Forwarded from የዘማሪ ዳዊት ክብሩ Zemari Dawit Kibru Official Telegram Channel (Dawit Kibru)

#ሁለተኛውን_ልደቱን_አስደናቂ_አደረገው!
📍እግዚአብሔር እልፍ ድንቅ ነገሮችን ትላንት አድርጓል፣ ዛሬም እያደረገ ነው ለወደፊትም ያደርጋል። ከድንቆች በላይ ግን ድንቅ ምንድነው ከተባለ ይህ ነው።
አምላክ ሰው የሆነበት፣ ሰውም አምላክን የሆነበት፣ ረቂቁ
ግዙፍ የሆነበት፣ ልዑሉ ትሑት የሆነበት ይህ ሁለተኛው ልደቱ
እጅግ ይደንቃል።
ታላቅነቱን በታናሽነት፣ ኃያልነቱን በደካማ ሥጋ ሰውሮ
መምጣቱ በጣሙን ይገርማል።
ሰማይና ምድር የማይችሉት አምላክ በማኅፀነ ማርያም መወሰኑ
እጅግ ያስደንቃል።
ሰማይ ዙፋኑ ምድር የእግሩ መረገጫ የሆነችለት አምላክ የዕለት
ጽንስ ሆኖ በማኅፀነ ማርያም ማደሩ በጣሙን ያስደንቃል።
የአስራ አምስት ዓመት ብላቴና እንድትሸከመው መፍቀዱ እጅግ ያስደንቃል።
የእግዚአብሔር ልጅ የሰው ልጅ ተብሎ መጠራቱ እጅግ
ያስደንቃል።
እኛን ወደሰማይ ሊያወጣ እርሱ ወደመሬት መውረዱ በጣም
ያስደንቃል።
እኛን ከክብር ዙፋን ላይ ሊያስቀምጥ እርሱ በውርደት በረት
መጣሉ እጅጉን ያስደንቃል።
እኛ ከመላእክት ጋራ እንድንዘምር እርሱ ከእንስሳት ጋራ በበረት
ማደሩ ያስደንቃል።
ባለዙፋን ባለበረት ሲሆን ማየት እጅግ ያስደንቃል።
ኃያል አምላክ ሕጻን ሆኖ መወለዱ ያስደንቃል። (ኢሳይያስ ሕጻን ተወለደልን አለ ማቴዎስ ደግሞ የተወለደው ንጉሥ ነው ይለናል። ሰብአ ሰገል ለዚህ ዘውዳቸውን አንሥተው ለሕጻኑ ሰግደዋል። በሚታይ ዕድሜ ቢሆን ኖሮ አይታሰብም አይሞከርም ነበር።)
#በሚታይ ሕጻንነቱ ግን ዘለዓለማዊ አባትነት አለው፣
#በሚታይ ሕጻንነት ዘለዓለማዊ ንግሥና አለው፣
#በሚታይ ሕጻንነት ዘለዓለማዊ አምላክነት ስላለው ዘውዳቸውን አንሥተው ለሕጻኑ ሰገዱለት።
ኃያል አምላክ ሕጻን ሆኖ መወለዱ እጅግ ያስደንቃል።
የዘለዓለም አባት "አንድ" ተብሎ ዘመን ሲቆጠርለት አረ
በጣሙን ያስደንቃል።
ከአንዲት ታናሽ ብላቴና ምግብ ሲለምን ማየት በጣም
ያስደንቃል።
ከአንዲት ታናሽ ብላቴና ምግብን ፈልጎ ማልቀሱ እጅግ
ያስደንቃል። እግዚአብሔርም አለቀሰ ሲባል እጅግ ያስደንቃል።
የእርሱ ማልቀስ የእርሷ እሹሩሩ ብሎ ማባበል እጅግ በጣም
ያስደንቃል።
የእርሱ መወለድ የእርሷ መውለድ በጣም ያስደንቃል።
የእርሱ ትሕትና የእርሷ ልዕልና እጅግ ያስደንቃል።
የተናቀ ማንነታችንን ያከበረበት፣ ጎስቋላ ብህርያችን ገንዘብ ያደረገበት
ሁለተኛው ልደቱ እጅግ ያስደንቃል።
የተናቁ ነገሮችን የመረጠበት ይህ ሁለተኛው ልደቱ እጅግ
ያስደንቃል።
(ከአገር የተናቀች ቤተልሄምን፣ ከፆታ ሴትን! (በሥርዐታቸው ሴት
በዘር ቆጠራ እንኳ እንደማትካተት ልብ ይሏል) ፣ከቦታ
የተናቀውን በረትን፣ከሥራ የተናቀ እረኝነትን) የመረጠበት
ያከበረበት ይህ ሁለተኛው ልደቱ እጅጉን ያስደንቃል።
.
.
.
.
አባ ጊዮርጊስ "የመጀመሪያውን ልደቱን (ከአብ ያለ እናት) ረቂቅ አደረገው። ሁለተኛውን ልደቱን (ከቅድስት ድንግል ማርያም ያለ አባት) አስደናቂ አደረገው።" ብሎ እንደተናገረ በእውነት ይህ ሁለተኛ ልደቱ እጅጉን ድንቅ ነው!!
ምድር እስከ ተዘረጋችበት ውኃም እስከፈሰሰበት ድረስ ያላችሁ በክርስቶስ ክርስቶሳውያን ሁሉ እንኳን ለልደቱ ለእግዚእነ አደረሳችሁ።
መልካም በዓል!!🤲🤲
©️ስምዐ_ጽድቅ_አርአያ

#አንዳንድ ልጆች ከወላጆቻቸው የሚበልጡበት ጊዜ አለ አንዳንድ ወላጆች ደግሞ በነገሮች ዕይታ ከልጆቻቸው የሚያንሱበትም ጊዜ አለ ። እናታችን ቅድስት ኢየሉጣ ይህን በመገንዘቧ ነበር ልጇን ሕፃኑ ቂርቆስን ስለ መልካም ምክሩ ልጇ ሆኖ ሳለ አባቴ ብላ ለመጥራት የተገደደችሁ ።
በእርግጥም የሥጋ ሞት እጅግ መራራና አስፈሪ ነው ። መድኅን ዓለም ክርስቶስ እንኳን ወዶ ፣ፈቅዶ የሞታችንን ጽዋ ሊጠጣልን ለካሳ፣ ለቤዛ መጥቶ ሳለ ጊዜው ደርሶ በአሙስ ምሽት የአይሁድ ወታደሮች ሊይዙት ሲመጡ ግን በአትክልት ቦታ በጌቴ ሰማኔ ሆኖ "አባት ሆይ ብትወድስ ይህች ጽዋ ከእኔ ትለፍ " ሲል ጸሎትን አድርጓል። #ማቴ 26÷39
#ይህም የሚያሳየን በመከራችን ጊዜ ወደ ሰማይ አባታችን መጸለይ እንደሚገባን ብቻ ሳይሆን የሥጋ ሞት ምነኛ አሰቃቂ ና አስፈሪ እንደሆነ ጭምር የሚያሳይ ነው ። ስለሆነም የቅድስት እየሉጣ ፍርሃት አያስደንቅም የሚያስደንቀውስ የልጇ እሳት መድፈር ነው ። “ አባት ሆይ፥ ይህን ከጥበበኞችና ከአስተዋዮች ሰውረህ ለሕፃናት ስለ ገለጥህላቸው አመሰግናለሁ፤ አዎን አባት ሆይ፥ ፈቃድህ በፊትህ እንዲህ ሆኖአልና።” #ሉቃስ 10፥21
በቤተክርስቲያናችን ታሪክ ገና በአፍላ ዕድሜያቸው በበሳልነታቸውና በአስተሳሰብ አድማሳቸው የተነሳ አረጋዊ ወይም ሽማግሌ ተብለው የተጠሩ ቅዱሳን አሉ ለምሳሌ ወደ ሀገራችን ከመጡ ከዘጠኑ ቅዱሳን መካከል ሮማዊው ኮከብ ዘሚካኤል(አቡነ አረጋዊ ዘደብረ ዳሞ) ማንሳት ይቻላል:: ዘሚካኤል አረጋዊ የሚል ስያሜን ያገኙት ገና አስራ አምስት ዓመት እንኳን ሳይሞላቸው ነበር።
#ቅዱስ_ወንጌል ከአንዱ ከተማ ቢያሳድዷችሁ ወደ ሌላይቱ ከተማ ሽሹ እንዳለ ከሮም መኮንን ሸሽታ ወደ ሌላ ሀገር ልጇን ይዛ ብትሄድ ያን የሸሸችሁ ክፉ መኮንን በዚህም ሀገር አገኛት የምታመልከውን አምላክ ክዳ የእርሱን ጣዖት እድታመልክም ጠየቃት ቅድስት ኢየሉጣ ግን ከእግዚአብሔር በቀር ሌሎች አማልክትን ማምለክ የሚገባ ወይም የማይገባ መሆኑን ይህን የሦስት ዓመት ልጄን ጠይቀው እርሱ ይንገርህ አለችሁ
መኮንኑም ቅዱስ ቂርቆስን በተመለከተው ጊዜ ፊቱ ብሩህና ደስተኛ ሕፃን እንደሆነ አስተዋለ ቀርቦም አንተ ደስተኛ ሕፃን እንዴት ነህ ሲል የማግባባት ሰላምታን አቀረበለት ሕፃኑ ቅዱስ ቂርቆስ ግን አዎን የኔ ደስታ ተጠብቆልኛል አንተ ግን ከዚህ እኩይ ሥራህ ካልተመለስ ልቅሶና ጥርስ ማፏጨት ጥልቅ ሐዘንም ይቆይሃል መጽሐፍ ለዝንጉዎች ተድላና ደስታ የላቸውም ይላልና አለው።“ለክፉዎች ሰላም የላቸውም ይላል አምላኬ።” #ኢሳ 57፥21
#መኳንንቱንና ጣዖታቱንም ሁሉ እረገማቸው ከኃይሉም ጽናት የተነሳ ሁሉ አደነቁ እግዚአብሔር ንግግርንና ኃይልን ሰጥቶታልና "ስለ እኔ ወደ ገዥዎች ወደ ነገሥታትም ትወሰዳላችሁ ። አሳልፈውም ሲሰጡአችሁ፥ የምትናገሩት በዚያች ሰዓት ይሰጣችኋልና እንዴት ወይስ ምን እንድትናገሩ አትጨነቁ፤ በእናንተ የሚናገር የአባታችሁ መንፈስ ነው እንጂ፥ የምትናገሩ እናንተ አይደላችሁምና። ተብሎ እንደተጻፈ #ማቴ 10÷18-20
መኮንኑም የሕፃኑን ንግግር በሰማ ጊዜ አፈረ ታላቅ የውኃ ጋን አዘጋጅታችሁ ውኃው እስከሚፍለቀለቅ በእሳት ላይ ጣዱት ውኃውም ሲፈላ ሕፃኑንና እናቱን በዚያ ጨምሯቸው ብሎ አዘዘ ።
#ጭፍሮችም እንደተባሉት አደረጉ የውኃው ፍላትም ድምጹ እንደ ክረምት ጊዜ ነጎድጓድ የሚያስፈራና የሚያስገመግም ሆነ ይህ ጊዜ የሕፃኑ እናት ቅድስት ኢየሉጣ ፈራች ሃይማኖቷም ከልቧ ተሸረሸረ ልጄ ሆይ ይህ ነገር ይቅርብን ንጉሥ ያለንን እንፈጽም አለችው።
ሕፃኑ ቅዱስ ቂርቆስ ግን ወደ ሰማይ አንጋጦ መላእክትን በጽረ አርያም ፣ ሐዋርያትን በስብከተ ዓለም ፣ ጻድቃንን በገዳም፣ ሰማዕታትን በደም ያጸናህ እናቴንም በሃይማኖት አጽናት ሲል ስለ እናቱ የእምነት መጉደል ወደ ፈጣሪው ጸለየ።
#እግዚአብሔርም የእናቱን ዐይነ ልቡና ገልጦ ለቅዱሳን ሰማዕታቱ ያዘጋጀውን የጽድቅ አክሊልን አሳያት ያን ጊዜ ቅድስት እየሉጣ በመንፈስ ተጽናናች ፣ በሃይማኖት ጸናች ንጉሡንና ጣዖታቱን ናቀች ልጇ ቂርቆስንም " #ልጄ_ስትሆን_አባት_ሆንክኝ " አለችሁ ተያይዘውም በእሳት ወደ ተፍለቀለቀው የውኃ ጋን ውስጥ ገቡ
#ከእግዚአብሔር_የተላከ_የመላእክት_አለቃ_ቅዱስ ገብርኤልም ከዐይን ጥቅሻ ፈጥኖ መጥቶ #በጌታችን_በመድኃኒታችን_በኢየሱስ_ክርስቶስ_መስቀል ያን ፍል ውኃ እንደ ክረምት ጊዜ ውርጭ አቀዘቀዘው። ሕፃኑና እናቱም ያለ ምንም ጉዳት ከጋኑ ወጡ። " #የእግዚአብሔር_መላእክ በሚፈሩት ሰዎች ዙሪያ ይሰፍራል ያድናቸውማል " እንዲል #መዝ 33÷7
.......... #ይቆየን............
#የእግዚአብሔር ቸርነት የመላእኩ ጠባቂየት የቅዱሳኑ የእናትና ልጅ በረከታቸው አይለየን !
አ.አ ኢትዮጵያ
ተክለ ኤል ኃ/ማርያም
ሐምሌ ፲ ፰/፳ ፻ ፲ ፫ ዓ.ም

🔴ዘማሪት ሰብለ ስፍር ተክለአብ አስበኝ_ ዘማሪ_ገብረዮሐንስ #ዘማሪት_ሲስተር_ሕይወት_ተፈራ
https://youtube.com/watch?v=q05QNqKfnUY&si=EPCiQUBYegyuKMee

YouTube
🔴ዘማሪት ሰብለ ስፍር ተክለአብ አስበኝ_ ዘማሪ_ገብረዮሐንስ #ዘማሪት_ሲስተር_ሕይወት_ተፈራ
Enjoy the videos and music you love, upload original content, and share it all with friends, family, and the world on YouTube.
Forwarded from የዘማሪ ዳዊት ክብሩ Zemari Dawit Kibru Official Telegram Channel (Dawit Kibru)
የወንድማችን የዘማሪ ሳሙኤል ከበደ ዝማሬ በራሱ ዩትዩብ ቻናል በቅርቡ ይለቀቃል እስከዚያው ቻናሉን በመቀላቀል ሰው ለመቀላቀል (ላልቶ ይነብብ ) በማጋራት ይቆዩን ❕❕🙏🙏🙏
https://youtube.com/@zemarisamuelkebede?si=EBUEOFfdS72lvFz7
https://youtube.com/@zemarisamuelkebede?si=EBUEOFfdS72lvFz7
Forwarded from የዘማሪ ዳዊት ክብሩ Zemari Dawit Kibru Official Telegram Channel (Dawit Kibru)
ይህን ዓመት ተወኝ አዲስ ዝማሬ ዘማሪ ሳሙኤል ከበደ | yhn amet tewegni adis zmare zemari sa...
https://youtube.com/watch?v=vy_GBT3XlYM&si=YI3oA0TyBB74l8wQ
https://youtube.com/watch?v=vy_GBT3XlYM&si=YI3oA0TyBB74l8wQ
YouTube
ይህን ዓመት ተወኝ አዲስ ዝማሬ ዘማሪ ሳሙኤል ከበደ | yhn amet tewegni adis zmare zemari samuel kebede
Kltiktokvideo .com/@samuelkebede02
https://t.me/+sQkovPBrfndjMjA8
🔴 ይህንን ቻናል SUBSCRIBE በማረግ አዲስ ዝማሬ ዎችን እዲሁም
ኦርቶዶክስሳዊ ትምህርቶችን ማግኘት ይቺላሉ
አዲስ ዝማሬ ይህንን ዓመት ተወኝ
ይህን ዓመት ተወኝ ፍሬን እንዳፈራ
ይህን ጊዜ ስጠኝ ወደ ቤትህ ልግባ
ከደጅህ እየዋልኩ ቤትህን አላውቅም
…