4-3-3 ስፖርት በኢትዮጵያ
567K subscribers
103K photos
309 videos
3 files
3.55K links
ከእሁድ እስከ እሁድ ፈጣን የመረጃ ምንጭ!

➮የሃገር ቤት ትኩስ ትኩስ መረጃዎች
➮የአፍሪካ መረጃዎችን በሙሉ
➮የአውሮፓ ታላላቅ ሊጎች ሙሉ መረጃ
➮ቁጥራዊ መረጃዎች እና ዳሰሳዎች
➮ጨዋታዎችን በቀጥታ ከየስታዲየሙ

ለማስታወቂያ ስራ @Promotion_4_3_3_Bot

⓸-⓷-⓷ስፖርት በኢትዮጵያ| 2017
Buy ads: https://telega.io/c/SPORT_433ET
Download Telegram
ከእንግሊዟ ማንችስተር ከተማ የመጡ የማንችስተር ሲቲ ደጋፊዎች አዲስ አበባ በሚገኘው የተስፋ አዲስ የካንሰር ህሙማን ህፃናት ማዕከል በመገኘት ድጋፍን በዛሬው ዕለት አደርገዋል።

ለማዕከሉ በዓይነት እና በገንዘብ የ140ሺ ብር ልገሳን ያደርጉ ሲሆን ለወደፊትም የተለያዩ ድጋፎችን ሌሎች ደጋፊዎችን ጭምር በማስተባበር እንደሚያደርጉ ቃል ገብተዋል።

ማንችስተር ሲቲ 💪

@Bisrat_Sport_433et @Bisrat_Sport_433et
የአውሮፓ ሻምፒየንስ ሊግ ንጉሶቹ ሪያል ማድሪዶች ዘንድሮ መጥፎ ሚባል ጊዜ እያሳለፉ ከሚገኙት ባየር ሙኒኮች ጋር በሻምፒየን ሊጉ ግማሽ ፍፃሜ ተፋጠዋል።

ማን የሚያሸንፍ ይመስላችኋል?

እስቲ ጨዋታውን ከሄኒከን ጋር አብረን የሚሆነውን እናያለን
ሊቨርፑል መሀመድ ሳላህን ለማቆየት እየሰራ ነው!

የመርሲሳይዱ ክለብ ሊቨርፑል አመራሮች ግብጻዊው የፊት መስመር ተጨዋች መሃመድ ሳላህ በክለቡ ይቆያል ብለው እንደሚጠብቁ ተናግረዋል፡፡

በቅርቡ ከኔዘርላንዳዊው አሰልጣኝ አርኔ ስሎት ጋር ከስምምነት ላይ የደረሰው ሊቨርፑል የፊት መስመር ተጨዋቹ መሀመድ ሳላህ በቀጣይ በክለቡ ይቀጥላል ብለው እንደሚጠብቁ ተናግረዋል፡፡

በዚህም አዲስ ከሚቀጠሩት አሰልጣኝ አርኔ ስሎት ጋር የሚቀጥለውን የውድድር አመት ሳላህ እንዲያሳልፍ የክለቡ ሀለፊዎች ምኞት እንደሆነ ተገልጿል፡፡

መሀመድ ሳላህ በሚቀጥለው አመት ውሉ መጠናቀቁን ተከትሎ ከክለቡ ጋር ስለመለያየቱ እስካሁን ያለው ነገር ባይኖርም ቢያንስ የሚቀጥለውን የውድድር አመት በሊቨርፑል እንደሚያሳልፍ ይጠበቃል፡፡

ባሳለፍነው ሳምንት መጨረሻ ላይ ሊቨርፑል ከዌስተሀም ዩናይትድ ጋር ነጥብ በተጋራበት ጨዋታ ከአሰልጣኝ የርገን ክሎፕ ጋር ከገባው አለመግባባት ጋር በተያያዘ ከክለቡ ሊለቅ ይችላል የሚሉ መላምቶች እንደነበሩ ይታወሳል፡፡

የመሀመድ ሳላህ፤ቨርጂል ቫንዳይክ እና ትሬንት አሌክሳንደር አርኖልድ ውል በ2025 መጠናቀቁን ተከትሎ እነዚህን ተጨዋቾች ለማቆየት ለአዲሱ የሊቨርፑል ስፖርቲንግ ዳይሬክተር ሪቻርድ ሂዩዝ የቤት ስራ እንደሆነ ተነግሯል፡፡[yigedeb abay]

@Bisrat_Sport_433et
@Bisrat_Sport_433et
በዚህ ሲዝን በሻምፒዮንስ ሊጉ ባደረጉት አሪፍ እንቅስቃሴ ትልቅ ሬቲንግ ያገኙ ግብ ጠባቂዎች ፡-

◉ 9.50 - አንድሪ ሉኒን vs ማንቸስተር ሲቲ (H)

◉ 8.78 - አንድሪ ሉኒን vs RB ሌፕዚግ (A)

◉ 8.45 - አንድሪ ሉኒን vs ብራጋ (H)

#UCL #FCBRMA

@Bisrat_Sport_433et @Bisrat_Sport_433et
የማንችስተር ዩናይትድ የአፕሪል ወር ምርጥ ተጫዋች እጩዎች

ሃሪ ማጓየር
ብሩኖ ፈርናንዴዝ
ጋርናቾ

@Bisrat_Sport_433et @Bisrat_Sport_433et
የሪያል ማድሪድ አሰላለፍ

04:00 | ባየር ሙኒክ ከ ሪያል ማድሪድ

@Bisrat_Sport_433et @Bisrat_Sport_433et
ቼልሲ በጆሴ ሞሪንሆ እየተመራ በቼልሲ በመጀመሪያ አመት የአሰልጣኝነት ጊዜያቸው ፕሪሚየር ሊጉን መብላታቸውን ያረጋገጡት ልክ በዛሬው ቀን ከ19 አመታት በፊት በ2005 ነበር 🤩

ቼልሲ በዛ አመት በ38 ጨዋታዎች 15 ጎሎችን ብቻ አስተናግዶ ነበር ሊጉን ያሸነፈው 😇

@Bisrat_Sport_433et
@Bisrat_Sport_433et
ኤርሊንግ ሃላንድ በዝነኛው የሞባይል ጌም ''Clash of Clans'' ላይ መካተት ችሏል ።

ሃላንድ ይሄንን ጌም ለአስር አመታት በላይ የተጫወተ ሲሆን በጌሙ ላይም የተካተተ የመጀመሪያው ሰው መሆን ችሏል ።

@Bisrat_Sport_433et
@Bisrat_Sport_433et
ሰላም ሰላም ውድ የ 4-3-3 ስፖርት በኢትዮጵያ ቤተሰቦች ዛሬ ደግሞ ለየት ባለሁኔታ ትኩረታችንን በሀገር ቤት ውስጥ በማድረግ ዞር ዞር እያልን የኢትዮጵያ ተሰፋኛ አካዳሚዮችን የምንቃኝበት ፕሮግራም እንጀምራለን

ዛሬ ለመግቢያ ያክል ወደ ሀዋሳ አቅንተን ፊላደልፊያን የእግርኳስ አካዳሚ የምንስቃኛችሁ ይሆናል አብራችሁን ትቆዩ ዘንድ ግብዧችን ነው።

@Bisrat_Sport_433et @Bisrat_Sport_433et
ፊላደልፊያ የእግርኳስ አካዳሚ ይባላል አካዳሚው መቀመጫውን ሀዋሳ በማድረግ ታላላቅ የወደፊት የብሔራዊ ቡድን ተሰፈኞችን ለማፍራት ተቋቁሞ የሚገኝ አካዳሚ ነው።

አካዳሚው በውስጡ በ 3 አየነት የዕድሜ ዕርከን ላይ የሚገኙ ተጫዋቾችን ለይቶ ያሰለጥናል አሁን ላይ በቡድኑ ውስጥ

ከ 10 ዓመት በታች 14 ታዳጊዎችን
ከ 13 ዓመት በታች 23 ታዳጊዎችን
ከ 15 ዓመት በታች 18 ታዳጊዎችን

በመያዝ በአጠቃላይ ከ 50 በላይ ታዳጊዎችን በመያዝ እያሰለጠን ይገኛል።

የአካዳሚው አላማ ዓላማ እና ህልም ያለውን ዜጋ ማብቃት ነው። እንዲሁም ስፖርት ለሰላም የሚለውን ለማረጋገጥ በህበረተሰቡ ዘንድ በጎ ተፅዕኖን መፍጠር በተጨማሪም ደግሞ ልጆች ያላቸውን የስራ ወዳድነት ባህሪ ታታሪነት ማስቀጠል ነው።

ተጫዋቾችን ለስኬት ማብቃት ብሎ በሀገራዊ እንዲሁም በአሁጉራዊ ውድድሮች ላይ ተሳታፊ መሆን የሚችል የሀገርን ስኳድ ከፍ ማድረግ የሚችል ተጫዋቾችን ለፍሬ ማብቃት ነው።

@Bisrat_Sport_433et @Bisrat_Sport_433et
ፊላደልፊያ እነዚህን አላማቸውን ወደ መሬት ለማውረድ የተመሠረተው እንደ ሀገራችን አቆጣጠር ባሳለፍነው ዓመት 2015 በወርሃ የካቲት 6 ላይ ነበር።

ይህም ድርጅት የተቋቋመው ለሀገር ስፖርት ማድግ መሠራት ያለበት ከታዳጊ ነው ብሎ በብዛት ሲናገር የምናውቀው አሰልጣኝ ጌዲዮን ተካ ነው።

ይህ አካዳሚ በሲዳማ ክልል ሀዋሳ ከተማ ውስጥ ህፃናት እና ታዳጊ ተጫዋቾችን ለማብቃት የቷቋቋመ የመጀመሪያው አካዳሚ መሆኑንም ከአካዳሚው ያናገርኳቸው ሰዎች ነገረውኛል።

አካዳሚው ምስረታውን ያደረገው በስፈር ወጣቶች አደራጅነት በተሰበሰቡ 45 ታዳጊዎች መሆኑን የአካዳሚው ታሪክ ይነገረናል።

ፕሮጀክቱ በሳምንት ሶስት ቀን የሚሰራ ሲሆን  1ኛ ሰኞ ድሪብል እና ፓስ 2ተኛ ሃሙስ ቴክኒክ እና ታክቲክ 3ተኛ ቅዳሜ ፊዚካል ማሳደጊያ ከድሪብል ጋር ነው የሚሰራው።

@Bisrat_Sport_433et @Bisrat_Sport_433et
አሰልጣኝ ጌዲዮን ሰለ ፊላደልፊያ 🗣

"አካዳሚው የተከፈተው ብቁ የሆነ ፍሬያማ የሀገር ልጆችን ለሰፊው የሀገራችን ህዝብ ማስተዋወቅ እና በዲስፕሊን ጉዳዮች ላይ ምስጉን የሆኑ ትውልዶችን ለመቅረፅ ነው።"

"ፕሮጀክቱ በዋናነት የሚሰራ ነገረ  ተጫዋቾችን ፖሲሽናል ፣አቋቋም ቦታ አያያዝ ታክቲካል ዲሲፒሊን ማድረግ ነው።"

የአካዳሚው ሰልጣኞች ሰለ አካዳሚያቸው 🗣

"በዚህ አካዳሚ ውስጥ ብዙ ነገር መገንባት እንፈልጋለን ምክንያቱም ብዙ ነገር የምናቅበት ምቹ ዕድላችን ነው።

"ከአሰልጣኛችን የሚሰጠንን ነገር በሃላፊነት እንሰራለን ሀገር ከእኛ የምትጠብቀውንም ነገር በሚገባ ለመስጠት ጠንክረን እንሰራለን።"

@Bisrat_Sport_433et @Bisrat_Sport_433et
ለአካዳሚው ቅርብ የሆኑ አካላት ሰለ አካዳሚው

ሽመልስ በቀለ 🗣

ምርጥ ተሰፋ ያላቸውን ተጫዋቾች አየቼበታል እርግጠኛ ደግሞ ይሳካላቸዋል ከአሰልጣኙ ጀምሮ እሰከ ተጫዋቾቹ ድረስ ሁሉም ያላቸው የስፖርት ፍቅር ደስ ይላል የዓላማቸውን ግብ ለመመታት ጠንክረው የሚሰሩ ናቸው።"

የሀዋሳ ከነማ ዋና ስራ አስኪያጅ አቶ ውቴሳ ኡጉሞ 🗣

"ከሀገር አልፎ በመላ አለም ሀገርን ማስተዋወቅ የሚችል ተሰጦ ያላቸው ባለ ራዕዮች የሚገኙበት አካዳሚ ነው።

የሲዳማ ክልል የፋይናንስ ሀላፊ አቶ ዘሪሁን ፍሬው 🗣

"ተስፋ ሰጪ አካዳሚ መሆኑን በ 10ጣቴ ፈርማለው ማድረግ ያለበኝ ለአካዳሚው በሙሉ ለማገዝ ከጎናቹ እገኛለው ይቅናቹ።"

ፕሮጀክቱ ሲጀመር ጀምሮ ከ አካዳሚው ጎን በመሆን ዕውቅና ያላቸውን ተጫዋቾች በማምጣት ለታዳጊዎች የሞራል ስንቅ ሲሆኑ የነበሩት የአካዳሚው አምባሳደር አቶ አንተነህ ገበየው (ካዬሶ) 🗣

"ለዚህ ድንቅ አካዳሚ ማሊያን ጨምሮ የተለያዩ ነገሮችን አበርክቻለው በዚህም እኮራለው ለሀገር ጥሩ ትውልድ ምርጥ አሻራ ሰላሳረፍኩ።"

በነገራችን ላይ አምባሳደር አንተነህ ለአካዳሚ ታዳጊዎች የተሻለን ነገን በማሰብ

ሽመልስ በቀለን ፣ ከነዓን ማዕርከነ እንዲሁም ጫላ ተሺታን

ወደ አካዳሚው በማምጣት ታዳጊዎች ልምድ እንዲያገኙ አድርገዋል እንዲሁም ተጋባዥ ተጫዋቾቹም ለአካዳሚው ኳስ ጨምሮ የተለያዩ ድጋፎችን አድርገው መልካም በበመኘት ተሸኝተዋል።

@Bisrat_Sport_433et @Bisrat_Sport_433et
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
ለአካዳሚው ሊሞሉ የሚገቡ ግብአቶች

. የመለማመጃ ማለያ እና ጫማ (ታኬታ) በብዛት

,የመጫወቻ ኳስ

. በቂ እና ሰፊ የመለማመጃ ስፍራ

. ኮኖችን ፣ መዘለያዎችን ጨምሮ ወዘት ለልምምድ የሚጠቅሙ መሰረተ ግብዓቶች

አሰልጣኝ ጌዲዮንም በመጨረሻም ጉዳዩ ለሚመለከታቸው የበላይ አካላት ያስተላለፈው መልዕክት

🗣 አላማችን ግልፅ ነው ከዘር ከ ሀይማኖት መከፋፈል እንዲሁም ከ ፖለቲካ አሰተሳሰብ የወጣ ጤናማ ስፖርታዊ አይምሮ መገንባት ነው ታዲያ ለዚህ አካዳሚ የበላይ አካል ተገቢውን እውቅና እና ደጋፍ እንዲሰጠን እጠይቃለሁ ከወዲሁ ለሚደረግለን ትብብር በአካዳሚው ስም አመሰግናለሁ።

@Bisrat_Sport_433et @Bisrat_Sport_433et
የዛሬው ፕሮግራማችን ይህንን ይመስል ነበር ያቀርብኩላቹ ሮቤል አብርሃም ነበርኩኝ !

በቀጣይ በዚህ ፕሮግራም መቅረብ የምትፈልጉ በሀገራችን ኢትዮጵያ የምትገኙ አካዳሚዎች @DETRYUO ላይ AC1 ን በማስቀደም ሰለ አካዳሚያቹ እንድታሳውቁን ግብዣችንን እናቀርባለን።

ያላቹን ጥያቄ ና አሰተያየት በ @Detryuo ላይ AC1 በማስቀደም መካፈል ትችላላችሁ።

አብራችሁን ሰለነበራቹ እናመሰግናለን ዳግም በሌላ ፕሮግራም እሰከ ምንገናኝ ቸር ሰንብቱ።

"የነገ የኢትዮጵያ ተስፋ እንፈጠር እግር ኳሳችን ታዳጊዎች ላይ በመስራት በዛላቂነት እናሳድግ"

@Bisrat_Sport_433et @Bisrat_Sport_433et
ሊሳንድሮ ማርቲኔዝ ወደ ልምምድ ተመልሷል!

አንዲሁም በተመሳሳይ ማርከስ ራሽፎርድም ወደ ልምምድ ተመልሷል።

@Bisrat_Sport_433et @Bisrat_Sport_433et
ባየር ሙኒክ ባለፉት 24 በሜዳቸው ባደረጉዋቸው የአውሮፓ ቻምፒየንስ ሊግ ጨዋታዎች የተሸነፉት በአንድ ጨዋታ ብቻ ነው።

@Bisrat_Sport_433et @Bisrat_Sport_433et