ዐውደ ምሕረት
3.42K subscribers
939 photos
24 videos
271 files
208 links
"ቤተ ክርስቲያን ባሕረ ጥበባት
አትመረመርም እጅግ ጥልቅ ናት"
Download Telegram
#አባቴ_ነውና_አዎን አውቀዋለሁ !
______

#ያለ_ተክለ_ሃይማኖት_ጸሎትና_ረድኤት
#ለኢትዮጵያ_ሰዎች_የመዳን_ተስፋ_የላቸውም

ሰይፍ አርእድ በተባለ በነዋየ ክርስቶስ መንግሥት ደግሞ ከንጉሥ ሠራዊት አንዱ ወደ ዋሊ ገዳም ሄደ ።ሁለት መነኮሳት አግኝቶ እጅ ነሳቸው ፤ ከወዴት ነህ? አሉት? ከሸዋ ክፍለ ሀገር ከዚያው ግራርያ ከምትባል አውራጃ ነኝ አላቸው። ተክለ ሃይማኖት የሚሉትን ታውቀዋለህ ? አሉት። #አባቴ_ነውና_አዎን_አውቀዋለሁ አላቸው።

#ወደ_መቃብሩ_ደርስሃል ? አሉት። አዎን ደርሻለሁ አላቸው። እነዚያም መነኮሳት ተነስሀው ሰገዱለት የእግሮቹንም ትቢያ ይልሱ እጆቹንም ይስሙ ጀመሩ። ጭፍራውም ጌቶቼ ይህንን ስለምን አደረጋችሁ?? አላቸው ። እኛ እናውቃለን አሉት። ዳግመኛም በተክለ ሃይማኖት የመቃብር ቦታ ሥጋ ወደሙን ተቀበልክን? አሉት። አልተቀበልኩም አላቸው። ከቅዱሱ መቃብር ዘንድ ቁርባን ያልተቀበልክ #እቡዘ_ልብ_ለምን_ሆንክ ? የተክለ ሃይማኖት አጽም ካረፈበት ቦታ ቁርባንን የተቀበለ ሁሉ ሲዖልን ዐያይም ሲል ከጌታ አንደበት በእውነት ሰማን ብለን በእውነት እንነግርሃለን አሉት።

#በውስጧም የሚቀበር ለዘለዓለም እንዳይጎዳም እኛም መንፈስ ቅዱስ በየሰዓቱ ይልቁንም በቁርባን ጊዜ እየወረደ በውስጧም መሥዋት ለሚያቀርቡ መዐዛ ያለውን ሽቱ ሲቀባቸው ዘወትር እናያለን ፤እንደ ብርሃን ደመና በላይዋ የረበበ ነው እንጂ ለሊትና ቀን ከእርሷ መንፈስ ቅዱስ አይርቅም።
እንዲሁ ዘወትር ይኖራል።በእርሷም የተቀመጠ የቆመ በውስጧም የተቀበረ በረድኤቷም የተጠጋ የተመሰገነ ነው። #ያለ_ተክለ_ሃይማኖት_ጸሎትና_ረድኤት_ለኢትዮጵያ_ሰዎች_የመዳን_ተስፋ_የላቸውም ። አሉት
ሌላም የተሰወረ ምሥጢር ነገሩትሌላውን ግን ልንጽፈው አንችልም መጽሐፍ የምንገልጠውም የምንሰውረውም ነገር አለ እንዳለ ይንንም ብለውት ከእርሱ ተሰወሩ።

" #አዎን_ለምንፍገመገም_ለኛ_ለኢትዮጵያውያን ያላንተ ረዳት የለንምና #ምልጃህ አትለየን " #አሜን!

#ገድለ_ተክለ_ሃይማኖት ምዕራፍ 50/60

አ.አ ኢትዮጵያ
ተክለ ኤል ኃ/ማርያም
ጥንተ ጽሕፈቱ #ግንቦት 11/2014ዓ.ም
Forwarded from Sami 🦴
🔴ቅድስት ክርስቶስ ሰምራ🌹እንኳን አደረሳችሁ🌹በዘማሪት ሲስተር ማኀደር ለታሪክ 🌹አዲስ ዝማሬ💐/New mezmur/
https://youtube.com/watch?v=tM3jdFxXdSs&si=lCt7XXjVGsSBHPiC
#ቤተ_ክርስቲያን አሙስ ላይ ናት !
_________

የአሙስ ማታ የጌታችን የአምላካችን የድኃኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስ ንግግር
___________

" #በዚች ሌሊት ሁላችሁ በእኔ ትሰናከላላችሁ፤ #እረኛውን እመታለሁ የመንጋውም በጎች ይበተናሉ የሚል ተጽፎአልና፤”
#ማቴዎ 26፥31

#ከፊት ይልቅ አሁን ላይ #ለቤተ_ክርስቲያን ትጉላት ! #አሙስ ላይ ናትና
ይነበብ 🙏🙏🙏🙏

መንፈሳዊ መርሐግብር ጥሪ !!!!

ለኢትዮጲያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ምዕመናን በሙሉ በቅድሚያ የታኃሳስዳር ደብረ ጽዮን ህንፃ ቤተክርስቲያን ለማሰራት እያደረጋችሁልን ስላለው ሁለንተናዊ ድጋፍ ከልብ እያመሰገንን ፤  ይህንን ስራ አጠናክረን ለማስቀጠል እና ለህንፃ ማሠሪያው ከዚህ የተሻለ እርዳታ ለማድረግ ያስችለን ዘንድ በአይነቱ የተለየ መርሐ ግብር በማዘጋጀት ለተለያዩ ሰዎች ጥሪ በማድረግ ላይ እንገናኛለን ። በመሆኑም ግንቦት 24/9/2017 ዓ.ም ከ 5:30 ጀምሮ በሚኖረን ልዩ መርሐ ግብር ለመሳተፍ 5 ኪሎ በሚገኘው መንበረ ፓትርያርክ ቅድስተ ቅዱሳን ማርያም ገዳም እንድትገኙልን ስንል በእመቤታችን ስም ጥሪያችንን እናስተላልፋለን።።

ላልሰሙ እንድታሰሙ በእመቤታችን ስም እንጠይቃለን !🙏🙏🙏

የታኅሳስዳር ደብረ ጽዮን ማርያም ልጆች ማኅበር
"ዐርገ በስብሐት ውስተ ሰማያት" የዘወትር ጸሎታችን ነው።አስቀድሞ በማኅፀነ #ድንግል ሥጋችንን ቃል ስለተዋሐደው በባሕርይ አምላክነት (በፈጣሪነት) ዐርጓል (ከፍ ከፍ ብሏል)።ሆኖም ግን እስከ ትንሣኤ ድረስ የትሕትናን ሥራ ከልዕልና ጋር ሲሠራ ቆይቷል።ከትንሣኤ በኋላ እስከ ዐርባ ቀን ድረስ ምሥጢረ መንግሥተ ሰማያትን ለቅዱሳን #ሐዋርያት ሲያስተምር ቆይቶ በአርባኛው ቀን በግርማና በስብሐት ወደ ሰማይ ዐረገ፤በአባቱም ቀኝ ተቀመጠ።

‎አካላዊ ቃል ከድንግል #ማርያም ነሥቶ የተዋሐደው ሥጋ ከአብ ከመንፈስ ቅዱስ ጋር አንድ የሆነው ማለትም ምልዐትን፣ ስፋትን ፣ርቀትን የአብ ልጅነትን ገንዘብ ያደረገው ቃል ሥጋን በተዋሐደበት (ጌታ በተፀነሰበት) ቅጽበት ነው።ዳግመኛ በትሕትና ሥራ ላይገለጥ ከብሮ የታየበት በዓሉ ደግሞ ዕርገት ነው።

‎ "ታስበው ዘንድ ሰው ምንድነው" እንዳለ ቅዱስ ዳዊት እንዲህ ባለ ክብር ሰውነታችንን ያከብር ዘንድ በእውነት እኛ ምንድነን?ዛሬ የእኛ ሰውነት በቅዱሳን በመላእክት ታጅቦ ወደ ሰማይ ወጣ።ድል ነሥቶ በአብ ቀኝ ተቀመጠ።

‎ "በክብር በምስጋና ወደ ሰማይ ዐረገ በአባቱም ቀኝ ተቀመጠ" ስንል ክርስቶስ ከአባቱ ቀኝ ተለይቶ ኖሮ ኋላ
‎ወደ አባቱ ቀኝ የሄደ አይደለም።ሰው የሆነበትን ዓላማ ፈጽሞ ሰይጣንን አሥሮ ሰውን ነፃ አውጥቶ በድል ነሺነት በአባቱ ቀኝ ተቀመጠ ማለታችን ነው።

#ዕርገትን ስናስብ

#የእግዚአብሔርን ውለታ እናስባለን (እኛን ያከበረበትን ክብር)
#ያዘጋጀልንን መንግሥተ ሰማያት እናስባለን።ተስፋችን ይለመልማል።
‎“ሄጄም ስፍራ ባዘጋጅላችሁ፥ እኔ ባለሁበት እናንተ ደግሞ እንድትሆኑ ሁለተኛ እመጣለሁ ወደ እኔም እወስዳችኋለሁ።”(ዮሐ 14፥3) "ሄጄም" ሲል ዕርገቱን ተናገረ።
#የዳግም ምጽአትን ፍርድን በማሰብ ራሳችንን እናዘጋጃለን።
‎“የገሊላ ሰዎች ሆይ፥ ወደ ሰማይ እየተመለከታችሁ ስለ ምን ቆማችኋል? ይህ ከእናንተ ወደ ሰማይ የወጣው #ኢየሱስ ወደ ሰማይ ሲሄድ እንዳያችሁት፥ እንዲሁ ይመጣል አሉአቸው።”(ሐዋ 1፥11)
#በመንግሥተ ሰማያት የሚኖረንን ዕርገታዊ ሕይወት እናስባለን።
‎ በክብር ላይ ክብር፣በጸጋ ላይ ጸጋ፣በጣዕም ላይ ጣዕም፣በመዓዛ ላይ መዓዛ በማያቋርጥ ከፍ ማለት መኖራችንን ተስፋ እናደርጋለን።
‎ "የሙታንን መነሣት የሚመጣውንም ሕይወት ተስፋ እናደርጋለን" "የሚመጣው ሕይወት" ምንድንነው?ከትንሣኤ በኋላ የሚኖረን የማያቋርጥ ሱታፌ #አምላክ (#እግዚአብሔርን መምሰል) ነው እንጂ!!!

‎ ከበዓለ ዕርገቱ ረድኤት በረከት ያሳትፈን!!
#ኢዮብ ክንፈ
‎ ግንቦት 21/2017 ዓ.ም

የአፎምያ ጥያቄ የባሕራን መልስ
#ቅዱስ_ሚካኤል
እርግብ የምታገባው አንድ ብቻ ነው። ቢሞት እንኳን ሌላ መጥቶ እንዳይተናኮላት ምላሷን ትሰነጥቃለች። ድንገት ቢመጣባት በደንብ መጮህ እንድትችል እና ሌሎች መጥተው ደርሰውላት እንዲያባርሩላት ነው። ቅድስት አፎምያን እንደ እርግ የምትኖር ደገኛ ሴት ነበረች።

የኬልቅያ መስፍን የነበረው የምትወደው ባሏ አስተራኒቆስ በሞት ከተለያት በኋላ በዕውቅ አስሎ የሰጣትን የቅዱስ ሚካኤል ሥዕል ይዛ በጾም በጸሎት ተስና ስትኖር ጸላዬ ሰናያት የመልካም ነገሮች ሁሉ ጠላት የሆነ ሰይጣን ዲያቢሎስ ደግ መነኩሴ መስሎ መቶ ጾም ጸሎት እንድትተው ሌላ ባል አግብታ ተድላ ደስታ እንድታደርግ መከራት እርሷ ግን አባ አለባበሶት ደግ ነበር ንግግሮት ግን የከፋ ነው። ጾም ፣ጸሎት ና ምጽዋት ደገኛ ሥርዓት አይደሉምን? ስለምንስ ዳግመኛ እንዳገባ ይመክሩኛል በሉ ከኔ ወግዱልኝ ብላ አሳፍረችው። ይህን ግዜ የደበቀውን ሰይጣናዊ ግብር ገልጦ ቆቡን ጥሎ ከቁራ ሰባት ጅ ጠቆረ ሰኔ አሥራሁለት ቀን ተመልሼ እመጣለሁ አጠፋሻለሁም ብሎ ዝቶባት እንደ ጢስ ተኞ እንደ ትብያ ተኖ ጠፍቶ ሄደ ።

ሰይጣን ዲያቢሎስ እንዳለሁም ግብሩን ለውጦ በሰኔ አሥራ ሁለት ቀንም የመላእከት አለቃ ቅዱስ ሚካኤልን መስሎ ባማረና በተዋበ ልብስ ወደ ቤቷ መጥቶ ተገለጠላት “ይህም ድንቅ አይደለም፤ ሰይጣን ራሱ የብርሃንን መልአክ እንዲመስል ራሱን ይለውጣልና።” ተብሎ እንደተጻፈ 2ኛ ቆሮ 11፥14

ቤቴን በብርሃንህ የሞላህ አንተ ማነህ ? አለችሁ የመላእክት አለቃ ቅዱስ ሚካኤል ነኝ ይህ ከብርሃኔ ተረጂ አላት ቆየኝ መጣው ብላ የቅዱስ ሚካኤል ወዳጂ የነበረው ባሏ አስተራኒቆስ አስሎ ነሰጣትን የቅዱስ ሚካኤልን ሥዕለ አድህኖ ይዛ መጣች ። እያመሳሰለችሽ ንጉሥ ለጭፍሮቹ መታወቂያ ማኅተቡን አትሞ አስይዞ ይልካቸዋል የእግዚአብሔር መላእክ ቅዱስ ሚካኤል ከሆንክ ማዕተመ መስቀልህ የንጉሥህ መታወቂያ በትረ መስቀልህ የታለ ?አለችሁ። እርሱም ሐሰተኛ የሐሰትም አባት ነውና እኛ በእግዚአብሔር ፊት የምንቆም መላእክት መስቀል መያዝ ለምናችን ጨርሶ አያስፈልገንም አላት ይህን ጊዜ አንተማ መላእኩ ቅዱስ ሚካኤል አይደለህም አላምንህም አለችሁ ያን ጊዜ እንዳ ወቀችበት ሲረዳ ግብሩ ቀይሮ በብርሃን የመላው ቤቷን በጽልመት መላው ቀንዱ በቀለ ፣ጥፍሩ እረዘረዘ፣ ዐይኑ ፈጠጠ ፣ጥርሱ ገጠጠ አንቺንስ ካላጠፋሁ ሠላሜን አላገኝም ብሎ ተወርውሮም አንቆ ያዛት ቅድስት እናት አፎምያም እውነተኛው ታላቁ መላእክ ቅዱስ ሚካኤል ሆይ እርዳኝ ብላ በጣር ውስጥ ሆና ተጣራች እውነተኛው የእግዚአብሔር መላእክም ከዐይን ጥቅሻ ፈጥኖ መጣና ዲያቢሎስን ረግጦ ያስጨንቀው ገባ ሰይጣንም ሚካኤል ሆይ ጊዜዬ ሳይደርስ እንዳታጠፋኝ በፈጣሪህ እለምንሃለው እያለ ጮኸ ቅዱስ ሚካኤልም ለቀቀው በኖ ተኖ ጠፋ ቅድስት እናት አፎምያንንም ያረጋጋት ጀመር ። “ #የእግዚአብሔር_መልአክ በሚፈሩት ሰዎች ዙሪያ ይሰፍራል፥ ያድናቸውማል።” እዳለ መጻሕፍ #መዝ (33) 34፥7

*አንባቢ ሆይ አንተስ በክርስቶስ ክርስቲያን ነኝ ትላለህንን እንግዲያውስ መስቀልህ የታል?
*አንባቢት ሆይ የንጉሥሱ የእግዚአብሔር ልጅ ነኝ ትያለሽን? መልካም ትያለሽ ግን የንጉሡ ደመ ማዕተብ በትረ መስቀልሽ ከወዴት አለ? የአፎምያ ጥያቄ ይህ ነበር መስቀልህ የታለህ? ለአፎምያ ትክለኛ ጥያቄ መልስ የሆናት እውነተኛው ቅዱስ ሚካዬል በትረ መስቀሉን ጨብጦ ይዞ በመታየት ነው።ወዳጄ የድልህ ዐርማ የሆነውም " ሁልጊዜ በልብህ አኑረው፥ በአንገትህም እሰረው። ስትሄድም ይመራሃል፤ ስትተኛ ይጠብቅሃል፤ ስትነሣ ያነጋግርሃል። " #ምሳ 6÷21-22 የደሃ አደጊቱ ልጅ ባሕራንም የሞት ደብዳቤውን ተቀብሎ የደስታ የፍስሐ የሰርግ ደብዳቤ አድርጎ የመለሰለት የደስታ ሁሉ መልስ ቅዱስ ሚካኤል በዚህች ዕለት በነገዱ ሁሉ ላይ የተሾመበት የሹመቱ በዓል ነው!

መንፈስ ቅዱስ ያወቀውን ሰይጣን የሸመቀውን ከጠላት የተንኮል እንቆቅልሽ ሁሉ የመላእክት አለቃ ቅዱስ ሚካኤል የደስታ መልስ ይሁንልን!

አ.አ ኢትዮጵያ
ተክለ ኤል ኃይለ ማርያም
ሰኔ ፲ ፪ ቀን /፳ ፻ ፲ ፫ ዓ.ም