Best ✍️
9 subscribers
4 photos
3 links
Download Telegram
🔥1
Best ✍️ pinned an audio file
Voice 005_sd
<unknown>
👍2
🥰1
🔥2🥰1
👍1
ኃጢአት መሥራት በራሱ  አስቀያሚ ነው፤ ኃጢአት ከሠሩ በኋላ በዚያ ኃጢአት መታበይ ግን እጅግ ጽኑ ደዌ ነው፡፡ ጽድቅን ሠርተው በዚያ በሠሩት ጽድቅ ከተኩራሩበት ጽድቁን ያጡታል፡፡ ይህ በኃጢአት ሲኾን ደግሞ የባሰ ነው፤ ወደ ከፋ ጥፋት ይወስደናልና፡፡ ከሠራነው ኃጢአት ይልቅ በሠራነው ኃጢአት መታበይ የሚያመጣው ፍዳ ኵነኔ እጅግ ጽኑ ነውና፡፡

#ቅዱስ_ዮሐንስ_አፈወርቅ
ንስሓና ምጽዋት - በገብረ እግዚአብሔር ኪደ
አንደበታችንን_እንጠብቅ!

አፉ ውስጥ ያለችውን ይህችን ትንሽዬ ብልት መቆጣጠር የማይችል ሰው ህይወቱ በመከራ እና በብስጭት የተሞላ መሆኑ የማይቀር ነው። ከአንደበታችን የሚወጡት ቃላቶች ከሰይፍ የላቀ፣ ከፈንጂ የባሰ ጉዳትን የማስከተል አቅም አላቸው።
#ማሳበባችንን_እንተው!

ማንኛውንም ውድቀት ላለመቀበል ሁሉንም ዓይነት ሰበቦች እና ምክንያቶችን እናመጣለን። ይህም ከስህተታችን እንዳንማር ያደርገናል። ለማሳበብ ለማሳበብማ አዳም ሔዋን ላይ አሳቧል፤ ሔዋንም እባብ ላይ አሳባለች… ታዲያ ማን ከእርግማኑ ተረፈ?።
ፀሎት_አየራችን_ይሁን

ፀሎት ከእግዚአብሔር ጋር የምንገናኝበት ዋነኛው መንገድ ነው… ከፀሎት ጋር ያልተቆራኘ ህይወት አየር በሌለበት ቦታ ላይ እንደመኖር ይቆጠራል! የጭንቀት እና የስጋት ሰንሰለት የትም እንዳንሄድ፣ ምንም ብሩህ ነገር እንዳናስብ ተብትቦ ይይዘናል፤

👉 ፀሎት እንዴት ይህንን የብረት ሰንሰለት ማቅለጥ እንደሚችል እንማርበታለን።
ጭንቀት_በእግዚአብሔር_ላይ_ማመጽ_ነው

አምላካችን እግዚአብሔር ጭንቀታችንን ሁሉ ለእሱ እንድንተው መክሮናል። እኛ ግን ብዙ ጊዜ በጭንቀት ራሳችንን ስናሳምም ነው የምንገኘው። የታዘዝነውን ከማድረግ ይልቅ በተፈጠረብን ችግር አማካይነት ሳናውቀው በተቃውሞ ውስጥ እንገባለን። የጭንቀት መድሃኒቱ የሚያስጨንቀንን ነገር ሁሉ ለአምላካችን መተው ነው።
መድኃኒታችንን_እንዋጥ

ይቅርታ ከብዙ በሽታዎች የሚፈሰው መድኃኒት ነው፡፡ ራሳችንን ከመመረዝ ነጻ ማውጣት የምንችለው በይቅርታ ነው፡፡ ይቅርታ ልክ የተቀደደ ልብስን እንደሚሰፋ የሚያውቅ መርፌ ዓይነት ነው። በየቀኑ የይቅርታን መድኃኒት እየዋጥን መፈወስ ስንችል ለምን ይሆን ራሳችንን የምንመርዘው?

© አቡነ ሺኖዳ ሳልሳዊ

       🌿 @Father_advice🌿 
             ✥••┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈••✥
      ✧━━━━━━━━━━━━━━━━━✧
                 ❍ㅤ    ⎙ㅤ  ⌲     ♡          
             ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ   ˢᵃᵛᵉ   ˢʰᵃʳᵉ  ˡᶦᵏᵉ   
3