Best ✍️
9 subscribers
4 photos
3 links
Download Telegram
Voice 005_sd
<unknown>
👍2
🥰1
🔥2🥰1
👍1
ኃጢአት መሥራት በራሱ  አስቀያሚ ነው፤ ኃጢአት ከሠሩ በኋላ በዚያ ኃጢአት መታበይ ግን እጅግ ጽኑ ደዌ ነው፡፡ ጽድቅን ሠርተው በዚያ በሠሩት ጽድቅ ከተኩራሩበት ጽድቁን ያጡታል፡፡ ይህ በኃጢአት ሲኾን ደግሞ የባሰ ነው፤ ወደ ከፋ ጥፋት ይወስደናልና፡፡ ከሠራነው ኃጢአት ይልቅ በሠራነው ኃጢአት መታበይ የሚያመጣው ፍዳ ኵነኔ እጅግ ጽኑ ነውና፡፡

#ቅዱስ_ዮሐንስ_አፈወርቅ
ንስሓና ምጽዋት - በገብረ እግዚአብሔር ኪደ
አንደበታችንን_እንጠብቅ!

አፉ ውስጥ ያለችውን ይህችን ትንሽዬ ብልት መቆጣጠር የማይችል ሰው ህይወቱ በመከራ እና በብስጭት የተሞላ መሆኑ የማይቀር ነው። ከአንደበታችን የሚወጡት ቃላቶች ከሰይፍ የላቀ፣ ከፈንጂ የባሰ ጉዳትን የማስከተል አቅም አላቸው።
#ማሳበባችንን_እንተው!

ማንኛውንም ውድቀት ላለመቀበል ሁሉንም ዓይነት ሰበቦች እና ምክንያቶችን እናመጣለን። ይህም ከስህተታችን እንዳንማር ያደርገናል። ለማሳበብ ለማሳበብማ አዳም ሔዋን ላይ አሳቧል፤ ሔዋንም እባብ ላይ አሳባለች… ታዲያ ማን ከእርግማኑ ተረፈ?።
ፀሎት_አየራችን_ይሁን

ፀሎት ከእግዚአብሔር ጋር የምንገናኝበት ዋነኛው መንገድ ነው… ከፀሎት ጋር ያልተቆራኘ ህይወት አየር በሌለበት ቦታ ላይ እንደመኖር ይቆጠራል! የጭንቀት እና የስጋት ሰንሰለት የትም እንዳንሄድ፣ ምንም ብሩህ ነገር እንዳናስብ ተብትቦ ይይዘናል፤

👉 ፀሎት እንዴት ይህንን የብረት ሰንሰለት ማቅለጥ እንደሚችል እንማርበታለን።
ጭንቀት_በእግዚአብሔር_ላይ_ማመጽ_ነው

አምላካችን እግዚአብሔር ጭንቀታችንን ሁሉ ለእሱ እንድንተው መክሮናል። እኛ ግን ብዙ ጊዜ በጭንቀት ራሳችንን ስናሳምም ነው የምንገኘው። የታዘዝነውን ከማድረግ ይልቅ በተፈጠረብን ችግር አማካይነት ሳናውቀው በተቃውሞ ውስጥ እንገባለን። የጭንቀት መድሃኒቱ የሚያስጨንቀንን ነገር ሁሉ ለአምላካችን መተው ነው።
መድኃኒታችንን_እንዋጥ

ይቅርታ ከብዙ በሽታዎች የሚፈሰው መድኃኒት ነው፡፡ ራሳችንን ከመመረዝ ነጻ ማውጣት የምንችለው በይቅርታ ነው፡፡ ይቅርታ ልክ የተቀደደ ልብስን እንደሚሰፋ የሚያውቅ መርፌ ዓይነት ነው። በየቀኑ የይቅርታን መድኃኒት እየዋጥን መፈወስ ስንችል ለምን ይሆን ራሳችንን የምንመርዘው?

© አቡነ ሺኖዳ ሳልሳዊ

       🌿 @Father_advice🌿 
             ✥••┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈••✥
      ✧━━━━━━━━━━━━━━━━━✧
                 ❍ㅤ    ⎙ㅤ  ⌲     ♡          
             ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ   ˢᵃᵛᵉ   ˢʰᵃʳᵉ  ˡᶦᵏᵉ   
3
በሕይወታችን ፀሀይ ከሚሆኑልን ይልቅ ጨረቃ የሚሆኑልን ሰዎች ያስፈልጉናል ፀሀይ የምትመጣው በቀንነው ብርሃን ሳለ ነው ነጣ ባለጊዜ ንጹሕ በሆንን ጊዜ በፈገግታ ጊዜ ጨረቃ ግን የምትመጣው በጨለማ ነው ቀን ተደብቃ ብትቆይም በማታ በጨለማ ጊዜ ትመጣለች በቸገረን ጊዜ በጠቆርንጊዜ በቆሸሽንጊዜ በተጎሳቆልንጊዜ ወደ አመሻሽ ትመጣለች አዎ በሕይወታችም ትልቅ ቦታ የሚሰጡን ከልብ የሚወድዱን እንደ ጨረቃ ያሉ ሰዎች ናቸው በደስታችን ጊዜ በቀንብርሃን ሳለ በፈገግታችንጊዜ ብዙወዳጆች ይኖሩን ይሆናል እውነተኛ ወዳጅ ግን በደስታጊዜ ብዙ ወዳጆች ባሉንጊዜ ራሱን ባይገልጥም እኛ ባናየውም ቀኑ በመሸ በችግር ጊዜ በጠቆርንጊዜ በሀዘንጊዜ ሁሉም ነገር በጨለመብንጊዜ የሚመጡልን ናቸው የሚደርሱልን እፎይ የሚያሰኙን ናቸው የችግር ጊዜ ወዳጅ አያሳጣን መልካም ማክሰኞ ተመኝሁ
አንድ የራስ ምታት የሚሰማውን ሰው ልታክሙት ትችሉ ይሆናል ነገር ግን የሰውዬው የራስ ምታት ከምን እንደተነሳ በጥልቀት አትመለከቱም ሰውዬው ጫና በዝቶበት ተጨንቆ ተደብቶ ሊሆን ይችላል ምናልባትም ውስጡ ክፉኛ ተጎድቶ ይሆናል ምናልባትም ብዙ ስለሚጨነቅ አዕምሮውን የሚያዝናናበት ጊዜ አላገኘ ይሆናል ስለዚህም የምትሰጡት መድኃኒት ምልክቶቹን የሚያጠፋ ብቻ ነው የሚሆነው ሆኖም በሽታው ከነስሩ ስላልተነቀለ በሌላ በኩል ብቅ ይላል እንደኔ እምነት ግን ምልክቶች ሳይሆኑ ሰዎች ናቸው መታከም ያለባቸው መልካም ቀን ተመኝሁ
ብዙ ሰው ያሰብኹት ሁሉ ምንም ሊሳካልኝ አልቻለም እያለ ያጉረመርማል እግዚአብሔርማ እኔን ሳይተወኝ አልቀረም እያለ ፈጣሪውን ያማርራል ይሰጠኛል ሳይሆን አገኘዋለሁ ብሎ ይጀምርና ሳይሆን ሲቀር በእጁ የነበረውን የነጠቀው ያህል አምላኩ ላይ ያለቅሳል ስታቅድ ያላስታወስከውን አምላክ ያቀድከው ሲፈርስ ስሙን እየጠራህ ስለምን ትወቅሰዋለህ በሕይወትህ መቼ ቦታ ሰጠኸው እንደ ፈቃዴ ካልሆነ አልህ እንጂ መቼ እንደ ፈቃድህ ይሁን ብለህ ጸለይህ ባላማከርከው ለምን ተከሳሽ ታደርገዋለህ ልሥራ ብለህ በተነሣህበትም ቀን እንዲሁ በግዴለሽነት ስሙን ጠርተህ እንደ ሆነም ራስህን መርምር በትክክል ጸልየህና በመንገድህ ሁሉ ይመራህ ዘንድ ፈቅደህ ከጀመርህ ግን ግድ የለም እረኛህን እመነው አንተ እንደ ሎጥ ከመረጥኸው እና ለጊዜው የገነት አምሳል ሆኖ ከሚታይህ ነገር ግን እግዚአብሔር ከማይከብርበት ከለምለሙ ሰዶምና ገሞራ ይልቅ አሁን ብዙም ለአይን የማይስበው በኋላ ግን ወተትና ማር የሚያፈሰው ለልጅ ልጆችህም ርስት የሚሆነው እግዚአብሔር የሚሰጥህ ከነአን ይሻልሃል መልካም ቀን
«መስጠም ማለት በውሃ ውስጥ መውደቅ ማለት አይደለም። የትኛውም አሳ በዚህ መንገድ መስጠም የሚለው ነገር አይገልጸውም፤ ነገር ግን በአየር ላይ ይሰጥማል። ስለዚህ የመስጠም ትርጉሙ ያንተ ባልሆነ ቦታ ላይ መውደቅ ነው!።»

―ከማህበራዊ ሚዲያ የተወሰደ_
​"የምትወጂው ወዳጅሽ ወይም አጋርሽ ጥሎሽ ሲሄድና ግንኙነታችሁ በክህደት ሲበላሽ አታልቅሽ። እግዚአብሔር አንቺ ካላየሽው ወደፊት ከሚመጣብሽ የከፋ ጥፋት ሊጠብቅሽ ስላለፈው ሊሆን ይችላል። አንዳንድ ጊዜ መለየት መከራ ሳይሆን፣ ፈጣሪ ላንቺ ያደረገልሽ ትልቅ ከምድር ክፋት የማምለጫ ምስጢር ነው።"
+ አቡነ ሺኖዳ ሣልሳዊ +
🔹 ለተጨማሪ የአባቶች ምክር ቻናላችንን ይቀላቀሉ፦
👉 https://t.me/Father_advice
​"አንድ ሰው ብዙ ከተናገረ ስህተት መሥራቱ አይቀሬ ነው። 'የንግግር 'ጥበብ ሁሉ መጀመሪያ ሰምቶ ማስተዋል፣ ከዚያም መናገር ነው። በብዙ ወሬ ውስጥ የሰላም ጠላት የሆነው ረብሻ አለ፤ በጥቂት የጥበብ ቃላት ውስጥ ግን የሕይወት ቅድስና አለ።"
+ ቅዱስ ኤፍሬም ሶርያዊ +
🔹 ለተጨማሪ የአባቶች ምክር ቻናላችንን ይቀላቀሉ፦
👉 https://t.me/Father_advice
ለሥልጣነ ክህነቱ የማይገባ' ካህን ብትመለከት፥ [በደፈናው] ክህነትን አትንቀፍ፡፡ ደገኛ የኾነውን የክህነት ሥልጣን ይዞ ያልተገባ ሥራን ሲሠራ በማየቱ ምክንያት፥ ከዚህ ተነሥቶ ሥልጣነ ክህነትን የሚነቅፍ አንድ ሰውስ እንኳን አይኑር፡፡

የአስቆሮቱ ይሁዳ ጌታችንን አሳልፎ ሰጥቷል፡፡ ይሁዳ እንዲህ በማድረጉ ግን ሐዋርያነት የሚነቀፍ ስለ ኾነ አይደለም፤ የይሁዳ የገዛ ነጻ ፈቃድ ችግር ነው እንጂ፡፡ የሚተቸውም ክህነቱ አይደለም፤ ጠማማው ነጻ ፈቃዱ ነው እንጂ፡፡

ስለዚህ አንተም ክህነትን አትንቀፍ፤ ክህነቱን ላልተገባ ሥራ የሚያውለውን ካህኑን እንጂ፡፡ ...

ሐኪም ሳይኾኑ ሐኪም ነን ያሉት ስንት ናቸው? በዚሁ ምክንያት በመድኃኒት ፈንታ መርዝ የሰጡትስ ስንት ናቸው? እየነቀፍኩ ያለሁት ሙያውን አይደለም፤ ሙያውን በአግባቡ የማይተገብሩትን ነው እንጂ፡፡

መርከቦች እንዲሰምጡ ያደረጉ መርከበኞችስ ስንት ናቸው? ነገር ግን ችግሩ የባሕር ላይ ጉዞ አይደለም፤ ሙያውን እንደሚገባ የማይተገብሩት ሰዎች ችግር ነው እንጂ፡፡

ስለዚህ አንተም አንድ ክፉ ክርስቲያን ብትመለከት በደፈናው የክርስትና ትምህርትን ወይም ሥልጣነ ክህነትን አትንቀፍ፤ ደገኛውን ሥልጣን ላልተገባ ሥራ የሚያውለውን ነው እንጂ፡፡"

(ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ፥ ትንቢተ ኢሳይያስን በተረጎመበት ፬ኛ ድርሳን ላይ ከተናገረው የተወሰደ)
«ጌታዬና አምላኬ ኢየሱስ ሆይ! ያለፈውን ዓመት ውጣ ውረድ፣ ጭንቀት፣ ውድቀትና በደል ሁሉ በቸርነትህ አልፈን ለዚህ አዲስ ዓመት አንደኛው ቀን ስለ አደረስከን ስምህ የተባረከ ይሁን። ዛሬ በባዶ እጃችን፣ ነገር ግን በትልቅ ተስፋ በፊትህ እንቆማለን። አዲሱን ዘመን ስንጀምር የወደፊቱ መንገድ🍃 ቢሰወርብንም፣
አዲሱን ቀን የምትመራው አንተ ሁሉን የምትችል አምላካችን እንደሆንክ እናምናለን።
አማኑኤል ሆይ! በዚህ በአዲሱ ዓመት የመጀመሪያ ቀን በፊትህ እንለምናለን፦

የነፍሳችን የቅርብ ሐኪም ሆይ! አዲሱን🍃 ዘመን ከእኛ ጋር ጀምር፣ ከእኛ ጋር ተመላለስ፣ እስከ መጨረሻውም አብረኸን ሁን። አሜን!

🌼መልካም አዲስ ዓመት🌼
🌻መስከረም 1/2019 ዓመተ ምሕረት🌻