሁኔታ ተጀመሯል።

የቦንጋ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት ደገላ ኤሬገኖ (ዶ/ር) ጨምሮ የሌሎች ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንቶችም በመክፈቻው ስነ-ስርዓት ላይ ታድመዋል።

ቦንጋ ዩኒቨርሲቲ 80 ስፖርተኞችን ለ10 የውድድር ዓይነት ለመፎካከር በስፍራው ይገኛል።

በቀጣይም ዩኒቨርሲቲያችን የሚወዳደርባቸውን ስፖርት አይነቶች እየተከታተልን የምናሳውቅ ይሆናል።

በድጋሚ ድል ለቦንጋ ዩኒቨርሲቲ ስፖርት ልዑክ እንዲሆን እንመኛለን።

በጋራ እንችላለን!
🙏🙏ብራቮ ቦንጋ ዩኒቨርሲቲ!!!!🙏🙏
****
በ10ኛው የመንግስት ከፍተኛ ት/ት ተቋማት የስፖርት ውድድር ላይ እየተካፈለ የሚገኘው ቦንጋ ዩኒቨርሲቲ ዛሬ ድል ቀንቶታል።
የቦንጋ ዩኒቨርሲቲ የእግር ኳስ ቡድን የቀብሪደሀር አቻውን ገጥሞ 2 ለ 1 በሆነ ውጤት በማሸነፍ በጣፈጭ ድል ጉዞውን ጀምሯል።
ለመላው የቦንጋ ዩኒቨርሲቲ ማህበረሰብ በሙሉ እንኳን ደስ አለን።
በድጋሚ ድል ለስፖርት ልዑካችን!
በጋራ እንችላለን!
በጋራ እንችላለን!
የቦንጋ ዩነቨርሲቲ የስፖርት ልዑክ ዛሬም ድል ቀንቶታል።
🏐🏐🏐🏐🏐🏐
በጅማ ዩኒቨርሲቲ አስተናጋጅነት እየተከናወነ በሚገኘው በ10ኛው የመንግስት ከፍተኛ ት/ት ተቋማት የስፖርት ፌስትቫል ላይ እየተሳተፈ የሚገኘው ቦንጋ ዩኒቨርሲቲ በርካታ ድሎችን አሳክቷል።
በኮርቦ ባህላዊ ስፖርት ለፍፃሜ በመድረስ የሜዳሊያ ሰንጠረዥ ውስጥ ለመግባት የቻለ ሲሆን በውጤቱም የብር ሜዳሊያ ማሳካት ተችሏል።
በተመሳሳይ ዜና የሴቶች የመረብ ኳስ ቡድን የሰላሌ አቻውን ገጥሞ 5 ለ 4 በሆነ ውጤት በማሸነፍ ወደ ምርጥ አራት ቡድን ውስጥ በመግባት ለዋንጫ የሚያደርገውን ግስጋሴ አጠናክሮ ቀጥሏል።
በተጨማሪም የወንዶች የቅርጫት ኳስ ቡድንም ምርጥ ስምንት ቡድን ውስጥ በመግባት ሌላ ስኬት አስመዝግቧል።
በዚህም ለመላው የዩኒቨርሲቲያችን ማህበረሰብ በሙሉ እንኳን ደስ አላችሁ እንኳን ደስ አለን ማለት እንፈልጋለን።
አሁንም ድል ለስፖርት ልዑካችን እንመኛለን!!🏀🏀
በጋራ እንችላለን!
ቦንጋ ዩኒቨርሲቲ በቦንጋ እና አካባቢው ለሚገኙ የ2ኛ ደረጃ ት/ቤት የት/ት ባለሙያዎች እና አመራሮች ስልጠና እየሰጠ ነው ፡፡
*****ጥር 27/2018 ዓ.ም*****
ለቦንጋ ከተማ እና ለቢሻው ወ/ዮሀንስ ጉድኝት የት/ት ባለሙያዎች እና አመራሮች የተዘጋጀው የአቅም ግንባታ ስልጠና በቦንጋ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት ደገላ ኤርገኖ (ዶ/ር) የመክፈቻ ንግግር ነበር የተጀመረው ፡፡
በንግግራቸውም በተለይ ቦንጋ ዩኒቨርሲቲ በት/ት ስብራቱ ላይ ያለውን ከፍተኛ የሆነ ክፍተት ለመሙላት ለሚያደርገው ትረት እንደዚህ አይነት የአቅም ግንባታ ስልጠናዎች በተለይ የት/ት ሴክተሩን በቅርበት ለሚመሩ አካላት መስጠቱ ፋይዳው የጎላ እንደሆነ አብራርተዋል፡፡
የማህበረሰብ አገልግሎታችን አሁን ላይ ጉድኝት በሚል የተቀየረ በመሆኑ በመስጠትም በመቀበልም መርህ በጋራ ተናበን የምንሰራበት መሆኑን እና ተመጋጋቢ የሆኑ ተግባራትን እንደመስራታችን ለጋራ ውጤት በጋራ መቆም እና ሀላፊነትን በመወጣት ጎልቶ ለመታየት የምንችለውን ሁሉ እናደርጋለን በማለት የስልጠናውን መጀመር በይፋ አብስረዋል፡፡
ስልጠናው ዛሬን ጨምሮ ለሁለት ቀን የሚሰጥ ሲሆን በተመረጡ ርዕሰ-ጉዳዮች ላይ ማለትም - ውጤታማ የስነ-ማስተማር ስነ - ዘዴ /Implementing Effective Teaching Method / ፣ የተማሪዎች ባህሪ ዙርያ / Students Behavior/፣ አካቶ ት/ት / Inclusive Education/ እና የቴክኖሎጂ እውቀት ለመማር ማስተማር ያለው ፋይዳ /Digital Literacy/ ናቸው፡፡
ስልጠናውን የቦንጋ ዩኒቨርሲቲ የማህበረሰብ ጉድኝት እና ቴክኖሎጂ ስርጸት ዳይሬክቶሬት በዋናነት እያስተባበረ ሲሆን በቀጣይም ተመሳሳይ የአቅም ግንባታ ስልጠናዎች እንደሚቀጥሉ ዳይሬክተሩ መ/ር አለማየሁ ወ/ማርያም ገልጸዋል፡፡
በጋራ እንችላለን!