👋ሰላም ለኩልክሙ,እፎ ሀለውክሙ አኃዉየ ወአኀትየ?(ሰላም ለሁላችሁ,እንደምን አላችሁ ወንድሞች እህቶቼ?)👋
✅ዮርዳኖስ ታዬ እባላለሁ።
ልሳነ ግእዝ ክፍል አንድ
ከዚህ በመቀጠል በሚኖሩን በተከታታይ ክፍለ ትምህርቶች መሰረታዊ የግእዝ ቋንቋ ትምህርቶችን እንማራለን።
በቅድሚያ ስለቋንቋው አጠቃላይ ምንነት እንመልከት።
⏺ልሳነ ግእዝ⏺
🎖የግእዝ ቋንቋ ረቂቅ የሆነ፣ራሱን የቻለ፣ጥንታዊና ቀዳማዊ ቋንቋ ነው።
🎖"ግእዝ" የሚለው ቃል "አግዐዘ-ነፃ አወጣ፣አርነት ወጣ" ከሚለው የግእዝ ግሥ የወጣ ሲሆን ትርጉሙም የነፃ አውጪዎች፣የነፃነት ቋንቋ ማለት ነው።
🎖 "ነፃ መውጣት" ከሚለው ፍቺው በተጨማሪም "ጸባይ፣ባህርይ፣መጓጓዝ" እየተባለ እንደየገባበት አውዳዊ ሀሳብ ሊፈታ ይችላል። ከዚህም በተጨማሪ "አንድ ወይም መጀመርያ" የሚል ፍቺ ሊሰጠው ይችላል።
🎖ይህ ቋንቋ በአፍሮ-እስያን(Afro Asiatic) የቋንቋ ነገድ፣በሴማውያን (Semetic) ንዑስ ነገድ ስር የሚመደብ ሲሆን የራሱ የሆኑ
🔺ፊደላት፣ 🔺የቁጥር አሐዝ፣ 🔺የንባብ ሥርዓት እንዲሁም 🔺የአጻጻፍ ሥርዓት ያለው ቋንቋ ነው።
🎖በጥንታውያን ኢትዮጵያውያን የተሰሩ የድንጋይ ላይ ጽሑፎች፣የተለያዩ ድርሳናት፣የታሪክ የምርምርና የጥበብ መጻሕፍት በብራና ላይ የተጻፉበት ቋንቋም ነው።
🎖 በውጭ ሀገራት ዮኒቨርስቲዎችም የቋንቋው ጥናትና ምርምር እስከ ሦስተኛ ዲግሪ ፕሮግራም እየተሰጠ ይገኛል።
🎖ቋንቋውን እስከ አሁን ድረስ በብቸኝነት እየተጠቀመችበት ያለችው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክሳዊት ተዋህዶ ቤተክርስቲያን መሆኗ እና ቋንቋውን ለቤተክርስቲያኒቷ እና ለአማኞቿ ብቻ በመተው ችግር ምክንያት ቋንቋው ሀገር ውስጥ መስፋፋት ሳይችል ቀርቷል። ነገር ግን ቋንቋው የኢትዮጵያ እንጂ የአንድ ሃይማኖት ተቋም ብቻ አለመሆኑን መረዳት ያስፈልጋል።
❓ለማንኛውም ጥያቄ እና አስተያየት እነዚህን አማራጮች ይጠቀሙ።
@geezcommentbot @ardietegeez_discussion
ardietegeez@gmail.com
📌 አንድ ሰው የግእዝ ቋንቋን ለማወቅ ከፈለገ በቅድሚያ🔺በፊደላት ጥናት መጀመር አለበት።
🎖 ፊደል ማለት "ፈደለ-ጻፈ" ከሚለው የግእዝ ግሥ የመጣ ሲሆን ትርጉሙም የቃል ወኪል ምልክት ማለት ነው።
🎖ፊደል የማንኛውም ጽሑፍ መነሻ፣የቋንቋ መገለጫ ስለሆነ የትኛውም ቋንቋ የራሱ የሆነ ፊደል ባይኖረው እንኳን በፊደል የማይገለፅ ቋንቋ አይኖርም ማለት ነው።
📌የግእዝ ቋንቋ ፊደላትና አመጣጣቸው
🎖የግእዝ ፊደላት አጻጻፍ የተጀመረው የአዳም ሦስተኛ ትውልድ በሆነው በነብዩ በሔኖስ ዘመን ነበር። ለዚህ ነብይ የግእዝ ፊደላት በጻፍጻፈ ሰማይ (በሰማይ ገበታነት) ታይቶት እንደነበር ይነገራል።
🎖በአጠቃላይ የግእዝ ፊደላት በብዛታቸው ሃያ ስድስት(፳፮)ናቸው።
እነርሱም :-
ሀ -ሀሌታው 'ሀ'
ለ
ሐ -ሐመሩ 'ሐ'
መ
ሠ -ንጉሡ 'ሠ'
ረ
ሰ -እሳቱ 'ሰ'
ቀ
በ
ተ
ኀ -ብዙኃኑ 'ኀ'
ነ
አ -አልፋው 'አ'
ከ
ወ
ዐ -ዓይኑ 'ዐ'
ዘ
የ
ደ
ገ
ጠ
ጰ
ጸ -ጸሎቱ 'ጸ'
ፀ -ፀሐዩ 'ፀ'
ፈ
ፐ ናቸው።
🎖ፊደላቱ በዚህ መልኩ ከመደርደራቸው በፊት ከስር በምትመለከቱት መልኩ ይደረደሩ ነበር።
አ
በ
ገ
ደ
ሀ
ወ
ዘ
ሐ
ኀ
ጠ
የ
ከ
ለ
መ
ነ
ሠ
ዐ
ፈ
ጸ
ፀ
ቀ
ረ
ሰ
ተ
ጰ
ፐ
ከነዚህ 26 ፊደላት በተጨማሪ የግእዝ ቋንቋ ሌሎችም ፊደላት አሉት።👇
📌የግእዝ ሕጹጻን(ዝርዋን)ፊደላት
🎖ዝርዋን የግእዝ ፊደላት የሚባሉት ፊደላት መሰረታቸው የግእዝ ፊደል ሆኖ በቅርጻቸውና በሚሰጡት ድምጽ ከመነሻ የግእዝ ፊደላቱ መጠነኛ ልዩነት ስላላቸውና እንደመነሻ የግእዝ ፊደላቱ በሰባት(፯)ዝርዝር ስለማይዘረዘሩ ነው። በአማርኛ መጠርያቸውም "የግእዝ ዲቃላ ፊደላት"ይባላሉ።
🎖የግእዝ ዝርዋን ፊደላት ከነመነሻ ፊደላቸው በሚከተለው ምስል👇 ቀርበዋል።

🔴ማስታወሻ🔴
🎖"ሸ፣ ቸ፣ ኘ፣ ኸ፣ ዠ፣ ጀ፣ ጨ፣ ቨ"
እነዚህፊደላት የግእዝ ፊደላት አይደሉም። ነገር ግን መነሻቸው ግእዝ የሆኑ የአማርኛ ፊደላት ናቸው።
🎖እነዚህ በአማርኛ ስነጽሑፍ ላይ የምንጠቀማቸው ፊደላት ከነመነሻ የግእዝ ፊደላቸው እንደሚከተለው ቀርበዋል።
መነሻ የግእዝ ፊደል የአማርኛ ፊደል
ሰ -------------------------- ሸ
ተ --------------------------- ቸ
ነ ---------------------------- ኘ
ከ --------------------------- ኸ
ዘ ---------------------------- ዠ
ደ ---------------------------- ጀ
ጠ ---------------------------- ጨ
በ____________________ቨ
🎖እነዚህ የአማርኛ ፊደላት እንደ ግእዝ አቻዎቻቸው ዲቃላ/ዝርዋን ፊደላት አሏቸው።
ለምሳሌ :-
ሸ-ሿ ጨ-ጯ
ቸ-ቿ ኘ-ኟ
ጀ-ጇ ዠ-ዧ ...

🤗የዛሬው መርሀግብር ይህን ይመስላል ።
🔄በቀጣይ
🎖የግእዝ ፊደላት አላስፈላጊ ድግግሞሽ ይታይባቸዋል?
🎖ተመሳሳይ ድምፅ እያላቸው ለምን በተለያየ ቅርፅ ቀረቡ?
🎖ፊደላቱስ መቀነስ አለባቸው ወይ?
የሚሉትን ጥያቄዎች በሰፊው እንመልሳለን።
❓ለማንኛውም ጥያቄ እና አስተያየት እነዚህን አማራጮች ይጠቀሙ።
@geezcommentbot @ardietegeez_discussion
ardietegeez@gmail.com
እሴብሓክሙ እምነ ልብየ ለኩልክሙ በይነ ተለውክሙኒ በውስተ ምሉዕ መርሃግብርየ።
(በመርሃግብሩ ሙሉ ስለተከታተላችሁኝ ሁላችሁንም ከልቤ አመሰግናለሁ።)🙏🙏
ምንጭ:- የአቡነ ጎርጎርዮስ ት/ቤት የግእዝ ቋንቋ መማሪያ መጻሕፍት እና ሌሎች የግእዝ ቋንቋ መጻሕፍት
@ardietegeez

👋ሰላም ለኩልክሙ,እፎ ሀለውክሙ አኃዉየ ወአሀትየ?(ሰላም ለሁላችሁ,እንደምን አላችሁ ወንድሞች እህቶቼ?)👋
ክፍል ሁለት
▶️በዛሬው መርሀግብራችን
🎖የግእዝ ፊደላት አላስፈላጊ ድግግሞሽ ይታይባቸዋል?
🎖ተመሳሳይ ድምፅ እያላቸው ለምን በተለያየ ቅርፅ ቀረቡ?
🎖ፊደላቱስ መቀነስ አለባቸው ወይ?
በሚሉትን ጥያቄዎች ዙሪያ በሰፊው እንማማራለን።
(የዛሬዉ ጽሑፍ ረዘም ያለ ቢሆንም በጣም ጠቃሚ ፍሬ ሀሳብ የያዘ ከመሆኑም በላይ በብዛት ያካተተው ምሳሌዎችን ስለሆነ በትዕግሥት ብታነቡት እና ብትጠቀሙበት እላለሁ።)
፩ - 🎖የግእዝ ፊደላት አላስፈላጊ ድግግሞሽ ይታይባቸዋል?
📌 የግእዝ ፊደላት ድግግሞሽ አይታይባቸውም!
ድግግሞሽ ማለት በቅርፅ፣ በዓይነት እና በይዘት ተመሳሳይነት ያላቸውን ነገሮች ከአንድ ጊዜ በላይ ማቅረብ ማለት ነው። በብዙዎች ዘንድ ተደጋግመዋል ተብለው የሚታሰቡት እነዚህ ፊደላት ግን ከድምፀታቸው በስተቀር በቅርፅም ይሁን በግልጋሎት ፍፁም የተለያዩ ስለሆኑ ተደጋግመዋል ማለት አይቻልም።
🤔 እነዚህ ተደጋግመዋል የተባሉት ፊደላት የትኞቹ ናቸው?
✂️ "ሀ" ፣ "ሐ" እና "ኀ"
✂️ "ሠ" እና "ሰ"
✂️ "አ" እና "ዐ"
✂️ "ፀ" እና "ጸ" ናቸው።
(ልዩ መጠሪያ ስማቸውን በትናንቱ መርሃግብር ላይ ጠቅሰናል።)
፪ - 🎖ተመሳሳይ ድምፅ እያላቸው ለምን በተለያየ ቅርፅ ቀረቡ?
📌ተመሳሳይ ድምፅ ቢኖራቸውም በተለያዩ ቅርፆች መቅረባቸው ያስፈለገው ፊደላቱ አገልግሎታቸው የተለያየ በመሆኑ ነው። አንዱ ፊደል መግባት በነበረበት ቦታ ሌላኛው (የድምፅ-አቻዉ) ፊደል ተተክቶ ቢገባ ቃሉን ትርጉም አልባ ያደርገዋል ወይም ደግሞ ያልተፈለገ ትርጉም ይሰጠዋል።
🤗ይህ እንዴት እንደሚሆን በርከት ባሉ ምሳሌዎች እንመልከት ።
(በምሳሌዎቹ ላይ የተዘረዘሩት የግእዝ
ግሶች/verbs እና ስሞች/nouns ሲሆኑ የፊደላት አጠቃቀም እና ያላቸውን የትርጉም ልዩነቶች በደንብ ያሳዩናል።)
ምሳሌ ፩ መሐረ፣ መሀረ ፣ መኀረ
ትርጉም :- መሐረ - ይቅር አለ
መሀረ - አስተማረ
መኀረ -🚫 ትርጉም የማይሰጥ
ምሳሌ ፪ ሀለወ ፣ ኀለወ ፣ ሐለወ
ትርጉም :- ሀለወ - አለ/ይኖራል/
ኀለወ - ጠበቀ
ሐለወ - 🚫 ትርጉም የማይሰጥ
ምሳሌ ፫ ዓመት ፣ አመት
ትርጉም :- ዓመት - ዘመን/የጊዜ መለኪያ
አመት - ሴት አገልጋይ
ምሳሌ ፬ ኀለየ ፣ ሐለየ ፣ ሀለየ
ትርጉም :- ኀለየ - አሰበ
ሐለየ - ዘመረ
ሀለየ - 🚫 ትርጉም የማይሰጥ
ምሳሌ ፭ ሰብሐ ፣ ሠብሐ
ትርጉም :- ሰብሐ - አመሰገነ
ሠብሐ - ሰባ/ወፈረ
ምሳሌ ፮ ቀሠመ ፣ ቀሰመ
ትርጉም :- ቀሠመ- ለቀመ
ቀሰመ - አጣፈጠ
ምሳሌ ፯ ሠረቀ ፣ ሰረቀ
ትርጉም :- ሠረቀ - ወጣ
ሰረቀ - ሰረቀ/ዘረፈ
ምሳሌ ፰ ፈፀመ ፣ ፈጸመ
ትርጉም :- ፈፀመ - ዘጋ
ፈጸመ - ጨረሰ
ምሳሌ ፱ ኀመየ ፣ ሐመየ ፣ ሀመየ
ትርጉም :- ኀመየ - አሰረ
ሐመየ - አማ( ሀሜት)
ሀመየ - 🚫 ትርጉም የማይሰጥ
ምሳሌ ፲ አርገ ፣ ዐርገ
ትርጉም :- አርገ - ሸመገለ
ዐርገ - ወጣ(ወደ ላይ ወጣ)
ምሳሌ ፲፩ ሠዐለ ፣ ሰአለ
ትርጉም :- ሠዐለ - ሳለ (ለስዕል)
ሰአለ - ለመነ
ምሳሌ ፲፪ ሀለለ ፣ ሐለለ ፣ ኀለለ
ትርጉም :- ሀለለ - በራ
ሐለለ - ደረቀ
ኀለለ - 🚫ትርጉም የማይሰጥ
ምሳሌ ፲፫ ኀብለ ፣ ሐብለ ፣ ሀብለ
ትርጉም :- ኀብለ - ደፈረ
ሐብለ - አበለ (ዋሸ)
ሀብለ - 🚫ትርጉም የማይሰጥ
ምሳሌ ፲፬ በጥሐ ፣ በጥኀ ፣ በጥሀ
ትርጉም :- በጥሐ - በጣ
በጥኀ - ደነቆረ
በጥሀ -🚫 ትርጉም የማይሰጥ
ምሳሌ ፲፭ ነስሐ ፣ ነስኀ ፣ ነስሀ
ትርጉም :- ነስሐ - ተመለሰ
ነስኀ - ሸተተ
ነስሀ - 🚫ትርጉም የማይሰጥ
ምሳሌ ፲፮ ሐመሰ ፣ ኀመሰ ፣ ሀመሰ
ትርጉም :- ሐመሰ - አምስት አደረገ
ኀመሰ - ዋኘ
ሀመሰ - 🚫 ትርጉም የማይሰጥ
ምሳሌ ፲፯ በፅአ ፣ በፅዐ
ትርጉም :- በፅአ - ተሳለ
በፅዐ - ከበረ
ምሳሌ ፲፰ ወፅአ ፣ ወጽአ
ትርጉም :- ወፅአ - ወጣ
ወጽአ - ድል ነሳ
ምሳሌ ፲፱ ገዝአ ፣ ገዝዐ
ትርጉም :- ገዝአ - ገዛ
ገዝዐ - ቆረጠ
ምሳሌ ፳ ጸልአ ፣ ጸልዐ
ትርጉም :- ጸልአ - ጠላ
ጸልዐ - ቆሰለ
ምሳሌ ፳፩ ሰብአ ፣ ሠብዐ
ትርጉም :- ሰብአ - ሰው ሆነ
ሠብዐ - ሰባ (70)
ምሳሌ ፳፪ ጸብሐ ፣ ፀብሐ
ትርጉም :- ጸብሐ - ጠለቀ
ፀብሐ - ገበረ
ምሳሌ ፳፫ ዐፀወ ፣ ዐጸወ
ትርጉም :- ዐፀወ - አንቀላፋ
ዐጸወ - ዘጋ
፫ - 🎖ፊደላቱስ መቀነስ አለባቸው ወይ?
📌ከላይ ከተዘረዘሩት ምሳሌዎች መረዳት እንደሚቻለው የፊደላቱ መቀያየር ጉልህ የትርጉም ለውጥ እንደሚያመጣ ነው።
🤔እና ፊደላቱ መቀነስ አለባቸው ትላላችሁ ? ወይስ ፊደላቱ በሚገባ ተጠንተው እንደየአገባባቸው ሳይቀነሱ ልንጠቀማቸው ይገባል ትላላችሁ ??🤷♀️
ሀሳባችሁን በ @geezcommentbot ላይ አሳውቁኝ📃

🎖የግእዝ ቁጥሮች
በሰፊው የምንማማርበት ርዕስ ይሆናል።
❓ለማንኛውም ጥያቄ እና አስተያየት እነዚህን አማራጮች ይጠቀሙ።
@geezcommentbot @ardietegeez_discussion
ardietegeez@gmail.com
እሴብሓክሙ እምነ ልብየ ለኩልክሙ በይነ ተለውክሙኒ በውስተ ምሉዕ መርሃግብርየ።
(በመርሃግብሩ ሙሉ ስለተከታተላችሁኝ ሁላችሁንም ከልቤ አመሰግናለሁ።)🙏🙏
ምንጭ:- የአቡነ ጎርጎርዮስ ት/ቤት የግእዝ ቋንቋ መማሪያ መጻሕፍት እና ሌሎች የግእዝ ቋንቋ መጻሕፍት
@ardietegeez
@ardietegeez
@ardietegeez
🔄በቀጣይ
🎖የግእዝ ቁጥሮች
በሰፊው የምንማማርበት ርዕስ ይሆናል።
❓ለማንኛውም ጥያቄ እና አስተያየት እነዚህን አማራጮች ይጠቀሙ።
@geezcommentbot @ardietegeez_discussion
ardietegeez@gmail.com
እሴብሓክሙ እምነ ልብየ ለኩልክሙ በይነ ተለውክሙኒ በውስተ ምሉዕ መርሃግብርየ።
(በመርሃግብሩ ሙሉ ስለተከታተላችሁኝ ሁላችሁንም ከልቤ አመሰግናለሁ።)🙏🙏
ምንጭ:- የአቡነ ጎርጎርዮስ ት/ቤት የግእዝ ቋንቋ መማሪያ መጻሕፍት እና ሌሎች የግእዝ ቋንቋ መጻሕፍት
@ardietegeez
@ardietegeez
@ardietegeez
👋ሰላም ለኩልክሙ,እፎ ሀለውክሙ አኃዉየ ወአሀትየ?(ሰላም ለሁላችሁ,እንደምን አላችሁ ወንድሞች እህቶቼ?)👋
ክፍል ሦስት
▶️የዛሬው መርሀግብራችን👇
🎖የግእዝ አሐዞች/ቁጥሮች
🤔ረጅም እድሜ ያስቆጠሩ እና በጥንት ኢትዮጵያውያን ሊቃውንት የተጻፉ መጻሕፍትን ሲያነቡ የገጽ ማውጫ፣ የህትመት ዘመን ወይም ደግሞ ለሌሎች ምክንያቶች ግልጋሎት ላይ የዋሉትን የግእዝ ቁጥሮች ለመረዳት ተቸግረው ያውቃሉ ?
🤔አልያም ደግሞ መጽሐፍ ቅዱስ እና ሌሎች ቅዱሳን መጻሕፍት ሲያነቡ ምዕራፍ እና ቁጥሮች የተገለፁባቸዉን የግእዝ ቁጥሮች መረዳት ተቸግረው ያውቃሉ ?
🤗መፍትሔው እነሆ 👇
📌የግእዝ ቋንቋ እንደ ማንኛውም ቋንቋ እራሱን የቻለ የነገሮችን ብዛት በትክክል የሚገልፅበት አሐዝ/ቁጥር አለው።የግእዝ ቁጥሮች አቆጣጠር "የአሐዝ ወይም የኁልቁ አቆጣጠር" በመባል ይጠራል። (ኁልቁ ማለት በግእዝ ቋንቋ ቁጥር ማለት ነው)
📌የግእዝ ቁጥሮች የምንላቸው በአሁኑ ሰዓት በኢትዮጵያ የቀን መቁጠሪያ ቀሌንቶን ላይ፣ የመጽሐፍ ቅዱስ ምዕራፍ እና ቁጥሮች ላይ እንዲሁም የቀደምት ኢትዮጵያውያን መጻሕፍት ላይ የሚገኙ በተለምዶ የአማርኛ/የኢትዮጵያ ቁጥሮች ብለን የምንጠራቸው ናቸው።
📌የግእዝ ኁልቁ አቆጣጠር በዓረብ ቁጥሮች(0,1,2,3...)ላይ ወካይ ምልክት ላለው ለ'ዜሮ'(0) የሚሆን ምልክት ባይኖረውም በፊደል "አልቦ" በማለት ይገልፀዋል።
📌መሰረታዊ የግእዝ አሐዞች ፣ ከነአነባበባቸው እና ከዓረብኛ አቻዎቻቸው ጋር እንደሚከተለው ቀርበዋል።
🎖አኀዝ በግእዝ፣በአማርኛና በእንግሊዝኛ
📖ዐ ዐልቦ፤ ባዶ፤ 0 Zero
📖፩ አሐድ፤ አንድ፤ 1
📖፪ ክልኤት፤ ኹለት፤ 2
📖፫ ሠለስት፤ ሦስት፤ 3
📖፬ አርባዕት፤ አራት፤ 4
📖፭ ኀምስት፤ አምስት፤ 5
📖፮ ሰድስት፤ ስድስት፤ 6
📖፯ ሰብዐት፤ ሰባት፤ 7
📖፰ ሰመንት፤ ስምንት፤ 8
📖፱ ተስዐት፤ ዘጠኝ፤ 9
📖፲ ዐሠርት፤ ዐሥር፤ 10
📖፲፩ ዐሠርቱ ወአሐዱ፤ አስራ አንድ፤ 11
📖፲፪ ዐሠርቱ ወክልኤቱ፤ አስራ ሁለት፤ 12
📖፲፫ ዐሠርቱ ወሠለስቱ፤ አስራ ሦስት፤ 13
📖፲፬ ዐሠርቱ ወአርባዕቱ፤ አስራ አራት፤ 14
📖፲፭ ዐሠርቱ ወኀምስቱ፤ አስራ አምስት፤ 15
📖፲፮ ዐሠርቱ ወሰድስቱ፤ አስራ ስድስት ፤ 16
📖፲፯ ዐሠርቱ ወሰብዐቱ፤ አስራ ሰባት፤ 17
📖፲፰ ዐሠርቱ ወሰመንቱ፤ አስራ ስምንት፤ 18
📖፲፱ ዐሠርቱ ወተስዐቱ፤ አስራ ዘጠኝ፤ 19
📖፳ ዕሥራ፤ ኻያ፤ 20
📖፴ ሠላሳ፤ ሠላሳ፤ 30
📖፵ አርብዓ፤ አርባ፤ 40
📖፶ ኀምሳ፤ ዐምሳ፤ 50
📖፷ ስድሳ፤ ስድሳ፤ 60
📖፸ ሰብዓ፤ ሰባ፤ 70
📖፹ ሰማንያ፤ ሰማኒያ፤ 80
📖፺ ተስዓ፤ ዘጠና፤ 90
📖፻ ምእት፤ መቶ፤ 100
📖፲፻ ዐሠርት ምእት፤ አንድ ሺህ፤ 1000
📖፼ እልፍ፤ ዐሥር ሽሕ፤ 10,000
📖፲፼ ዐሠርት እልፍ፤ መቶ ሺህ፤ 100,000
📖፻፼ አእላፍ፤ መቶ እልፍ፤ 1,000,000 Million
📖፻፼፼ ትእልፊት፤ ሽሕ አእላፍ፤ 1,000,000,000 Billion
📖፼፼፼ ምእልፊት፤ እልፍ አእላፋት፤ 1,000,000,000,000 Trillion
🔴ማስታወሻ 🔴
ከአስራ አንድ እስከ አስራ ዘጠኝ ያሉትን ቁጥሮች በጻፍንበት የአጻጻፍ ስልት ሌሎችንም ቁጥሮች መጻፍ እንችላለን።
ለምሳሌ
🟢ኻያ ኹለት ቁጥርን ስንጽፍ ፳፪ አድርገን ሲሆን የግእዝ ስሙም "ዕስራ ወክልዔቱ" ነው።
🟢ሠሳሳ አራት ቁጥርን ስንጽፍ ፴፶ አድርገን ሲሆን የግእዝ ስሙም "ሠላሳ ወሠለስቱ" ነው።
🟢መቶ አርባ ስድስት ቁጥርን ስንጽፍ ፻፵፮ አድርገን ሲሆን የግእዝ ስሙም "ምእት ወአርብዓ ወሰደስቱ" ነው።
🟢አንድ ሺ ሃምሳ ስምንት ቁጥርን ስንጽፍ ፲፻፶፰ አድርገን ሲሆን የግእዝ ስሙም "አሰርቱ ምእት ኀምሳ ወሰመንቱ" ነው።
🟢ሁለት ሺህ አንድ መቶ ኻያ ኹለት ቁጥርን ስንጽፍ ፳፻፳፪ አድርገን ሲሆን የግእዝ ስሙም "ዕሥራ ምዕት ዕሥራ ወክልዔቱ" ነው።
🟢የዛሬውን ቀን በግእዝ አሐዞች በመጠቀም ብንጽፈው 24/07/2012 ዓ.ም 👉 ፳፬/፯/፳፻፲፪ ዓ.ም ይሆናል።
🟢1987 የሚለውን ዓመተ ምሕረት በግእዝ አሐዞች ስንገልፀው ፲፱፻፹፯ ይሆናል። ሲነበብም "አሠርቱ ወተስዓቱ ምዕት ሰማንያ ወሰብዓቱ" ይሆናል።
🟢ሁለት ሺህ አስራ ኹለት /፳፻፲፪/የሚለው ዓመተ ምሕረት በግእዝ ፊደል ሲፃፍ "እስራ ምዕት አሠርቱ ወክልኤቱ" ተብሎ ነው።
🟢ስምንት መቶ ሃምሣ አንድ ሺህ ስድስት መቶ ኻያ አንድ (851,621) የሚለው ቁጥር በግእዝ አሐዝ ሲፃፍ ፹፭፼፲፻፳፩ ሲሆን የግእዝ ስሙም "ሰማንያ ወኀምስቱ እልፍ ዐሠርቱ ወሰደስቱ ምእት ዕሥራ ወአሐዱ" ነዉ።
📝መልመጃ ጥያቄዎች
የሚከተሉትን የዓረብ ቁጥሮች ወደ ግእዝ አቻዎቻቸው በመቀየር አስቀምጡ።
🔹67
🔹904
🔹3802
🔹199,318
🔹2,080,001
መልሶቻችሁን በ 👉 @geezcommentbot ላኩልን። እስክ ቅዳሜው መርሀግብራችን ድረስ ፭ቱንም ጥያቄዎች በትክክል ለምትመልሱ ተሳታፊዎች አንድ ጥሩ የግእዝ ቋንቋ መማሪያ መጽሐፍ 📔በPDF ሽልማት ይኖራችኋል።ትክክለኛዎቹን መልሶች በቅዳሜው መርሀግብር መግቢያ ላይ እናሳውቃለን።ሁላችሁም ተሳተፉ 🤗🤗🤗
📌ለተጨማሪ ምሳሌዎች የሚከተለውን PDF ይመልከቱ።👇