Bahir Dar Customs
643 subscribers
1.29K photos
10 videos
33 files
168 links
Download Telegram
👍2
👍5🤔1
በኢትዮጵያ ጉምሩክ ኮሚሽን ባህር ዳር ቅ/ጽ/ቤት ከአራቱ ተቋማት የ2015 በጀት ዓመት የቅንጅት ስራዎች አፈፃፀም ግምገማ አካሄደ፡፡
ሐምሌ 15/2015 ዓ.ም

በኢትዮጵያ ጉምሩክ ኮሚሽን ባህር ዳር ቅ/ጽ/ቤት የ2015 በጀት አመትን የቅንጅት ስራዎች ከፌደራል ፖሊስ አመራሮች፣ከገቢዎች ሚኒስተር ባህር ዳር ቅ/ጽ/ቤት አመራሮች፣ ከፌደራል ወንጀል ምርመራ ባህር ዳር አመራሮች እና ከፌደራል ኢኮኖሚ ጉዳዮች ባህር ዳር አቃቢ ህግ አመራሮች በጉምሩክ ኮሚሽን ባህርዳር ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ስራ አስኪያጅ ቢሮ በቀን 15/11/2015ዓ.ም ለመገምገም የተገናኙ ሲሆን የቅ/ጽ/ቤቱ ስራ አስኪያጅ አቶ አለነ መሐሪ ለግምገማው የመክፈቻ ንግግር ካቀረቡ በኋላ የዓመቱ የስራ አፈጻጸም ሪፖርት በህግ ተገዥነት ዘርፍ ምክትል ስራ አስኪያጅ በአቶ አባቡ ፀጋ ቀርቧል፡፡
በበጀት አመቱ የነበሩ ጠንካራና ደካማ ጎኖች እንዲሁም ያጋጠሙ ችግሮች ተነስተው ውይይት የተደረገባቸው እና በተነሡ ጉዳዮች ለይ ማብራሪያ በመስጠት እንዲሁም በቀጣይ በጀት አመት የበለጠ በመቀራረብና በመናበብ የተሻለ ውጤት ማምጣትና የአጥፊዎችን ተጠያቂነት ማረጋገጥ ይገባል በማለት ውይይቱን አጠናቀዋል።


"ስለምትከታተሉን ከልብ እናመሰግናለን!!
ከደንበኞች ትምህርትና ድጋፍ ቡድን
ባህር ዳር

ጉምሩክ ኮሚሽን ባህር ዳር ቅ/ጽ/ቤትን የተመለከቱ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/BahirDarCustomsBranch
በድረ ገጽ፦ www.ecc.gov.et
በቴሌግራም፦ https://t.me/BahirDarCustoms
በኢንታግራም፡https://www.instagram.com/invites/contact/?i=1feknwgnp27tr&utm_content=pbktsa4
👍7