Awraq Hustle Hub
2.1K subscribers
300 photos
63 videos
18 files
106 links
Not a Guru. Just a Brother Who Shares What Works.

Here I share tips, ideas, and real ways to start and grow your hustle. From making money online to leveling up your skills, we cover it all.
https://linktr.ee/lamlak
Download Telegram
ከስራችን በስተጀርባ ምን እያየን ነው?

ብዙ ሰው ሰኞን የሚጀምረው "ዛሬ ምን ልስራ?" ብሎ ነው፤ የ Awraq Hustle Hub ቤተሰቦች ግን መጠየቅ ያለባቸው ጥያቄ ሌላ ነው፦

👉"ዛሬ በገበያው ውስጥ ሁሉም የሚያየው፣ ግን ማንም ትኩረት ያልሰጠው ክፍተት (Gap) ምንድነው?

እውነተኛው የቢዝነስ እድገት የሚመጣው ጠንክሮ በመስራት ብቻ ሳይሆን፤

👉ሌሎች በቸልታ የሚያልፉትን ነገር ቀድሞ በመረዳት ነው!
👉ሰዎች ምን ላይ እያማረሩ ነው?
👉የትኛው አሰራር ነው አሰልቺና ጊዜ የሚፈጅ የሆነው? (ያ አዲስ የቢዝነስ ሃሳብ ነው!
👉በዙሪያችን ያሉት ሰዎች በብዛት የሚጠቀሙት ግን መሻሻል ያለበት አገልግሎት የቱ ነው?

📌ዛሬው የቤት ስራ
ዛሬ ስራ ስትሰሩ ወይም መንገድ ላይ ስትጓዙ አንድ ለየት ያለ

🤔"ለምን እንዲህ ሆነ?" የምትሉትን ነገር አስተውሉ።
ያ አስተያየታችሁ ነገ የትልቅ ፕሮጀክት መጀመሪያ ሊሆን ይችላል።
🔥108
📌 Saved Messages-ን በዚህ መልኩ ተጠቀሙት

ሁላችንም የሆነ ጠቃሚ ነገር ስናገኝ Saved Messages ላይ "Forward" እናደርጋለን፤ ግን በኋላ ስንፈልገው አናገኘውም፤ ሰዓት እናባክናለን!

ይሄን ቀላል ነገር ሞክሩት፦

👉ማንኛውንም ነገር ሴቭ ስታደርጉ ከስሩ #Hashtag ጨምሩበት።

ጥሩ የቪዲዮ ሃሳብ ከሆነ፡ #Content

የማርኬቲንግ ትምህርት ከሆነ፡ #Marketing

ለወደፊት የምታነቡት ከሆነ፡ #ReadLater

በኋላ ላይ Search ምልክቷን ነክታችሁ Hashtag-ን ስትጫኑ፤ የፈለጋችሁት ነገር ተከታትሎ ይመጣል።

ጥቅሙ፦ ጭንቅላታችሁ ነገሮችን "የቱ ጋር ነበር?" ብሎ ከመጨነቅ ነፃ ይሆናል፤ ለስራችሁ ስትቀመጡ ደግሞ የት መጀመር እንዳለባችሁ ግልጽ ይሆንላችኋል።
👏2011
ተማሪ ሆናችሁ የያዛችሁትን skill ወደ ገቢ መቀየር (Freelancing) የገንዘብ ነፃነትን ከመስጠቱም በላይ ለወደፊት የሙያ ህይወታችሁ ትልቅ መሰረት ይጥላል።

ይህ መመሪያ አላስፈላጊ ውጣ ውረዶችን ቀንሳችሁ በቀጥታ ወደ ስራ እንድትገቡ የሚረዳችሁ ነው።👇

https://www.tiktok.com/@lamlak_/video/7618233294374669589?is_from_webapp=1&sender_device=pc&web_id=7585932136604386817
5
ለአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች በሙሉ ትልቅ እድል ይዘንላችሁ መተናል🙌

ተማሪ ሆናችሁ በእጃችሁ ያለውን ስልክና ኢንተርኔት ተጠቅማችሁ የራሳችሁን ገቢ መፍጠር የምትችሉበትን መንገድ ከ AAU Men's partnership club ጋር በመተባበር ልናሳያችሁ ዝግጁ ነን።

🔥 በተጨማሪም ለተሳታፊዎች የሚሆን የ10,000 ብር ሽልማት (Giveaway) አዘጋጅተናል!

በፕሮግራሙ የምንማራቸው፦

የFreelance አስተሳሰብ (Mindset)

ገቢ የሚያስገኙ የክህሎት አይነቶች

ደንበኞችን የት ማግኘት ይቻላል?

የግል ብራንድን መገንባት

📌የመጀመሪያውን client እንዴት ማግኘት እንደምንችል?

📍 ቦታ፦ AAU ማንዴላ ሆል (Mandela Hall)
📅ን፦ ቅዳሜ(March 21)
🕒 ሰዓት፦ ከቀኑ 8:00 LT ጀምሮ

⚠️ ልዩ ማሳሰቢያ፦ ፕሮግራሙ ለአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ብቻ ሳይሆን ከዩኒቨርሲቲው ውጭ ላላችሁ ተማሪዎችም ክፍት ነው፤ መታወቂያችሁን ይዛችሁ በመምጣት መሳተፍ ትችላላችሁ።

ለመመዝገብ 👇
https://awraq-workshop.vercel.app/
5🔥2👏2🥰1
“ምን እንደምፈልግ አላውቅም” ብላችሁ አታውቁም?

ብዙዎቻችን ጓደኞቻችን ወይም LinkedIn ላይ የምናያቸው ሰዎች ሁሉ የሕይወት ካርታቸው የተሳለላቸው ይመስለናል።

ሁሉም ሰው "Scaling" እያደረገ፣ እያደገ ወይም እየገነባ እንደሆነ እናስባለን፤እኛ ግን ጭጋግ ውስጥ የቆምን ይመስለናል።

ግን ችግሩ መንገዱ መጥፋቱ ሳይሆን፣ አንድ እርምጃ ለመራመድ "በቂ እርግጠኝነት" እስክናገኝ መጠበቃችን ቢሆንስ 🤔

"ፍጹም የሆነውን መንገድ" የመጠበቅ አባዜ እንዴት ወደ ኋላ እንደሚያስቀረን እና ካለንበት ጭጋግ ወጥተን እንዴት አቅጣጫችንን እንደምናገኝ በዝርዝር እናውራ

watch here👇
https://youtu.be/flKZ2TGHGHU
2🔥2
ቆጠራው ተጀምሯል... 2 ቀናት ብቻ!

የቅዳሜው workshop የአስተሳሰብ ለውጥ ብቻ ሳይሆን የኪስ ለውጥም የሚጀምርበት ነው🙌

በማንዴላ አዳራሽ ተገናኝተን ስለ ዲጂታል ገቢ እናወራለን።

🎁 የ 10,000 ብር ሽልማት!
🎓 ከAAU ውጭ ላሉ ተማሪዎችም ክፍት ነው (መታወቂያ እንዳትረሱ)

እዚሁ በመመዝገብ ቦታችሁን ያዙ👇
https://awraq-workshop.vercel.app/
11
ዒድ ሙባረክ!
14👍3
ነገ በዚህ ሰዓት... ማንዴላ አዳራሽ እንገናኛለን!

ብዙ ተማሪዎች የሚመረቁት በዲግሪ ብቻ ነው፤ ጥቂቶቹ ግን በskill፤ በገቢ እና በተሞክሮ ጭምር ይመረቃሉ። እናንተ የየትኛው ወገን መሆን ትፈልጋላችሁ?

ነገ ቅዳሜ፣ በካምፓስ ቆይታችሁ እንዴት የገንዘብ ነፃነትን መገንባት እንደምትችሉ በተግባር የምናይበት ቀን ነው።

ለምን መምጣት አለባችሁ?

የአስተሳሰብ ለውጥ (Mindset Shift)

የskill ዝርዝራችሁን ወደ ብር የመቀየር ጥበብ

የ10,000 ብር ሽልማት! 💰

📍 ቦታ፦ አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ (6 ኪሎ) - ማንዴላ አዳራሽ
📅ን፦ ነገ ቅዳሜ
📌 ለAAU ተማሪዎች ያልሆናችሁ፦ መታወቂያችሁን መያዝ እንዳትረሱ!

ቦታችሁን አሁኑኑ ያዙ👇
🔗 https://awraq-workshop.vercel.app/
👍5🔥2
ተማሪ እያላችሁ ገቢ መፍጠር "ህልም" ሳይሆን "Skill" ነው!

ያንን Skill እንዴት እንደምትገነቡ ዛሬ እናሳያችኋለን🙌

ዛሬ ቅዳሜ
ማንዴላ አዳራሽ (6 ኪሎ)
መታወቂያ መያዝ እንዳይረሳ!

ያልተመዘገባችሁ እዚሁ ተመዝገቡ👇
https://awraq-workshop.vercel.app/
9🔥1
For the event participants
Thank you so much 🙌
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
7👍1
Happening know with my 3rd batch students 🔥
🔥125🕊2