BeWide Technologies
266 subscribers
96 photos
20 links
Pioneering AI-powered software development, IT solutions, and branding for transformative growth. From intelligent web design and custom systems to dynamic mobile apps

Elevate your digital presence with us

Be wide—Be wise

Contact us through @BeWideTech
Download Telegram
Eid Mubarak! May your heart be filled with joy and your home with laughter.

Bewide Technologies
Be Wide - Be Wise
@BeWide_Tech
❤8
Wishing you joy, good health, and endless blessings this Eid al-Adha.  

Bewide Technologies
Be Wide - Be Wise
@BeWide_Tech
❤5
WIDE THINKING.
WISE BUILDING.

Bewide Technologies
Be Wide - Be Wise
@BeWide_Tech
❤6
BeWide Technologies
Photo
🎓 ታላቅ የስኬት ምዕራፍ!

ሱና ዩኒቨርሲቲ ወደ ዘመናዊ ዲጂታል አስተዳደር ሥርዓት በይፋ ተሸጋግሯል! 🎉
መስከረም/02/2019 ዓ.ል ሱና ዩኒቨርሲቲ ኦፊሻላዊ ዲጂታል ሥርዓቶቹን በተሳካ ሁኔታ አጠናቆ ወደ ስራ አስግብቷል! 🎉

በመስከረም 2/2019 ዓ.ል በተካሄደው የፕሮጀክት ማጠናቀቂያና ርክክብ ስነ-ስርዓት ላይ ለBeWide Technologies የምስጋና ምስክር ወረቀት በሸይኽ ዶ/ር መሀመድ ሐሚዲን ተበርክቶላቸዋል።
በወጣት ኢትዮጵያውያን ሶፍትዌር መሐንዲሶችና ቴክኖሎጂ ባለሙያዎች ቡድን BeWide Technologies ጋር በተደረገዉ ዉል መሰረት ወደ ስራ የገቡት የዲጂታል ሥርዓቶችም፡

ኦፊሻላዊ ድረ-ገጽ (Official Website www.sunnahuniversity.edu.et
የመማሪያ አስተዳደር ሥርዓት (Learning Mmanagment System Link: Courses)
የተማሪዎች የትምህርት መዝገብ አስተዳደር ሥርዓት (Student Academic Record Mmanagment System Link: Sunnah University Portal)

እነዚህ ዲጂታል ሥርዓቶች ለዩኒቨርሲቲው የሚያበረክቱት አስተዋፅኦ የላቀ ነው፦

📌 የትምህርት አሰጣጥን ቀልጣፋና ዘመናዊ ማድረግ
📌 የተማሪዎችን የትምህርት መዝገብ በአስተማማኝ እና በተደራጀ መልኩ ማስተዳደር
📌 ለሚመለከታቸው አካላት መረጃ በቀላሉ ተደራሽ ማድረግ
📌 የአስተዳደር ስራዎችን ጊዜና ጉልበት ቆጣቢ በማድረግ
📌 ከሀገር ዉስጥ እና ከውጭ ሆነው የዒልም ትምህርትን መከታተል ፈልጎ የቦታ እና ጊዜ ገደብ እንቅፋት ለሆኑባቸዉ ሙስሊም ማህበረሰብ ክፍል ዘላቂ መፍትሄ ይሆናል።
📌 የዳዕዋ አካዳሚን በይፋ ለማስጀመር የሱና ዩኒቨርሲቲን የሚያግዝ ተጨማሪ ኃይል ይሆናል።

በመሆኑም ሱና ዩኒቨርሲቲ በኢስላማዊ እሴቶች ላይ የተመሰረተ ትምህርት ከመስጠትም ባለፈ፣ ይህንን ዘመናዊ ቴክኖሎጂ በመተግበር ኢስላማዊ ትምህርት ተቋማት ከዘመኑ ጋር አብረው መራመድ እንደሚችሉ በተግባር ያሳየ ትልቅ ምሳሌ ሆኗል። ይህም ለሌሎች ተመሳሳይ ተቋማት አርአያ የሚሆን ጅምር ነው። በሀገር አቀፍ ደረጃም ሲታይ፣ የኢትዮጵያ ወጣት ቴክኖሎጂ ባለሙያዎች በራሳቸው አቅምና ችሎታ ለከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ደረጃውን የጠበቀ ዲጂታል መፍትሔ መስጠት እንደሚችሉ በተጨባጭ ማሳያ ሆኗል፤ ይህም ለሀገራችን ዲጂታል ትራንስፎርሜሽን ጉዞ የበኩሉን አስተዋፅኦ የሚያደርግ ነው።

ይህንን ውጤታማ ስራ ላበረከቱት ወጣት ኢንጂነሮችና ቴክኖሎጂ ባለሙያዎች ልባዊ ምስጋናችንን እናቀርባለን! የናንተ ትጋትና ችሎታ ለብዙ ወጣቶች መነሳሳት ይሆናል።

©ዳዕዋ ቲቪ

@BeWide_Tech
❤5👏5😍1