1ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 4:7 📜
አንተ እንድትበልጥ ማን አድርጎሃል? 🤔 ያልተቀበልኸውስ ምን አለህ? 🧐 የቀበልህ ከሆንህ ግን እንዳልተቀበልህ የምትመካ ስለ ምንድር ነው? 🤷♂️
አንተ እንድትበልጥ ማን አድርጎሃል? 🤔 ያልተቀበልኸውስ ምን አለህ? 🧐 የቀበልህ ከሆንህ ግን እንዳልተቀበልህ የምትመካ ስለ ምንድር ነው? 🤷♂️
BIBLICAL WAY
እግዚአብሔር የሚመለከው በተገደበና በሚገድብ የአምልኮ ስርዓት ነው።😊
መጽሐፍ ቅዱሳዊ አምልኮ
እግዚአብሔር ሊመለክ የሚገባ በተገደበ የአምልኮ ስርዓት ነው ማለት የሚገድብ አካል አለ ማለት ነው፤ እግዚአብሔርን እንደ ፈለግን አልያም ስሜታችን እንዳሻው እንዳናመልከው፣ ይህም ቅዱስ ቃሉ ነው። እግዚአብሔር የሚታወቀው እርሱ በገለጠው መንገድ ብቻ እንደመሆኑም መጠን የሚመለከውም እርሱ በፈለገው መንገድና በሰፈረው መስፈርት ነው። እግዚአብሔርን ባላለው መንገድ ማምለክ እርሱ ያላዘዘውን መስዋዕት ማቅረብ ከብሉይም ጀምሮ የሚያስቀጽፍ ነው(ዘሌ 10:1-3፣ 2ኛ ሳሙ 6:6-8)
ሁለተኛው ደግሞ እግዚአብሔር በቃሉ መሠረት በተገደበ የአምልኮ ስርዓት ሲመለክ ሰውን ይገድባል። ለምሳሌ ከሌዋውያን ውጪ የክህነት ስራን መስራት የሚችል አልነበረም። ንጉስ ዖዝያንም የሞተው ካላጠንኩ በማለቱ ነው። ሌዋውያንም መስዋዕት ሲያቀርቡ በፈለጉት መንገድ ሳይሆን እግዚአብሔር እንዳዘዘው ነው (ዘሌ 1-7)......
በአዲስ ኪዳንም እንደዛው እግዚአብሔር በቃሉ እንደሰፈረው ሊመለክ፣ እንዳዘዘው ቤተ ክርስቲያን ልትመራ ይገባታል። ይህም በጸሎት፣ በዝማሬ እና በእግዚአብሔር ቃል አገልግሎት፣ ምስጢራትን (ጥምቀትና የጌታ እራት) በመውሰድ፣ ድሆችን በመርዳት፣ ወላጅ የሌላቸውን ሕጻናት እንዲሁም ባል የሌላቸውን መበለቶች በመጠየቅ እግዚአብሔርን ልናመልክ፣ በጉባኤ ውስጥም መንፈስ ቅዱስ የስርዓት እንጂ የሁከት አምላክ አይደለምና ስርዓቱን በጠበቀ መልኩ መሆን አለበት። (1ኛ ቆሮ 14:40)
በባህሪው የእግዚአብሔር የትኛውም ትዕዛዝ ሰውን የሚገድብ ነውና።
ሁለት አይነት አመለካከት አለ በሪፎርሜሽን ዘመን የአበው ሉተርና የአበው ካልቪን 😁
Lutheran / Normative Principle: በቅዱስ ቃሉ ያልተከለከለ ነገር በአምልኮ ሊፈቀድ ይችላል።
Reformed / Regulative Principle: በአምልኮ ውስጥ በቃሉ የታዘዘ ነገር ብቻ እንደ አምልኮ አካል መደረግ አለበት። (ይህንን ስል እነ ማይክራፎንን ወይም ዘመናዊ የሙዚቃ መሳሪያ ጨምረን each and every detail አይደለም...Just የአምልኮ elementቶችን ለማለት ፈልጌ ነው።)
የካልቪንን/Reformed view እጋራለው
❤3
Name it claim it ✊??
To my great distress 😟, I sometimes hear people say, in their zeal for fervency and efficacy in prayer🙏, that we should never qualify our prayer requests with the words "if it be Your will.😳" Some will even say that to attach those words, those conditional terms, to our prayers is an act of unbelief🙄. We are told today that in the boldness of faith we are to "name it and claim it💪." I suppose I should be more measured in my response to this trend, but I can't think of anything more foreign✈️🪐 to the teaching of Christ. We come to the presence of God in boldness🔥, but never in arrogance😤🙅♂. Yes, we can name and claim those things God has clearly promised in Scripture🙋♂. For instance, we can claim the certainty of forgiveness if we confess our sins before Him🤲, because He promises that. But when it comes to getting a raise 💰, purchasing a home 🏠, or finding healing from a disease 🏥, God hasn’t made those kinds of specific promises anywhere in Scripture. Therefore, we are not free to name and claim those things. 🙏
R.C. Sproul, The Lord’s Prayer, p. 60.(emoji added😁)
❤3🎉1
ሁሉ ነገር social media ላይ የሚገኝበት ይህ ዘመን የሰዎችን የእርስ በእርስ ግንኙነት እየቀነሰ ሁሉም አጠገቡ ያለውን ማህበር ችላ ብሎ ስልኩ ውስጥ ያለውን ማህበር ያሳድዳል። ሁለት ሰዎች አንድ ቤት ቁጭ ብለው አይነጋገሩም፤ አንገታቸው ስልካቸው ላይ እንደተደፋ ነው። የክርስቲያኖችም ኑሮ በተመሳሳይ መንገድ እየተጓዘ ይገኛል ህብረቶቻችን በከባዱ እየተጎዱ ነው። ቤተክርስቲያን ከመሄድ ራሳችንን መዝሙርና ስብከት በመስማት ምንሸውድ የነበርን፣ የምንሸውድ፣ ወይም ለመሸወድ እቅድ ያለን በዚህ ጊዜ እንበዛለን። ሰራተኛው በጌታቀን ቤተክስቲያን ከመሄድ ይልቅ ስራውን መሄድ ይመርጣል ለህሊናው ማርከሻ ደግሞ መዝሙር ይሰማል፣ ተማሪው ጥናቱን መርጦ ላይብረሪ ይገባል ውስጡ ላለው ወቀሳ መልስ በመሃል ስብከት ይሰማል፣ በእርሱ ቤት በአንድ ድንጋይ ሁለት ወፍ እየመታ ነው።
መጽሐፍ ግን እንዲህ ይላል
ዕብራውያን 10:25 NASV
[25] አንዳንዶች ማድረጉን እንደተዉት መሰብሰባችንን አንተው፤ ይልቁንም ቀኑ እየተቃረበ መምጣቱን ስታዩ እርስ በርሳችን እንበረታታ።
መዝሙር ማዳመጥ፣ ስለ እግዚአብሔር ማንበብና ማወቅ፣ የግል ጊዜ ከእግዚአብሔር ጋር ማሳለፍ(ቃሉን ማጥናት፣ማሰላሰል ፣ ጸሎት)፣ በራሳቸው የእግዚአብሔር ጸጋ ወደ እኛ የሚፈስበት መንገዶች ወይም መሳሪያዎች ከቅዱሳን ሕብረት ጋር ሲጣመሩ ደግሞ ቅድስናችን ያድጋል።
#ቤተክርስቲያን #እንሂድ

👍11❤4
1 ዮሐንስ 1:8-10 NASV
[8] ኀጢአት የለብንም ብንል፣ ራሳችንን እናስታለን፤ እውነቱም በእኛ ውስጥ የለም።
[9] ኀጢአታችንን ብንናዘዝ ኀጢአታችንን ይቅር ሊለን፣ ከዐመፃም ሁሉ ሊያነጻን እርሱ ታማኝና ጻድቅ ነው።
[10] ኀጢአት አልሠራንም ብንል፣ እርሱን ሐሰተኛ እናደርገዋለን፤ የእርሱም ቃል በእኛ ውስጥ የለም።
[8] ኀጢአት የለብንም ብንል፣ ራሳችንን እናስታለን፤ እውነቱም በእኛ ውስጥ የለም።
[9] ኀጢአታችንን ብንናዘዝ ኀጢአታችንን ይቅር ሊለን፣ ከዐመፃም ሁሉ ሊያነጻን እርሱ ታማኝና ጻድቅ ነው።
[10] ኀጢአት አልሠራንም ብንል፣ እርሱን ሐሰተኛ እናደርገዋለን፤ የእርሱም ቃል በእኛ ውስጥ የለም።
❤8
መዝሙር 139:23-24 NASV
[23] እግዚአብሔር ሆይ፤ መርምረኝ፤ ልቤንም ዕወቅ፤ ፈትነኝ፤ ሐሳቤንም ዕወቅ፤ [24] የክፋት መንገድ በውስጤ ቢኖር እይ፤ በዘላለምም መንገድ ምራኝ።
[23] እግዚአብሔር ሆይ፤ መርምረኝ፤ ልቤንም ዕወቅ፤ ፈትነኝ፤ ሐሳቤንም ዕወቅ፤ [24] የክፋት መንገድ በውስጤ ቢኖር እይ፤ በዘላለምም መንገድ ምራኝ።
❤5
ቃል ሥጋ ሆነ (ዮሐ 1:14)፣ የማይሞተው ሞትን፣ የማይገደበው ውሱንነትን፣ አምላክ ሰውነትን ተቀበለ። በዚህም ምክንያት ለእኛ ክርስቶስ ፍጹም ሰው፣ የተፈተነ በኃጢአት ግን ያልወደቀ(ዕብ 4:15)፣ የዓለምን ኃጢአት የሚያስወግድ የእግዚአብሔር በግ(ዮሐ 1:29)፣ ሆኖ ወደዚህ ምድር መጣ፤ የገዛ ወገኖቹም አልተቀበሉትም። መጽሐፍም እንደሚል "ለተቀበሉት በስሙም ለሚያምኑት የእግዚአብሔር ልጆች የመሆን ሥልጣንን ሰጣቸው"(ዮሐ 1:12)። እግዚአብሔርን አባት እኛንም ልጆች አደረገን ይህንንም ማረጋገጫ ሌላ አጽናኝ የተባለውን ጳራቅሊጦስ፣ ወደ እውነት ሁሉ የሚመራውን(ዮሐ 16:13)፣ አባ አባ ብለን የምንጮህበት የልጅነታችንን ማረጋገጫ(ሮሜ 8:15) ለቤዛ ቀን የታተምንበትን መንፈስ ቅዱስ ሰጠን(ኤፌ 1:13፣ 4:30) ። በሰማያዊ ስፍራ በመንፈሳዊ በረከት ሁሉ ባረከን(ኤፌ 1:3)፣ ዓለም ሳይፈጠር በፊት በፊቱ ቅዱስ ነውር የሌለው እንድንሆን በክርስቶስ መርጦ(ኤፌ 1:4)፣ በክርስቶስ የቤዝሆት ስራ አማካኝነት የበደላችንን ስርየት አገኘን(ኤፌ 1:7)። ሁሉን እንደፈቃዱ ምክር የሚሰራ(ኤፌ 1:11)፣ በሰማይ ሆኖ የወደደውን በምድር የሚያደርግ(መዝ 115:3) እግዚአብሔር ሉዓላዊውም አምላክ ቤተሰቡ አደረገን ዓለም ሳይፈጠር በፊት ልጁን በመንፈሱ የሚወድበት ፍቅሩንም ለምርጦቹ አፈሰሰ(ዮሐ 17:23)።
እኛ አሕዛብ ኃጢአት እና በበደላችን ሙት በዚህ አለም ገዢ ስር፣ የሥጋችንን እና የልቦናችንን ፈቃድ የምናደርግ፣ የቁጣ ልጆች፣(ኤፌ 2:1-3) በሥጋ በተገረዙት ያልተገረዙ የተባልን፣ ለተስፋው ቃል እንግዶች እና መጻተኞች፣ ተስፋ ያልነበረን፣ (ኤፌ 2:11-13) ከታላቅ ፍቅሩ እና ከምህረቱ የተነሳ በበደላችን ሙት ሳለን ከክርስቶስ ጋር ህይወትን ሰጠን፣ በጸጋው አዳነን፣ በሚመጡ ዘመናትም እየቀደሰን የጸጋውን ባለጠግነት በኛ ሊያሳይ ወደደ፣ ጸጋው በእምነት በኩል አዳነን ይህም የእርሱ ስጦታ እንጂ የኛ ሥራ አልነበረበትም(ኤፌ 2:4-10)።
በዚህ በአዱሱ ኪዳን እግዚአብሔር አዲስን ፍጥረት በክርስቶስ ፈጠረ(2ኛ ቆሮ 5:17) በአይሁድ በአህዛብ መካከል የነበረኽን የጥል ግድግዳ በሥጋው አፍርሶ ከሁለቱ አንድን ሰው ሰራ። እኛም እግዲህ ከዚህ ወዲያ ያልተገረዙ ላንባል ልባችንን ገረዘ፣ መጻተኞች እና እንግዶች ላንባል የተስፋውን ቃል ለኛ አወረሰን፣ አሁን እኛ ቤተሰብና ወዳጆች ሆንን(ኤፌ 2፡14-19) ። መጽሐፍ "ልጁ በብዙ ወንድሞች ዘንድ በኩር እንዲሆን" (ሮሜ 8:29)እንደሚል እርሱ ከሙታን በኩር ሆኖ እኛንም ከእርሱ ተከትለን የሙታን ትንሳኤን ተስፋ ተቀበልን። የሚበሰብሰው ወደ ማይበሰብሰው(1ኛ ቆሮ 15:52) በሚለወጥበት ጊዜ ደግሞ ይሄ በእውን ሆኖ በሥጋችን ትንሳኤ ይረጋገጣል። በኩር ወንድማችን ክርስቶስ ከሞት እንደተነሳ እኛም እርሱን በሚመስል ትንሳኤ ተነስተን ከእርሱ ጋር ለዘላለም እንከብራለን።
ማንም እንዳይመካ ከሥራ አይደለም(ኤፌ 2:9)፣ የሚመካ በእግዚአብሔር ይመካ ተብሎ እንደተጻፈ ዛሬም ለመዳናችን በእግዚአብሔር እንመካለን።

❤2
The best believers, who are certainly freed from the condemning Power of sin, still need to make it their business to mortify the indwelling power of sin all their life. 🙏✨
John owen, Mortification of Sin
John owen, Mortification of Sin
❤2
Forwarded from Good Christian Books Shelf
መንፈስ ቅዱስ ሆይ በውስጣችን የሚኖረውን ገለባውን የሃጢአት ሃይል በእሳትህ አቃጥለው። የሃጢአት መሻታችንን በእሳትህ አንጻው። ዘወትር ገዳዩን ሃጢአታችንን በእሳትህ አጥራው። በኛ አቅም እንዳያገኝ በሃይልህ አድቅቀው። እንዳይበረታብን አድክመው። እንዳይስፋፋም ግታው። በህይወት እንዳይኖርም ግደለው። አሜን።
❤6
Forwarded from ቅዱስ ማኅበር (Honelgn Abate)
"ፀልዩልን" ስንላቸው፣ "እሺ" የሚሉን ሰዎች ከቤተክርስቲያን አይለቁብን።
የራሳቸው ጉዳይ የሌለባቸው ይመስል የሰው ችግር ቁጭ ብለው የሚሰሙ እና "እፀልይልሀለው" የሚሉ፣ ተሸካሚ ልቦች ይበርክቱልን።
@lera_koinonia
የራሳቸው ጉዳይ የሌለባቸው ይመስል የሰው ችግር ቁጭ ብለው የሚሰሙ እና "እፀልይልሀለው" የሚሉ፣ ተሸካሚ ልቦች ይበርክቱልን።
@lera_koinonia
❤11
አሁን እሺ ድመት ከመጽሐፍ ቅዱስ ያላት ችግር ምንድነው ?...ከዚህ በፊት አንዴም በመጽሐፍ ቅዱስ እንዳልተጠቀሰች ሰምቻለው😂...ከዚያ ዛሬ የደግሞ ቲክቶክ ላይ ድመት ቁርዓንን እንደማትረግጥ አየው መጽሐፍ ቅዱስ ላይ ግን ትራመዳለች 😭
😁6
በህልሜ ይሄ ቻናል 530 subscriber ደርሶ አይቼ ነበር። ይኸው ተነስቼ ስገባ still 460 ነው። 😭😭...ህልም እልም 😁
😁4🌚1
Forwarded from Yeshua Apologetics
አንድ ምክር ልምከራችሁ!
ከሥነ መለኮት ጥናታችሁ ጎን ለጎን በቻላችኹት አቅም መንፈሳዊያን ሁኑ፤ ሳይሆኑ የተራመዱ ብዙዎች በዚህ መንገድ ሲሄዱ ፖፑላሪቲን አግኝተው በክርስትና ህይወታቸው አንቀላፍተዋል። አንዳንዶች ከአንዱ ወደ አንዱ ሃይማኖት ሲቀይሩ፣ ሌሎች ሊብራል፣ አግኖስቲክ ሲከፋም ኤቲይስት ሆነው አይተናል። ታዲያ ምን እያልን ነው? ለምታምኑት ነገር ስትሟገቱለት መንፈሳውያን(የጸሎት ሰው፣ ከቃሉ ጋር ህብረት ያላችሁ፣ ቤተክርስቲያን ህብረት ያላችሁ) ሁኑና ሞግቱ። ምናልባት ተሟጋቻችሁ በሙግቱ እናተን ከረታችሁ እንኳን ያቺ መንበርከኪያችሁን ሙግቱ አይመታውምና የጸሎት ሰው ሁኑ!
@Yeshua_Apologetics

2 ጢሞቴዎስ 1:8-10 NASV
[8] እንግዲህ፣ ስለ ጌታችን ለመመስከር ወይም የርሱ እስረኛ በሆንሁት በእኔ አትፈር፤ ነገር ግን በእግዚአብሔር ኀይል ስለ ወንጌል ከእኔ ጋራ መከራን ተቀበል። [9] እኛ ስላደረግነው አንዳች ነገር ሳይሆን፣ ከዕቅዱና ከጸጋው የተነሣ ያዳነን፣ ወደ ቅዱስ ሕይወትም የጠራን እርሱ ነው። ይህም ጸጋ ከዘላለም ዘመናት በፊት በክርስቶስ ኢየሱስ ተሰጠን፤ [10] አሁን ግን ሞትን ደምስሶ በወንጌል አማካይነት ሕይወትንና ኢመዋቲነትን ወደ ብርሃን ባወጣው በመድኀኒታችን በክርስቶስ ኢየሱስ መምጣት ተገልጧል።

Forwarded from Remnants
📢ሰላም እንደምን አላችሁ?
ጌታ ቢረዳን እና ብንኖር
ነገ (እሮብ) ማታ ከ3:00 ጀምሮ በዚሁ Telegram live “የጉባኤ አምልኮ” ን በሚመለከት ስለ አምለኮ ምንነት፤ በቤተክርስቲያን ውስጥ አምልኮ እንዴት መሆን አለበት እነዚህና የመሳሰሉ ሀሳቦች ላይ ከወንድም ካሌብ (የሎሌ ወንጌላዊት ቤተ ክርስቲያን ሽማግሌ) ጋር በዚሁ ቴሌግራም ቻናል እንገናኛለን
ይህንን ማስታወቂያ ሼር በማድረግና ሌሎችን በመጋበዝ እንዲገኙ እንጋብዛቸው
ፀጋና ሰላም ይብዛላችሁ🙌
@remnant_s

🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻እንኳን ለሌላ የለውጥ አመት በሰላም🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻 አደረሳችሁ 🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻 በምድር ላይ ብዙ ቅዱሳንን እንዲሁም እርኩሳንን፣ ጻድቃንን እንዲሁም ኃጢአንን፣ አጥፊዎችን እንዲሁም አልሚዎችን፣ ምሁራንን እንዲሁ መሃይሞችን ነገስታትን እንዲሁም ሕዝብን፣ ጌቶችን እንዲሁም ባሪያዎችን፣ ወላጆችን እንዲሁም ልጆችን፣ ሲወለዱ፣ ሲያድጉ፣ ሲያረጁ ደግሞም ሲሞቱ አይተናል። እንዲሁም ፍጡር…
ዛሬ የመጨረሻው የ2018 ቀን ነው እና አመቱን ሙሉ ቁጭ ብዬ ልቃኝ ብል በዓመቱ መጀመሪያ ላይ እንደተናገርኩት ብዙ ለውጥ በህይወቶቼ ነበሩ። በዚህ አመት የተውኳቸው ብዙ አመለካከቶች፣ ልምምዶች ዕሳቤዎች ወዘተ ጥቂት አይደሉም፣ የሸመትኳቸውም እንደዛው ብዙ ናቸው። በሌላ በኩል ደግሞ በ2017 ከኔ ጋር እንዳይሻገሩ የተመኘኋቸው ድክመቶቼ ተሻግረው ዛሬም 2018 "በቃ በእነዚህ ሁኔታዎች ላይ የመጨረሻ አመት ይሁን" ብዬ እግዚአብሔርን የምለምንባቸው ችግሮች አሉብኝ። ነገም አዲስ አመት ስለሆነ radically እንደማይጠፉ አውቃለው። በክርስቶስ አዲስ ፍጥረት ስሆን ያልተወኝ መከራ እና ፈተና በኢትዮጽያውያን አዲስ አመት ይተወኛል የሚል ቃልም ሆነ ዋስትና የለኝም። ይህ ማለት ግን በኃጢአት ጸንቼ ለመኖር ለራሴ እያመቻቸው ሳይሆን፤ በቀጣይም አመት የሚጠብቀኝን ትግል acknowledge ማድረጌ ነው። እግዚአብሔርን ስላለፈው አመት አመሰግነዋለው ብዙ ረድቶኛል፤ ያለጸጋው ብርታትም በክርስትና ሕይወት አንዳች መራመድ አልችልም ነበር። ቀጣዩም አመት በብዙ ታማኝነቱን የማይበት አመት እንደሚሆን ተስፋ አደርጋለው። እርሱን በማወቅ የማድግበት፣ በብዙ ምበረታበት፣ መንፈሳዊ ፍሬዎች በሕይወቴ የሚበዙበት፣ የሥጋ ሥራዎች የሚቀንሱበት አመት ይሁንልኝ ስል ለራሴ ተመኘሁ። 😊
ለእናንተም ተመሳሳዩን እመኛለው ወንድምና እህቶቼ😇... እግዚአብሔር መፈለግን እና ማድረግን በውስጣችሁ እያኖረ ወዳሰበላችሁ ዓላማ የሚያሳድግበት፣ የክርስቶስን ምስል እያብለጨለጫችሁ ከክብር ወደ ክብር የምትኖሩበት ዓመት ይሁንላችሁ። 🤗
ለእናንተም ተመሳሳዩን እመኛለው ወንድምና እህቶቼ😇... እግዚአብሔር መፈለግን እና ማድረግን በውስጣችሁ እያኖረ ወዳሰበላችሁ ዓላማ የሚያሳድግበት፣ የክርስቶስን ምስል እያብለጨለጫችሁ ከክብር ወደ ክብር የምትኖሩበት ዓመት ይሁንላችሁ። 🤗
❤9
🌼 መስከረም 1/2019 ዓም 🌼
🌻 እንኳን አደረሳችሁ አደረሰን 🌻
🌼🌼 አምና በዚህ ሰዓት እንደተመኘነው ዘንድሮን በእውቀቱ ፈቃድ እያሳደገን እግዚአብሔር ምስጋና፣ ክብር፣ አምልኮ ይግባው🙌...አሁን ሀ ብለን ዛሬ የምንቀበለው ዓመት ደግሞ በምናልፍበት ቀናት በሙሉ የእምነታችን ትዕግስት እየጨመረ፣ በመከራ ሁሉ እየጸናን፣ እየተጽናናን ሌሎችንም እያጽናናን የምናልፍበት፣ በአመቱ መጨረሻም ዞር ብለን ስናይ በመንገዳችን የእግዚአብሔርን የጸጋ አሻራ ብቻ የምንመለከትበት፣ "ከእኔ" የማንልበት አመት ያርግልን። 🌼🌼

❤4