ከሀሰተኛ መረጃ እራሳችሁን ጠብቁ!
'የመሰቦ ሲሚንቶ ፋብሪካ' ዋና ስራ አስከያጅ አቶ ክብረአብ ተወልደ በቤታቸው ውስጥ እያሉ ከ30 ሚልዮን ብር ካሽ ጋር በቁጥጥር ስር እንደዋሉ ተደርጎ በማህበራዊ ሚዲያ የሚሰራጨው መረጃ #ሀሰተኛ ነው።
አቶ ክብረአብ ተወልደ ፥ መረጃው ውሸት እንደሆነ፣ እሳቸው በስራ ላይ እንደሚገኙና አሁንም ወደፊትም እንዲህ አይነት ነገር እንደማይኖር በራሳቸው እርግጠኛ መሆናቸውን ለአሶሼትድ ፕሬስ ጋዜጠኛው ኤልያስ መሰረት ተናግረዋል።

#Ethiopia : የኦሮሞ ህዝብ የሚመራው አካል እጦት ነው እንጂ ለረጅም ግዜ በጭቆና ቀንበር ስር መኖር የሚገባው አልነበረም:: መኖርን አብሮ መኖርን እንዲሁም ድል ማድረግን የሚያውቅ ህዝብ ነው:: ይህን ከመሰለ መሀበረሰ የወጡ ጥቂት ገለሰቦች ናቸው የኦሮሞን ድል ጥላሸት ለመቀባት የሚሰሩት:: ከአሁን በኃላ ግን ይህን ማድረግ አይችሉም:: እነዚህ ሰዎች ለህወሓት ተላላኪ ሆነው ህዝቡን መበጥበጥ አይችሉም:: ህወሓትም የኦሮሞን መሬት መልሶ አይረግጥም:: እንደነዚህ አይነት ሀይሎች ተሸንፈዋል ሽንፈታቸውም ይቀጥላል:: ህዝባችን የአካባቢውን ሰላም መጠበቅ አለበት:: በጎሳ በሀይማኖት ሊከፋፍሉት የሚፈልጉን መከላከልም ይጠበቅበታል::
አቶ ሽመልስ አብዲሳ የኦሮሚያ ክልል ምክትል ፕሬዘዳንት ዛሬ በጨፌ ኦሮሚያ 12 ተኛ መደበኛ ጉባኤ ላይ ከተናገሩት የወሰድኳት ነች::

ከ330 ሺሕ በላይ ሥራዎች ከስመዋል!
በተጠናቀቀው በጀት ዓመት ከ3.3 ሚሊዮን በላይ ሥራዎች ሊፈጠሩ ችለው የነበር ቢሆንም በኮሮና ወረርሽኝ ምክንያት ከ330 ሺሕ በላይ ሥራዎች መክሰማቸው እንደተረጋገጠ የሥራ ፈጠራ ኮሚሽን ይፋ አድርጓል፡፡ እነዚህ የሥራ ዕድሎች ዘንድሮ ተፈጥረው ከሰባት ወራት ቆይታ በኋላ ለመክሰም የተገደዱ ናቸው፡፡
ይህ ይባል እንጂ እስካሁን የተፈጠሩት ሦስት ሚሊዮን የሥራ ዕድሎች ምንም እንኳ የታሰበውን አፈጻጸም ለማሳካት ቢያስችሉም፣ ከሚያስገኙት ገቢ መጠንና ከሚሰጡት የሥራ ዋስትና አኳያ ብዙ ችግሮች እንዳሉባቸው ነው የተነገረው፡፡
በመጪዎቹ አምስት ዓመታት ውስጥ 14 ሚሊዮን የሥራ ዕድሎችን ለመፍጠር፣ በአሥር ዓመታት ውስጥም ለ20 ሚሊዮን ዜጎች የሥራ ዕድሎችን ለመፍጠር እቅድ ተይዟል፡፡ የሥራ ፈጠራ ኮሚሽን ኮሚሽነር ኤፍሬም ተክሌ (ዶ/ር) ከመጪው ዓመት ጀምሮ ሥራ ላይ ሊውል የሚችል 384 ሚሊዮን ዶላር የገንዘብ ድጋፍ ከውጭ መገኘቱን ገልጸዋል፡፡
(Reporter)

ባለፉት ቀናት መደበኛ ስብሰባውን ሲያካሂድ የቆየው ጨፌ ኦሮሚያ 90 ቢሊየን ብር ሆኖ የቀረበለትን የ2013 የኦሮሚያ ክልል መንግስት በጀት በሙሉ ድምጽ አጽድቆታል። ጨፌው የ2012 በጀት ዓመት 8 ነጥብ 7 ቢሊየን ብር ተጨማሪ በጀትን ከተመለከተ በኋላም በሙሉ ድምጽ አጽድቋል። በተጨማሪም የቀረቡለትን የተለያዩ አመራሮችም ሹመትም ተቀብሎ አጽቋል።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ሙሉ በሙሉ በኢትዮጵያ የተገጣጠመ የመጀመሪያ በኤሌክትሪክ ኃይል አማካኝነት የሚሠራ መኪና ስጦታ ተበረከተላቸው።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ዛሬ ጠዋት በኤሌክትሪክ ኃይል አማካኝነት የሚሠራ እና የሀዩንዳይ ኩባንያ አካል በሆነው ማራቶን ሞተርስ ሙሉ በሙሉ በኢትዮጵያ የተገጣጠመ የመጀመሪያ መኪና በስጦታነት ተቀብለዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ለሀዩንዳይ ፕሬዚደንት ባቀረቡት ጥያቄ መሠረት፣ በኢትዮጵያ የኤሌክትሪክ መኪናዎችን የመገጣጠም ሥራ መጀመሩን የጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/ቤት አስታውቋል።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ሙሉ በሙሉ በባትሪ የሚሠራውን እና የካርቦን ልቀት የማያስከትለውን መኪና በተቀበሉበት ወቅት፣ ይህን የመሳሰሉ የሙዓለ ነዋይ ፍሰት የሚያስገኙ ሥራዎች በሀገራችን የአየር ንብረት ለውጥን ለመቋቋም እና ለአረንጓዴ ልምላሜ ከፍተኛ ድጋፍ እንደሚያደርጉ ተናግረዋል።
ይህን በኢትዮጵያ የተገጣጠመ መኪና ለየት የሚያደርገው፣ የተለየ የኃይል ማደያ ሳያስፈልግ በየትኛውም ቦታ ባትሪውን ለመሙላት መቻሉ መሆኑ ተገልጿል።
አዲስ ሚዲያ ኔትዎርክ(ኤ ኤም ኤን) ሐምሌ 20፤2012

ሀብታቸውን ያላስመዘገቡ የመንግስት ተሿሚዎች ስም ዝርዝር ለህዝብ ይፋ ያደረጋል ተባለ
#Ethiopi : የፌደራል የሥነምግባር እና የፀረ-ሙስና ኮሚሽን 90 በመቶ የሚሆኑ የመንግስት ተሿሚዎች ፣ የህዝብ ተመራጮች እና ሌሎች የሀብት ምዝገባዉ የሚመለከታቸዉ አካላት ሀብትና የገቢ ምንጭ ማስመዝገባቸውን አስታውቋል፡፡
በኮሚሽኑ የሀብት ማሳወቅና ምዝገባ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ መስፍን በላይነህ ለብስራት ሬድዮ እንደተናገሩት በበጀት ዓመቱ በሀገር አቀፍ ደረጃ የ84 ሺህ 460 ሀብት አስመዝጋቢዎችን ሀብትና የገቢ ምንጭ ለመመዝገብ ታቅዶ ይገኛል፡፡
ኮሚሽኑ የሀብት ምዝገባዉ መጠናቀቂያ ቀን እስከ ሰኔ 30 ቀን 2012 ዓ.ም ድረስ መሆኑን ገልፃ የነበረ ቢሆንም ፤ በሀገሪቱ ተፈጥሮ በነበረው አለመረጋጋት ሀብታቸውን ማስመዝገብ ያልቻሉ አካላት አስከ ሀምሌ 30 ቀን 2012 መራዘሙን ይፋ አድርጓል፡፡
በነዚህ ቀሪ ቀናቶች ምዝገባውን ያልከወኑ 10 በመቶ የመንግስት ተሿሚዎች ሃብታቸውን እንዲያስመዘግቡ ጥሪ ቀርቧል፡፡
አንደ አቶ ተስፋዬ ማብራሪያ እነዚህ ተሿሚዎች በስምም ሆነ በተቋማቸው የተለዩ በመሆናቸው ደብዳቤ እንዲደርሳቸው ተደርጓል፡፡ ይህንኑ በመገዘብ በቀሩት አጭር ቀናት ውስጥ ሀብታቸውን የማያስመዘግቡ ከሆነ ኮሚሽኑ ስም እየተጠቀሰ ለህዝብ ይፋ ያደረጋል ብለዋል፡፡
በትግስት ላቀው

የኦሮሚያ ክልል ምክር ቤት (ጨፌ ኦሮሚያ) ለ2 ቀናት ያካሄደውን ስብሰባ የተለያዩ ውሳኔዎችን ማምሻውን አጠናቋል።
ምክር ቤቱ የኦሮሚያ ክልል የ2013 አጠቃላይ በጀት 90 ቢሊየን ብር እንዲሆን የቀረበውን የውሳኔ ሃሳብ በሙሉ ድምፅ አፅድቋል።
የተለያዩ ሹመቶችም ለጨፌው አባላት ቀርበው ፀድቀዋል።
በዚሁ መሠረት ዶ/ር መንግስቱ በቀለ የኦሮሚያ ጤና ቢሮ ሃላፊ፣ አቶ ታረቀኝ ጉሉልታ ደግሞ የክልሉ የመሬት አስተዳደር እና አጠቃቀም ቢሮ ሃላፊ ሆነዋል።
ወ/ሮ መስከረም ከበደ የኦሮሚያ ገቢዎች ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር፣ አቶ አህመድ ሰይድ የክልሉ ህብረት ስራ ማስፋፊያ ኤጀንሲ ዋና ዳይሬክተር እንዲሆኑ በምክር ቤቱ ተሹመዋል።
አቶ ፍቃዱ ተሠማ፣ አቶ ሣዳት ነሻ እና አቶ አወል አብዱልሃኪም ደግሞ ክልሉን በፌዴሬሽን ምክር ቤት ወክለው እንዲሰሩ መርጧቸዋል፡፡
3ቱ ሰዎች ከአሁን ቀደም ክልሉን በፌ/ም/ቤት ወክለው የነበረው በትምህርት ምክንያት ወደ ተለያዩ ሀገራት የሄዱን ይተካሉ ተብሏል።
ምክር ቤቱ የኦሮሚያ የመጠጥ ውሃ እና የፍሳሽ አገልግሎት አዋጅን ጨምሮ የተለያዩ ህጎችንም አፅድቋል።
(ሸገር fm)

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ከኢንቨስትመንት እና የሥራ ዕድል ፈጠራ ብሔራዊ ኮሚቴ ጋር ተወያዩ
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ከኢንቨስትመንት እና የሥራ ዕድል ፈጠራ ብሔራዊ ኮሚቴ ጋር ተወያይተዋል። በውይይቱም ያለፈውን ዓመት የሥራ ዕድል ፈጠራ ክንዋኔዎች የተገመገሙ ሲሆን ለቀጣዩ ዓመትም ጠቅላይ ሚኒስትሩ አቅጣጫ ሰጥተዋል።
የበጎ ፈቃደኝነት ማስፋት፣ በጎ ፈቃደኝነትን ከቅጥር ቅድመ ሁኔታዎች መካከል አንዱ ማድረግ፣ የአውቶማቲክ ስልቶች ትግበራን ማበረታታት፣ የፋይናንስ ዘርፉን ለወጣቶች፣ ለአርሶ አደሮች እና አነስተኛ ትርፍ በሚያስገኙ ሥራዎች ለተሠማሩ ድጋፍ ለመስጠት በሚያስችል መልክ ማጠናከር ከተጠቀሱት አቅጣጫዎች መካከል ይገኙበታል።

የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ምክር ቤት ለ2013 በጀት የቀረበውን ከ4 ነጥብ 4 ቢሊዮን ብር በላይ አአጽድቋል።የምክር ቤቱ 11ኛ መደበኛ ጉባዔ የተለያዩ የማሻሻያ አዋጆችን በማጽደቅ ተጠናቋል፡፡
ለበጀት ዓመቱ እንዲውል ከተያዘው በጀት ውስጥ 1 ቢሊዮን 9 ሚሊዮን 557 ሺህ 048 የሚሆነው በክልሉ ከሚሰበሰብ ገቢ የሚሸፈን ነው።
3 ቢሊዮን 50 ሚሊዮን 63 ሺህ 244 የሚሆነው ደግሞ ከማዕከላዊ መንግስት ግምጃ ቤት በድጎማ እና ቀሪው ደግሞ ከተለያዩ ተቋማት የውስጥ ገቢ፣ ከዘላቂ ልማት ግቦች ማሳኪያ እንዲሁም ከውጪ ከሚገኝ ዕርዳታ የሚገኝ መሆኑ ተገልጿል፡፡

በቻይና የአሜሪካ ዲፕሎማቶች ከሀገሪቱ መውጣት ጀምረዋል፡፡
ቻይና በቼን-ግዱ የሚገኝው የአሜሪካ ቆንሱል መዝጋቷን ተከትሎ ነው ዲፕሎማቶቹ ከሀገሪቷ መውጣት የጀመሩት፡፡
ሀገሪቷ ቆንሱሉን እንዲዘጋ ትዛዝ ያስተላለፈችው፣ አሜሪካ በሂውስተን የሚገኝውን የቻይና ቆንሱል መዝጋቷን ተከትሎ ነው፡፡
ዲፕሎማቶቹ በቼንግዱ የአሜሪካ ቆንስል ቅጥር ግቢ ለቀው ሲወጡ የሚያሳይ ተንቀሳቃሽ ምስል በተለያዩ የማህበራዊ ሚዲያዎች ላይ ተለቋል፡፡
በቼንግዱ የሚገኙ ያካባቢው ነዋሪዎችም ፣ዲፕሎማቶቹ አካባቢውን ለቀው ሲወጡ በግል ስልካቸው ፎቶ ሲነሱም እንደነበረ ነው ቢቢሲ ያተተው፡፡
የፕሬዝደንት ዶናልድ ትራምፕ አስተዳደር ከቤጂንግ መንግሥት ጋር፣ በንግድ፣ በኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ እና በሆንግ ኮንግ ጉዳዮች በተደጋጋሚ ሲነታረክ ይስተዋላል።
አሜሪካ ቆንሱሉን መዝጋቷን ተከትሎ፣ ቻይና በወቅቱ ሀገሪቷ የፈጸመችው ድርጊት አለም አቀፍ ህግን የጣሰ እና የሁለቱን ሀገራት ግኑኝነት ያሻከረ ድርጊት ነዉ ማለቷ ይታወሳል፡፡

ኢትዮጵያ የታጁራ ወደብን መጠቀም ጀመረች
የኢትዮጵያ ባህር ትራንስፖርት እና ሎጅስቲክስ አገልግሎት ድርጅት የታጁራን ወደብን በይፋ መጠቀም ጀምሪያለው ብሏል፡፡ የመጀመሪያዋ መርከብም የድንጋይ ከሰል ጭነት ጭና በወደቡ እያራገፈች ነው ሲሉ የድርጅቱ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ሮባ መገርሳ ለካፒታል ገልጸዋል፡፡
ወደቡ ለጥቅል ጭነት/ general cargo እንቅስቃሴ ማገልገል ቢችልም በጅቡቲ በኩል ያለው የመንገድ ግንባታ ባለመጠናቀቁ ከ 3 አመት በፊት የተገነባው ወደብ ወደስራ መግባት ሳይችል ቆይቶ ነበር፡፡
ሆኖም ባለፈው ህዳር 120 ኪ.ሜ የሚረዝመው እና ታጁራን ከ ኢትዮጵያ ድንበር በበልሆ በኩል የሚያገናኘው የመንገድ ግንዳታ መጠናቀቁ ወደቡን ወደስራ እንዲገባ ማድረግ አስችሏል፡፡የ120ኪ.ሜትሩ የታጁራ በልሆነ መንገድ በኩዌት ፈንድ ድጋፍ በ156 ሚሊየን ዶላር የተገነባ ነው፡፡
(CAPITAL )

ወደ ኢትዮጵያ ለመምጣት ለምትፈልጉ በሙሉ!
(የኢትዮጵያ አየር መንገድ)
ወደ ኢትዮጵያ ለመምጣት ሲያቅዱ ከመግባትዎ በፊት ባሉት 5 ቀናት ውስጥ ተመርምረው ከኮቪድ-19 ነፃ መሆንዎትን የሚገልፅ የምርመራ ውጤት (PCR SAR-CoV) መያዝዎን ያረጋግጡ።
ቀናቱም ለምርመራ ናሙና ከሰጡበት ቀን አንስቶ ቦሌ አለም አቀፍ ኤርፖርት እስከደረሱበት ሰዓት የሚታሰብ ይሆናል።
እንዲሁም በቦሌ አለም አቀፍ የመንገደኞች ማስተናገጃ እንደደረሱ የኮቪድ ምርመራ ተደርጎልዎት ለ14ቀናት በቤትዎ እንዲቆዩ የሚያደርግ መመሪያም ወጥቷል።
ከኮቪድ 19 ነፃ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ ማስረጃ ያልያዙ መንገደኞች ለ7 ቀናት በአስገዳጅ ለይቶ ማቆያ ውስጥ በራሳቸው ወጪ እንዲቆዩ ይደረጋል።
ከላይ የተዘረዘሩት መመሪያዎች ትራንዚት መንገደኞችን አይመለከትም።
ለተጨማሪ መረጃ : www.ethiopianairlines.com/aa/travel-updates/updates-on-covid-19(coronavirus)
@fana90_tv

#UPDATE
በኮሮና ቫይረስ መያዙ የተጠረጠረው የመጀመሪያው ሰሜን ኮሪያዊ #ነጻ መሆንኑን በምርመራ ማረጋገጧን ደቡብ ኮሪያ ገልፃለች።
ግለሰቡ ከሰሜን ኮሪያ ወደ ደቡብ ኮሪያ ከሦስት (3) ዓመታት በፊት መምጣቱ የተገለፀ ሲሆን ባለፈው ሳምንት ግን ወደ ትውልድ አገሩ ተመልሶ ነበር።
ከደቡብ ኮሪያ ወደ ሰሜን ኮሪያ የተሻገረው በደቡባዊ ደሴቲ አካባቢ በሚገኝ የቱቦ ማስተላለፊያ ውስጥ በመሹለከለክና በመዋኘት እንደነበር #BBC አስነብቧል።

2 ልጆቿን በኮቪድ-19 ያጣችው እናት!
ፍሎሪዳ ውስጥ ነዋሪ የሆነችው ' ሞንቴ ሂክስ ' የምትባል እናት በኮሮና ቫይረስ ምክንያት የሁለት (2) ልጆቿን ህይወት አጥታለች።
የመጀመሪያው የ20 ዓመት ልጇ ሲሆን እሱ ህይወቱ ካለፈ ከ11 ቀን በኃላ ደግሞ የ22 ዓመት ሴት ልጇን በዚህ አስከፊ በሽታ ተነጥቃለች።
እስካሁን ድረስ እጅግ መሪር በሆነ ሀዘን ውስጥ የምትገኘው ሞንቴ ሂክስ ከ NBC ጋር በነበራት ቃለ መጠይቅ ' ሰዎች እራሳቸውን እንዲጠብቁ ፣ ወረርሽኙን እንደቀልድ እንዳያዩት ' መክራለች።