BBC Amharic
1.57K subscribers
5.65K photos
257 videos
7 files
355 links
➠ ፈጣን እና ተዐማኒ መረጃ፣
➠ የስፓርት እና መዝናኛ ዘገባዎች፣
➠ የምሁራን እይታዎችና መጽሐፈቶች፣
➠ የአለም ሙሉ መረጃና የታሪክ መዛግብቶች ።

🎬 "ተመራጭ የዜና ምንጭ"
ለማንኛውም አስተያየት እና ጥቆማ?
👇👇👇👇👇👇👇👇👇
Comment. @Bbc_asteyayet_bot
Download Telegram
በኢትዮጵያ ተጨማሪ 170 ሰዎች የኮሮና ቫይረስ ተገኘባቸው፤ የተጨማሪ 3 ሰዎች ሕይወት አለፈ

@Dire_Tube_news
@Dire_Tube_news
በኢትዮጵያ ተጨማሪ 245 ሰዎች የኮሮና ቫይረስ ተገኘባቸው።

በ24 ሰዓታት ውስጥ 245 ሰዎች የኮሮና ቫይረስ ሲገኝባቸው፤ የ7 ሰዎች ህይወት አለፈ።ኢትዮጵያ ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ በተደረገው 5709 የላብራቶሪ ምርመራ 245 ሰዎች የኮሮና ቫይረስ እንደተገኘባቸው የጤና ሚኒስቴር አስታወቀ።በአጠቃላይ በሀገራችን ቫይረሱ በምርመራ የተገኘባቸው ሰዎች ቁጥር 2915 መድረሱንም የጤና ሚኒስትር ዶክተር ሊያ ታደሰ አስታውቀዋል።
●ሰበር ዜና ❗️

በኢትዮጵያ ተጨማሪ 399 ሰዎች የኮሮናቫይረስ ተገኘባቸው❗️


ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ በተደረገው 4848 የላብራቶሪ ምርመራ ሶስት መቶ ዘጠና ዘጠኝ (399) ሰዎች የኮሮና ቫይረስ ተገኝቶባቸዋል፡፡ በአጠቃላይ በሀገራችን ቫይረሱ በምርመራ የተገኘባቸው ሰዎች ቁጥር 4469 ደርሷል።
በሌላ መልኩ በትላንትናው ዕለት ዘጠና አምስት (95) ሰዎች (82 ከአዲስ አበባ፣ 8 ከአማራ ክልል፣ 2 ከሶማሊ ክልል ፣ 1 ከትግራይ ክልል፣ 1 ከኦሮሚያ ክልል እና 1 ሰው ከጋምቤላ ክልል) ያገገሙ ሲሆን በአጠቃላይ በሀገራችን ከበሽታው ያገገሙ ሰዎች ቁጥር 1122 ነው።




@etv_zena
@etv_zena
@etv_zena
ሌ/ጀ ጌታቸው ጉዲና (የመሀንዲስ ዋና መምሪያ ሀላፊ) በመጠናቀቅ ላይ የሚገኘውን የቃሊቲ ሴንተራል ዲፖ ፕሮጀክት መጎብኘታቸውን የኢፌዴሪ መከላከያ ሰራዊት ይፋዊ ገፅ አሳውቋል።

ስለፕሮጀክቱ ፦

- በ25 ሄክታር ያረፈ ነው፤ 22 ብሎክ የአልባሳት እና ሌላ 22 ብሎክ ደግሞ የመኪና መለዋወጫ ግምጃ ቤት ተገንብቶበታል።

- ባለ 3 ወለል 32 ቢሮዎች የያዘ የአስተዳደር ህንጻም ተሰርቷል፡፡ አንድ የትልቅ የመኪና እና ሁለት የትንንሽ መኪና ማከማቻም ተጠናቋል።

- 3 ኪሎ ሜትር በሚረዝመው የጊቢው አጥር ዙሪያ 8 የጥበቃ ማማ የተሰራ ተሰርቷል።

- ለ1 ሻምበል አባላት የሚሆን መኖሪያ ፣ መመገቢያ ፣ መጸዳጃ እና መዝናኛ ተገንብቷል፡፡

- ፕሮጀክቱ በአሁኑ ሰአት 97 በመቶ ደርሷል ፤ ቀሪው በተያዘለት ጊዜ ለማጠናቀቅ የፕሮጀክቱ ሰራተኞች ርብርብ እያረጉ እንደሚገኙ ተገልጿል።

@BBC_AMHARIC
የዘንድሮው የኖቤል የሰላም ሽልማት ተሸላሚ የአለም ምግብ ፕሮግራም (WFP) ሆኗል!

@BBC_AMHARIC
በአዲስ አበባ የውስጥ ለውስጥ መንገዶችን በማጠር የዘጉ አካላት ተጠያቂ ሊሆኑ ነው!

የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ባለሥልጣን በከተማዋ የተለየዩ አካባቢዎች የሚገኙ የውስጥ ለውስጥ መንገዶችን በማጠር በህዝብ ሀብት ላይ ህገወጥ ተግባራት በሚፈፅሙ አካላት ላይ ህጋዊ እርምጃ ለመውሰድ የሚያስችል የቅድመ ዝግጅት ስራዎችን እያከናወንኩ ነኝ ሲል ገለጸ፡፡

እርምጃውንም ከመውሰዱ አስቀድሞ በተለያዩ የግንዛቤ መስጫ አግባቦች አስፈላጊውን የማስተማር ስራዎችን በማከናወንና ማስጠንቀቂያ በመስጠት ላይ እንደሚገኝም ጠቁሟል፡፡

ባለሥልጣን መስሪያቤቱ ይህ ድርጊት ተፈጽሞባቸዋል ካላቸው አካባቢዎች ውስጥ ለቡ መብራት ኃይል፣ ለቡ ፖሊስ ጣቢያ፣ ሆፕ ዩኒቨርሲቲ፣ ቫርኔሮ ሬስቶራንት ጀርባ፣ ቆጣ ኮንደሚኒየም ፣ ጀሞ አንድ ናሆም መጋጠሚያ ፊውቸር ት/ቤት፣ አሮጌ አውሮፕላን ማረፊያ፣ ጅግጅጋ ሰፈርና ሌሎችም ይጠቀሳሉ ሲል አስ
@BBC_AMHARIC
ጠ/ሚ ዐቢይ የዓለም ምግብ ፕሮግራም የ2020 የኖቤል የሰላም ሽልማት በማሸነፉ የደስታ መልዕክት አስተላለፉ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 29፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ የዓለም የምግብ ፕሮግራም የ2020 የኖቤል የሰላም ሽልማት በማሸነፉ የእንኳን ደስ አላችሁ መልዕክት አስተላለፉ። ጠቅላይ ሚኒስትሩ ባስተላለፉት የደስታ መልዕክት ለፕሮግራሙ ዋና ዳይሬክተር ዴቪድ ቤስሌይ የ2020 የሰላም ሽልማት በማሸነፋችሁ እንኳን ደስ አላችሁ ብለዋል። የዓለም የምግብ ፕሮግራም ረሃብን ለመዋጋት ባደረገው ጥረት የፈረንጆቹ 2020 የሰላመ ኖቤል አሸናፊ መሆኑ…

https://ጠ/ሚ ዐቢይ የዓለም ምግብ ፕሮግራም የ2020 የኖቤል የሰላም ሽልማት በማሸነፉ የደስታ መልዕክት አስተላለፉ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 29፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ የዓለም የምግብ ፕሮግራም የ2020 የኖቤል የሰላም ሽልማት በማሸነፉ የእንኳን ደስ አላችሁ መልዕክት አስተላለፉ። ጠቅላይ ሚኒስትሩ ባስተላለፉት የደስታ መልዕክት ለፕሮግራሙ ዋና ዳይሬክተር ዴቪድ ቤስሌይ የ2020 የሰላም ሽልማት በማሸነፋችሁ እንኳን ደስ አላችሁ ብለዋል። የዓለም የምግብ ፕሮግራም ረሃብን ለመዋጋት ባደረገው ጥረት የፈረንጆቹ 2020 የሰላመ ኖቤል አሸናፊ መሆኑ…

https://@BBC_AMHARIC/ጠ-ሚ-ዐቢይ-የዓለም-ምግብ-ፕሮግራም-የ2020-የኖቤ/
ምርጫ ቦርድ ከኦነግ አመራር አባላት የቀረቡለትን አቤቱታዎች አስመልክቶ ውሳኔ አሳለፈ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 29፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ከኦሮሞ ነጻነት ግንባርን /ኦነግ/ አመራር አባላት የቀረቡለትን አቤቱታዎች አስመልክቶ ውሳኔ ማሳለፉን አስታወቀ፡፡   ቦርዱ በእነ አቶ ዳውድ ኢብሣ የሚመረጥ/የምትመረጥ አንድ፤ በእነ አቶ አራርሶ ቢቂላ የሚመረጥ/የምትመረጥ ሌላ አንድ፤ እንዲሁም እነዚህን ሁለት በባለጉዳዮቹ የሚመረጡትን ባለሙያዎች በሰብሳቢነት የሚመራ/የምትመራ ሌላ አንድ ባለሙያ ቦርዱ መርጦ በመመደብ የባለሙያዎች ጊዜያዊ ጉባኤ…@BBC_AMHARIC
የእንጦጦ ፓርክ ነገ ይመረቃል ተባለ

የጠቅላይ ሚንስቴር ጽህፈት ቤት ለኢትዮ ኤፍ ኤም እንዳስታወቀው የእንጦጦ ፓርክ ነገ ቅዳሜ መስከረም 30 ቀን 2013 ዓ.ም የተለያዩ እንግዶች በተገኙበት ይመረቃል።

ፓርኩ አገርኛ ስያሜዎችን እና መዝናኛ ዘርፎችን ባካተተ መንገድ የተገነባ ሲሆን ለበርካታ ዜጎች የስራ ዕድል መፍጠሩም ተገልጿል።


የፓርኩ ምርቃት ከተከናወነ በኋላም ለጎብኚዎች ክፍት እንደሚሆን ይጠበቃል።
@BBC_AMHARIC
''በዩኒቨርስቲዎች ያሉ ወጣቶች ለኛ መልካም እድል ናቸው ብለን እናምናለን''|ሎሬት የትነበርሽ ንጉሴ

የኢትዮጰያ ዕርቀ ሰላም ኮሚሽን ከሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር ጋር በጋራ በሚሰራበት ሁኔታ ላይ ተወያይቷል።

በውይይቱ ላይ የኮሚሽኑ ም/ ሰብሳቢ ወ/ሮ የትነበርሽ ንጉሴ በዩኒቨርስቲዎች ያሉ ወጣቶች ለኛ መልካም እድል ናቸው ብለን እናምናለን። የሰላም መገንባት ስራዎች ላይም የነሱ አስተዋፅኦ ከፍተኛ በመሆኑ እንሰራበታለን ሲሉ ገልጸዋል፡፡

ሁለቱ ተቋማት በጋራ በሆኑ ጉዳዮች ተባብሮ ለመስራት የሚያስችል የጋራ መግባቢያ ስምምነት ሰነድ ተፈራርመዋል። የጋራ ክንውን እቅድ አዘጋጅቶ ለመስራትም ስምምነት ላይ መድረሳቸው ተገልጿል።
@BBC_AMHARIC
ለአራት አመት በማሊ የታጣቂ ቡድን ታግተው የነበሩት የ75 አመቷ ፈረንሳዊት ሀገራቸው ሲገቡ ፕሬዝዳንት ማክሮን አቀባበል አድርገውላቸዋል።

ሶፊ ፒትሮኒን የተባሉ የእርዳታ ድርጅት ሰራተኛ በምእራብ አፍሪካዊቷ ማሊ ከዛሬ አራት አመት በፊት ለስራ በሚንቀሳቀሱበት ወቅት ታፍነው የተወሰዱ ሲሆን ሰሞኑ ከታገቱበት ስፍራ ተለቀው ዛሬ በሰሜን ምእራብ ፈረንሳይ በሚገኘው ቪላ ኮብሌይ ኤርፖርት ሲደርሱ የሀገሪቱ ፕሬዝዳንት ኢማኑኤል ማክሮንን ጨምሮ ቤተሰቦቻቸው አቀባበል አድርገውላቸዋል።

ሶፊ ፒትሮኒን ከአራት ጣልያኖች ጋር የታገቱና አብረው የተለቀቁ ሲሆን ከታገቱበት ለመለቀቅ ገንዘብ ይከፈል አይከፈል የተነገረ ነገር ባይኖርም በታገቱበት ወቅት በአንድ ቦታ ተወስኖ ከመቀመጥ ውጭ ድብደባም ይሁን ስድብ አልደረሰብኝም ብለዋል ሲል አልጀዚራ ዘግቧል።
@BBC_AMHARIC
ይህ በማህበራዊ ሚዲያ የተሰራጨው ፎቶ እጅግ ልብ ይነካል ።የአንበጣ መንጋ ማሳቸውን ሲያወድም እኚህ ኢትዮጵያዊ ገበሬ በጨርቅ በማባረር ሲጮሁ ይታያል ።አብዛኞቻችን ይሄን ጩሀት አልሰማን ይሆናል ። ግን እወነታው በአንበጣ ተወረናል! ገበሬው ተጨንቋል! !
ጠ/ሚ ዐቢይ ከእስራኤሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያሚን ኔታንያሁ ጋር በስልክ ተወያዩ

አዲስ አበባ ፣ መስከረም 29፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ከእስራኤሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያሚን ኔታንያሁ ጋር የስልክ ውይይት አደረጉ፡፡ ውይይቱ በዋናነት በቀጠናዊ ጉዳዮች ላይ ያተኮረ እንደነበር ጠቅላይ ሚኒስትር ኔታንያሁ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው አስፍረዋል፡፡ በውይይታቸው ወቅት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ እስራኤል ከተባበሩት ዓረብ ኢሚቴቶች እና ባህሬን ጋር ለደረሰችው ታሪካዊ ስምምነት ለእስራኤሉ ጠቅላይ ሚኒስትር የእንኳን…

https://www.fanabc.com/ጠ-ሚ-ዐቢይ-ከእስራኤሉ-ጠቅላይ-ሚኒስትር-ቤ/