Biyya Lallaba Arsii(የአርሲ ሀገረ ስብከት)
368 subscribers
1.35K photos
31 videos
7 files
207 links
Download Telegram
Sooma Haadha Keenya Qulqulleettii Dubroo Maariyaamii(Subaa'ee) Guyyaa Saddeettaffaa

Eebbifamoo Abbaa Keenya Abuna Eelsa'i Hangafa Phaaphaasii Biyyoota Lallabaa Arsii fi Naannoo Somaalee Jijjigaa Miseensa Qulqulluu Sinoodosii bakka argamanitti Sirni Qulqulleessaa Raawwateera.

Mana Kiristaanaa Kaatediraala Tulluu Qorichaa Fayyisaa Addunyaa Asallaatti.

የእናታችን የቅድስት ድንግል ማርያም ጾመ ፍልሰታ (ሱባኤ) 8ኛ ቀን

ብፁዕ አባታችን አቡነ ኤልሳዕ የአርሲና ሶማሌ ክልል ጅጅጋ ስብከት ሊቀ ጳጳስ የቅዱስ ሲኖዶስ አባል በተገኙበት።
በአሰላ ደብረ መድኀኒት መድኀኔዓለም ካቴድራል ቤተ ክርሰቲያን የቅዳሴ ሥነሥርዓት ተጠናቀቀ።

Arsi Diocese Public Relations Department
© Biyya Lallaba Arsiitti Kutaa Sab-Qunnamtii
© የአርሲ ሀገረ ስብከት ህዝብ ግንኙነት ክፍል

© የአርሲ ሀገረ ስብከት ሚድያ Miidiyaa Biyya Lallaba Arsii ...✍️

👉 Liinkii Gadii Kana Hordofuudhan Gara Chaanaaliiwwan Miidiyaa Keenyatti Dabalamaa
👉 ከታች ያሉትን ሊንክ በመጫን ወደ ቻናሎቻችን ተቀላቀሉ

👉 FACEBOOK👇👇👇👇👇ፌስቡክ
https://www.facebook.com/share/1bp49TDKhZ/

👉 TIKTOK👇👇👇👇👇ቲክቶት
tiktok.com/@miidiyaa.ku.la.arsii

WhatsApp 👇👇👇👇👇ዋትሳፕ
https://whatsapp.com/channel/0029Vb6ZyoHId7nSWz2Uq73X

Inistagram👇👇👇👇👇ኢንስታግራም
https://www.instagram.com/miidiyaablarsii?igsh=MXRsaDgyeXJwdDdkdQ==

Telegram Chanal 👇👇👇👇👇ቴሌግራም
https://t.me/Arsi21

Telegram Group👇👇👇የግሩፕ ቴሌግራም
https://t.me/+do8_6-C5_ek4MjFk

Telegram Cominicate
@BIYYALALLABAARSII

IMO👇👇👇👇👇ኢሞ
https://call.imo.im/BiyyaLallabaArsii
የእናታችን የቅድስት ድንግል ማርያም ጾም(ፍልሰታ) የሱባኤ 10ኛ ቀን ብፁዕ አባታችን አቡነ ኤልሳዕ የአርሲ እና ሶማሌ ክልል ጅግጅጋ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ የቅዱስ ሲኖዶስ አባል በተገኙበት በሁሩታ ታሪካዊና ጥንታዊቷ መንበረ ጵጵስና ደ/መ ቅድስት ማርያም ቤተ ክርስቲያን የቅዳሴ ሥነሥርዓት፣ የውዳሴ ማርያምና የቅዳሴ ማርያም አንድምታ ተከናውኗል።

ብፁዕነታቸው ቤተ ክርስቲያንን ሲያገለግሉ ለነበሩት በዛሬው ዕለት ለአራት አገልጋዮች የማዕረግ ስም ሰተዋቸዋል፣
1ኛ ዲ/ን አቢቲ በአርሲ ሀገረ ስብከት ሎዴ ሄጦሳ ወረዳ ቤተ ክህነት ጸሐፊ መጋቤ ሠላም ዲን አቢቲ

2ኛ መ/ር ቀሲስ አለማየሁ በአርሲ ሀገረ ስብከት የሎዴ ሄጦሳ ወረዳ ቤተ ክህነት ሰባኬ ወንጌል ልሳነ ክርስቶስ መ/ር አለማየሁ

3ኛ መ/ር አንዱዓለም በአርሲ ሀገረ ስብከት የሁሩታ ደ/መ ቅድስት ማርያም ቤተ ክርሰቲያን ሰባኬ ወንጌል ለሆኑት መጋቤ ሐዲስ መ/ር አንዱዓለም

4ኛ. ዲ/ን ዮሐንስ በአርሲ ሀገረ ስብከት የሁሩታ ደ/መ ቅድስት ማርያም ቤተ ክርስቲያን ጻሐፊ ለሆኑት ዲ/ዮሐንስ ላዕከ ሔራን ደ/ን ዮሐንስ ተብለው የማዕረግ ስም ተሰጥቷቸዋል።

በመጨረሻም ህዝቡን ቃለ እግዚአብሔር አስተምህሮ ባርከው አባታዊ ቃለ ምዕዳንና ቡሬኬ ሰጥቷል፣ መርኃ ግብሩም በብፁዕነታቸው ቡራኬና ጸሎት ተጠናቀዋል።

የብፁዕነታቸው ቡራኬና ጸሎት አይለየን🙏

Sooma Haadha Keenya Qulqulleettii Dubroo Maariyaamii (Subaa'ee) Guyyaa 10ffaa Biyya Lallaba Arsii Mana Lubummaa Aanaa Loodee Heezosaa Magaalaa Hurutaatti Mana Kiristaanaa Teessoo Phaaphaasii Tulluu Maawwi'i Qulqulleettii Maariyaamii Hurutaatti Bakka Eebbifamoo Abbaa Keenya Abuna Eelsa'i Hangafa Phaaphaasii Biyyoota Lallabaa Arsii fi Naannoo Somaalee Jijjigaa Miseensa Qulqulluu Sinoodosii argamanitti sirni Qulqulleessaa, Hiikkaan(Andimataan Galata Maariyaamii fi Qulqulleessaa Maariyaamii/Wuddaasee Maariyaamii fi Qiddaasee Maariyaamii) raawwateera.

Eebbifamummaan isaanii Tajaajiltoota Mana Kiristaanaa Tajaajilaa turan 4f Maqaa Kabajaa laataniiru.

1ffaa. Dn Aabbittii Biyya Lallaba Arsiitti Barreessaa Mana Lubummaa Aanaa Loodee Heexosaa Sooraa Nageenyaa Dn Aabbittii

2ffaa. Luba Barsiisaa Alamaayyoo Biyya Lallaba Arsiitti Lallabaa Wangeelaa Mana Lubummaa Aanaa Loodee Heexosaa Qooqa Kiristoos Barsiisaa Alamaayyoo

3ffaa. Barsiisaa Andu'aalem Biyya Lallaba Arsii Mana Lubummaa Aanaa Loodee Heexosaatti Lallabaa Wangeelaa Mana Kiristaanaa Teessoo Phaaphaasii Tulluu Maawwi'i Qulqulleettii Maariyaamii Hurutaa Sooraa Haaraa Barsiisaa Andu'aalem

4ffaa. Dn Yohaannis Biyya Lallaba Arsii Mana Lubummaa Aanaa Loodee Heexosaatti Barreessaa Mana Kiristaanaa Teessoo Phaaphaasii Tulluu Maawwi'i Qulqulleettii Maaroyaamii Hurutaa Sooraa Gaarii jechuudhan maqaa Kabajaa laataniiru.

Dhumarrattis Eebbifamummaan isaanii Amantoota Wangeela Barsiisanii Eebbisanii Jecha Abbummaa fi Eebba kennanii sagantaanis Eebba fi Kadhannaa Eebbifamummaa isaanitiin xummurameera.

© Arsi Diocese Public Relations Department
© Biyya Lallaba Arsiitti Kutaa Sab-Qunnamtii
© የአርሲ ሀገረ ስብከት ህዝብ ግንኙነት ክፍል

© የአርሲ ሀገረ ስብከት ሚድያ Miidiyaa Biyya Lallaba Arsii ...✍️

👉 Liinkii Gadii Kana Hordofuudhan Gara Chaanaaliiwwan Miidiyaa Keenyatti Dabalamaa
👉 ከታች ያሉትን ሊንክ በመጫን ወደ ቻናሎቻችን ተቀላቀሉ

👉 FACEBOOK👇👇👇👇👇ፌስቡክ
https://www.facebook.com/share/1bp49TDKhZ/

👉 TIKTOK👇👇👇👇👇ቲክቶት
tiktok.com/@miidiyaa.ku.la.arsii

WhatsApp 👇👇👇👇👇ዋትሳፕ
https://whatsapp.com/channel/0029Vb6ZyoHId7nSWz2Uq73X

Inistagram👇👇👇👇👇ኢንስታግራም
https://www.instagram.com/miidiyaablarsii?igsh=MXRsaDgyeXJwdDdkdQ==

Telegram Chanal 👇👇👇👇👇ቴሌግራም
https://t.me/Arsi21

Telegram Group👇👇👇የግሩፕ ቴሌግራም
https://t.me/+do8_6-C5_ek4MjFk

Telegram Cominicate
@BIYYALALLABAARSII

IMO👇👇👇👇👇ኢሞ
https://call.imo.im/BiyyaLallabaArsii
እንኳን ለደብረ ታቦር በዓል በሰላም አደረሳችሁ
የደብረ ታቦር በዓል ብፁዕ አባታችን አቡነ ኤልሳዕ የአርሲ እና ሶማሌ ክልል ጅግጅጋ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ የቅዱስ ሲኖዶስ አባል በተገኙበት በአርሲ ሀገረ ስብከት ሄጦሳ ወረዳ በኢተያ ደብረ ታቦር እግዚአብሔር አብ ቤተ ክርሰቲያን በመንፈሳዊ ድምቀት ተከበረ።

የአርሲ ሀገረ ስብከት ሚድያ Miidiyaa Biyya Lallaba Arsii
#ነሐሴ_13_2018_ዓ_ም
#አርሲ_ኢተያ_ኢትዮጵያ

Ayyaanni Tulluu Taabor Bakka Eebbifamoo Abbaan Keenya Abuna Eelsa'i Hangafa Phaaphaasii Biyyoota Lallabaa Arsii fi Naannoo Somaalee Miseensa Qulqulluu Sinoodosii Argamanitti Biyya Lallaba Arsii Mana Lubummaa Aanaa Heexosaa Mana Kiristaanaa Tulluu Taabor Waaqa Abbaa Itayyaatti haala Afuurawaa fi hoo'aa ta'een kabajamee oole.

ደብረ ታቦር (የታቦር ተራራ)

“ደብረ ታቦር” የሁለት ቃላት ጥምር ነው፡፡ “ደብር” እና “ታቦር” ፡፡ በዚህም መሠረት “ደብር” ማለት ተራራ፣ “ታቦር” ደግሞ በናዝሬት አካባቢ በሰማርያ አውራጃ በገሊላ ወረዳ የሚገኝ የረጅም ተራራ ስም ነው፡፡ ደብረ ታቦር ማለት የታቦር ተራራ ማለት ነው፤ የታቦር ተራራ የአይሁድ ማኅበረሰብ በዕብራይስጥ ቋንቋ ከፋር ታቦር (kfar-Tovor) ሲሉት፤ የእንግሊዘኛ ተናጋሪዎች (Transfiguration mount) ይሉታል፤ ብርሃነ መለኮቱ የተገለጠበት ተራራ እንደ ማለት ነው፡፡

ይህንን ተራራ ሁለቱ ወንጌላውያን ቅዱስ ማቴዎስና ቅዱስ ማርቆስ “ረጅሙ ተራራ” ሲሉት ቅዱስ ጴጥሮስ ደግሞ “ቅዱስ ተራራ” በማለት ጠርቶታል /ማቴ. ፲፯፥፩፤ ማር.፱፥፩፤ ፪ጴጥ ፩፥፲፮-፲፰/፡፡ በዚህ ተራራ ላይ ጌታችን አምላካችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ብርሃነ መለኮቱን እንደሚገልጽ አስቀድሞ ልበ አምላክ ክቡር ዳዊት በመዝሙሩ “ታቦርና አርሞንኤም በስምህ ደስ ይላቸዋል” ብሎ ተናግሮ ነበር /መዝ. ፹፰፥፲፪/፡፡ ጌታችን አምላካችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በዚህ ተራራ ላይ ብርሃነ መለኮቱን በመግለጡ፤ ተራሮችም የፈጣሪያቸውን ተዓምራት በማየታቸው የነቢያት ትንቢት ተፈጽሟል፡፡

የደብረ ታቦር ተራራ በምድረ እስራኤል ከገሊላ ባሕር በምዕራባዊ ደቡብ በኩል 17 ኪ.ሜ ርቀት ላይ የሚገኝ ሲሆን፤ ከናዝሬት ከተማ በስተምሥራቅ፣ ከዮርዳኖስ ወንዝ በስተምዕራብ አቅጣጫ የሚገኝ ቅዱስ ተራራ ነው፡፡ ደብረ ታቦር ከፍታው ከባሕር ጠለል (ወለል) 572 ሜትር ነው፡፡ በመስኩ ጥናትና ምርምር ያደረጉ ሊቃውንት የታቦርን ተራራ ሥዕላዊ በሆነ መንገድ ሲገልጹ የተገለበጠ የሻይ ስኒ /Down Tea cup/ ይመስላል ይሉታል፡፡ በጥንት ዘመን ደብረ ታቦር ለእስራኤላውያን በጦርነት ጊዜ ሲያሸንፉ የሚደሰቱበት፣ ሲሸነፍም መደበቂያቸው እንደነበር ታሪክ ያስታውሳል፡፡

በዚህ ተራራ ነቢዩ ሳሙኤል ትንቢት ተናግሮበታል፡፡ ንጉሥ ሳኦልም ከሦስት ሰዎች ጋር ተገኝቶበታል /፩ኛ ሳሙ.፲፥፫/፡፡ ርእሰ አበው አብርሃምና ኖኅ በዚህ ተራራ ላይ ቀስተ ደመና ተተክሎ አይተዋል፡፡ አባታችን ኖኅም ይህንን ተራራ “መካነ ብርሃን፤ የብርሃን ቦታ” ብሎ ጠርቶታል፡፡ ኢየሱስ ክርስቶስ በዚህ ተራራ ላይ ክብሩን እንደገለጠና የዚህም ተራራ ስም ታቦር መሆኑን ሐዋርያት በሲኖዶሳቸው ገልጠዋል፡፡ ኢትዮጵያዊው ሊቅ ቅዱስ ያሬድም ይህንን ረጅም ተራራ ደብረ ታቦር እያለ በድጓው ጽፏል፡፡ በዓለ ደብረ ታቦር ጌታችን ምሥጢረ መለኮቱን የገለጠበት፤ ብርሃን የታየበትና ድምፀ መለኮቱ የተሰማበት ዕለት ስለሆነ “የብርሃን በዓል” (Transfiguration) ይባላል፡፡

ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በፊሊጶስ ቂሳርያ ደቀመዛሙርቱን “ሰዎች የሰውን ልጅ ማን ይሉታል?” ብሎ ጠየቃቸው፡፡ ቅዱስ ጴጥሮስም “አንተ የሕያው እግዚአብሔር ልጅ ነህ!” ብሎ መሰከረ /ማቴ ፲፮፥፲፮/፡፡ ቅዱስ ጴጥሮስ የሃይማኖት መሠረት የሆነውን የጌታችንን ነገረ ተዋሕዶ ከመሰከረ ከስድስት ቀን በኋላ አዕማድ ሐዋርያት ተብለው የተጠሩትን ጴጥሮስ፣ ያዕቆብና ዮሐንስን ይዞ ወደ ተራራ አወጣቸው፡፡ ጌታችን ብርሃነ መለኮቱን በደብረ ታቦር የገለጠው ከተስእሎተ ቂሣርያ በስድስተኛው ቀን (ነሐሴ ፲፫ ቀን) ነው፡፡

ደብረ ታቦር ተራራን ለምን መረጠ?

ጌታችን አምላካችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ብርሃነ መለኮቱን ለመግለጽ የታቦር ተራራን የመረጠው፤ሌሎች ተራራሮችን ያልመረጠው ስለምንድን ነው? ቢባል ትንቢትና ምሳሌውን ለመፈጸም ነው፡፡ ትንቢቱ፡- “ታቦር ወአርሞንኤም በስመ ዚአከ ይትፌስሑ ወይሴብሑ ለስምከ ታቦርና አርሞንኤም በስምህ ደስ ይላቸዋል” /መዝ. ፹፰፥፲፪/ በማለት ነቢዩ ዳዊት ትንቢት ተናግሮ ነበርና ጌታም ብርሃነ መለኮቱን በታቦር ተራራ በመግለጹ ይህ ትንቢት ተፈጽሟል፡፡ ምሳሌው፡- ምሳሌው ይፈጸም ዘንድ ነው፤ ይኸውም መስፍኑ ባርቅ ሲሣራን በታቦር ተራራ ድል ነስቶታል /መሳ. ፬፥፬—፳፬/፡፡

ተራራ የወንጌል ምሳሌ ናት፡፡ ተራራ ሲወጡት ያስቸግራል፤ ከወጡት በኋላ ግን ከታች ያለውን ሁሉ ሲያሳይ ደስ ይላል፡፡ ወንጌልም ሲማሯት ታስቸግራለች፡፡ ከተማሯት በኋላ ግን ጽድቅንና ኃጢአትን ለይታ ስታሳውቅ ደስ ታሰኛለች፡፡ አንድም ተራራ የመንግሥተ ሰማያት ምሳሌ ነው፡፡ ተራራን በብዙ ጻዕር እንዲወጡት መንግሥተ ሰማያትንም በብዙ መከራ ያገኟታልና /ሐዋ.፲፬፥፳፪/፡፡ አንድም ተራራ የቤተክርስቲያን ምሳሌ ናት፡፡ በደብረ ታቦር ምስጢረ ሥላሴ እንደተገለጠ በቤተ ክርስቲያንም የቅድስት ሥላሴ አንድነትና ሦስትነት ይነገርባታልና፡፡ ተራራ መሠረቱ ከመሬት አናቱ ከሰማይ እንደሆነ ሁሉ፤ ቤተ ክርስቲያንም መሠረቷ በምድር ሲሆን ራሷ (ክርስቶስ) በሰማይ ነውና፡፡ የቤተክርስቲያን አገልጋዮቿ የተጠሩት ከምድር (ከዓለም) ሲሆን ክብራቸው ግን በሰማይ ነው፡፡ ቅዱስ ጳውሎስ “እኛስ ሀገራችን በሰማይ ነውና” እንዲል /ፊልጵ.፫፥፳/፡፡ በዚህም መነሻነት ጌታችን በልዩ ልዩ ኅብረ አምሳል ለደቀመዛሙርቱ ነገረ ተዋሕዶውን አስረዳቸው፡፡

ከነቢያት ሁለቱን ከሐዋርያት ሦስቱን ስለምን አመጣ?

ሁለቱን ከነቢያት ሦስቱን ከሐዋርያት ስለምን አመጣ ቢሉ ደብረ ታቦር የቤተክርስቲያን ምሳሌ መሆኑን ሲያስረዳ ነው፡፡ በቤተክርስቲያን ነቢያት ያስተማሩት ብሉይ ኪዳንና ሐዋርያት የሰበኩት ሐዲስ ኪዳን ይነገራሉና፡፡ በደብረ ታቦር ነቢያት፣ሐዋርያት እንደ ተገኙ ሁሉ፤ዛሬ በቤተክርስቲያን ብሉይና ሐዲስ ኪዳን ይሰበካል፡፡ ሥርዐተ ቅዳሴ የሚፈጽሙ ልዑካን አምስት መሆናቸውም በደብረ ታቦር የተገኙትን ሙሴን፣ኤልያስን፣ጴጥሮስን፣ያዕቆብንና ዮሐንስን ያስታውሱናል፡፡ ዘወትር በቤተ መቅደሱ የሚፈተተው ቅዱስ ሥጋውና ክቡር ደሙ ደግሞ በደብረ ታቦር ብርሃነ መለኮቱን የገለጠው የጌታችን የመድኀኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስ ቅዱስ ሥጋውና ክቡር ደሙ ነው፡፡ አንድም ደብረ ታቦር የመንግሥተ ሰማያት ምሳሌ ነው፡፡ በሕግ በሥርዐት ያገቡ ሰዎችም፣በንጽሕና በድንግልና በምንኩስና የአምላካቸውን ፈቃድ የሚፈጽሙ መናንያን፣ባሕታውያን፣መነኮሳት አንድ ሆነው መንግሥተ ሰማያትን እንደሚወርሷት ለማጠየቅ ከሕጋውያን ሙሴን ከደናግል ደግሞ ኤልያስን አመጣ፡፡ ሙሴን ከመቃብር አስነሥቶ ኤልያስን ከብሔረ ሕያዋን አምጥቶ በደብረ ታቦር ተራራ አብረውት እንዲገኙ ያደረገው ደቀ መዛሙርቱ ሙሴ ነው ወይም ኤልያስ ነው በማለት ሲጠራጠሩ እንዳይኖሩ መለኮታዊ
👍1
ትምህርት ለመስጠትም ነው፡፡

ቡሄ(ሔ)

የደብረ ታቦር በዓል በምእመናን ዘንድ ቡሄ(ሔ) በመባል ይታወቃል፡፡ ቡሄ በሀሌታው “ሀ” እና በሐመሩ “ሐ” ይጻፋል፡፡

በሀሌታው “ሀ” ሲጻፍ “ቡሄ” ማለት “የበራ የደመቀ የጐላ ብርሃን የብርሃን በዓል እንደ ማለት ነው ይህም በቅዱስ ወንጌል እንደተጻፈው ጌታችን በደብረ ታቦር ብርሃነ መለኮቱን በገለጠ ጊዜ ፊቱ እንደ ፀሐይ በማብራቱ፥ ልብሱም አጣቢ በምድር ላይ ሊያነጣው እስከማይችል ድረስ በጣም ነጭ አንጸባራቂ ሆነ እንዲል፡፡ /ማቴ. ፲፯፥፩፤ ማር.፱፥፪፤ ሉቃ፱፥፳፱/፡፡ ጌታችን ብርሃነ መለኮቱን የገለጠበት በዓል የሚዘከርበት እና ለበዓሉም ችቦ ስለሚበራ “የብርሃን በዓል” በማለት “የቡሄ በዓል” እንላለን፡፡ ወቅቱ የክረምት ፤ጨለማ አልፎ የብርሃን የሚወጣበት፤ ሰማይ ከጭጋጋማነት ወደ ብሩህነት የሚለወጥበት የመሸጋገሪያ ወቅት ነው፡፡ “ቡሄ ከዋለ የለም ክረምት፤ ዶሮ ከጮኸ የለም ሌሊት” እንዲሉ፡፡

በሐመሩ “ሐ” ሲጻፍ “ቡሔ” ማለት ደግሞ “ደስታ ፍሥሐ” ማለት ይሆናል፡፡ ይኸውም በትንቢት እንደተጻፈው “ታቦር ወአርሞንኤም በስመ ዚአከ ይትፌስሑ ወይሴብሑ ለስምከ፤ ታቦርና አርሞንኤም በስምህ ደስ ይላቸዋል” እንዲል /መዝ. ፹፰፥፲፪/፡፡ በዚህ ትንቢታዊ ቃል መሠረት በወቅቱ የጌታ ብርሃን በዙሪያቸው አብርቷል ከታቦርም እስከ አርምንዔም ተራራ ድረስ ታይቷል፡፡ ይህም መለኮታዊ ብርሃን በወረደበት ጊዜ ከብቶቻቸውን ይጠብቁ የነበሩ በታቦርና በአርሞንኤም አካባቢ ያሉ መዓልቱ የሌሊቱን ቦታ ስለ ወሰደው በሁኔታው ሐሴትን አድርገዋል፡፡

ጌታችን ብርሃነ መለኮቱን በገለጠበት ዕለት እረኞች ከብርሃኑ የተነሣ እየተገረሙና እየተደነቁ ወደ ቤት አልተመለሱም ነበር፡፡ የልጆቹን መዘግየት ያዩ ወላጆች ችቦ አብርተውና ዳቦ ይዘው ፍለጋ ወጥተዋል፡፡ ‹ቡሄ› ለሚሉ ልጆች ሙልሙል ዳቦ የሚሰጠውና በበዓሉ ችቦ የሚበራውም ከዚህ ታሪክ በመነሣት ነው፡፡ ለክርስትና ልጅ፣ ለአማች፣ ለምራት፣ ለዘመድ አዝማድ ዅሉ የቡሄ ዳቦ ይሰጣል፡፡ ልጆችም ዳቧቸውን እየገመጡ ጅራፍ ሲገርፉ ይውላሉ፡፡

ጅራፍ

ጌታችን ብርሃነ መለኮቱን ሲገልጥ ነጎድጓዳማ ድምፅ መሰማቱን የብርሃን ጎርፍም መውረዱን በማሰብ በሀገራችን በኢትዮጵያ ያሉ ወጣቶች ለነጎድጓዱ ምሳሌ አድርገው ጅራፍ በማጮኽ፣ የብርሃን ጎርፍ ምሳሌ አድርገው ችቦ በማብራት ያከብሩታል፡፡በደብረ ታቦር በዓል በትውፊታዊ መልኩ ጅራፍ መገመድ(መጥለፍ) እና ጅራፍ ማጮኽ ሁለት ዓይነት ምስጢር የያዘ ትውፊታዊ ተግባር ነው፡፡ የመጀመሪያው ግርፋቱንና ሞቱን እናስብበታለን፡፡ ሁለተኛው ደግሞ ፤ድምፁን ስንሰማ የባሕርይ አባቱን የአብን ምስክርነት ቃል፤ እንደ ነጎድጓድ ድምፅ ያስታውሰናል፡፡የጅራፍ ትውፊታዊነት /ውርስ/፣ መጽሐፋዊ ትምህርትና ምስጢር ጠብቆ ለትውልድ እንዲተላለፍ ለማድረግ ጨዋታውን በተራራማ አካባቢ፣ ከመኖሪያ ቤት ርቆና፣ በሜዳ ማድረጉ ጠቃሚ ነው፡፡

ችቦ

ችቦ የጌታችንን ብርሃነ መለኮት መገለጥ የሚያመለክት ነው፡፡ በመሆኑም ችቦ ለኩሰን በዓሉን እናከብራለን፡፡ የዚህ ትውፊታዊ አመጣጥ በብርሃኑ ድምቀት የቀኑን መምሸት ያልተረዱ እረኞች በሜዳ ቀርተዋልና ወላጆች ከመንደር ችቦ ለኩሰው ልጆቻቸውን ፍለጋ ሔደዋልና ታሪኩን እያዘከርን በዓሉት እናከብራለን፡፡ የችቦው መንደድም ሌላ ትርጉም አለው፡፡ አንድ ምእመን ለሌላው ምእመን መካሪ አስተማሪ መሆኑን፣ መከራ እየተቀበለም አርአያ፣ ምሳሌ፣ ብርሃን መሆኑን ያሳያል፡፡ በሃይማኖትም አርአያ ምሳሌ ይሆንላቸዋል፡፡

ሙሉሙል

“ሙልሙል/ኀብስቱ” በታቦር ተራራ ዙሪያ ለነበሩት እረኛች ወላጆቻቸው ምግባቸውን ይዘው መሄዳቸውን ያጠይቃል፡፡ አንድም የኀብስቱ ምሳሌነት ለክርስቶስ ነው “አነ ውእቱ ኅብስተ ሕይወት ዘወረደ እምሰማያት” እንዲል /ዮሐ፮፥፴፪/፡፡

በችቦ ብርሃን ልጆቻቸውን ፍለጋ የወጡ ወላጆች ዳቦ ጋግረው ይዘውላቸው ወጥተዋል፡፡ ስጦታው ቤተሰባዊነትን፣ ፍቅርንና መተሳሰብን መግለጫ ነው፡፡ ወደ ቤታችን “ ቡሄ ” እያሉ ለሚመጡ አዳጊዎችም፤ ዘምረው እንዳበቁ የሚሰጥ “ሙልሙል” ዳቦ አለ፡፡ ሕፃናቱም ሊዘምሩ ሲመጡይሰጣል፡፡ ሕፃናቱ የደቀመዛሙርት ምሳሌ ናቸው፡፡ መዝሙራቸው ደግሞ ሐዋርያት “የምሥራች” ይዘው የመምጣታቸው ምሳሌ ነው፡፡ ሐዋርያት በገቡበት አገር አስተምረው አጥምቀው የጸጋ ልጅነትን አሰጥተው በረከት አድለው እንደሚሔዱም፣ ልጆችም ዘምረው፣ አመስግነው፣ መርቀው “ውለዱ ክበዱ፣ ሀብት አግኙ፣ የመንግሥተ ሰማያት ወራሾች ያድርጋችሁ ….” ይላሉ፡፡

እንደ መውጫ

የደብረ ታቦር በዓል በቤተክርስቲያናችን ከዋዜማው ጀምሮ እስከ በዓሉ ፍጻሜ ድረስ ማሕሌት ይቆማል፡፡ ሊቁ ቅዱስ ያሬድ ስለ በዓሉ የደረሰው “በታማኞችህ ነቢያት በሙሴና በኤልያስ ፊት የባሕርይ ልጅነትህን መሰከርኩልህ” የሚለው መዝሙር በመዘመር ለበዓሉ ልዩ ድምቀት ተሰጥቶት ይውላል፡፡ የአብነት ተማሪዎች እንደ ቅዱሳን ሐዋርያት ትምህርት ሃይማኖትን የሚማሩ ናቸውና ለሐዋርያት ነገረ መለኮቱን የገለጠ አምላክ እንዲገልጥላቸው በዓለ ደብረ ታቦርን በተለየ ድምቀት ያከብሩታል፡፡ አባቶቻችን ቀደምት ኢትዮጵያውያን ሃይማኖታዊ በዓላትን በትምህርት ከማስተላለፍ ባሻገር ምሳሌነታቸውን በባሕላችን ውስጥ እንድንይዘው በማድረግ ሃይማኖታዊ አስተምህሮው ለሁሉም የኅብረተሰብ ክፍል እንዲገለጽ ያደርጋሉ፡፡

በአጠቃላይ ኦርቶዶክሳውያን የደብረ ታቦርን በዓል ስናከብር ቅዱስ ጴጥሮስ “ለእኛ በዚህ መኖር መልካም ነው” እንዳለው በደብረ ታቦር በምትመሰለው በቤተክርስቲያን ውስጥ ሆነን የቤተ ክርስቲያናችን ሕግና ሥርዐት አክብረን፣ በቤቱ ጸንተን እስከ ሕይወታችን ፍጻሜ መኖር ይኖርብናል፡፡ በዓሉን ስናከብር በምስጋና በመዘመር እንጂ ሌሎች ሃይማኖታዊ መሠረት የሌላቸውን ባሕላዊ ነገሮች በማተኮር መሆን የለበትም፡፡

በአጠቃላይ በዓለ ደብረ ታቦር ከእነዚህ ምስክር ካላቸው ትምህርቶቹ፣ ምሥጢር ከሚራቀቅባቸው ትርጓሜያቱና ከትውልድ ትውልድ በቅብብል በተላለፈው ቅዱስ ትውፊት ጋር ሃይማኖታዊ ባሕል ሆኖ ሊቀጥል ይገባዋል፡፡ ይህን ማድረግ የሚቻለው ግን አዳጊዎች ሃይማኖታዊ ትውፊቱን ይዘው እንዲያድጉ ጥቆማ በመስጠት፣ ግጥም በመግጠምና ምሥጢሩን በማብራራት የመጀመሪያዎቹ ባለድርሻዎች ወላጆች ናቸው፡፡

ወስብሐት ለእግዚአብሔር

ዋቤ መጻሕፍት
✍️ መጽሐፍ ቅዱስ
✍️ መጽሐፈ ስንክሳር
✍️ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ታሪክ
✍️ በዓላት
✍️ ኢንሳይክሎፒዲያ(መድብል)

የብፁዕነታቸው ጸሎትና ቡራኬ አይለየን🙏

© Arsi Diocese Public Relations Department
© Biyya Lallaba Arsiitti Kutaa Sab-Qunnamtii
© የአርሲ ሀገረ ስብከት ህዝብ ግንኙነት ክፍል

© የአርሲ ሀገረ ስብከት ሚድያ Miidiyaa Biyya Lallaba Arsii ...✍️

👉 Liinkii Gadii Kana Hordofuudhan Gara Chaanaaliiwwan Miidiyaa Keenyatti Dabalamaa
👉 ከታች ያሉትን ሊንክ በመጫን ወደ ቻናሎቻችን ተቀላቀሉ

👉 FACEBOOK👇👇👇👇👇ፌስቡክ
https://www.facebook.com/share/1bp49TDKhZ/

👉 TIKTOK👇👇👇👇👇ቲክቶት
tiktok.com/@miidiyaa.ku.la.arsii

WhatsApp 👇👇👇👇👇ዋትሳፕ
https://whatsapp.com/channel/0029Vb6ZyoHId7nSWz2Uq73X