#Ethiopia : Breaking News Loading........ በጃል ዳኦድ ኢብሳ የሚመራው ኦነግ ለሁለት ተከፍለ:: ጉለሌ የሚገኘው የኦነግ ቢሮ እርስ በእርስ ችግር በተፈጠረ አለመግባባት በፌደራል ፖሊስ ተከቧል ተጨማሪ መረጃዎችን ይዤ እመለሳለው::
#Ethiopia : ኦነግ ለሁለት ተሰነጠቀ❗
የኦነግ አባል የሆኑት
1.አራርሶ ቢቂላ
2.ኢብሳ ነጋዋ
3.አቶምሳ ኩምሳ
4.ጀቤሳ ጋቢሳ
5.ቶሌራ አዳባ
6.ዋቆ ኬኔ
የሚባሉት ለዛሬ እሁድ ስብሰባ ጠርተው ነበር ይሁን እንጂ የተቀረው የኦነግ አመራር በዳዉድ ኢብሳ የሚመራው ከላይ የተጠቀሱት የኦነግ አመራሮች ወደ ስብሰባ አዳራሽ ማለትም ጉለሌ የሚገኘው እንዳይገቡ በቄሮዎችን አስደርገዋል።
አሁን ላይ ጉለሌ የሚገኘው የኦነግ ጽህፈት ቤት ውዝግብ ተፈጥሯዊ አከባቢውም በአሁኑ ሰዓት በፌዴራል ፖሊሶች እየተጠበቀ ይገኛል።

ሰበር ዜና‼️
#Ethiopia : የመሰቦ ሲሚንቶ ስራአስከያጅ የዓድዋው ተወላጅ አቶ ክብረአብ ተስፋማርያም በቤቱ ውስጥ እያለ በካሽ ከነ 30 ሚልዮን ብሩ በቁጥጥር ስር ውለዋል!!
የማነህ ንጉሴ (ፈንቅል)

#Ethiopia : የአቶ ዳውድ ኢብሳ ቤት ለደህንናታቸው በማለት ቤታቸው በፀጥታ ሀይሎች እየተጠበቀ ነው ።ከቤት እንዲቆዩም ተደርገዋል። የኦሮሞ ነፃ አውጪ ግንባር ሊቀ መንበር አቶ ዳውድ ኢብሳ ቤታቸው በፀጥታ ሀይሎች እየተጠበቀ ሲሆን ስልካቸውም ዝግ እንደሆነ እና ከቤት መውጣትም ሆነ እሳቸውምን ለመጠየቅ ወደ ቤታቸው መዝለቅ እንደማይቻል ጋዜጠኛ ዳዊት አንደሻው በፌስ ቡኩ የቅርብ ቤተሰቦቻቸውን አዋርቶ ዛሬ ፅፏል።
Good news የፌደራል መንግስት፣ ብልጽግና ፓርቲና የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ኃላፊዎች ከትግራይ ተወላጅ ባለሃብቶች ጋር ተወያዩ
#Ethiopia : የፌደራል መንግስት፣ የብልጽግና ፓርቲና የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ኃላፊዎች ከትግራይ ተወላጅ ባለሃብቶች ጋር በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ ውይይት አካሂደዋል።
በውይይቱ ላይም "የፌደራል መንግስት ጦርነት ሊከፍትብን ነው፣ መንግስት የትግራይ ክልልንና ተወላጆችን እያገለለ ነው፣ ወዘተ" የሚሉ የፕሮፖጋንዳ ትርክቶች ለፖለቲካ ፍጆታ ከመዋላቸው ባለፈ መሬት ላይ የሌሉ መሆናቸውን በመተማመን ላይ መደረሱን የአዲስ አበባ ብልፅግና ፓርቲ ጽህፈት ቤት ያወጣው መረጃ ያመልታል።
ከዚህ በተጨማሪም ማንኛውም በህጋዊ መንገድ ልማት ላይ፣ የሀገር እድገት ላይ መዋእለ ንዋያቸውን የሚያፈሱ የትግራይ ባለሀብቶች መንግስት ከጎናቸው እንደሚቆምም ቃል እንደተገባላቸውም ተገልጿል።
ይህን ጉዳይ እየተከታተለ የሚያስፈፅም ተወካዮች መሰየማቸውም ነው የተገለፀው።
“አገር ሊፈርስ ነው ጓዝህን ጠቅልለህ ወደ ክልልህ ግባ” የሚለውን ውዥንብር ፕሮፖጋንዳ ሳይታለሉ ራሳቸውን አረጋግተው ሊሰሩ እንደሚገባም ተወያይቷል።
“ይህ በንዲህ እንዳለ፣ ኢትዮጵያ የሁሉም አገር ናት፤ ሁላችንም ሰርተን የምንለወጥባት ሀገር እንጂ የምንሸማቐቅባት ሀገር አለመሆንዋንም ከግንዛቤ ሊገባ ይገባል” ተብሏል በውይይት መድረኩ ላይ።
#FBC

#Ethiopia : ዛሬ በአዲስ አበባ ጉለሌ የአንድ የተቃዋሚ ፖርቲ የእርስ በእርስ ኩዴታ ከሽፏል:: ኦነግን ለአመታት የመሩትን ጃል ዳኦድ ኢብሳን አንስቶ በቦታው ጃል አራርሶ ቢቂላን ለመተካት የተደረገው የውስጥ ሽኩቻ ይለ ጥፋትና መገዳደል ከሽፏል:: ፌደራል ፖሊስ የኦነግን ቢሮና የጃል ዳኦድ ኢብሳን ቤት በመክበብ ጥበቃ በማድረግ ላይ ነው::
ምስል ከፋይል
ምስል ከፋይል
#Ethiopia : ህጥሴሴሴሴ ይድፋህ ለምትሉኝ አሜን አብሮ ይድፋን ይማረህ ለምትሉኝ አሜን አብሮ ይማረን! የሪፐፕሊካን ጋርድ የሰው ነፍስ ሳይጠፋ በጉለሌና በጃል ዳኦድ ኢብሳ ቤት በመድረስ ያለውን ችግር በስልትና በብልሀት ተቆጣጥሮታል::
#Ethiopia : ዲሞክራሲ የማይገባውን በቦሌም በባሌም አስገብተህ መከራህን በላህ አይደል? አይዞን ብዙሀኑ ኢትዮጵያዊያም ከጎንህ ነው!!
#AbiyMustGoForward
#AbiyMustGoForward
#Coronavirus : በተባበሩት አረብ ኤሚሬቶች ትናንት የኮሮና ተሕዋሲ ከተገኘባቸው 13 ሰዎች 2ቱ ኢትዮጵያውያን መሆናቸውን የአገሪቱ ጤና ጥበቃ ሚኒስቴር አስታወቀ። ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ እንዳለው ተሕዋሲው የተገኘባቸው 13ት ሰዎች በሙሉ ከሌላ አገር የተጓዙ ናቸው።
የጤና ጥበቃ ምኒስትር ድዔታ ዶክተር ሊያ ታደሰ መረጃው እንደደረሳቸው አረጋግጠው ጉዳዩን እየተከታተሉ መሆኑን ገልጸዋል። የአረብ ኤሚሬቶች የጤና ጥበቃ ሚኒስቴር «ሁሉም ለ24 ሰዓታት ክትትል እየተደረገላቸው ሲሆን በጥሩ ሁኔታ ላይ ይገኛሉ» ብሏል።
Via Eshete Bekele

ከሀሰተኛ መረጃ እራሳችሁን ጠብቁ!
'የመሰቦ ሲሚንቶ ፋብሪካ' ዋና ስራ አስከያጅ አቶ ክብረአብ ተወልደ በቤታቸው ውስጥ እያሉ ከ30 ሚልዮን ብር ካሽ ጋር በቁጥጥር ስር እንደዋሉ ተደርጎ በማህበራዊ ሚዲያ የሚሰራጨው መረጃ #ሀሰተኛ ነው።
አቶ ክብረአብ ተወልደ ፥ መረጃው ውሸት እንደሆነ፣ እሳቸው በስራ ላይ እንደሚገኙና አሁንም ወደፊትም እንዲህ አይነት ነገር እንደማይኖር በራሳቸው እርግጠኛ መሆናቸውን ለአሶሼትድ ፕሬስ ጋዜጠኛው ኤልያስ መሰረት ተናግረዋል።

#Ethiopia : የኦሮሞ ህዝብ የሚመራው አካል እጦት ነው እንጂ ለረጅም ግዜ በጭቆና ቀንበር ስር መኖር የሚገባው አልነበረም:: መኖርን አብሮ መኖርን እንዲሁም ድል ማድረግን የሚያውቅ ህዝብ ነው:: ይህን ከመሰለ መሀበረሰ የወጡ ጥቂት ገለሰቦች ናቸው የኦሮሞን ድል ጥላሸት ለመቀባት የሚሰሩት:: ከአሁን በኃላ ግን ይህን ማድረግ አይችሉም:: እነዚህ ሰዎች ለህወሓት ተላላኪ ሆነው ህዝቡን መበጥበጥ አይችሉም:: ህወሓትም የኦሮሞን መሬት መልሶ አይረግጥም:: እንደነዚህ አይነት ሀይሎች ተሸንፈዋል ሽንፈታቸውም ይቀጥላል:: ህዝባችን የአካባቢውን ሰላም መጠበቅ አለበት:: በጎሳ በሀይማኖት ሊከፋፍሉት የሚፈልጉን መከላከልም ይጠበቅበታል::
አቶ ሽመልስ አብዲሳ የኦሮሚያ ክልል ምክትል ፕሬዘዳንት ዛሬ በጨፌ ኦሮሚያ 12 ተኛ መደበኛ ጉባኤ ላይ ከተናገሩት የወሰድኳት ነች::

ከ330 ሺሕ በላይ ሥራዎች ከስመዋል!
በተጠናቀቀው በጀት ዓመት ከ3.3 ሚሊዮን በላይ ሥራዎች ሊፈጠሩ ችለው የነበር ቢሆንም በኮሮና ወረርሽኝ ምክንያት ከ330 ሺሕ በላይ ሥራዎች መክሰማቸው እንደተረጋገጠ የሥራ ፈጠራ ኮሚሽን ይፋ አድርጓል፡፡ እነዚህ የሥራ ዕድሎች ዘንድሮ ተፈጥረው ከሰባት ወራት ቆይታ በኋላ ለመክሰም የተገደዱ ናቸው፡፡
ይህ ይባል እንጂ እስካሁን የተፈጠሩት ሦስት ሚሊዮን የሥራ ዕድሎች ምንም እንኳ የታሰበውን አፈጻጸም ለማሳካት ቢያስችሉም፣ ከሚያስገኙት ገቢ መጠንና ከሚሰጡት የሥራ ዋስትና አኳያ ብዙ ችግሮች እንዳሉባቸው ነው የተነገረው፡፡
በመጪዎቹ አምስት ዓመታት ውስጥ 14 ሚሊዮን የሥራ ዕድሎችን ለመፍጠር፣ በአሥር ዓመታት ውስጥም ለ20 ሚሊዮን ዜጎች የሥራ ዕድሎችን ለመፍጠር እቅድ ተይዟል፡፡ የሥራ ፈጠራ ኮሚሽን ኮሚሽነር ኤፍሬም ተክሌ (ዶ/ር) ከመጪው ዓመት ጀምሮ ሥራ ላይ ሊውል የሚችል 384 ሚሊዮን ዶላር የገንዘብ ድጋፍ ከውጭ መገኘቱን ገልጸዋል፡፡
(Reporter)

ባለፉት ቀናት መደበኛ ስብሰባውን ሲያካሂድ የቆየው ጨፌ ኦሮሚያ 90 ቢሊየን ብር ሆኖ የቀረበለትን የ2013 የኦሮሚያ ክልል መንግስት በጀት በሙሉ ድምጽ አጽድቆታል። ጨፌው የ2012 በጀት ዓመት 8 ነጥብ 7 ቢሊየን ብር ተጨማሪ በጀትን ከተመለከተ በኋላም በሙሉ ድምጽ አጽድቋል። በተጨማሪም የቀረቡለትን የተለያዩ አመራሮችም ሹመትም ተቀብሎ አጽቋል።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ሙሉ በሙሉ በኢትዮጵያ የተገጣጠመ የመጀመሪያ በኤሌክትሪክ ኃይል አማካኝነት የሚሠራ መኪና ስጦታ ተበረከተላቸው።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ዛሬ ጠዋት በኤሌክትሪክ ኃይል አማካኝነት የሚሠራ እና የሀዩንዳይ ኩባንያ አካል በሆነው ማራቶን ሞተርስ ሙሉ በሙሉ በኢትዮጵያ የተገጣጠመ የመጀመሪያ መኪና በስጦታነት ተቀብለዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ለሀዩንዳይ ፕሬዚደንት ባቀረቡት ጥያቄ መሠረት፣ በኢትዮጵያ የኤሌክትሪክ መኪናዎችን የመገጣጠም ሥራ መጀመሩን የጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/ቤት አስታውቋል።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ሙሉ በሙሉ በባትሪ የሚሠራውን እና የካርቦን ልቀት የማያስከትለውን መኪና በተቀበሉበት ወቅት፣ ይህን የመሳሰሉ የሙዓለ ነዋይ ፍሰት የሚያስገኙ ሥራዎች በሀገራችን የአየር ንብረት ለውጥን ለመቋቋም እና ለአረንጓዴ ልምላሜ ከፍተኛ ድጋፍ እንደሚያደርጉ ተናግረዋል።
ይህን በኢትዮጵያ የተገጣጠመ መኪና ለየት የሚያደርገው፣ የተለየ የኃይል ማደያ ሳያስፈልግ በየትኛውም ቦታ ባትሪውን ለመሙላት መቻሉ መሆኑ ተገልጿል።
አዲስ ሚዲያ ኔትዎርክ(ኤ ኤም ኤን) ሐምሌ 20፤2012

ሀብታቸውን ያላስመዘገቡ የመንግስት ተሿሚዎች ስም ዝርዝር ለህዝብ ይፋ ያደረጋል ተባለ
#Ethiopi : የፌደራል የሥነምግባር እና የፀረ-ሙስና ኮሚሽን 90 በመቶ የሚሆኑ የመንግስት ተሿሚዎች ፣ የህዝብ ተመራጮች እና ሌሎች የሀብት ምዝገባዉ የሚመለከታቸዉ አካላት ሀብትና የገቢ ምንጭ ማስመዝገባቸውን አስታውቋል፡፡
በኮሚሽኑ የሀብት ማሳወቅና ምዝገባ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ መስፍን በላይነህ ለብስራት ሬድዮ እንደተናገሩት በበጀት ዓመቱ በሀገር አቀፍ ደረጃ የ84 ሺህ 460 ሀብት አስመዝጋቢዎችን ሀብትና የገቢ ምንጭ ለመመዝገብ ታቅዶ ይገኛል፡፡
ኮሚሽኑ የሀብት ምዝገባዉ መጠናቀቂያ ቀን እስከ ሰኔ 30 ቀን 2012 ዓ.ም ድረስ መሆኑን ገልፃ የነበረ ቢሆንም ፤ በሀገሪቱ ተፈጥሮ በነበረው አለመረጋጋት ሀብታቸውን ማስመዝገብ ያልቻሉ አካላት አስከ ሀምሌ 30 ቀን 2012 መራዘሙን ይፋ አድርጓል፡፡
በነዚህ ቀሪ ቀናቶች ምዝገባውን ያልከወኑ 10 በመቶ የመንግስት ተሿሚዎች ሃብታቸውን እንዲያስመዘግቡ ጥሪ ቀርቧል፡፡
አንደ አቶ ተስፋዬ ማብራሪያ እነዚህ ተሿሚዎች በስምም ሆነ በተቋማቸው የተለዩ በመሆናቸው ደብዳቤ እንዲደርሳቸው ተደርጓል፡፡ ይህንኑ በመገዘብ በቀሩት አጭር ቀናት ውስጥ ሀብታቸውን የማያስመዘግቡ ከሆነ ኮሚሽኑ ስም እየተጠቀሰ ለህዝብ ይፋ ያደረጋል ብለዋል፡፡
በትግስት ላቀው

የኦሮሚያ ክልል ምክር ቤት (ጨፌ ኦሮሚያ) ለ2 ቀናት ያካሄደውን ስብሰባ የተለያዩ ውሳኔዎችን ማምሻውን አጠናቋል።
ምክር ቤቱ የኦሮሚያ ክልል የ2013 አጠቃላይ በጀት 90 ቢሊየን ብር እንዲሆን የቀረበውን የውሳኔ ሃሳብ በሙሉ ድምፅ አፅድቋል።
የተለያዩ ሹመቶችም ለጨፌው አባላት ቀርበው ፀድቀዋል።
በዚሁ መሠረት ዶ/ር መንግስቱ በቀለ የኦሮሚያ ጤና ቢሮ ሃላፊ፣ አቶ ታረቀኝ ጉሉልታ ደግሞ የክልሉ የመሬት አስተዳደር እና አጠቃቀም ቢሮ ሃላፊ ሆነዋል።
ወ/ሮ መስከረም ከበደ የኦሮሚያ ገቢዎች ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር፣ አቶ አህመድ ሰይድ የክልሉ ህብረት ስራ ማስፋፊያ ኤጀንሲ ዋና ዳይሬክተር እንዲሆኑ በምክር ቤቱ ተሹመዋል።
አቶ ፍቃዱ ተሠማ፣ አቶ ሣዳት ነሻ እና አቶ አወል አብዱልሃኪም ደግሞ ክልሉን በፌዴሬሽን ምክር ቤት ወክለው እንዲሰሩ መርጧቸዋል፡፡
3ቱ ሰዎች ከአሁን ቀደም ክልሉን በፌ/ም/ቤት ወክለው የነበረው በትምህርት ምክንያት ወደ ተለያዩ ሀገራት የሄዱን ይተካሉ ተብሏል።
ምክር ቤቱ የኦሮሚያ የመጠጥ ውሃ እና የፍሳሽ አገልግሎት አዋጅን ጨምሮ የተለያዩ ህጎችንም አፅድቋል።
(ሸገር fm)

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ከኢንቨስትመንት እና የሥራ ዕድል ፈጠራ ብሔራዊ ኮሚቴ ጋር ተወያዩ
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ከኢንቨስትመንት እና የሥራ ዕድል ፈጠራ ብሔራዊ ኮሚቴ ጋር ተወያይተዋል። በውይይቱም ያለፈውን ዓመት የሥራ ዕድል ፈጠራ ክንዋኔዎች የተገመገሙ ሲሆን ለቀጣዩ ዓመትም ጠቅላይ ሚኒስትሩ አቅጣጫ ሰጥተዋል።
የበጎ ፈቃደኝነት ማስፋት፣ በጎ ፈቃደኝነትን ከቅጥር ቅድመ ሁኔታዎች መካከል አንዱ ማድረግ፣ የአውቶማቲክ ስልቶች ትግበራን ማበረታታት፣ የፋይናንስ ዘርፉን ለወጣቶች፣ ለአርሶ አደሮች እና አነስተኛ ትርፍ በሚያስገኙ ሥራዎች ለተሠማሩ ድጋፍ ለመስጠት በሚያስችል መልክ ማጠናከር ከተጠቀሱት አቅጣጫዎች መካከል ይገኙበታል።

የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ምክር ቤት ለ2013 በጀት የቀረበውን ከ4 ነጥብ 4 ቢሊዮን ብር በላይ አአጽድቋል።የምክር ቤቱ 11ኛ መደበኛ ጉባዔ የተለያዩ የማሻሻያ አዋጆችን በማጽደቅ ተጠናቋል፡፡
ለበጀት ዓመቱ እንዲውል ከተያዘው በጀት ውስጥ 1 ቢሊዮን 9 ሚሊዮን 557 ሺህ 048 የሚሆነው በክልሉ ከሚሰበሰብ ገቢ የሚሸፈን ነው።
3 ቢሊዮን 50 ሚሊዮን 63 ሺህ 244 የሚሆነው ደግሞ ከማዕከላዊ መንግስት ግምጃ ቤት በድጎማ እና ቀሪው ደግሞ ከተለያዩ ተቋማት የውስጥ ገቢ፣ ከዘላቂ ልማት ግቦች ማሳኪያ እንዲሁም ከውጪ ከሚገኝ ዕርዳታ የሚገኝ መሆኑ ተገልጿል፡፡

በቻይና የአሜሪካ ዲፕሎማቶች ከሀገሪቱ መውጣት ጀምረዋል፡፡
ቻይና በቼን-ግዱ የሚገኝው የአሜሪካ ቆንሱል መዝጋቷን ተከትሎ ነው ዲፕሎማቶቹ ከሀገሪቷ መውጣት የጀመሩት፡፡
ሀገሪቷ ቆንሱሉን እንዲዘጋ ትዛዝ ያስተላለፈችው፣ አሜሪካ በሂውስተን የሚገኝውን የቻይና ቆንሱል መዝጋቷን ተከትሎ ነው፡፡
ዲፕሎማቶቹ በቼንግዱ የአሜሪካ ቆንስል ቅጥር ግቢ ለቀው ሲወጡ የሚያሳይ ተንቀሳቃሽ ምስል በተለያዩ የማህበራዊ ሚዲያዎች ላይ ተለቋል፡፡
በቼንግዱ የሚገኙ ያካባቢው ነዋሪዎችም ፣ዲፕሎማቶቹ አካባቢውን ለቀው ሲወጡ በግል ስልካቸው ፎቶ ሲነሱም እንደነበረ ነው ቢቢሲ ያተተው፡፡
የፕሬዝደንት ዶናልድ ትራምፕ አስተዳደር ከቤጂንግ መንግሥት ጋር፣ በንግድ፣ በኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ እና በሆንግ ኮንግ ጉዳዮች በተደጋጋሚ ሲነታረክ ይስተዋላል።
አሜሪካ ቆንሱሉን መዝጋቷን ተከትሎ፣ ቻይና በወቅቱ ሀገሪቷ የፈጸመችው ድርጊት አለም አቀፍ ህግን የጣሰ እና የሁለቱን ሀገራት ግኑኝነት ያሻከረ ድርጊት ነዉ ማለቷ ይታወሳል፡፡